AppTech Learning Center
231 subscribers
25 photos
4 links
Internationally Accredited Learning Center in Addis Ababa
Download Telegram
ቴሌግራማቹን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ📵

ቴሌግራም ላይ ከማንኛውም ሰው በ cutt.ly ወይም bit.ly የሚጀምር ማንኛውም ሊንክ ተልኮላችሁ ስታገኙ እንዳትከፍቱት ምክንያቱም ሰሞኑን የመጣ ቫይረስ አለ ሙሉ ለሙሉ የተፃፃፋችሁትን እና Join ያደረጋችሁትን ቻናሎች ሁሉ ያጠፋውና እንደ አዲስ ነው አካውንት ክፈቱ የሚላቹ ይሔ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ነው ።

👉እንደዚህ ዓይነት ሊንኮች በምታውቋቸው ሰዎች ስም ጭምር ሊላክላችሁ ይችላል ነገር ግን በጭራሽ እንዳትከፍቱ።

👉በተጨማሪም ከሀከሮች አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት Password Two-Step Verification(Go through the previous Post ) On አድርጉ!
👍8
"ሕፃን: ተወልዶናል: ወንድ: ልጅም: ተሰቶናል: አለቅነቱም: በጫንቃዉ: ላይ: ይሆናል። ስሙም: ድንቅ: መካር: ሃያል: አምላክ: የዘላለም: አባት: ተብሎ: ይጠራል።"ኢሳ.9-6.
እንኳን: ለጌታችን: ለመድኃኒታችን: ለኢየሱስ:ክርስቶስ: የልደት:በዓል:በሰላም: አደረሳችሁ። በዓሉ: የሰላም: የፍቅር: የመተሳሰብ: ጊዜ: ይሁንልን።
🙏5🥰3👍1
1🔥1
ኮምፒውተሮች ሽባ ሆነው ዋሉ፤

ዛሬ አርብ አያሌ ሆስፒታሎች፣ አየር መንገዶች፣ አነሥተኛ የንግድ ድርጅቶች እና የግል ኮምፒውተሮች ሳይቀሩ "ሰማያዊ ሰሌዳ" (Blue Screen) መስለው፣ ከአገልግሎት ጥቅም ውጪ ሆነው ውለዋል። በዚህም ሰበብ አየር መንገዶች በረራ አቋርጠው ተጓዦች ሲጉላሉ ውለዋል። ሆስፒታሎችና ሌሎች ድርጅቶችም ሥራ ፈትተው ውለዋል። አሶሼትድ ፕሬስ እንዳለው ከሆነ የችግሩ ሰበብ የሶፍትዌር ዕድሳት (software update) ነው።

"A faulty software update caused technological havoc worldwide on Friday, grounding flights, knocking down some financial companies and news outlets, and disrupting hospitals, small businesses and government offices" ነው ያለው።

CrowdStrike/ ክራውድስትራይክ የተባለ "cybersecurity firm/ ድርጅት" ነው የሶፍትዌሩ ባለቤት። ድርጅቱ ላይ የተከሰተው ችግር ደንበኛ መሥሪያ ቤቶቹ የሚጠቀሙት Microsoft Windows ላይ ችግር በመፍጠሩ ከአየር መንገድ እስከ ሆስፒታል ድረስ ሥራቸውን ለማቆም ተገድደው ውለዋል። ችግሩ አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልተቀረፈም ::

የዓለማችን አብዛኛው ሀብትና ንግድ በጥቂት ድርጅቶች የሚንቀሳቀስ ስለሆነ አንድ ቦታ ችግር ሲፈጠር ሁሉም ተያይዞ ገደል ይገባል። የከፋ ችግር አይምጣ ነው እንጂ ቢመጣ ዓለማችን ምን ያህል ተጋላጭ እንደሆነ እያየነው ነው።
1👍1🔥1🤔1🥱1🥴1
👍21
6🙏4
“ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ የለም።
  — ሉቃስ 24፥5
  መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንልን።
🥰21🙏1