AppTech Learning Center
231 subscribers
25 photos
4 links
Internationally Accredited Learning Center in Addis Ababa
Download Telegram
ኮምፒውተሮች ሽባ ሆነው ዋሉ፤

ዛሬ አርብ አያሌ ሆስፒታሎች፣ አየር መንገዶች፣ አነሥተኛ የንግድ ድርጅቶች እና የግል ኮምፒውተሮች ሳይቀሩ "ሰማያዊ ሰሌዳ" (Blue Screen) መስለው፣ ከአገልግሎት ጥቅም ውጪ ሆነው ውለዋል። በዚህም ሰበብ አየር መንገዶች በረራ አቋርጠው ተጓዦች ሲጉላሉ ውለዋል። ሆስፒታሎችና ሌሎች ድርጅቶችም ሥራ ፈትተው ውለዋል። አሶሼትድ ፕሬስ እንዳለው ከሆነ የችግሩ ሰበብ የሶፍትዌር ዕድሳት (software update) ነው።

"A faulty software update caused technological havoc worldwide on Friday, grounding flights, knocking down some financial companies and news outlets, and disrupting hospitals, small businesses and government offices" ነው ያለው።

CrowdStrike/ ክራውድስትራይክ የተባለ "cybersecurity firm/ ድርጅት" ነው የሶፍትዌሩ ባለቤት። ድርጅቱ ላይ የተከሰተው ችግር ደንበኛ መሥሪያ ቤቶቹ የሚጠቀሙት Microsoft Windows ላይ ችግር በመፍጠሩ ከአየር መንገድ እስከ ሆስፒታል ድረስ ሥራቸውን ለማቆም ተገድደው ውለዋል። ችግሩ አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልተቀረፈም ::

የዓለማችን አብዛኛው ሀብትና ንግድ በጥቂት ድርጅቶች የሚንቀሳቀስ ስለሆነ አንድ ቦታ ችግር ሲፈጠር ሁሉም ተያይዞ ገደል ይገባል። የከፋ ችግር አይምጣ ነው እንጂ ቢመጣ ዓለማችን ምን ያህል ተጋላጭ እንደሆነ እያየነው ነው።
1👍1🔥1🤔1🥱1🥴1
👍21
6🙏4
“ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ የለም።
  — ሉቃስ 24፥5
  መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንልን።
🥰21🙏1