እነዚህ መረጃች ህወሓት ዳግም ጦርነት ስለመቀስቀሱ ይጠቁሙ ይሆን ?
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወሓት በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ የሰላም ስምምነት ፊርማ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ መፈረሙ ይታወሳል፡፡ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ዝርዝር ዕቅድ ላይ በኬንያ ናይሮቢ ለቀናት የተካሄደው ውይይትም በስምምነት ፊርማ ተቋጭቷል፡፡ ኢትዮጵያ ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት ያላትን ቁርጠኝነት በተለያየ መንገድ የገለጸች ሲሆን፤ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴም ገብታለች፡፡
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን ህወሓት በአደባባይ ለሰላም ስምምነቱ ተገዢ መሆኑን እየገለጸ ሲለው በህቡዕ ሲያሰኘው ደግሞ በግልጽ ከሰላም ስምምነቱ ተቃራኒ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡
ህወሓት ከሚቆጣጠራቸው የትግራይ አካባቢዎች የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የቡድኑ ታጣቂዎች በሚንቀሳቀሱበት የኮረም ግንባር በሰሰላ ስምረት፣ ሰላም በቃልስ፣ ደንቃ እና አድሺን ቀበሌዎች በርካታ የአካባቢው ወጣቶች በግዳጅ ታፍሰው ለውትድርና ስልጠና ወደ ማይጨው አቅጣጫ ተወስደዋል።
ህወሓት በተለያዩ አካባቢዎች ኃይል የማደራጀት እና ምልመላ የማካሄድ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ በማስገደድ ቀለብ የመውሰድ እንቅስቃሴውን የቀጠለ ሲሆን፤ በማይጨው፣ በመሆኒ እና በመቀሌ ዙሪያ የወጣቶች አፈሳ እያካሄደ ይገኛል፡፡ የታፈሱት ወጣቶችም ወደ ገረብ ግባ ማሰልጠኛ እየተወሰዱ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በደቡብ ግንባር በጦርነቱ ተፈናቅለው የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀዬአቸው እንዳይመለሱ በህወሓት ታጣቂዎች ክልከላ እየተደረገባቸው ሲሆን፤ ህወሓት በደቡብ ግንባር በተደጋጋሚ ማኅበረሰቡን በማስገደድ የታጣቂ ቀለብ ማሰባሰቡን በመቀጠሉ ከፍተኛ ምሬት እየተፈጠረ ይገኛል።
.:
ህወሓት ሰሞኑን ከመቀሌ በማዕከላዊ ኮሚቴው ስም ባወጣው መግለጫ የሰላም ስምምነቱን በግልጽ የሚቃወም መንፈስ ያለው ሀሳብ አንስቷል፡፡ እንደ መግለጫው ህወሓት ስምምነቱን ‹‹እኔ አልፈረምኩም›› ብሎ ሸምጥጦ ክዷል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መግለጫው የሰላም ስምምነቱን እንደሚደግፍ ያነሳል፡፡
የህወሓትን የፖለቲካ ሴራ ጠንቅቀው የሚያውቁ አካላት ጉዳዩ በጥንቃቄ መፈተሽና መታየት እንዳለበት ይመክራሉ፡፡ ህወሓት በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትጥቅ እንደሚፈታ መስማማቱ ለይምሰል ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬያቸውንም ይገልጻሉ፡፡ እኛም ከላይ የተጠቀሱት መረጃች ህወሓት ዳግም ጦርነት ስለመቀስቀሱ ይጠቁሙ ይሆን ? እንላለን፡፡
በሱሌማን አብደላ
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች አዲሱን የቴሌግራም ቻናላችንን ይወዳጁ።👇
t.me/AmharicNewsOn

Telegram
Amharic News
News & media web
ሰበር ዜና!
********
ሳይጠበቅ አልሻባብ በስብሰባ ላይ ያሉ ባለስልጣናትን በመክበብ ከባድ ተኩስ ከፈተ!
በሶማሊያ ሞቃድሾ በዚህ ሰዓት ባለስልጣናቱ በተሰበሰቡበት ከየት እንደመጣ ያልታወቀ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ቦታውን በመክበብ ከባድ የተኩስ ሩምታ መክፈቱን አልጄዚራን ጨምሮ አለም አቀፍ ሚዲያ በሰበር ዜና ዘግበዋል።
በጉዳዩ ላይ ከዚህ በላይ ዝርዝር መረጃ ለመስጠትም አስቸጋሪ ነገር መፈጠሩን ዘገባው ጠቁሟል።
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች አዲሱን የቴሌግራም ቻናላችንን ይወዳጁ።👇
t.me/AmharicNewsOn
********
ሳይጠበቅ አልሻባብ በስብሰባ ላይ ያሉ ባለስልጣናትን በመክበብ ከባድ ተኩስ ከፈተ!
በሶማሊያ ሞቃድሾ በዚህ ሰዓት ባለስልጣናቱ በተሰበሰቡበት ከየት እንደመጣ ያልታወቀ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ቦታውን በመክበብ ከባድ የተኩስ ሩምታ መክፈቱን አልጄዚራን ጨምሮ አለም አቀፍ ሚዲያ በሰበር ዜና ዘግበዋል።
በጉዳዩ ላይ ከዚህ በላይ ዝርዝር መረጃ ለመስጠትም አስቸጋሪ ነገር መፈጠሩን ዘገባው ጠቁሟል።
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች አዲሱን የቴሌግራም ቻናላችንን ይወዳጁ።👇
t.me/AmharicNewsOn
መልካም ዜና
***********
በሰላም ስምምነቱ መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ከአቅጣጫው ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፖች እየገቡ ይገኛሉ በዚህም መሰረት ትጣቂዎቹ ማይቅነጣል፣ ዛላምበሳ፣ ነበለት፣ ጨርጨር፣ ኩኩፍቶ፣ ሕጉምብርዳ፣ በሪ ተኸላይን ኣበርገለን ከተባሉ ቦታዎች እየለቀቁና ቦታውን ለመከላክያ ሰራዊት እያስረኩቡ ይገኛሉ::

በፍትህና በፀጥታ ዘርፍ የኢፌዲሪ የፋይናንስ ዘርፍ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ቴወድሮስ በቀለን ጨምሮ የመረጃና ደህንነት አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የብሔራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
የብሔራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ ከተቋቋመና ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች መያዝ መጀመሩንና ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የብሔራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ ወደ ስራ መግባቱን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት እና የፍትህ ሚኒስቴር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኮሚቴው በሦስት ንዑስ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን የህግ፣ የመረጃና የፋይናንስ ኮሚቴ ስለመሆናቸው ተነግሯል።
ብሔራዊ ኮሚቴው እስካሁን በሰራቸው ስራዎችና በኮሚቴው አስፈላጊነት ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የኢፌዲሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈተና ተገን በማድረግ በሀገር ሀብትና ንብረት ላይ ዘረፋ መፈፀሙንና የሙስና ወንጀል የብሔራዊ ደህንነት ስጋት እየሆነ መምጣቱን አንስተዋል።
የሙስና ወንጀልን ለመከላከል ብሎም በሀገር ላይ የዝርፊያ እና የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የሚፈፅሙትን አካላት ተጠያቂ ለማድረግ ነው ብለዋል።
የመንግስትን ሙሉ አቅም በመጠቀም ከህዝብ ጋር በመሆን ይህን አደጋ ለመቀልበስ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል።

የመቀሌ ሕዝብ ደኅንነት ሊጠበቅ ይገባዋል
የኢትዮጵያ መንግሥት ለሕዝብ እና ለሀገር ሰላም ሲባል በሰላም ስምምነቱ የገባውን ቃል ሳይውል ሳያድርና ሳያንጣባጥብ በመፈጸም ላይ ይገኛል።
ይህን የሽግግር ወቅት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም በአንዳንድ የመከላከያ ኃይላችን ባልደረሰባቸው የትግራይ አካባቢዎች ኅብረተሰቡን ሰላም የሚነሡ የተደራጁ ዘረፋዎች እየተካሄዱ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በተለይም በመቀሌ ከተማ በመንግስትና በንግድ ተቋማት ላይ በፓትሮል የታገዘ ከፍተኛ ዝርፊያ መኖሩን መረጃዎች እየጠቆሙ ነው። ሕዝቡም በከፍተኛ ምሬት ላይ መሆኑን በስልክና በሌሎችም መንገዶች እያሳወቀ ይገኛል። በሰላም ስምምነቱ ምክንያት ከግጭት የሚያተርፉት ትርፍ የቀረባቸው አካላት ይሄንን እንደሚያደርጉ አያጠራጥርም። ይህን ወንጀል የሚፈጽሙ ሁሉ ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ሊገነዘቡ ይገባል።
መንግሥት በአካባቢው የሚገኙና የሕዝብ ደኅንነት የሚገዳቸው አካላት ከሕዝቡ ጎን ቆመው ወንጀለኞችን እንዲታገሉ ጥሪ እያደረገ የሕዝቡን ደኅንነት ለመጠበቅ ያለበትን ኃላፊነት ለመፈጸም አስፈላጊውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጥ ይወዳል።
ታኅሣሥ 8/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ መቐለ በረራ ይጀምራል
***
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ (ረቡዕ) ጀምሮ ወደ መቐለ ከተማ በረራ ሊጀምር መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ።
ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገው የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለሁለት ዓመታት ያህል ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።
በፌዴራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎም ወደ ክልሉ በጊዜያዊነት በቀን አንድ በረራ በማድረግ አገልግሎቱን እንደሚጀመር ነው ሥራ አስፈጻሚው ያስታወቁት።

ምን እየተካሄደ ነው?
የአሜሪካ ልዩ ጦር ኢትዮጵያና በአፍሪቃ ቀንድ ነገ ጀምሮ ይሰማራል
የአሜሪካ ብሔራዊ ዘብ US National guard የሚባሉ ልዩ ወታደሮች ናቸው በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ይሰማሉ የተባለው። ይኸው የልዩ ጦር ከጥር 04 2023 ጀምሮ ወደ ተመደበበት ቀጣና ጉዞ እንደሚያደርግ አሜሪካን ሚሊቴሪ ኒውስ እና የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘግበውታል።
ይኸው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ጦር በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በሶማሊያ፣ (ሶማሊላንድ) ጅቡቲ እና በኬንያ የተወሰኑ አካባቢዎች እንደሚሰፍር የተገለፀ ሲሆን ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳም ከዝርዝሩ ውስጥ ተጠቅሰዋል።
የብሔራዊ ጥበቃው አመራሮች ስለ ጦሩ ስምሪት ዝርዝር ከመናገር መቆጠባቸው በሪፖርቶች የተጠቆመ ሲሆን፤ በተለይም ጦሩ ምን ያህል ቁጥር ይኖረዋል' ለሚለው ምላሽ መስጠት ከደህንነት ጉዳይ ጋር በተገናኘ ለመግለፅ አለመፈለጋቸው ነው የተዘገበው።
የሆነ ሆኖ የልዩ ጦሩ ቆይታ ከብሔራዊ ዘብ ክፍሉ ከፍተኛው እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፤ የቆይታ ጊዜያቸውን በተመለከተም ብሔራዊ ዘቡ ቁርጥ ያለ መርሃ ግብር ይፋ አለማድረጉ ነው የተጠቀሰው።

Amharic News/አማርኛ ዜና/ ክፍል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።
#Amharic News/አማርኛ ዜና/ የእናንተው ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ!

የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ!
የአማራ ልዩ ኃይል፣ ኢትዮጵያ ችግር በገጠማት ወቅት እንደ ብሔራዊ ጦር ያገለገለ የአገር ዘብ ነው። አማራን አዋርዳለሁ ብሎ የመጣውን ደግሞ ልኩን አሳይቶታል። የዘንድሮው ጀብዱማ ልዩ ነው። ትህነግ በሰላም ስምምነት ከባድ መሳርያ ጠጋግኖ አስረከብኩ ከማለቱ በፊት የአማራ ልዩ ኃይል በቡድን መሳርያ ከባድ መሳርያ ማርኮታል።
በአስቸጋሪው ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ኃይልን አምኖበት "ከባድ መሳርያውን እንካ ተዋጋበት" ብሎት ተዋግቶ ድል አምጥቶበታል። ይህ ሰራዊት ኢትዮጵያን ለማዳን ከትህነግ ጋር ተናንቆ ክብር ያስጠበቀ የአገር ባለውለታ ነው።
ትህነግ ከባድ መሳርያ ለመስጠት ብቻ አይደለም፤ በክፋቱ ባያስረክብ እንኳ ትጥቅ ለመደበቅም የተገደደው በእነዚህ ነብሮች መስዋዕትነት ጭምር ነው። ትህነግ ዓለምን ለምኖ ተኩስ ይቁምልኝ ያለው የእነዚህን ጀግኖች ተኩስንም ነው። ትህነግ ከወ*ረ*ረው ቀጠና ወጥቶ ወደ ጉድጓዱ የሸሸው በእነዚህ ጀግኖች መስዋዕትነት ጭምር ነው። ትህነግና ወዳጆቹ እምበር ተጋዳላይን ትትው ሰላም ሰላም ያሉት በእነዚህ አንበሶች ጠንካራ ክንድ ጭምር ነው። አማራ ብቻ ሳይሆን ውለታ የሚያውቅ፣ አገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይኮራባቸዋል። ትህነግና ወዳጆቹ ደግሞ ሰላም አሉ ቅብጥርጥስ የእነዚህ ጀግኖች ክንድ ያረፈበት ጠባሳቸውና ሽንፈቱ እየጠዘጠዛቸው ይቆያል።
የሰላም ስምምነት እያለ ካድሬው በአደባባይ የሚያወራበትን እነዚህ ጀግኖች ከወንድሞቻቸው ጋር ሆነው ባመጡት ድል የተገኘ ነው። በእነዚህ ጀግኖች ምክንያት ጠ*ላ*ት አንገት ደፍቷል። ወገን አንገቱን ቀና አድርጓል!
ይህ ጦር እነ ስብሃት "አከርካሪውን ሰብረነዋልና አይነሳም" ካሉት ከአማራው አብራክ የወጣ ነው። የራሱን ህዝብ ብቻ ሳይሆን እንደ አባቶቹ የአገር ክብር ያስጠበቀ ኃይል ነው። ትህነግ እያፈረ ይመሰክራል! የኢትዮጵያ መከላከያ ዛሬም በኩራት መስክሯል።
ፎቶው ትህነግን እስከ ሰፈሩ ድረስ ያጥረገረገው የአማራ ልዩ ኃይል ከግዳጅ ሲመለስ የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አንግቦ የሚመለሰው የመከላከያ ሰራዊቱም፣ መንግስትም፣ ጠላትም የሚያውቀው አገራዊ ግዳጁን ተወጥቶ ሲመለስ ነው። ይህ ባለውለታ ጦር ከመከላከያ ጋር ለግዳጅ ትህነግ ቀጠናዬ ነው እስከሚለው ድረስ ሲያስጨንቀው ወዳጅም ጠላትም አይቷል። ይህ ጀግና ጦር የፈፀመውን ጀብዱ፣ የሰራውን ታሪክና ውለታ ሳስብ ደስታዬ ወደር የለውም!

ቆጣሪዎት በየወሩ መነበቡን ይከታተሉ፤ ካልተነበበልዎትም ወዲያውኑ ለማዕከላችን ያመልክቱ
*******
ወድ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን፤ የሚጠቀሙበት የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በተቀመጠለት የማንበቢያ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየወሩ መነበብ እያለበት ቤትዎ ዝግ በመሆኑ ወይም በልዩ ልዩ ምክንያት ቆጣሪዎት በየወሩ ሳይነበብ እንደቀረ እርግጠኛ ከሆኑ በአቅራቢዎት ለሚገኝ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ወዲያውኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡
ለመሆኑ የቆጣሪ አለመነበብ በደንበኞች ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቆጣሪ ባለመነበቡ ምክንያት ቢል ሳይዘጋጅልዎት ከቀረ ለተጨማሪ ወጪ ሊዳርጎት ይችላል፡፡
ለምሳሌ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ ሆነው በመስከረም ወር 90 ኪ.ዋ.ሰዓት እንዲሁም በጥቅምት ወር 120 ኪ.ዋት ቢጠቀሙ ቆጣሪዎት በየወሩ ተነቦ ቢል በየወሩ ቢዘጋጅልዎት፡-
• በመስከረም ወር 90*0.767= 69.03 ብር፡፡ በዚህ ላይ የአገልግሎት ክፍያ ብር 42 ሲጨመር ጠቅላላ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳቡ 111.03 ብር ይመጣል፡፡
• በጥቅምት ወር 120*1.625=195 ብር፡፡ በዚህ ላይ የአገልግሎት ክፍያ ብር 42 ሲጨመር ጠቅላላ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳቡ 237 ብር ይመጣል ማለት ነው፡፡
ሆኖም ቆጣሪዎት በመስከረም ወር ሳይነበብ ቀርቶ ንባብ ባይገባልዎት እና የመስከረም ወር የአገልግሎት ክፍያ 10 ብር ብቻ ቢከፍሉ እና የመስከረምና የጥቅምት ንባብ በአንድ ላይ ቢገባ የሚኖርብዎት ክፍያ 210 ኪ.ዋ.ሰዓት x 2.000=420 ብር ሲደመር መስከረም ወር 10 ብር እና የጥቅምት ወር የአገልግሎት ክፍያ 42 ብር በድምሩ 472 ብር ይከፍላሉ፡፡
ይህ ማለት የሚገባው ኪ.ዋ.ሰዓት በጨመረ ቁጥር ወደ ሚቀጥለው የተጨማሪ የክፍያ እርከን(ደረጃ) የኪ.ዋ.ሰዓት ክፍያ ስለሚገባ በየወሩ የተጠቀሙበት የፍጆታ ሂሳብዎት እየገባ በየወሩ ቢከፍሉ ከሚጠበቅብዎት ክፍያ ብር በ123.97 የበለጠ ገንዘብ ያወጣሉ ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን፤ የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎት በማንበቢያ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲነበብ ቤትዎ ዝግ ባለማድረግ እና በልዩ ልዩ ምክንያት ሳይነበብ መቅረቱን እርገጠኛ ከሆኑ በአቅራቢያዎት ለሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላችን በአካል ቀርበው ሪፖርት በማድረግ ከተጨማሪ ወጪ እንዲድኑ እንጠይቃለን፡፡
ለመረጃ ይረዳዎት ዘንድ አሁን በስራ ላይ ያለውን የመኖሪያ ቤት ደንበኞች የታሪፍ መረጃ አያይዘናል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት አስመልክቶ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፤
___
ንቅናቄያችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት «ከአንዳንድ ክልሎች የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግስትን በመጣል በኃይል ስልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው» ሲሉ ሪፖርት ማቅረባቸውን ከተለያዩ ሚዲያ ዘገባዎች እና ከውስጥ ምንጮቻችን አረጋግጧል፡፡
ከንቲባዋ በሪፖርታቸው ይህን መሰል አደገኛ ከፋፋይ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ማድረጋቸው አገረ መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥል እና በማናቸውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው የዓለም አቀፍ ወንጀል ጥሪ ነው፡፡ ዜጎች በነፃነት ተዘዋውረው የመስራት እና የመኖር ሰብዓዊ መብት ያላቸው መሆኑ ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሥምምነቶች ድንጋጌዎች እና በሥራ ላይ ባለው ሕገ-መንግስት ጭምር የተረጋገጡ ተፈጥሯዊ መብቶች ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ ከንቲባዋ «የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ» እየተባለ በሚጠራው ጽንፈኛ እና በአንድ ወቅት መንግስት ራሱ «የሽብርተኞች መጠቀሚያ ነው» ብሎ በፈረጀው ሚዲያ በተከታታይ የወጡ ቅስቀሳዎች ቅጥያ የሆነ አደገኛ የወንጀል ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ ዓለም አቀፍ ከተማን በከንቲባነት እመራለሁ ከሚል የመንግስት ባለስልጣን እንዲህ ዓይነት አደገኛ ቅስቀሳ በሪፖርትነት መሰማቱ እስካሁን ሲፈፀሙ ለነበሩ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች እና እየታወጀ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከለላ የሚሆን አሳፋሪ የወንጀል ድርጊት ጥሪ ነው፡፡
በመሆኑም ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ይኼንን አደገኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ትኩረት በመስጠት አስቀድሞ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ታሪካዊ ጥሪ እያደረግን፤ በተለይ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ይኼንን ባያደርግ በሩዋንዳ የፈፀመውን ታሪካዊ ስህተት የሚደግመው መሆኑን ማስረገጥ እንሻለን፡፡
በሌላ በኩል የፌደራል መንግስቱም ሆነ ገዥው የብልጽግና ፓርቲ ይኼንን አደገኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ያደረጉትን ግለሰብ ከስልጣን እንዲያነሳ እና ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ እያቀረብን፥ መሰል ድርጊት በድጋሚ እንዳይፈፀም መንግስታዊ ማረጋገጫ ጭምር እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)
አዲስ አበባ፥ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ
መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም.

ግብፅ ኃላፊነት ከጎደለው ንግግር እና ማስፈራሪዎቿ እንድትታቀብ ኢትዮጵያ አሳሰበች
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የህዳሴ ግድብን በተመለከተ “ሁሉም አማራጮች ክፍት ናቸው” በማለት የሰጡትን መግለጫ ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ሲል ውድቅ አደረገ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ፥ ግብጽ የዓባይ ግድብን አስመልክታ ለኢትዮጵያ ማስፈራሪያ የታከለበት መግለጫ ሰጥታለች ብሏል፡፡
ይህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር እና የአፍሪካ ህብረት ድንጋጌን በግልጽ የሚጥስ መሆኑን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ይህ ድርጊት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ራሷኑ ግብጽና ሱዳን በፈረንጆቹ መጋቢት 2015 ያደረጉትን ስምምነት የጣሰም ነው ብሏልሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡
በዚህም ግብጽ ተገቢ ያልሆኑና ህገወጥ መግለጫዎችን ከማውጣት እንድትቆጠብ አሳስቧል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም የሚመለከታቸው አካላት ግብጽ የዓለም አቀፉ ግንኙነት ደንብን እየጣሰች መሆኗን ልብ ሊሉ ይገባልም ነው ያለው።
ግብፅ በማስፈራራትና ከህግ ውጭ ነገሮችን በማድረግ ፍላጎቷን ልታሳካ እንደማትችልም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡
ሆኖም በመከባበርና በመተማመን እንዲሁም የዓለም አቀፉን ህግ ባከበረ መልኩ ከሆነ ሀገራቱ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር መግባባት ላይ ይደረሳሉ የሚል ጽኑ እምነት እንዳለውም ነው የገለጸው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያ አሁንም ሁሉም ወገን አሸናፊ እንዲሆን የሚል አቋማ ላይ እንደሆነችም አስታውቋል።