Arada Times
7.92K subscribers
5.46K photos
95 videos
2 files
691 links
ለማስታወቂያ እና ጥቆማ በዚህ ያናግሩን 👉 https://t.me/mo_anbesa
Download Telegram
ታሰሩ‼️

📍የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት የነበሩት ታደሰ ወረደ፣ አማካሪያቸው አቶ ኢሳይያስ ታደሰና የደህንነት ኃላፊ የነበሩት ሌላ አንድ ኮሎኔል ሌሊቱን በመቀሌ ከቤታቸው በፖሊስ ተከበው ከተወሰዱ በኋላ ታስረዋል።
👍1
Latest update

በወልቃይት አዲስ የጦርነት ግንባር ተቀስቅሷል። በተያያዘ በፀሊሞይ የጀመረው ውጊያ እንደቀጠለ ነው። በራያ ጨርጨር፤ በአፋር፤ በሰቆጣ እና በወልዲያ መስመርም ግጭቱ ቀጥሏል።
👍2❤1
ሰበር ዜና

📍ወደ ላሊበላ የሚደረጉ የአየር በረራዎች ተቋረጡ! ምክንያቱ አልታወቀም
❤3
Update‼️

📍የስልክ እና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ‼️

በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ትላንት ምሽት ሲቆራረጥ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት፣ ዛሬ ንጋት ላይ በሙሉ ክልሉ መቋረጡ ተረጋገጠ።
❤2👍2
📍የቴሌኮም ሰራተኞች ታስረዋል‼️

የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክን ያገደው ህወሓት መሆኑ ታውቋል። በህወሓት የደህንነት መሪዎች ኔትወርክ እንዲያቋርጡ ተጠይቀው «አናቋርጥም፣ማቋረጥ የምንችለው ከፌዴራል መንግሥቱ ስንታዘዝ ብቻ ነው» ያሉ የተቋሙ ሰራተኞች ታስረዋል።
❤3
ሳፋሪኮም ለመግዛት ሰልፍ‼️
ህወሓት በመላው ትግራይ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክን ሙሉ ለሙሉ በድንገት መዝጋቱን ተከትሎ የመቀለ ነዋሪዎች ሳፋሪኮም ለመግዛት ከፍተኛ ሰልፍ እየታየ ይገኛል።
❤4
ታስረዋል‼️

📍የቀድሞው የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳድር ፕረዚደንት የነበሩት ጀነራል ታደሰ ወረደ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል።
❤3
ባንኮች ስራ አቆሙ‼️

​በትግራይ ክልል የሚገኙ የባንክ ሂሳቦች (አካውንቶች) ለጊዜው ሙሉ በሙሉ እንዳንቀሳቀሱ መታገዳቸው ተሰምቷል። ​ከዚሁ ጋር ተያይዞ በክልሉ የሞባይል ዳታ እና የድምፅ አገልግሎቶች መቋረጡ ይታወሳል።
❤2👍2
‹‹የሕወሓት አመራሮች በቀናት ውስጥ በድሮን ይመታሉ›› The Economist

ተነባቢው መጽሔት ዘ ኢኮኖሚስት ባለፈው ረቡዕ የተቀሰቀሰውን አዲስ ግጭት በተመለከተ ሰፊ ዘገባን አስነብቧል፡፡ ትብብር የፈጠሩ አማጺዎች የኢትዮ ጅቡቲን መስመር ለመቁረጥ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጧል፡፡
❤3😁1
ለተቀናጀ የህክምና እርዳታ ወደ ህንድ ሀገር አቅንታ የነበረችው ታዳጊ ማዕዶት ስለሺ የካንሰር ህመሟ በሙሉ ሁኔታ ማገገሙን የሚያሳይ የምርመራ ውጤት በማግኘቷ ወደ ሀገሯ መመለሷ ተበሰረ። ታዳጊ ማዕዶት የደም ካንሰር ህመም አጋጥሟት በሀገር ውስጥ የኬሞቴራፒ ህክምና ስትከታተል የቆየች ሲሆን፣ ተጨማሪ የመቅኔ ንቅለ ተከላ ህክምና እንድታገኝ በህዝብ በተሰበሰበ ገንዘብ ወደ ህንድ ተልካ እንደነበር ይታወቃል።
​ሆኖም በህንድ ሀገር በተደረገላት ጥልቅ የላብራቶሪና የፍሎሳይቶሜትሪ የምርመራ ውጤቶች መሠረት፣ በሰውነቷ ውስጥ ይገኝ የነበረው የካንሰር ህዋስ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱና መጽዳቱ ተረጋገጧል። በዚህም ምክንያት ተጨማሪ የንቅለ ተከላ ህክምና ሳያስፈልጋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገሯ ተመልሳለች። የህክምና ባለሙያዎች እንደገለጹት በሀገር ውስጥ የወሰደችው ህክምና ከፍተኛ ውጤት በማምጣቱ አሁን ላይ ከበሽታው ነጻ መሆኗ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በቀጣይም ለአምስት ዓመታት ያህል መደበኛ ክትትል ብቻ የሚደረግላት ይሆናል።
​የታዳጊ ማዕዶትን በደስታ ወደ ሀገሯ መመለስ ተከትሎ ወዳጆቿ በተገኙበት ልዩ የደስታና የምስጋና ስነ-ስርዓት የተደረገላት ሲሆን፣ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላደረገላት ድጋፍና ጸሎት ቤተሰቦቿ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል
❤8🔥3👍1
"አግዢኝ ማርያም" አለቻት.....እርሷም አግዛት ከካንሰር ዳነች❤️❤️❤️❤️
***
በደም ካንሰር ስትሰቃይ የነበረችው እና '' ትሞቻለሽ '' የሚሉ ሰዎች ያፍሩብኝ ዘንድ " ድንግል ማርያም አድኝኝ " ስትል "አግዢኝ ማርያም" በሚል ዝማሬ በእንባ ተማጽኖ ያቀረበችው ህፃን ማዕዶት ስለሽ አይቶ ያላነባ የለም።
እነሆ በአካል የማያውቃት እና በማኅበራዊ ሚዲያ መስኮት የተመለከታት ሁሉ ሲያለቅስላት እና ለአምላካቸው ስለት ሲሳሉላት እና ሲማጸኑ ቆይተዋል።
ተዓምራዊ በሆነ ሂደት ለህክምና በሄደችበት ህንድ ሀገር ሙሉ የካንሰር ህክምናውን ሳትጀምር ካንሰሩ ከደሟ ጠፍቶ ነጻ ሆና መመለሷ ተሰምቷል።
❤️❤️❤️❤️
❤14
ሰበር‼️

📍በኮምቦልቻ ኤርፖርት ግቢ ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰማ፤ በረራዎች ለጊዜው ተቋርጠዋል።

በኮምቦልቻ ኤርፖርት ግቢ ውስጥ ከለሊቱ 8 ሰዓት ተኩል አካባቢ ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱንና አሁን ላይ በረራዎች ለጊዜው መቋረጣቸው ተሰምቷል። ፍንዳታውን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ማንም አካል ወደ ኤርፖርቱ ግቢ መግባት እንዳይችል ጥብቅ ክልከላ የተደረገ ሲሆን፣ የጸጥታ አካላት አካባቢውን ከበው ይገኛሉ።

ከትናንት ጀምሮ በደብረዘይት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ግቢ፣ በባህር ዳር ኤርፖርትና በኮምቦልቻ ኤርፖርቶች ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ድሮኖች ወይም ረጅም ርቀት ተጓዥ መሳሪያዎች ጥቃት እንደተፈጸመ በሶሻል ሚዲያ ገጾች ላይ ሰፊ ዘገባዎች ሲሰራጩ ቆይተዋል።
❤11
ሰበር ዜና‼️

መከላከያ ሠራዊት ራያ አላማጣ ከተማን ገብቷል።
❤4😁3
በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
😁1
አዲስ አበባ የተሰማው ፍንዳታ‼️

በትናንትናው ዕለት ምሽት በአዲስ አበባ ፍንዳታዎች መስማታቸውን ሮይተርስ የዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

የፍንዳታ መንስኤው በወታደራዊ ተቋማት ላይ የድሮን ጥቃት ሊሆን እንደሚችል የገለፀ ቢሆንም የመረጃውን ትክክለኛነት እንዳላረጋገጠ ዘግቧል። መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ የሰጠው መረጃ የለም።
❤3
ግሼን‼️

ዛሬ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ አመታዊው የግሼን ደብረከርቤ ንግስ በዓል ሲከበር ውሏል።❤️❤️❤️
❤22👏1
አዲስ አበባ በሚገቡ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ከዛሬ መስከረም 22 አስከ 24  ቀን ድረስ የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የጉዞ ገደብ ተጣለ።
 
1.  በሱሉልታ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ በጫንጮ እና ፍቼ ከተሞች እንዲቆሙ
 
2.  በገላን ገበያ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ሽኖ እና ሰንዳፋ ከተማ፣
 
3. በቡራዩ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሆለታ ከተማ እንዲቆሙ፣
 
4.  በሰበታ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ደግሞ ወሊሶ ከተማ እንዲቆሙ ተወስኗል።
 
5.  በተጨማሪም በአዳማ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ እና ከአዲስ አበባ የሚወጡ ተሽከርካሪዎች በፍጥነት መንገድ  ብቻ መጠቀም የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።
 
በሌላ በኩልም በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ያሉ የጉዞ አውቶብሶች፣ የታክሲዎች፣ የህዝብ ትራንስፖርት፣ የቤት ተሽከርካሪዎች እና ሌሎችም ከመስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጁላቸው በቂ የፓርኪንግ ቦታዎች ብቻ እንዲቆሙ ጥሪ አድርጋል፡፡
የህወሓት ኃይሎች መዲናዋን ለቅቀው መውጣታቸውን የክልሉን ጋዜጠኛ እና ነዋሪዎችን ጠቅሶ የፈረንሳይ የዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) ዘገበ። ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር በመሆን ከትግራይ ኃይሎች ጋር እየተዋጋ ያለው 'የትግራይ የሰላም ኃይሎች' በበኩሉ የክልሉን ዋነኛ አውሮፕላን ማረፊያ መቆጣጠሩን መግለጹን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
Latest update!
የኢፌድሪ አዲሱ መንግስት ምስረታ በዛሬው እለት ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን፤ በጠዋት የታቀደው ቀጥታ ስርጭት እስካሁን አልጀመረም።
😁3❤1
የምስራች‼️

​በትግራይ ክልል ታግደው የነበሩ የባንክ ሂሳቦች ተለቀው ሥራ መጀመራቸው ተገለጸ።
❤5👏2😁1