Amhara Media Corporation
55.1K subscribers
30.8K photos
46 videos
27 files
21.5K links
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Download Telegram
"አቅምን በውጤት፤ ፈተናን በስኬት" በሚል መሪ መልዕክት ለክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በክልሉ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሥልጠና መድረክ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ግርማ የሽጥላ በአንድ ፖለቲካዊ ዕይታ በአንድ አቋም ለተራዘመ ጊዜ የሕዝብን ትግል መምራት እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የዓለም አሰላለፍም በየጊዜው ከኢኮኖሚያዊ፣ ከፖለቲካዊና ቴክኖሎጂ ዕድገቱ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ትግሉን በሚገባ ለመምራት የሚያስችል ብቁ ተቋም መገንባት አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሱት ኃላፊው ባለፉት የለውጥ ጊዜያት የብልጽግና ፓርቲ በውስጥም በውጭም ብዙ ፈተናዎችን ለማለፍ ትግል ተደርጓል ብለዋል።

አቶ ግርማ አያይዘውም በዚህ ትግል እያንዳንዱን ፈተና እንደ መሰላል በመጠቀም መቀየር የምንችልበትን ዕድል መፍጠርም ችለናል ነው ያሉት።

ባለፉት የሰጠነው ሥልጠና እንዳለ ኾኖ አሁንም ተጨማሪ ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ በመኾኑ የብልጽግናን አመራርና አባላትን ለማሰልጠን ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መኾኑን አቶ ግርማ ጠቁመዋል።

ይህ ሥልጠና ያለንን አቅም ለውጤት ፈተናዎችን ደግሞ በስኬት ማጠናቀቅ የምንችልበት ኹኔታ እንዴት ማምጣት እንደሚቻልና የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለተሻለ ውጤት እንዲሠሩ ማብቃት ላይ እንደሚያተኩርም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ መረጃ ማጣሪያ https://www.facebook.com/game of act heck
Live stream started
Live stream finished (24 minutes)
Live stream started
Live stream finished (45 minutes)
በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በጫካ የነበሩ ከ300 በላይ ታጣቂዎች ለመንግሥት እጃቸውን ሰጡ።

ጎንደር፡ ታኅሣሥ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ታጣቂዎቹ እጃቸውን እንዲሰጡና መንግሥትም የሰላም ዕድሎችን እንዲያመቻች ከፍተኛ ሥራዎችን መሥራታቸው ተገልጿል።

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሣለኝ ጣሰው፤ ታጣቂዎች እጃቸውን እንዲሰጡና ሰላም እንዲፈጠር የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።

ከታህሳስ ስምንት ጀምሮ ከ300 በላይ ታጣቂዎች ከነትጥቃቸው ለመንግሥት እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን ገልጸዋል።

አቶ ደሣለኝ ታጣቂዎቹ የአመለካከት ስልጠና እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

ወደ ሰላም አማራጭ ያልገቡት ታጣቂዎች ሰላምን መርጠው ከመጡ መንግሥት ለማስተናገድ ዝግጁ መኾኑንም ኃላፊው ጠቅሰዋል።

የሰላም ሂደቱን በአካባቢው የነበረውን የጸጥታ ችግርና ጥፋት የሚያስተካክል መኾኑን አቶ ደሣለኝ ገልጸዋል።

የቅማንት የማንነትና ራስ አሥተዳደር ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደኾኑ የተናገሩት አቶ ፍቃዱ ማሞ፤ በአካባቢው የነበረውን የሰላም እጦት ለመመለስ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ዕድል እንደተቀበሉ ተናግረዋል።

ከኃይል ይልቅ የሰላም አማራጭን መከተል ለሕዝብና ለሀገር ስለሚጠቅም በማመን ለመንግሥት እጃችንን ሰጥተናል ብለዋል።

የኮሚቴው አባል ኤልሳቤጥ አባይ በበኩሏ፤ ታጥቆ በጫካ መንቀሳቀስ ከጉዳትና ከሞት በስተቀር ትርፍ ስለሌለው ወደ ቀያችን ተመልሰን በሰላም ለመኖርና ለማልማት ነው እጅ የሰጠነው ብላለች።

ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመንግሥት በሠላም እጃቸውን እንዲሰጡ ጥረት እያደረጉ መኾኑን አቶ ፍቃዱና ኤሌሳቤጥ ተናግረዋል።
የሽምግልና ሂደቱን ሲያከናውኑ የነበሩት አባ ሃብተማርያም ያሣይ፤ በጫካ የነበሩ ወጣቶችን በስልክ በማነጋገር ወደ ማኅበረሰቡ እንዲመለሱ በማድረግ ያከናወነው ሥራ ስኬታማ ነበር ብለዋል። በቀጣይ ከማኅበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ሠላሙ መሠረት እንዲኖረው እንሠራለን ብለዋል።

የሀገር ሽማግሌው አቶ ዋኘው ወረደ የአካባቢውን ልማት ለማስቀጠል ሠላሙን ማረጋገጥ ስለሚገባ ታጣቂዎቹ እጅ እንዲሰጡ ተደርጓል ብለዋል።

አካባቢው ትርፍ አምራች በመኾኑ ሠላሙን እያረጋገጥን ልማቱን ለማስቀጠል ሥራችን ይቀጥላል ብለዋል።

ከ19 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችም ወደ ቤታቸው ተመልሰው መደበኛ ህይወታቸውን እንዲኖሩና ወደ ልማት እንዲመለሱ መደረጉን አቶ ዋኘው ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ አገኘሁ አበባው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ መረጃ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck
አብደራፊ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜራ ክልል የምትገኘው አብደራፊ ከተማ ከሁለት ዓመት በኃላ የተቋረጠባትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ዛሬ ምሽት አግኝታለች፡፡

ከተማዋ ዳግም ተጠቃሚ የሆነችው የመካከለኛ የዝቅተኛ መስመር የጥገና ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው፡፡

በትናንትናው እለት የዳንሻ ከተማ ዳግም ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስታወቁ ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ መረጃ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck