በትላንትናው እለት በቻይና ከሽፎ ወደ ምድር የወደቀው የ SVOM launch ሮኬት በቦታው ሁኔታውን ካዩ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተቀረፀ ምስል ሲሆን
2ተኛው ደግሞ ሀገራቶች ጨረቃ ላይ ለሚያደርጉት የሳይንስ ጦርነት በዚሁ ቪዲዮ ስር የተሰጡ ሀሳቦች እንዲሁም ተቃራኒ ተገዳዳሪ ሀገራቶች አላማቸው ሲከሽፍ በሌላ ሀገር ባሉ ጠፈርተኞች ሲብጠለጠሉ እንዲሁም
ይህ ወደ ምድር የወደቀው ሮኬት በተደጋገመ ጊዜ በአካባቢው እንዲሁም በሰው ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ በስሩ ገልፀዋል ይህም የቻይና ጠፈርተኞች አስቀድመው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተናግረዋቸዋል🤒 በጨረቃ ላይ የሚደረገው የአዲስ(ድንግል) የጨረቃ ክፍል ጉዞ ትንቅንቅ እንደቀጠለ ነው🌘
ምንጭ china space flight
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!

👍2
የምሽት እይታ የአባይ ወንዝ ከ አይኤስኤስ(ISS) የተለቀቀውን ምስል እንካቹ አልኩኝ😯
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
👍4❤2
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በዚህ ሚስጥራዊ የምድራችን ስፍራ አንታርክቲካ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ከነበራቸው የአለም መንግስታት ውስጥ የሁለተኛው አለም ጦርነት ዋና አቀጣጣይ የነበረው የጀርመኑ ናዚ መንግስት በዋናነት ይጠቀሳል። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ናዚዎች እስከሚሸነፉበት ጊዜ ድረስ ከአንታርክቲካ ጋር የተገናኘ አንዳች ሚስጥራዊ ተልእኮን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ነበሩ።
ናዚዎች ጥርነቱን መሸነፋቸውን ተከትሎ እንደ America, england,እና Russia ያሉ የአለማችን ታላላቅ መንግስታቶችን አሁንም ድረስ ለበርካቶች ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ሙሉ ትኩረታቸውን አንታርክቲካ ላይ አድርገዋል። ይህን የሀያላኑ ሀገራት ሚስጥራዊ ተልዕኮ መሰረት በማድረግ ላለፉት በርካታ አመታት በአንታርክቲካ ዙሪያ ብዙ Conspiracy theoryዎች መሰማት ችለዋል። አንዳንዶች ከአንታርክቲካ በረዶ ግግር ስር ሺህ ዘመናትን ያስቆጠሩ እንደ pyramid ያሉ እጅግ አስገራሚ ጥንታዊ ስልጣኔ ቅሪቶች ሊገኙ እንደሚችሉ ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ አሁን ላይ በሰፊው መታየት በጀመሩት በማይታወቁ በራሪ አካላት ወይም UFO ዎች እና በሚስጥራዊው የአንታርክቲካ ግዛት መካከል አንዳች ግንኙነት ሳይኖር እንደማይቀር ይናገራሉ። እንደ አውሮፓውያ ዘመን አቆጣጠር በ1969 አመተ ምህረት ናሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ ላይ ማረፍ በቻለበት mission ላይ ተሳታፊ የነበረው Buzz aldrin የተሰኘው ተመራማሪ በአንድ ወቅት አንታርክቲካ ላይ የተገኘ አንድ ሚስጥራዊ ነገር የመጎብኘት እድል አግኝቶ ነበር። ይህ ተመራማሪ ጉብኝቱን ጨርሶ ወደ ቤቱ ከተመለሰ በሗላ ለማንም ያልነገረው በጉብኝቱ ጊዜ ያየው እና ያስጨነቀው አንዳች ነገር እንደነበር በቅርቡ የሚገኙ ሰዎች ተናግረዋል። ከቀናቶች በሗላ ይህ ተመራማሪ.... ክፍል 2 ነገ 1 ሰአት ይቀጥላል

👍14❤3
ክፍል - 2 "ሁላችንም አደጋ ላይ ነን"Buzz aldrin
ከቀናቶች በሗላ ይህ ተመራማሪ በ twitter አካዎንቱ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ፅፎ ነበር "we all are in dangers"(ሁላችንም አደጋ ላይ ነን)የሚል ፅሁፍ አስቀምጦ ብዙም ሳይቆይ ወዲያው የፃፈውን ከገፁ ላይ ደልቶታል። ነገር ግን ብዙዎች ጋር ደርሶ ስለነበር በስክሪን ሹት ተይዞ ለምን እንደዛ ሊል ቻለ ? ለምንስ መልሶ ማጥፋት አስፈለገ ? ምንድን ነበር ሊነግረን ፈልጎ የዋጠው በሚል ብዙዎች ቪዲዮ ሰርተውበታል። ይህ ያልተመለሰ እና በበዝ አድሪል ብቻ ታፍኖ ያለ ያልተዘጋ ዶሴ ነው እኔም ከተአማኒ ገፆች ላይ ያለውን የሱን መልእክት ከላይ በምስል 1 አጋርቻችሗለው።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1947 አሜሪካ በአንታርክቲካ ላይ ባደረገችው አሰሳ እና ጥናት ላይ ዋና ተሳታፊ የነበረው ከላይ በምስሉ 2 ያስቀመጥኩት Admiral richardson የሰጠው መረጃ ደግሞ በአንታርክቲካ ዙሪያ ይሰሙ የነበሩ የconsipiracy theoryዎች የበለጠ እንዲቀጣጠሉ አድርጓል። Admiral richardson በአንታርክቲካ እና በአርክቲክ አካባቢዎች ባደረገው ሰፊ አሰሳ እና ጥናት ይታወቃል።
ነገር ግን ይህ ሰው በአንድ ወቅት ወደ ውስጠኛው የምድራችን ክፍል ስላደረገው ያልተለመደ ጉዞ የሚያውቁ ሰዎች በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ1947 አመተ ምህረት መስከረም ወር ላይ Admiral richardson አውሮፕላኑን አስነስቶ አቅጣጫውን በአንታርክቲካ ሰማይ ላይ አድርጎ በማብረር ላይ እያለ....
ክፍል 3 ይቀጥላል...

👍16🔥2❤1
ሁለት ምንነታቸው የማይታወቁ በራሪ አካላት ከፊት ለፊት ያቋርጡትና አውሮፕላኑ ሙሉ ለሙሉ ከቁጥጥሩ ውጪ ይሆንበታል ።ይህን ተከትሎ በማይታወቁ በራሪ አካላት መሪነት አውሮፕላኑ ወደ አንድ አቅጣጫ መጓዝ ይጀምራል። ከቆይታ ጉዞ በሗላ በበረዶ በተከበበ አንድ ዋሻ ውስጥ አውሮፕላኑን ያርፋል። እንደ አድሚራል ሪቻርድሰን መረጃ ከሆነ አውሮፕላኑ ከሱ ቁጥጥር ውጪ ሆኖ በዛ በዋሻ ውስጥ እንደገባ እና በዋሻው ውስጥም አንድ ረቂቅ ታላቅ ስልጣኔ የሚገኝበት ልዩ ስፍራ ላይ መድረስ እንደቻለ ይናገራል።
በዚህ ሚስጥራዊ የምድር ስር ግዛት ውስጥ በሰው ሊገነባ የማይቻል እጅግ የረቀቀ ስልጣኔ ከማስተዋሉም በተጨማሪ ሌሎች ሚስጥራዊ ነገሮችን ማየቱን የግል ህይወቱን በሚተርከው መፅሀፉ ውስጥ ፅፎታል። ይህን የአድሚራል ሪቻርድሰን መረጃን ተከትሎ አንታርክቲካ ምድር ውስጥ ወደሚገኝ የሚስጥራዊ አለም የሚወስድ መተላለፊያን የያዘ ግዛት እንደሚሆን ተመራማሪያን ያወሳሉ ለዚህም ነው ሀያላን ሀገራት አሁንም ድረስ በየፊናቸው አንታርክቲካ ላይ ምርምራቸውን እየከወኑ ያሉት። ከላይ የጠቀስኩላቹን የአድሚራል ሪቻርድ መረጃ ትልቁ የ HISTORY የዩቱብ ቻናል በሚገርም መልኩ በተማራማሪዎች አስውቦ አጠር ቀንጨብ አርጎ ዘግቦታል ሊንኩ 👉https://youtu.be/66SP6IGBn9Y?si=ftuZ_BLvL6FbVxQL
ጨርሰናል። ሀሳብ ካለ ማጋራት ይፈቀዳል
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
በዚህ ሚስጥራዊ የምድር ስር ግዛት ውስጥ በሰው ሊገነባ የማይቻል እጅግ የረቀቀ ስልጣኔ ከማስተዋሉም በተጨማሪ ሌሎች ሚስጥራዊ ነገሮችን ማየቱን የግል ህይወቱን በሚተርከው መፅሀፉ ውስጥ ፅፎታል። ይህን የአድሚራል ሪቻርድሰን መረጃን ተከትሎ አንታርክቲካ ምድር ውስጥ ወደሚገኝ የሚስጥራዊ አለም የሚወስድ መተላለፊያን የያዘ ግዛት እንደሚሆን ተመራማሪያን ያወሳሉ ለዚህም ነው ሀያላን ሀገራት አሁንም ድረስ በየፊናቸው አንታርክቲካ ላይ ምርምራቸውን እየከወኑ ያሉት። ከላይ የጠቀስኩላቹን የአድሚራል ሪቻርድ መረጃ ትልቁ የ HISTORY የዩቱብ ቻናል በሚገርም መልኩ በተማራማሪዎች አስውቦ አጠር ቀንጨብ አርጎ ዘግቦታል ሊንኩ 👉https://youtu.be/66SP6IGBn9Y?si=ftuZ_BLvL6FbVxQL
ጨርሰናል። ሀሳብ ካለ ማጋራት ይፈቀዳል
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
👍16❤3
⭕ሳይንቲስቶች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ ላይ ዋሻ ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል።
ዋሻው ቢያንስ 100 ሜትር ጥልቀት እንዳለው የተጠቀሰ ሲሆን፤ ለሰዎች መኖሪያ ቋሚ መሠረት ለመገንባት ተስማሚ ቦታ ሊሆን ይችላል ብለዋል ሳይንቲስቶቹ።
🔻ዝርዝር መረጃውን ነገ ከተንቀሳቃሽ ምስል ጋር አያይዤ እለቅላችሗለው
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
ዋሻው ቢያንስ 100 ሜትር ጥልቀት እንዳለው የተጠቀሰ ሲሆን፤ ለሰዎች መኖሪያ ቋሚ መሠረት ለመገንባት ተስማሚ ቦታ ሊሆን ይችላል ብለዋል ሳይንቲስቶቹ።
🔻ዝርዝር መረጃውን ነገ ከተንቀሳቃሽ ምስል ጋር አያይዤ እለቅላችሗለው
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
👍10❤5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌘በጨረቃ ላይ ስለተገኘው ዋሻ❗
የሰው ልጅ በቋሚነት በጨረቃ ላይ መኖር መቻሉን ለማረጋገጥ ሀገራት እየተሽቀዳደሙ ይገኛሉ።
ሳይንቲስቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ ላይ ዋሻዎች እንዳሉ የተገነዘቡት ከ50 ዓመታት በፊት ነበር። እ.ኤ.አ. በ2010 ደግሞ ሳይንቲስቶች የዋሻ መግቢያዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብለው ያሰቧቸውን ጉድጓዶች ፎቶ ማግኘት ቻሉ።
ነገር ግን ተመራማሪዎቹ ዋሻዎቹ ምን ያህል ጥልቅ ሊሆኑ እንደሚችሉ ወይም ሊፈርሱ እንደሚችሉ ማወቅ አልቻሉም ነበር።
የጣሊያን ትሬንቶ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች ፕሮፌሰር ሎሬንዞ ብሩዞን እና ፕሮፌሰር ሊዮናርዶ ካርረር፤100 ሜትር ያህል ጥልቀት እንዳለው የተገመተውን ዋሻ ማግኘታቸው ለጥያቄው መልስ እንደሰጠ ተገልጿል።
ምንም እንኳን የዋሻውን አጠቃላይ ስፋት ለመረዳት ብዙ የሚቀረው ነገር እንዳለ ቢነገርም።
ሳይንቲስቶቹ ወደ ዋሻው ዘልቆ ለመግባት ራዳር የተጠቀሙ ሲሆን፤"ማሬ ትራንኩሊታቲስ" በተባለው አለታማ ሜዳ ላይ ያለው ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ዋሻውን አግኝተዋል ነው ተባለው።
ዋሻው እስካሁን ሙሉ በሙሉ አለመመርመሩ የተገለጸ ሲሆን፤ ተመራማሪዎቹ ግን መሬት ላይ ዘልቆ የሚገባው ራዳር፣ ካሜራዎች ወይም ሮቦቶች ካርታውን ለመመርመር እንደሚጠቅሙ ተስፋ ያደርጋሉ።
በዋሻው ውስጥ ያሉት ቋጥኞች በጠፈር የአየር ጠባይ የተበላሹ ወይም የሚሸረሸሩ ስላልሆኑ፤ በቢሊዮን ለሚቆጠሩ ዓመታት ወደ ኋላ የተመለሰ ሰፊ የጂኦሎጂ መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ ሲል BBC ዘግቧል።
🔻ሌሎች ትኩስ መረጃዎችንም እያሰባሰብኩ ነው። ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja

👍13❤4🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የናሳ አስተዳዳሪ የሆነው Bill Nelson በትዊተር ገፁ እንዲህ ሲል ተናግሯል 🌒"በዚህ ትልቅ የጠፈር ማጓጓዣ መገጣጠሚያ ህንፃ ውስጥ ቆመናል። እና ከኋላዬ ያለው የጠፈር ማስጀመሪያ ስርዓት የመጀመሪያው ደረጃ ነው። ወደ ጨረቃ የሚያጓጉዘው ይህ ሲሆን, 212 ጫማ ከፍታ አለው፣ በጠቅላላው 320 ጫማ አካባቢ።
ይህ ወርቃማ የጠፈር ምርምር ዘመን ነው፣ ምክንያቱም ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ሰዎችን ወደ ጨረቃ የምኖስድበት ይሆናል ብሎም ወደ ማርስ ለማቅናት የምንችልበት መንገድ ይሆነናል፡፡ እና ይህ ሁሉም ነገር የሚፈረክበት የስራው ጅማሬ ቦታ ነው።" በማለት በትላንትናው እለት ከቦታው ሆኖ መልዕክቱን አስተላልፏል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
ይህ ወርቃማ የጠፈር ምርምር ዘመን ነው፣ ምክንያቱም ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ሰዎችን ወደ ጨረቃ የምኖስድበት ይሆናል ብሎም ወደ ማርስ ለማቅናት የምንችልበት መንገድ ይሆነናል፡፡ እና ይህ ሁሉም ነገር የሚፈረክበት የስራው ጅማሬ ቦታ ነው።" በማለት በትላንትናው እለት ከቦታው ሆኖ መልዕክቱን አስተላልፏል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja
@Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
👍11❤7
ሰበር:- የቻይና ተመራማሪዎች በጨረቃ ላይ መኖርያ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጡብ እያመረቱ ነው
ከፍተኛ ቴክኖሎጂን የተላበሱ ናቸው የተባሉት ጡቦች በጨረቃ ላይ የምርምር ጣብያዎችንና የመኖርያ ቤቶችን ለመገንባት ይውላሉ ተብሏል።
ጡቦቹ በምድር ላይ ጥቅም ላይ ከሚውሉት ቀይ ጡቦች እና የግንባታ ብሎኬቶች ሶስት እጥፍ ጥንካሬ አላቸው
ቻይና በጨረቃ ላይ መኖርያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችሉ “ሉናር ብሪክስ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸውን ጡቦች በማምረት ላይ እንደምትገኝ ተነገረ፡፡
የሀገሪቱ ተመራማሪዎች በቅርብ ጊዜ ውስጥ በዓለም ላይ የመጀመሪያውን የምርምር ጣብያ እና መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያገለግሉ የጨረቃ አፈርን ጨምሮ የተለያዩ ቴክኖሎጂን የተላበሱ ጡቦችን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ጨረቃን ለመቆጣጠር እና አዳዲስ ግኝቶችን ለማስተዋወቅ አለምአቀፋዊ ፉክክር ውስጥ ከፊት ከሚጠቀሱ ሀገራት መካከል ቤጂንግ አንዷ ስለመሆኗ ሚስጥር አይደለም፡፡
በዚህ አመት መጀመሪያ ላይም ከዚህ ቀደም ተደርሶበት በማይታወቅ በጨረቃ የጨለማ ክፍል ላይ መንኮራኩሯን በማሳረፍ ጠቃሚ የአፈር ናሙናዎችን ወደ ምድር ይዛ በመምጣት የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።
ሰዎችን ጨረቃ ላይ ማሰረፍ እና ለረጅም ጊዜ ማቆየት ደግሞ ቀጣዩ እቅዷ ይመስላል።
በዚህም አካላዊ ግፊት እና ከጸሀይ የሚመጣን ከፍተኛ ጨረር መቋቋም ይችላል የተባለው “ሉናር ሶይል ብሪክስ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ጡብ በ2025 ወደ ጨረቃ ተልኮ እስከ አመቱ መጨረሻ ሙከራ እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡
በሙከራ ጊዜው ጨረቃ ከፍተኛ መጠን ያለው የጠፈር ጨረሮች (ኮስሚክ ራድየሽን) ስላላት ተመራማሪዎች ጡቦች በጨረቃ ላይ የሚገኝውን ጨረር ምን ያህል መቋቋም እንደሚችሉ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ፡፡
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!

👍19❤7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Breaking ዛሬ ከምሽቱ 1:30 ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ በርካታ ዞኖች ይህ በቪድዮ ላይ የሚታየው ግዙፍ 'ነገር' ሰማይ ላይ መታየቱን በአካባቢ ያሉ ሰዎች መመልከታቸውን እያሳወቁኝ ይገኛሉ
ምዕራብ ጉጂ ዲምቱ አካባቢ ያለ አንድ ነዋሪ "በጣም አስፈሪ የሆነ ግዙፍ ነገር ከሰማይ ሲወርድ ነበር፣ ግቢ ውስጥ ያለነው ሰራተኞች በግርምት ተሰባስበን ነው ያየነው። እየተቀጣጠለ ሚወርድ ነው ሚመስለው፣ ክስተቱ የሕዋ ከሆነም ብታጣሩልን" በማለት ገልፆታል።
ቪድዮው ላይ የሚታየው ምን እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ካሳውቁ የማጋራቹ ይሆናል።
በቅርብ ቀናት የጠፈር ስብርባሪ ኬንያ ውስጥ ባለ አንድ ገጠራማ ቦታ መውደቁ ይታወሳል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
ምዕራብ ጉጂ ዲምቱ አካባቢ ያለ አንድ ነዋሪ "በጣም አስፈሪ የሆነ ግዙፍ ነገር ከሰማይ ሲወርድ ነበር፣ ግቢ ውስጥ ያለነው ሰራተኞች በግርምት ተሰባስበን ነው ያየነው። እየተቀጣጠለ ሚወርድ ነው ሚመስለው፣ ክስተቱ የሕዋ ከሆነም ብታጣሩልን" በማለት ገልፆታል።
ቪድዮው ላይ የሚታየው ምን እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ካሳውቁ የማጋራቹ ይሆናል።
በቅርብ ቀናት የጠፈር ስብርባሪ ኬንያ ውስጥ ባለ አንድ ገጠራማ ቦታ መውደቁ ይታወሳል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
👍9❤2
#አዲስመረጃ ትናንት ምሽት በደቡባዊ ኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የታየው ክስተት የሰው ሰራሽ ጠፈር ስብርባሪ ወደ ምድር ንፍቀ ክበብ ሲመለስ የተፈጠረ መሆኑን የአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ አስታወቀ
- ስብርባሪው የቻይና ሺጂያን-19 መንኩራኩር ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል
ትናንት ከምሽቱ 1:30 ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ በርካታ ዞኖች አንድ ግዙፍ 'ክስተት' ሰማይ ላይ መታየቱን በአካባቢ ያሉ ሰዎች መመልከታቸውን ሲናገሩ እና ምስሎችን ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲያጋሩ ቆይተዋል።
በዚህ ዙርያ ስፔስ ኤጀንሲ (European Space Agency) እንደለፀው በኢትዮጵያ እንዲሁም በአጎራባች የታየው ክስተት ሰው ሰራሽ የጠፈር ቁስ ስብርባሪ ወደ ምድር ንፍቀ ክበብ ሲመለስ (re-entry ሲያደርግ) መሆኑን አብራርቷል።
ኤጀንሲው አክሎም ስብርባሪው የቻይናው ሺጂያን-19 (ShiJian-19) ሊሆን እንደሚችል ጨምሮ ገልጿል።
"በየአመቱ ከመቶ ቶን በላይ የሰው ሰራሽ የጠፈር ቁሶች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው ወደ መሬት ይመለሳሉ" ያለው የአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ ይህም በየአመቱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ክስተቶች መታየት ምክንያት ነው ብሏል።
አክሎም "አንዳንዱ [የጠፈር ቁስ ስብርባሪ] መሬት ላይ ሊወድቅ ይችላል፣ ነገር ግን እንደ ጠፈር ሮኬት ያሉ ሁሉንም ቁሶች ተቆጣጥሮ ሰው በማይኖርበት አካባቢ እንዲወድቁ ማድረግ አይቻልም። አነስተኛ ቁሶች ራሳቸው ተቃጥለው ያልቃሉ፣ ትልልቅ አካላትን ግን ተቆጣጥሮ ወደ ምድር መመለስ ገና እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፣ እድገቱም ዘገምተኛ ነው" በማለት የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ተናግሯል።
የትናንት ምሽቱ ክስተት እንደ ምዕራብ ጉጂ፣ ወላይታ፣ አርባ ምንጭ እና ሞያሌ አካባቢ መታየቱ የተገለፀ ሲሆን በኬንያ ማርሳቢት ግዛትም መታየቱ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በበኩሉ የክስተቱን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ሁኔታውን በቅርበት እያጣራን እንደሚገኝ አስታውቋል።
የጠፈር ስብርባሪ ማለት አገልግሎታቸው ያበቃ ሳተላይቶች፣ ግልጋሎት የማይሰጡ መንኩራኩሮች፣ የሮኬት ማቀጣጠያ ተተኳሾች፣ ከጠፈር ላይ ግጭት የተረፉ ስብርባሪዎች እንዲሁም በጠፈር በረራ ወቅት ተገንጥለው ያመለጡ ቁሳቁሶች ሊሆኑ እንደሚችሉ መረጃዎች ይጠቀማሉ።
እነዚህ በከፍተኛ ፍጥነት የሚጓዙ ስብርባሪዎች ለሌሎች ሳተላይቶች ስጋት ቢሆኑም መሬት ላይ ላሉ ሰዎች የሚፈጥሩት የሞት ወይም የአካል ጉዳት ስጋት ከአንድ ትሪሊየን ውስጥ አንድ ብቻ መሆኑን የ 'ዘ ኦሮስፔስ ኮርፖሬሽን' መረጃ ይጠቁማል።

👍10
ዛሬ ጥር 4,2017 መቱ ላይ በ2:01 ላይ (በጠዋቱ) የፀሐይዋ ቀለም ይህን ይመስል ነበር። ምንድነው ብላቹ ታስባላቹ ?
ሰሞኑን በኢትዮጵያን(መሬት መንቀጥቀጥ) እንዲሁም በአሜሪካ(እየቀጠለ ያለው ሰደድ እሳት) እና በተለያዩ ሀገራት እየታየ ያለው climate change ጥሩ እንዳልሆነ ይታወቃል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
ሰሞኑን በኢትዮጵያን(መሬት መንቀጥቀጥ) እንዲሁም በአሜሪካ(እየቀጠለ ያለው ሰደድ እሳት) እና በተለያዩ ሀገራት እየታየ ያለው climate change ጥሩ እንዳልሆነ ይታወቃል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
👍11❤2
🗣"ወደ ማርስ🌔 እንሄዳለን" Donald trump🥵
በበአለ ሲመታቸው ላይ "በኔ ስልጣን ዘመን ወደ ማርስ እንሄዳለን የአሜሪካንን ባንዲራም እንተክላለን በማለት ተናግረዋል ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ" ኤለን መስክም ደስታቸውን ሲገልፁ ታይተዋል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
በበአለ ሲመታቸው ላይ "በኔ ስልጣን ዘመን ወደ ማርስ እንሄዳለን የአሜሪካንን ባንዲራም እንተክላለን በማለት ተናግረዋል ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ" ኤለን መስክም ደስታቸውን ሲገልፁ ታይተዋል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
👍7❤1
ሰበር፦ የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለ
የአሜሪካ ጠፈር ሳይንስ ምርምር ማዕከል ወይም ናሳ እንደገለጸው ከሆነ አሜሪካ በዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ በመቶዎች እጥፍ ሀይል ያለው የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ወደ ምድር እየመጣ ነው ብሏል፡፡
የአንድ ስታዲየም ስፋት መጠን አለው የተባለው ይህ የጠፈር አለት በመጠኑ ባለፉት ስምንት ዓመታት ወደ ምድር ከመጡት ውስጥ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አፍሪካ፣ ፓስፊክ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ ይህ ጠፈር አለት ያርፍበታል ተብሎ ከሚጠበቁ ቦታዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ስለዚህ የተሰጋለት የጠፈር አለት ምንነት ? መቼ ያርፋል ተብሎ ይጠበቃል ? መረጃውን አሰባስቤ ወዲያው እማጋራቹ ይሆናል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
የአሜሪካ ጠፈር ሳይንስ ምርምር ማዕከል ወይም ናሳ እንደገለጸው ከሆነ አሜሪካ በዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ በመቶዎች እጥፍ ሀይል ያለው የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ወደ ምድር እየመጣ ነው ብሏል፡፡
የአንድ ስታዲየም ስፋት መጠን አለው የተባለው ይህ የጠፈር አለት በመጠኑ ባለፉት ስምንት ዓመታት ወደ ምድር ከመጡት ውስጥ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አፍሪካ፣ ፓስፊክ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ ይህ ጠፈር አለት ያርፍበታል ተብሎ ከሚጠበቁ ቦታዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ስለዚህ የተሰጋለት የጠፈር አለት ምንነት ? መቼ ያርፋል ተብሎ ይጠበቃል ? መረጃውን አሰባስቤ ወዲያው እማጋራቹ ይሆናል።
ለተጨማሪ: @Andromeda_Mereja ን ይከታተሉ !እንዲሁም ለወዳጆ ያጋሩ!
👍19❤2
ኤኤፍፒ የጠፈር ሳይንስ ባለሙያው ብሩስ ቤትስን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የጠፈር አለቱ እንዲሰባበር እና ጉዳት ወደ ማያደርስ ቦታ ለማሳረፍ ጥረቶች በመደረግ ላይ ነው፡፡
ዓለም አቀፉ የጠፈር አለት ማስጠንቀቂያ ማዕከል በበኩሉ ወደ ምድር እየመጣ ያለውን የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ናሳ እንደተነበየው ከሆነ ይህ የጠፈር ዓለት አሁን ባለበት ፍጥነት መሰረት ወደ ምድር በፈረንጆቹ 2032 ላይ ወደ መሬት ይደርሳል፡፡
እስካሁን ባለው የጠፈር አለት ታሪክ ከ66 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የተከሰተው ከፍተኛ ውድመት እንዳደረሰ የተገለጸ ሲሆን 75 በመቶ በምድር ላይ የነበሩ ስነ ህይወቶችን አጥፍቷልም ተብሏል፡፡
ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርዝመት ነበረው የተባለው ይህ የጠፈር ዓለት ባረፈበት ስፍራ ዳይኖሰሮችን ጨምሮ በርካታ ዝርያዎችን እንዳጠፋም ይታመናል፡፡
በቅርቡ ተከስቷል የተባለው የጠፈር አለት በ1908 በሳይቤሪያ የረፈ ሲሆን እስከ 2 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ዛፎችን እንዳቃጠለ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ ወደ ምድር እየመጣ ነው የተባለው ይህ ግዙፍ ዓለት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ካይነቲክ ኢመፓክተር የተሰኘ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጉዳት ወደማያደርስ መልኩ መቀየር እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ይሁንና ይህንን ቴክኖሎጂ ለመተግበር ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የበለጸጉ ሀገራት ወጪውን የሚሸፍኑት በአለቱ ሊጠቁ እንደሚችሉ ከተገነዘቡ ብቻ መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡

👍5❤3
ሰበር:- በማርስ ላይ ምንነቱ ያልታወቀ ቅርጽ ያለው አካል ተገኘ
በናሳ ማርስ ኦርቢተር ካሜራ የተቀረፀው ምስል ‘ቀይዋ ፕላኔት’ በመባል በምትታወቀው ማርስ ላይ ህይወት ሰለመኖሩ አመላካች ነው እየተባለ ነው።
በማርስ ላይ የተገኘው 235 ካሬ ሜትር የሚሆን ስፋት ያለው ምንነቱ ያልታወቀው አካል ባለ አራት ማዕዘን ቅርጽ እንዳለው ከተነሳው ፎቶ ለማዬት ተችሏል።
ሆኖም ምስሉ በባለሙያዎች ሳይንሳዊ ማብራሪያን ባይሰጥበትም ብዙዎች የአልታወቁ በራሪ አካላት (ዩኤፍኦ) ስለመኖራቸው አመላካች ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡
ምስሉ በተለያዩ ማህበራዊ የትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ሲሆን የብዙ ሰዎችን ቀልብ ስቧል። ታዋቂው የፖድካስት አዘጋጅ እና ኮሜዲያን ጆው ሮውገን በኤክስ ገጹ ምስሉን ‘እንግዳ ነገር’ ከሚል ጽሁፍ ጋር አጋርቶት የብዙዎችን ትኩረት መሳብ ችሏል።
አሜሪካዊው ባለሃብት ኤለን መስክ ጉዳዩን የሚመረምሩ ጠፈርተኞች መላክ ይገባናል ሲል ለጆው በኤክስ ላይ ምላሽ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል በማርስ ላይ እንዲህ አይነት ቅርስ መገኘቱ ምንም አዲስ ነገር አይደለም፣ ምናልባትም በንፋስ እና በአፈር መሸርሸር የተፈጠረ ሊሆን ይችላል የሚሉ ወገኖችም መኖራቸውን ሜይል ኦንላይን አስነብቧል።

👍21❤5🔥1
ከ50 ዓመታት በኋላ ወደ ጨረቃ በሚደረገው ታሪካዊ ጉዞ ላይ የተነሣው አስገራሚው የመሬት ምሥል
****
የናሳ የአርቴሚስ-2 ጠፈርተኞች ከመሬት ተነሥተው ወደ ጨረቃ የሚያደርጉትን ጉዞ ግማሽ መንገድ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ፣ አስደናቂ የሆነ የመሬትን ምሥል ከጠፈር ላይ ልከዋል።
ይህ ጉዞ የሰው ልጅ ከ50 ዓመታት በኋላ ከመሬት ምሕዋር ወጥቶ ወደ ጨረቃ እያደረገው የሚገኘው ታሪካዊ ጉዞ ሲሆን፤ በጉዞው ላይ አስገራሚውን የመሬት ምሥል ከሕዋ ላይ በመላክ ሥራቸውን ጀምረዋል።
የተልዕኮው አዛዥ ሪድ ዋይዝማን ያነሡት እና "ሄሎ ወርልድ" የተሰኘው ምሥል፣ መሬት ከኦሪዮን መንኮራኩር መስኮት በኩል እንዴት እንደምትታይ የሚያሳይ ሲሆን፤ በምሥሉ ላይ ሰፊው የአትላንቲክ ውቅያኖስ፣ የምዕራብ ሰሃራ እና የአይቤሪያን ልሳነ ምድር ጎልተው ይታያሉ።
ዋይዝማን መጀመሪያ ላይ ፎቶግራፉን ለማንሣት አስቸጋሪ እንደነበር ገልጸው፣ ፎቶውን ለማንሣት ሲሉ የብርሃን መጠንን (Exposure) ማስተካከል ፈታኝ ሆኖባቸው እንደነበር ለቁጥጥር ማዕከሉ ተናግረዋል።
ጠፈርተኞቹ ይህንን ወሳኝ ምዕራፍ ያሳኩት መንኮራኩሯ ከመሬት ከተነሳች ከሁለት ቀናት ከአምስት ሰዓታት በኋላ ነው።
አርቴሚስ-2 ጠፈርተኞቹን ይዛ በጨረቃ ዙሪያ በመዞር ወደ መሬት የምትመለስ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ ሚያዝያ 6 መንኮራኩሯ በጨረቃ የጀርባ አቅጣጫ (Far Side) ትዞራለች።
ናሳ እ.ኤ.አ በ1972 በአፖሎ 17 ጠፈርተኞች ከተነሣው ምሥል ጋር የአሁኑን ምሥል በማነጻጸር፣ "ባለፉት 54 ዓመታት ብዙ ርቀት ተጉዘናል፤ ነገር ግን አንድ ያልተለወጠ ነገር አለ፦ መኖሪያችን መሬት አሁንም ከጠፈር ስትታይ እጅግ ውብ ናት!" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ታሪክ ተሰርቷል፡ የአርቴሚስ 2 (Artemis II) ጠፈርተኞች በሰላም ወደ ምድር ተመለሱ!
ከግማሽ ክፍለ ዘመን ቆይታ በኋላ የሰውን ልጅ ወደ ጨረቃ ምህዋር ይዞ የተጓዘው የናሳ (NASA) ታሪካዊው የአርቴሚስ 2 ተልዕኮ በድል ተጠናቀቀ።
አራቱ ጠፈርተኞች በጨረቃ ዙሪያ ያደረጉትን የ10 ቀናት ጉዞ አጠናቅቀው፣ ዛሬ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ በሰላም አርፈዋል።
ይህ ተልዕኮ እ.ኤ.አ በ1972 ከተካሄደው የአፖሎ ፕሮግራም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰውን ልጅ ወደ ጨረቃ አቅራቢያ ያደረሰ ድንቅ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።
ጠፈርተኞቹ ጨረቃ ላይ ባያርፉም፣ የወደፊቱን የሰው ልጅ የጨረቃ ላይ ኑሮ እና ወደ ማርስ የሚደረገውን ጉዞ የሚያሳልጥ ወሳኝ መረጃዎችን ይዘው ተመልሰዋል።
ጠፈርተኞቹ ከምድር ርቀው እስከ 400,000 ኪሎ ሜትር በመጓዝ የሰው ልጅ በጠፈር ታሪክ የተጓዘበትን ከፍተኛ ርቀት አስመዝግበዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ አንዲት ሴት እና ጥቁር አሜሪካዊ ጠፈርተኛን የያዘው ይህ ቡድን፣ የጠፈር ምርምርን የሁሉንም ዘር እና ጾታ ተሳትፎ ያረጋገጠበት ሆኖ ተመዝግቧል።
የአርቴሚስ 2 ስኬት የሰው ልጅ በጨረቃ ላይ በቋሚነት እንዲኖር ለታለመው አርቴሚስ 3 (Artemis III) ተልዕኮ አረንጓዴ መብራት አብርቷል።
ይህ ስኬት የአሜሪካ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ሁሉ ድል ነው! የሰው ልጅ ዳግም በጨረቃ ላይ የሚቆምበት ጊዜ እጅግ ቀርቧል።
እንዲሁም አሜሪካውያን እና የዓለም የጠፈር ተመራማሪዎች "ምድርን ጥለን እንሄዳለን" በሚል ሳይሆን፣ የሰውን ልጅ ህልውና ለማስቀጠልና አዳዲስ አማራጮችን ለመፍጠር ሌሊት ከቀን እየሰሩ ይገኛሉ። ዛሬ ላይ ይህ ህልም ከሳይንስ ልብወለድነት ወጥቶ ወደ እውነታነት እየተቀየረ ነው!
via NASA

❤11👍2