ኦርቶዶክሳዊነት 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
6.91K subscribers
6.49K photos
313 videos
25 files
263 links
✝️ ኦርቶዶክሳዊነት

📖 ዕለታዊ መንፈሳዊ መልእክቶች 📃ስንክሳር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የኦርቶዶክስ ትምህርት

እግዚአብሔር ወደ ብርሃን ይምራን
Download Telegram
🕊                        💖                       🕊

🕊  💖  እንኳን  አደረሳችሁ  💖  🕊


🕊 " በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል ! " 🕊

▬▬▬▬▬▬   †   ▬▬▬▬▬▬

❝ ኑ ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ ፤ እርሱ ሰብሮናልና ፥ እርሱም ይፈውሰናል ፤ እርሱ መትቶናል ፥ እርሱም ይጠግነናል።

ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል ፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል ፥ በፊቱም በሕይወት እንኖራለን። ❞

[ ትንቢተ ሆሴዕ . ፮ ፥ ፩ ]


════════════════
                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟
🕊                        💖                       🕊
🕊                        💖                       🕊

🕊  💖  እንኳን  አደረሳችሁ  💖  🕊

ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት !

════════════════

❝ ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤ ደግሞም። ክርስቶስን አስነሥቶታል ብለን [በገዛ ሥልጣኑ ተነሥቷል ብለን] በእግዚአብሔር ላይ ስለ መሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን ግን የማይነሡ ከሆነ እርሱን አላስነሣውም።

ሙታን የማይነሡ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሣማ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ። ❞ [ ፩ቆሮ.፲፭፥፲፬ ]

🕊

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
▸ አግአዞ ለአዳም
ሰላም
▸ እምይእዜሰ
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም

❝ ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞

🕊

❝ ሞት ሆይ ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል ፥ መቃብርም ሆይ ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡ ❞ [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

════════════════
                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟
🕊                        💖                       🕊
Audio
🕊

[ † እንኳን አምላካችን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ላረፈባት የመጀመሪያዋ ዕለተ ሰንበትና ለቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† አምላካችን እግዚአብሔር በ፮ [6] ቱ ቀናት ፳፪ [22] ቱን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ በ፯ [7] ኛዋ ዕለት ደክሞት ያይደለ ለእኛ ያስተምረንና ሰንበትን ይቀድስልን ዘንድ አረፈ::

ዕለተ ሰንበት ማለት አንዳንድ ልባቸውን ያሳወሩ ሰዎች እንደሚያወሩት የሥራ መፍቻ ቀን ሳትሆን :-
፩. ከሥጋዊ ተግባራችን ታቅበን መንፈሳዊ ተግባራትን [፮ [6] ቱ ቃላተ ወንጌልን] የምንፈጽምባት:

፪. ለጊዜውም ቢሆን ጥቂት እርፍ ብለን አማናዊቷን ዕረፍተ መንግስተ ሰማያት የምናስብባት ዕለት ናት::

እንደ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትም ለሰንበተ ክርስቲያን ቀዳሚውን ቦታ ሰጥተን ቀዳሚት ሰንበትንም እንደሚገባ ልንጠቀምባት ይገባል::

† የሰንበት ጌታዋ: የምሕረትም አባቷ ጌታችን እግዚአብሔር ለዕረፍተ መንግስቱ የተዘጋጀን ያድርገን::

🕊 † ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ †  🕊

† ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤል የነበረው ቅ/ል/ክርስቶስ በ፭፻ [500] ዓመት አካባቢ ሲሆን የጼዋዌ [ምርኮ] አባልም ነበር:: እሥራኤልና ይሁዳ ወደ ባቢሎን በምርኮ ሲወርዱ አብሮ ወርዷል:: ቅዱሱ ከ፬ [4]ቱ ዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ሐረገ ትንቢቱም በ፵፰ [48] ምዕራፎች የተዋቀረ ነው::

በዘመኑ ሁሉ ቅድስናን ያዘወተረው ቅዱሱ ከደግነቱ የተነሳ በጸጋማይ [ግራ] ጐኑ ተኝቶ ቢጸልይ ፮፻ [600] ሙታንን አስነስቷል:: ወገኖቹ እሥራኤልንም ያለ መታከት አስተምሯል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት ታላቁን ራዕይ እንዳየ ታስተምራለች:: ነቢዩ በፈለገ ኮቦር ካያቸው ምሥጢራት እነዚህን ያነሷል :-

፩. እግዚአብሔርን በዘባነ ኪሩብ ተቀምጦ ሲሠለስና ሲቀደስ አይቶታል:: የኪሩቤልንም ገጸ መልክእ በጉልህ ተመልክቷል:: [ሕዝ.፩፥፩]

፪. በመጨረሻው ቀን ትንሳኤ ሙታን : ትንሳኤ ዘጉባኤ እንደሚደረግም ተመልክቷል:: [ሕዝ.፴፩፥፩]

፫. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ኆኅት ኅትምት/ኆኅተ ምሥራቅ [የምሥራቅ ደጅ] ሁና አይቷታል::

ይሕ የምሥራቅ ደጅ [በር] ለዘለዓለም እንደታተመ ይኖራል:: የኃያላን ጌታ ሳይከፍት ገብቶ: ሳይከፍት ወጥቷልና:: [ሕዝ.፵፬፥፩] በመጨረሻ ሕይወቱ እሥራኤል ለክፋት አይቦዝኑምና ነቢዩን አሰቃይተው ገድለውታል::

† ከነቢዩ በረከት አምላኩ ያድለን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]

፩. እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ
፪. ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ
፫. ቅዱስ ዲዮስቆሮስ [ክፉ ላለመናገር ድንጋይ ጐርሶ የኖረ አባት]
፬. ቅድስት ታኦድራ
፭. ቅዱስ አርሳኒ
፮. ቅዱስ ያሬድ ካህን [ልደቱ]

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
፫. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ [አባ ገብረ ሕይወት]
፬. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
፭. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

" እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ: ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ: ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና :- በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ:: የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ:: " † [ኢሳ.፶፮፥፬-፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
ማዕዶት


በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ከትንሳኤ እሁድ ቀጥሎ ያለው ሰኞ "ማዕዶት" ይባላል። ማዕዶት ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም መሻገር ማለት ነው። እንግዲህ በጥንተ ታሪክ እስራኤላውያን የፋሲካን በግ አርደው ደሙን በራፋቸው ላይ በመቀባት ከግብፅ የባርነት ምድር ወደ ከነዓን [ተስፋይቱ ምድር] የተሻገሩበትን ታሪክ ያስታውሰናል ማዕዶትን ስናስብ።

ለእኛም በክርስቶስ ኢየሱስ ላለን ከሞት ወደ ህይወት በክርስቶስ ትንሳኤ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ዘላለም ሕይወት መሻገራችንን የምናበስርበት ዕለት ነው። የድል አዋጃችንን በዚህ ሳምንት መቃብር ፈርሶ፣ ሞት ተሸንፎ የሰው ልጅ የቀድሞ ክብሩን መመለሱን የምስራች የምንልበትም ቀን ነው።

በዚህ ሳምንትም፤  የክርስቶስ ትንሳኤ ለሰው ልጅ ሁሉ የተሰጠ የነፃነት ስጦታ መሆኑ ይታወጃል፣ በቤተክርስቲያን ሥርዓት ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናል እየተባለ በደስታ ይዘመራል።እንዲሁ ከትንሳኤ እስከ ዳግም ትንሳኤ ያሉት 8 ቀናት እንደ አንድ ዕለት (እንደ እሁድ) ስለሚቆጠሩ፣ ረቡዕና አርብን ጨምሮ ጾም አይጾምባቸውም።

ማዕዶት መሻገር እንደመሆኑ እኛም ከክፋት ወደ በጎነት፣ ከጥል ወደ ፍቅር፣ ከጭንቀት ወደ ተስፋ የምንሻገርበት ይሁንልን!

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፥ በአማን ተንሥአ!
🕊                        💖                       🕊

፩. ሰኞ [ ማዕዶት ]

════════════════
                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟

ማዕዶት ማለት [ ዐደወ-ተሻገረ ] ከሚል የግእዝ ግስ የተወረሰ ሲሆን በጥሬው "መሻገር" ማለት ነው:: ይሕም በደመ ክርስቶስ ተቀድሰን: በትንሳኤውም ድኅነት ተደርጐልን መከራን: መርገምን: የኃጢአትን ባሕር: አንድም ባሕረ እሳትን መሻገራችንን ያመለክታል::

- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ
- ከባርነት ወደ ነጻነት
- ከጨለማ ወደ ብርሃን
- ከሞት ወደ ሕይወት
- ከኃጢአት ወደ ጽድቅ
- ከሲዖል ወደ ገነት
- ከገሐነመ እሳት ወደ መንግስተ ሰማያት
አዳምንና እኛን ልጆቹን አሸጋግሮናል::

አባታችን አዳምና ልጆቹ ከሲዖል የወጡት በዕለተ ዐርብ በሠርክ ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ ዕለት እዲታሰብ ታዛለች::

ጌታችን ምርኮን ማርኮ: ጥጦስ መንገድ ጠራጊ ሆኖለት ወደ ገነት ሲያስገባቸው ለድንግል ማርያም አሳይቷታል:: እመ አምላክም በፍጹም ልቧ ደስ ተሰኝታለች:: አዳምና ልጆቹ እመቤታችንን ከላይ ሆነው እጅ ነስተዋታል:: እርሷ የድኅነታቸው ምክንያት ናትና::

════════════════
                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟
🕊                        💖                       🕊
1
Audio
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

እንኳን አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

† ሚያዝያ ፮ [ 6 ] †

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት እነዚህን ታላላቅ ቅዱሳን ታስባለች:-

† 🕊 ቅድስት ማርያም ግብፃዊት 🕊 †

† በዚች ቀን በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያም አረፈች። ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ሁና ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። እድሜዋ አስራ ሁለት አመት በሆናት ጊዜ የመልካም ስራና የሰው ሁሉ ጠላት ሸንግሎ አሳታት በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ እርሱ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና ።

በዚህም በረከሰ ስራ ውስጥ ኖረች በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር። ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት።

ከእሳቸውም ጋራ ትሄድ ዘንድ ልቧ ተነሳሳ ከብዙ ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች። ባለ መርከቦችም የመርከብ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው ኢየሩሳሌምም እስከ ደረሰች ይህን ስራ አልተወችም።

የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም።

ከዚህም በኃላ ስለ ረከሰ ስራዋ አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሔር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስእል አየች።

በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጅአቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ እኔ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት።

ቤተ ክርስቲያን ፈጥና ገባች በገባችም ጊዜ የበአሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኃላ አምላክን ወደ ወለደች ወደ እመቤታችን ወደ ከበረች ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ ወደ እርሷ መሪር ልቅሶ እያለቀሰች ረጅም ፀሎትን ፀለየች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ከዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ እረፍትንና ድኀነትን ታገኚ አለሽ የሚል ቃል ወጣ።

ከእመቤታችን አምላክን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ይህን ቃል ተቀብላ ወድያውኑ ወጣች። በውጪም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ግርሽ ሰጣትና አምባሻ ገዛችሸት።

ከዚያም በኃላ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት አመት ኖረች ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር።

እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች ከዚያም ከገዛችው አምባሻ ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለት ሁለት ቀን ሶስት ሶስት ቀን ፁማ ከዚያ አምባሻ ጥቂት ትቀምስ ነበር በአለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች።

በዚያችም በዮርዳኖስ በረሀ እየተዘዋወረች አርባ አባት አመት ሲፈፀምላት እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ቅዱስ ዘሲማስ ወደዚያች በረሀ መጣ። በሱ ደብር ላሉ መነኲሳት ልማዳቸው ስለሆነ በየአመቱ ወደ በረሀ ወጥተው የከበረች የአርባ ቀን ፆም እስከ ምትፈፀም በፆምና በፀሎት ተፀምደው በገድል ይቆያሉ ።

ስለዚህም ዘሲማስ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚፅናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሄርን ለመነው። በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን  ምትሀት መሰለችው በፀለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት።

ወደርሷም ሄደ እርሷ ግን ከእርሱ ሸሸች ወደርሷም ይደርስ ዘንድ ከኃላዋ በመሮጥ ተከተሉት። ከዚህም በኃላ ዘሲማስ ሆይ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ እከለልበት ዘንድ ብላ በስሙ ጠራችው።

በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት እርስበርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጥተው በላዩዋ ይፀልይላት ዘንድ ለመነችው እርሱ ካህን ነውና ካህን ሰለሆነ።

ከዚህም በኃላ ገድሏን ታስረዳው ዘንድ ቅዱስ ዘሲማስ ለመናት ከእርሷ የሆነውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። እርሷም በሚመጣው አመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እሺ አላት።

አመትም በሆነ ጊዜ ስጋውንና ደሙን በፅዋ ውስጥ ያዘ ደግሞ በለስ ተምርንና በውኃ የራሰ ምስርን ይዞ ወደርሷ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ቅድስት ማርያምን በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ስትሄድ አያት ወደርሱም ደርሳ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ በአንድነትም ፀለዩ ከዚህም በኃላ ስጋውንና ደሙን አቀበላት።

በለሱን ተምሩንና ምስሩንም አቀረበላትና ትመገብለት ዘንድ ለመናት ስለ በረከት ከምስሩ በእጇ ጥቂት ወሰደች። ደግሞም በሁለተኛው አመት ወደእርሷ ይመለስ ዘንድ ለመነችው ።ሁለተኛ አመትም በሆነ ጊዜ ወደዚያ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ያቺ ቅድስት ሴት ሙታ አገኛት በራስጌዋም ድኀዪቱን ግብፃዊት ማርያምን ከተፈጠረችበት አፈር ውስጥ ቅበራት የሚል ፅሁፍ አገኘ።ከፅሁፉ ቃልም የተነሳ አደነቀ።

ያን ጊዜም ከግርጌዋ አንበሳን ሲጠብቃት አየ እርሱ መቃብርዋን በምን እቆፍራለሁ ብሎ ያስብ ነበር በዚያም ጊዜ ያ አንበሳ በጥፍሮቹ ምድሩን ቆፈረ የከበረ ዘሲማስም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት ።

ወደ ገዳሙም ተመልሶ ለመነኮሳቱ የዚችን የከበረች ግብፃዊት ማርያምን ገድሏን እንዳስረዳችው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገራቸው እጅግም አደነቁ ምስጉን ልኡል እግዚአብሄርንም አመስገኑት። መላው እድሜዋም ሰማንያ አምስት ሆኗታል።

🕊 ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 🕊

በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤው ሳምንት ለሀዋርያው ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጉኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም  ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሳትህን አመንኩ አለ።

ጌታችንም ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት። በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኀኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ ፣በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች ።