Amhara Media Corporation
55.4K subscribers
30.7K photos
46 videos
27 files
21.4K links
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Download Telegram
የአማራ ክልልን በስድስት ወራት ብቻ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች መጎብኘታቸውን የክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
https://www.amharaweb.com/የአማራ-ክልልን-በስድስት-ወራት-ብቻ-ከ7-ነጥ/
የአማራ ክልልን በስድስት ወራት ብቻ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች መጎብኘታቸውን የክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች እንቅስቃሴ ግን አነስተኛ መሆኑን ነው ቢሮው የገለጸው፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የላልይበላ፣ የግሸን ማርያም፣ የተድባበ ማርያም፣ የጎዜ መስጂድ፣ የአንኮበር ቤተመንግሥት፣ የዘንገና ሐይቅ፣ የጭስ ዓባይ ፏፏቴ፣ የጣና ገዳማት፣ የጎንደር አብያተ-ክርስቲያናትና ቤተ-መንግሥታት፣ [...]
በኩር ጋዜጣ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም ዕትም
https://www.amharaweb.com/በኩር-ጋዜጣ-መጋቢት-27-2013-ዓ-ም-ዕትም/
በኩር ጋዜጣ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም ዕትም Download
ለ2013/2014 የመኸር እርሻ ወቅት 271 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የእጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
https://www.amharaweb.com/ለ2013-2014-የመኸር-እርሻ-ወቅት-271-ሺህ-ኩንታል-ምርጥ/
ለ2013/2014 የመኸር እርሻ ወቅት 271 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የእጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የምርጥ ዘር አቅርቦትና ቁጥጥርን በተመለከተ የአማራ ክልል የእጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሙሉጌታ ደባሱ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ [...]
ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ወደ ግንባታ እንዲገቡ የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡
https://www.amharaweb.com/ታጥረው-የተቀመጡ-ቦታዎች-ወደ-ግንባታ-እን/
ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ወደ ግንባታ እንዲገቡ የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በመንግሥት እና በተቋማት ጭምር ለልማት ተብለው ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች በከተማዋ እድገት ላይ እንቅፋት መሆናቸውን ያነጋገርናቸው የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ነግረውናል። ነዋሪዎቹ ለቤተ መጽሐፍት ማዕከል ግንባታ ተብሎ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠውን ቦታ እንደ ማሳያ አንስተዋል። [...]
350 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) 350 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ዛሬ ወደ ሀገራቸው
ተመልሰዋል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለምአቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ
አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
የጉምሩክ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ከ3 ወር በላይ በፈጀ ኦፕሬሽን የኮንትሮባንድ እቃዎች፣ ኮንትሮባዲስቶችንና ተባባሪዎቻቸውን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ የኮንትሮባንድ እቃዎች፣ ኮንትሮባዲስቶችንና ተባባሪዎቻቸውን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተከናወኑ ሥራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ኮንትሮባዲስቱ በአዋሽ መቆጣጠሪያ ጣቢያ የፌዴራል ፖሊስ ኀላፊ የሻለቃ አዛዥ የሆነ ግለሰብን በጥቅም በመደለልና ከፌዴራል ፖሊስ አባላትና እና ከአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሰዎችን መልምሎ እንዲያሰማራ በመመሳጠር የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቀላሉ ለማሳለፍ እየሠራ መሆኑን ጥቆማ የደረሰው የጉምሩክ ኮሚሽን ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ የኦፕሬሽን ሥራ ለ3 ወር በመሥራት የኮንትሮባንድ እቃዎች፣ ኮንትሮባንዲስቶች እና ተባባሪዎቻቸው ጭምር በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት፡፡ በዚህም 6 ሚሊዮን 196 ሺህ ብር ግታዊ ዋጋው ያለው እቃ መያዙን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነሩ እንዳሉት በኦፕሬሽኑ 3 የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ ዋናው ኮንትሮባንዲስት እና የኮንትሮባንድ እቃውን ሲያጓጉዝ የነበረ ሾፌር ፣ አንድ የአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሠራተኛ፣ ኮንትሮባንዲስቱ እንዳይያዝ ሽፋን ሲሰጥ የነበረ አንድ የመተሃራ ፖሊስ አዛዥ ጨምሮ 7 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡ በጉቦ መልክ ሊሰጥ የነበረ 200 ሺህ ብርም እንደተያዘ አመላክተዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ለኦፕሬሽኑ መሳካት ሚናቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 9 ሺህ 38 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 2 ሺህ138 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና
ሚኒስቴር ገለጸ።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 217 ሺህ 327 መድረሱን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
በሌላ በኩል 1 ሺህ 54 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 163 ሺህ 22 ሰዎች ከበሽታው
አገግመዋል።
"ትምህርት ሕዝቡን ወደ አንድ ለማምጣትና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠር እንደ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል" የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ሙሐመድ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የመጀመሪያው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመካሄድ ላይ ነው።
በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘላቂነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ በሚኖራቸው አስተዋጽዖ ላይ ያተኮረ ነው።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአፍሪካ ደረጃ ለመፍጠር ለታሰበው ቀጣናዊ ትስስር የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ሙሐመድ "ትምህርት ህዝቡን ወደ አንድ ለማምጣትና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠር እንደ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል" ነው ያሉት።
የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ድኤታ ፕፌሰር አፈወርቅ ካሱ ፎረሙ በኢጋድ አባል ሀገራት መካከል የአካዳሚክና የምርምር ሥራዎችን በማጠናከር ቀጣናዊ ትስስርን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው በኢጋድ አባል ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በቀጣይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችሉ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትር ዲኤታው መግለጻቸውን የዘገበው የሶማሌ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ነው።
“ከሚደርስብን ጥቃት ቀድሞ ደርሶ ሊታደገን የሚችል አካል አላገኘንም” በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የአቤ ደንጎሮ ወረዳ ነዋሪዎች
https://www.amharaweb.com/ከሚደርስብን-ጥቃት-ቀድሞ-ደርሶ-ሊታደገን/
"ከሚደርስብን ጥቃት ቀድሞ ደርሶ ሊታደገን የሚችል አካል አላገኘንም" በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የአቤ ደንጎሮ ወረዳ ነዋሪዎች ባሕር ዳር፡ መጋቢት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች አሁንም የጸጥታ ችግር እንዳለና በስጋት ውስጥ መሆናቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች ለአሚኮ ተናግረዋል። ባሳለፍነው እሁድም በተፈጸመ የተደራጀ ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን፣ በሀብትና በንብረት ላይ ዝርፊያና ውድመት [...]
“የዓባይ ወንዝ የዘገየ ፍትሕ”
https://www.amharaweb.com/የዓባይ-ወንዝ-የዘገየ-ፍትሕ/
“የዓባይ ወንዝ የዘገየ ፍትሕ” ባሕር ዳር፡ መጋቢት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት 10 ዓመታት በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ በጉልህ ይነሳል- በዓባይ ውኃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል ያለው ውዝግብ፡፡ አንዳንድ የዜና ማዕከላት ደግሞ ጉዳዩን “የውኃ ጦርነት” አድርገው ሲዘግቡትም ይስተዋላል፡፡ በየወቅቱ የሚወጡት የዓባይ ውኃ አጠቃቀም ውዝግብ ዘገባዎች ከታሪካዊ ዳራ፣ ከዓለም አቀፍ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች [...]
የእንጨት ውጤቶችን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት መዘጋጀቱን የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ገለጸ፡፡
https://www.amharaweb.com/የእንጨት-ውጤቶችን-ወደ-ውጭ-በመላክ-የውጭ/
የእንጨት ውጤቶችን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት መዘጋጀቱን የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ገለጸ፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የእንጨት ውጤቶችን በአብዛኛው ከቱርክ፣ ከቻይና፣ ከኢጣሊያ እና ከሌሎች የአውሮፓ እና ኤሲያ ሀገሮች ታስገባለች፡፡ ለዚህም ከ110 ሚሊዮን ዶላር በላይ በዓመት ወጭ ታደርጋለች፡፡ የአማራ ደን ኢንተርፕራዝም በክልሉ የደን ውጤቶችን እሴት ጨምሮ በማምረት ከውጭ የሚገባውን መተካት እና የውጭ [...]
ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ አረፉ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶክተር) ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ዛሬ ተገልጿል፡፡ ብጹዕነታቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በልዩልዩ ኃላፊነትና በመንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ጠባቂነት ያገለገሉት አባት ናቸው፡፡
ብፁዕነታቸው ከባራምባራስ ተስፋ ተክሉ እና ከወይዘሮ ታህሣ ኃይሉ የተወለዱት በ1930 ዓ.ም ግንቦት ወር በትግራይ ክልል ብዘት ወረዳ ነበር፡፡ በተወለዱ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽህፈት ቤት መግለጹን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅትን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
በሲሚንቶ ግብይት የወጣውን የዋጋ ተመን ተግባራዊ ባላደረጉ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
https://www.amharaweb.com/በሲሚንቶ-ግብይት-የወጣውን-የዋጋ-ተመን-ተ/
በሲሚንቶ ግብይት የወጣውን የዋጋ ተመን ተግባራዊ ባላደረጉ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የዋጋ ንረትን ለመከላከል ከመሠረታዊ የምግብ ፍጆታዎች በተጨማሪ በሲሚንቶ ምርትም የዋጋ ተመን ወጥቶለት ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡ የተወሰነውን የዋጋ ተመን አተገባበር በተመለከተ በባሕር ዳር ከተማ ተዘዋውረን ምልከታ አድርገናል፡፡ በዚህም [...]
በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊየን በላይ ትኩረት ያላገኙ የኅብረተስብ ክፍሎች የሥራ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሠራር መፈጠር እንዳለበት የሥራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ገለጸ፡፡
https://www.amharaweb.com/በኢትዮጵያ-ከ20-ሚሊየን-በላይ-ትኩረት-ያላገ/
በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊየን በላይ ትኩረት ያላገኙ የኅብረተስብ ክፍሎች የሥራ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሠራር መፈጠር እንዳለበት የሥራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ከአጋር አካላት ጋር ባለፉት ስምንት ወራት የተከናዎኑ ተግባራትን ገምግሟል፡፡ በግምገማው እንደተገለጸው ባለፉት ስምንት ወራት ሥራ ሊፈጠርላቸው ከሚገቡ 20 ሚሊየን ትኩረት ያላገኙ የማኅረስብ ክፍሎች ውስጥ ሁለት [...]