የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኔምቤክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ‘የሲቢኢ ኑር ዒድ ኤክስፖ 2018’ ባዛር እና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል ተከፍቷል።
ኤክስፖውን መርቀው የከፈቱት የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን ሙስሊሙ ህብረተሰብ የዒድ አልፈጥር በዓል ግብይቶቹን በአንድ አካባቢ በቅናሽ ዋጋ እንዲፈፅም እና በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል ባንኩ ኤክስፖውን በስፖንሰርነት እንዲዘጋጅ ማድረጉን ገልፀዋል።
ባንኩ የረመዷን ወርን “አብሮነት እና በጎነት በረመዷን” በሚል መሪ ቃል በሚካሄዱ የተለያዩ መርሐ ግብሮች ከደንበኞች እና ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ እያሳለፈ መሆኑንም ተናግረዋል።
ባንኩ በአሁኑ ጊዜ ከ8 ሚሊዮን በላይ የሲቢኢ ኑር ደንበኞች እንዳሉት ገልፀው፣ በዚሁ ዘርፍም ከ266 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል።
በተለያዩ የሥራ ዘርፍ ለተሠማሩ ደንበኞች ከ210 ቢሊዮን ብር በላይ ፋይናንስ ማቅረቡንም አመልክተዋል።

ኢራን በመጪው ክረምት በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ እንደማትሳተፍ የሀገሪቱ የስፖርት ሚኒስቴር አህማድ ዶንያማሊ ተናግረዋል።
የኢራን የስፖርት ሚኒስቴር አህማድ ዶንያማሊ አሜሪካ እና እስራኤል በጣምራ የከፈቱት ጦርነት የሀገሪቱን ሁለንተናዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን መግደሉን ተከትሎ በዓለም ዋንጫው አንሳተፍም ብለዋል።
ግጭቱ አሁን በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ እየተስፋፋ ሲሆን ኢራን በአካባቢው የሚገኙትን የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፖች በመምታት የበቀል እርምጃ እየወሰደች ነው።
የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ የጋራ አስተናጋጅነት የሚካካሄድ ሲሆን ኢራን በሎስ አንጀለስ ከኒውዚላንድ እና ቤልጂየም እንዲሁም በሲያትል ግብፅን እንደምትገጥም አስቀድሞ የወጣው መርሃ-ግብር ያሳያል።
ሆኖም ዶንያማሊ ኢራን በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ እንደማትጓዝ በመግለጽ ቡድኑ የመሳተፍ እድል እንደሌለው አጥብቀው ተናግረዋል።
ሚንስቴሩ “ይህ ብልሹ መንግስት (አሜሪካ) መሪያችንን ከገደለ ወዲህ በዓለም ዋንጫው ላይ የምንሳተፍበት ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ የለንም።
በኢራን ላይ ከተወሰዱት ተንኮል አዘል እርምጃዎች አንጻር ፤ በስምንት ወይም በዘጠኝ ወራት ውስጥ ሁለት ጦርነቶች ለማስተናገድ ተገደን በርካታ ሺህ ወገኖቻችን ተገድለዋል። ስለዚህ በዚህ መንገድ የመሳተፍ ምንም ዕድል የለንም" ሲሉ ተደምጠዋል።
የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የትራምፕ አስተዳደር ኢራንን በአለም ዋንጫው ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ገልፀው ነበር።

👍2
የዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ በታሪክ ከፍተኛ የተባለውን የነዳጅ ክምችት ወደ ገበያ ሊለቅ መሆኑ ተገለፀ።
የዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ (IEA) አባል ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ በተቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ የተከሰተውን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ለማረጋጋት 400 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ከስትራቴጂክ ክምችታቸው ወደ ገበያ ለመልቀቅ ተስማሙ።
ይህ ውሳኔ በኤጀንሲው ታሪክ ከፍተኛው የተቀናጀ የነዳጅ ምርትን ለመልቀቅ የተደረገ ውሳኔ መሆኑ ተገልጿል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ፋቲህ ቢሮል በሰጡት መግለጫ፣ እርምጃው በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ምክንያት የተፈጠረውን የአቅርቦት እጥረት ለመተካት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
አባል ሀገራቱ በአሁኑ ወቅት ከ1.2 ቢሊዮን በርሜል በላይ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ክምችት እንዳላቸውም ጠቁመዋል።
ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ይህ እርምጃ የተከሰተውን የነዳጅ ገበያ ጫና ሊቀንስ ይችላል። ሆኖም የሆርሙዝ ወሽመጥ ለረጅም ጊዜ ተዘግቶ የሚቆይ ከሆነ ከፍተኛ የአቅርቦት ችግር ሊፈጠር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ኤጀንሲው የገበያውን ሁኔታ በቅርበት መከታተሉን እንደሚቀጥል ማስታወቁንም ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

❤1
የቡና ዋጋና የዶላር ምንዛሬ ይጨምራል በሚል ተስፋ የቡና ምርትን ሸሽገው በሚያቆዩና ወደ ገበያ በማያወጡ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ይመር ዳውድ እንደገለፁት ፤ በአሁኑ ወቅት ቡናን ወደ ገበያ ያለማውጣት ችግር እየተስተዋለ መሆኑንና ይህም ወደ ውጭ የሚላከው የቡና መጠን እንዲቀዛቀዝ ማድረጉን ተናግረዋል።
በሀገሪቱ የምርት እጥረት አለመኖሩን የጠቀሱት ሥራ አስፈጻሚው፤ ያለውን ምርት በፍጥነት ወደ ገበያ በማቅረብ የኤክስፖርት ገቢውን ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ ሊቀንስ እንደሚችል ጥናቶች ማረጋገጣቸውን የገለጹት አቶ ይመር፤ "ምርት የሚሸሽጉ አካላት ላይ ከዚህ በኋላ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
አርሶ አደሮችም ሆኑ ነጋዴዎች በእጃቸው ያለውን ምርት ለገበያ እንዲያቀርቡም ጥሪ አቅርበዋል።

መጥፎ ጓደኛ በፍጥነት ሊያስረጆት እንደሚችል በጀርመን ሀገር የተሰራዉ ጥናት አመላከተ
ከአመጋገብ እስከ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፣ በርካታ ምክንያቶች በሰውነት ዕድሜ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ፣ ግን አንድ አዲስ ዘገባ እንዳመላከተዉ በአስቸጋሪ ሰዎች የማያቋርጥ ውጥረት የተነሳ ባዮሎጂያዊ እርጅናን እንደሚያፋጥነው አመላክቷል፡፡
በሐምቡርግ፣ ጀርመን በሚገኘው የኤምኤስኤች ሕክምና ትምህርት ቤት የሥነ ልቦና ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ሴባስቲያን ኦክለንበርግ የጻፉት እና በሳይኮሎጂ ቱዴይ የታተመው ዘገባው “መርዛማ የሆኑ ሰዎች በባህሪያቸው ከፍተኛ ጭንቀት ሊፈጥሩ ይችላሉ” ብሏል።
ሪፖርቱ "አስጨናቂዎች" ተብለው በተገለጹት ግለሰቦች ላይ የተደረጉ ጥናቶችን መርምሯል፡፡በአንድ ሰው ማህበራዊ አውታረ ውስጥ በተደጋጋሚ ችግሮች የሚፈጥሩ ወይም ጭንቀትን ይጨምራሉ፡፡ተመራማሪዎች ለእነዚህ ግለሰቦች መጋለጥ ከፈጣን ባዮሎጂያዊ እርጅና ጋር እንደሚዛመድ አረጋግጠዋል።
እያንዳንዱ መጥፎ ጓደኛ በግምት 1.5 በመቶ የእርጅና ፍጥነት ባዮሎጂያዊ ዕድሜን ይጨምራሉ።"በአማካኝ በማህበራዊ ህይታቸዉ ውስጥ መጥፎና መርዛማ ሰዎች ያላቸው በጎ ፈቃደኞች ላይ በተሰራዉ ጥናት ባዮሎጂያዊ ዕድሜያቸዉ ከእነርሱ ተመሳሳይ የልደት ዕድሜ ካላቸው ሰዎች ጋር ሲነጻጸሩ 9 ወራት ከፍ ብለዉ ታይተዋል" ሲል ዘገባው ገልጿል።
"የሚገርመው ነገር መርዛማ ከሆኑ የትዳር ጓደኛ ይልቅ መጥፎ ባህሪ ያላቸዉ የቤተሰብ አባላት ወይም ጓደኞች በእርጅና ላይ ተጽእኖ አሳድረዋል"፡፡ጥናቱ ሰዎች "መርዛ አስተሳሰብ ካላቸዉ ሰዎች መራቅ" አለባቸው ሲል ይደመድማል፡:

🤯1
የAI ቻት ቦቶች ለታዳጊ ወጣቶች የደህንነት ስጋት እየሆኑ ነው ተባለ።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻት ቦቶች (AI Chatbots) ታዳጊ ወጣቶች የጥቃት ድርጊቶችን እንዲያቅዱ እና ራሳቸውን እንዲጎዱ የሚያበረታቱ መረጃዎችን እየሰጡ መሆኑን CNN ዘግቧል።
ተመራማሪዎች እንደ ታዳጊ ወጣቶች በመምሰል ባደረጉት ሙከራ፣ ታዋቂ የሆኑ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቻትቦቶች የጥቃት ድርጊቶችን ለማቀድ፣ ራስን የመጉዳት ሃሳቦችን ለማበረታታት እና አደገኛ ድርጊቶችን ለመፈጸም የሚያስችሉ ዝርዝር መመሪያዎችን እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል።
ምንም እንኳን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኩባንያዎች የደህንነት መጠበቂያዎች አሉን ቢሉም፣ ታዳጊዎቹ ጥያቄዎቻቸውን በሌላ መንገድ ሲያቀርቡ ቻት ቦቶቹ በቀላሉ ጥንቃቄ የጎደለው ምላሽ እንደሚሰጡም ታይቷል። ቻትቦቶቹ ከሰዎች ጋር የሚቀራረብ ስሜት ስለሚፈጥሩ፣ በተለይ ስሜታቸው በቀላሉ የሚነካ ታዳጊዎች ከእነዚህ ሮቦቶች ጋር ጥልቅ የሆነ ግንኙነት እንዲመሰርቱ ያደርጋቸዋል።
ይህ ደግሞ ቻትቦቶቹ የሚሰጡትን የተሳሳተ ምክር እንደ እውነት እንዲቀበሉ የሚያደርግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡በጥናቱ ወቅት ቻትቦቶቹ በትምህርት ቤት ውስጥ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል እና የጥቃት ስልቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ሲያጋሩ ተስተውለዋል።
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ የደህንነት ስርዓታቸውን ለማሻሻል እየሰሩ መሆኑን ቢገልጹም፣ ተቺዎች ግን ትርፍን ከደህንነት በማስቀደማቸው ለወጣቶች ህይወት አደጋ እየፈጠሩ ነው ይላሉ።
በመሆኑም የታዳጊዎች የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲኖር፣ ወላጆች ልጆቻቸው ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት በቅርበት እንዲከታተሉ እና የሚመለከታቸው አካላት በቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

❤1👍1
አዋሽ ባንክ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን በይፋ ስራ አስጀመረ።
ባንኩ ያስጀመራቸው እነዚህ መተግበሪያዎች አዋሽ ሬሚት፣ አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ እና አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት የተሰኙ ሲሆኑ፣ በባንክ አገልግሎት ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍቱ ታምኖባቸዋል።
በይፋ ስራ ከጀመሩት መተግበሪያዎች መካከል ቀዳሚው አዋሽ ሬሚት ሲሆን፣ መተግበሪያው በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቪዛ (Visa) ወይም የማስተር ካርድ (MasterCard) አማራጮችን በመጠቀም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በቀጥታ ወደ አዋሽ ባንክ ሂሳብ ወይም ወደ "አዋሽ ብር ፕሮ" ዋሌት ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የገንዘብ ዝውውር እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
ሁለተኛው መተግበሪያ አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ ደግሞ ኮንሰርቶችን፣ ስፖርታዊ ውድድሮችን፣ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎችን እና መሰል ኩነቶችን የሚያዘጋጁ አካላት ትኬቶችን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መንገድ እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ነው።
በተጨማሪም ባንኩ ይፋ ያደረገው አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት ሲስተም የሕንፃ ባለቤቶችንና ተከራዮችን የዕለት ተዕለት ግንኙነት ለማቅለል የተዘጋጀ ነው።
መተግበሪያው የህንፃ ኪራይ አስተዳደርን፣ የፋይናንስ ክትትልን፣ የወለል ፕላኖችን እና የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ በዲጂታል መንገድ ለመምራት የሚያስችል ሲሆን፣ በተለምዶ የሚሰራውን በእጅ የተደገፈ የኪራይ አያያዝ ወደ ዘመናዊና ግልጽ አሰራር እንደሚቀይረው ተገልጿል።

ግሎባል ባንክ 1447ኛውን የረመዳን ፆም ወር ምክንያት በማድረግ በየሲር ለና የበጎ አድራጎት ድርጅት የኢፍጣር መርሃ ግብር አከናወነ።
በዚህ መርሃ ግብር ከ200 በላይ የሚሆኑ አቅመ ደካሞች ህፃናት እና አረጋውያን ተሳታፊ ሆነዋል።
የባንኩ የማርኬቲንግ እና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ፍቃዱ እንደገለፁት፦ ባንኩ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ በማድረግ በአካባቢ ጥበቃ በትምህርት እና በጤና ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ባንኩ ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ አቅመ ደካሞች ራሳቸውን እንዲችሉ የሙያ ስልጠናዎችን እና ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማመቻቸት ረገድ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ ዘርፎች እያከናወነ ያለውን የበጎ አድራጎት ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
በዝግጅቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የባንኩ የሸሪያ አማካሪ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በኬንያ ጉንዳን ሰርቆ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ቻይናዊ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።
"ጂያንት አፍሪካን ሃርቨስተር አንትስ" የሚባሉት የጉንዳን ዝርያወች በእስያ እና አውሮፓ ያሉ የቤት እንስሳት አርቢዎች ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈለጋሉ።
በዚህም አንዲት ንግስት ጉንዳን እስከ 200 ዩሮ ሊትሸጥ ትችላለች።
ታዲያ ይህን የተረዳው ዣንግ የተባለ ግለሰብ ከሁለት ሺህ በላይ ሕይወት ያላቸውን የጉንዳን ንግስቶች በሻንጣው ውስጥ ደብቆ ከሀገር ለማውጣት ሲሞክር በጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በሻንጣው ውስጥ በልዩ ሁኔታ የታሸጉ ቱቦዎችን ይዞ ነበር።
በእነዚህ ቱቦዎች ውስጥ ወደ 1,950 የሚጠጉ የአትክልት ጉንዳን ንግስቶች ነበሩ።
ነገር ግን የፀጥታ ኃላፊዎች ጥልቅ ፍተሻ ሲያካሂዱ ሌላ 300 የሚሆኑ በሶፍት ወረቀት የተጠቀለሉ ሕይወት ያላቸው ጉንዳኖችን አገኙ።
የኬንያ ዱር አራዊት አገልግሎት ይህ ሰው ተራ ሰብሳቢ ሳይሆን የኮንትሮባንድ ቡድን መሪ ነው ሲሉም ከሰዋል።
በ2025 በተመሳሳይ አውሮፕላን ማረፊያ ሁለት ቤልጄማውያን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ጉንዳኖችን ይዘው ሲወጡ የተያዙ ሲሆን ዣንግም በወቅቱ የተለየ ፓስፖርት በመጠቀም ከኬንያ መሸሽ ቢችልም በዚኛው ግን አለተሳካለትም።
ዣንግ ለአምስት ቀናት በምርመራ እንዲቆይ ትእዛዝ ተላልፏል።
ባለሥልጣናት ስልኩን እና ላፕቶፑን በመመርመር በኬንያ ውስጥ ጉንዳን ማደን ወደሚካሄድባቸው ሌሎች ከተሞችም ምርመራቸውን እያሰፉ ነው ።
የኬንያ ዱር አራዊት አገልግሎት በባንኮክ ዛሬ ሌላ ከኬንያ የተላከ የጉንዳን ጥቅል መያዙን አሳውቋል።
ይህም የዚህ ሕገወጥ ንግድ መጠን ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ አመላካች ነው።

በኢትዮጵያ ጥቁር አውራሪስ ሙሉ በሙሉ የጠፋ የዱር እንስሳት መሆኑ ተገለፀ፡፡
በሌላ በኩል በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ህገወጥ አደን የዋልያዎችን ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ አድርሶታል።
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እንዳስታወቀው ባለፉት አመታት በተለያዩ ብሄራዊ ፓርኮች የሚገኙ በርካታ የዱር እንስሳትን ከመጥፋት የመታደግ ስራ ቢሰራም ሙሉ በሙሉ የጠፉ ዝርያዎች አሉ።
በጥናት የተደገፈ ቁጥራዊ መረጃ ተሰርቶ ባይረጋገጥም በርካታ የዱር እንስሳት ዝርያዎች መጥፋታቸውንና ሌሎችም የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ተመላክቷል።
ከኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ከጠፉ የዱር እንስሳት መካከል ጥቁር አውራሪስ አንዱ ስለመሆኑም ባለስልጣኑ አረጋግጧል።
በሌላ በኩል፤ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የሚስተዋለው ህገወጥ የዋልያ አደን የዋልያዎችን ቁጥር እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳደረሰው ባለስልጣኑ ጠቁሟል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በምትገኘው በኢራኗ ካርግ ደሴት ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀማቸውን አስታወቁ።
ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ፥ በኢራን ደቡብ ምዕራብ የባህር ዳርቻ በምትገኘው በካርግ ደሴት ላይ በሚገኙ የኢራን ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ ተይቶ የማይታወቅ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቀዋል።
ጥቃቱ መጠነ ሰፊ መሆኑን የጠቀሱት ትራምፕ፥ በቀጣይ የነዳጅ መሰረተ ልማቶችን ሊጠቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
ጥቃቱን በመቃወም በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኢራን ዋና ከተማ በመውጣት በአሜሪካ እና በእስራኤል የሚደርሱ የማጥቃት ዘመቻዎችን ተቃውመዋል።
እ.ኤ.አ በየካቲት 28 ጦርነቱ ከተጀመረበት ግዜ አንስቶ፥ እስራኤልና ከሜሪካ በኢራን ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች 1ሺ 450 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
በተመሳሳይ እስራኤል በሰሜናዊ ሊባኖስ የጤና ተቋማት ላይ ባደረሰችው ጥቃት12 የጤና ባለሙያዎች መገደላቸውንና ይህም103 ህጻናትን ጨምሮ በእስራኤል ጥቃት የሞቱ ሰዎች 773 አድርሶታል ተብሏል።
ኢራን እየወሰደች ባለው የሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃትም፥ ኳታር እና ባህሬንን ጨምሮ በባህረ ሰላጤው አካባቢ ያሉ ሀገራት የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል። ዘገባው የአልጀዚራ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ድረስ ከ9 ሚሊዮን 36 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለፁት፣ ቦርዱ የመራጮች ምዝገባን ለማድረግ ከቁሳቁስ ስርጭት ጀምሮ የሰው ሃይል የማሰልጠን እና መሰል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አድርጎ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል፡፡
ቦርዱ ከ52 ሺ 152 በላይ የምርጫ ጣቢያዎችን አቋቁሞ ወደ ትግበራ ገብቷል።
ከነዚህ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል 6 ሺ 300 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ ወደ ስራ አለመግባታቸውንም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከመራጮች ምዝገባ ባለፈ የእጩዎች ምዝገባ ማከናወኑን ገልጸው የፓርቲዎች የክርክር መድረክ፣ የፓርቲዎች የገንዘብ ድጋፍ፣ የነፃ የአየር ሰዓት እና መሰል ስራዎች በአግባቡ መሰራታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

የሰው ልጅ እና የቴክኖሎጂ ውህደት በስዊድን፤ ምቾት ወይስ የነፃነት ስጋት?
ቁልፍ መያዝ፣ የባቡር ትኬት መቁረጥ አልፎ ተርፎም የባንክ ካርድ መያዝ ታሪክ ሊሆን ነው? በስዊድን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሰውነታቸው ውስጥ አንድ አስገራሚ ነገር እያስገቡ ይገኛሉ።
ይህ የሩዝ ፍሬ የሚያክል ጥቃቅን መሳሪያ የሰዎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ሙሉ በሙሉ እየቀየረ ቢሆንም፣ በጤና ባለሙያዎች እና በግል መረጃ ደህንነት ተሟጋቾች ዘንድ ግን ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል።
በተለይ በ2024 የወጡ አዳዲስ የህክምና ሪፖርቶች ያልተጠበቀ አደጋ ሊኖር እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው።

ከአንድ ወር በላይ ደሞዝ ሳይከፈላቸው የቆዩ
በኤል ሳልቫዶር አንድ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ የሚሰለፉ ተጫዋቾች ጥያቄያቸው የተሰጣቸው ምላሽ አስገራሚም አስደንጋጭም ሆኗል።
ተጫዋቾቹ ደሞዛችሁን ለማግኘት ፀጉራችሁን ተላጩ ተብለዋል።
ዋን ፉትቦል የተባለ የስፖርት ድረ ገፅ ከወደ ኤል ሳልቫዶር አገኘሁት ብሎ ያወጣው ዘገባ ብዙዎችን ያዝናናም ያሳዘነም ሆኗል።
ሲዲ ሄርኩለስ የተባለው የሃገሪቱ የመጀመሪያ ዲቪዚዮን ውስጥ የሚገኝ ክለብ ተጫዋቾች ከአንድ ወር በላይ ደሞዝ ሳይከፈላቸው፣ የላብ መተኪያም ሳያገኙ ነገር ግን ከአሰላለፋቸው ሳይጎድሉና ለክለባቸውም ፎርፌ ሳያሰጡ በትዕግስት ቆይተዋል።
ነገር ግን ችግር ሲበረታባቸው እና ገንዘብ የግድ የሚያስፈልጋቸው ጊዜ ላይ ሲደርሱ ደሞዛችን ይከፈለን የሚል ጥያቄን ለክለቡ አመራሮች ያቀርባሉ።
በዚህ ጊዜ ነው ታዲያ ከክለቡ አመራሮች ለተጫዋቾቹ ያልተጠበቀና አስደንጋጭ፣ ጉዳዩን ለሚሰማ ደግሞ አስገራሚ የሆነው መልስ የተሰማው።
ከግብ ጠባቂ እስከ ቋሚ ተሰላፊና ተጠባባቂ ድረስ የሚገኙ ሙሉ የክለቡ ተጫዋቾች የቀረባቸውን ደሞዝ ለማግኘት የራስ ፀጉራቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዲላጩና መላጣ እንዲሆኑ አመራሮቹ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ይህን ካላደረጉ ግን ብለዋል የክለቡ ኃላፊዎች፤ ይህን ካላደረጉ ግን ተጫዋቾቹ የዘገየውን ደመወዛቸውን ጭራሽ አያገኙም።
ይህን ተከትሎ ተጫዋቾቹ በምላሻቸው ከክለቡ አመራሮች የተሰጠው መመሪያ እጅግ አስነዋሪ፣ ከውል ውጭ የሆነና በፍፁም የማንቀበለው ነው ብለዋል።
በዚህ ምክንያትም ጉዳዩን ወደ ሳልቫዶር እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመውሰድ መደበኛ ክስ ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆኑን የመረጃ ምንጩ ሲዲ ሄርኩለስ አስነብቧል።

አሁን ላይ ጉዳዩ በሃገሪቱ መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ ከባድ ወደሚባል ደረጃ ደርሷልም ብሏል ዘገባው።
ደመወዝ መክፈል የክለብ የሕጋዊ ግዴታ ሆኖ ሳለ ተጫዋቾችን በግዴታ ፀጉራችሁን ተላጩ ብሎ መጠየቅ የሰው ክብርን ማዋረድ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
እንደ FIFA ደንብ፤ ክለቦች ከውል ውጭ በሆነ መልኩ ተጫዋቾቻቸው ላይ ሰብዓዊ ክብርን የሚገፍ ተግባር መፈፀምን አጥብቆ ያወግዛል።
ክለቡ በፍርድ ቤት ክስ ከተመሰረተበት
ለተጨዋቾቹ ከደሞዛቸው ውጪ መቀጫ እንዲከፍል በፍርድ ቤት ከመገደድ ባለፈ በዲቪዚዮኑ ነጥብ ቅነሳ ወይም እገዳ ሊደርስበት ይችላል።
ይህ ጉዳይ በእግር ኳስ ዓለም ውስጥ እጅግ ያልተለመደ መሆኑን ተከትሎ ብዙዎች እየተከታተሉት ይገኛሉ።

ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከዘፈኑ ዓለም መውጣቱን አስታወቀ።
ታዋቂው ዘፋኝ "ከእንግዲህ በዘፈኑ ዓለም የለሁም" በማለት ወደ መንፈሳዊ አገልግሎት መመለሱን ገለጸ።
የዘፈን ዓለምን "ውስብስብ፣ አጋንንታዊና ቆሻሻ" አስመስሎታል። "የጠፋው ልጅ ተገኝቷል" በማለት ወደ እምነቱ መመለሱን አረጋግጧል።
በ2003 ዓ.ም የፃፈው "እሰይ" ዝማሬ የናፍቆት ዘመኑን እንደሚያሳይ ተናግሯል። ለሌሎች አርቲስቶችም መንገዱን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርቧል።
#አቤል #ከዘፈን_ዓለም_ወጣ #መንፈሳዊ_አገልግሎት #እሰይ

ለጥራት አገልግሎት ሲባል የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በስራ ሰዓት የእጅ ስልክ መጠቀምን ከለከለ።
ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሚገኙ ከ7,000 በላይ ሰራተኞች በመደበኛ የስራ ሰዓት የግል የእጅ ስልክ መጠቀም አይችሉም።
ቢሮው የግብር ከፋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ወስኗል።
በተደረገ ሰፊ ውይይት ላይ እንደተገለጸው፣ በስራ ሰዓት የግል ስልክ መርበድበድ እና የስራ ኮምፒውተርን ለግል ጉዳይ መጠቀም ለአገልግሎት መጓተት ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል።
ሰራተኞቹም አዲሱን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ እና ግብር ከፋዩን በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ይህ እርምጃ የመንግስት ተቋማት ተገልጋይን ለማርካት ለሚሰሩት ስራ እንደ ምሳሌ ይወሰዳል ተብሎ ይጠበቃል።
#አዲስአበባ #ገቢዎችቢሮ #አገልግሎት #ሪፎርም #ዜና