✨✨ፍቅር ቅብ-7✨✨
እህቴ እግር ማውጣቷን ጠብቃ እናቴም እግር አወጣች....
ብዙ ጥያቄ አሸክማን ደብዛዋን አጠፋች....ለወቀሳ እንኳን የሚሆን የተሸነቆረች ደይቃ አልተወችልንም..... የመጨረሻዋ ምሽቷ ላይ እንኳን የመሄድ አዝማሚያ አላሳየችንም....
እናቴ ከመሄዷ በፊት ጥድፊያ ያለበት ሙያ ስታስተምረኝ እንዴት አልጠረጠርኩም .....ጠብቃ ነበር.....አባቴ የሚወዳቸውን ምግቦች አጣፍጬ መስራት እስክጀምር ታግሳለች....ጠብቃ ነበር....እህቴ እግር እስክታወጣ በትዕግስት ጠብቃለች....'እህት ሁለተኛ እናት ናት' ብላ እጇን አስይዛ መቼም እንደማልተዋት በስሟ ስታስምለኝ መጠርጠር ነበረብኝ አይደል....አልጠረጠርኩም።
እህቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የደብረብርሃን አረቄ እንደቀመሰ ሰው እየተንገዳገደች በእግሯ ስትሄድ አይታት ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ እንዴት አልጠረጥርም....
ጡጦ አስጠጣጠብ እና አዘገጃጀት ከጥናት ሰአቴ ቀንሳ ስታስጠናኝ እንዴት አላስተዋልኩም....
በአስር አመቴ ስለ ወር አበባ ቁጭ አርጋ ስታስረዳኝ እና እኔ ባልኖር እንደዚህ አድርጊ ብላ ሞዴስ አጠቃቀም ስታስተምረኝ እንዴት ዝግጅቷ አይተገለፀልኝም....
**
የአመት በአል እለት ማልዳ ቤተክርስትያን ስማ ትመጣ ነበር.... ከእንቅልፋችን ስንነሳ ከቤተክርስትያን ተመልሳ ሽንሽኗን ለብሳ ጉድ ጉድ ስትል ማየት ለምደናል....
ቀጤማው....ቡናው....እጣኑ.....የማናለቦሽ ዲቦ ዘፈን....እና እናቴ ናቸው ለኔ የበአል ጠዋት ትውስታዎች።
በሆነኛው ቀን በአል ግን ቀጤማውም ቡናውም እጣኑም የማናለቦሽ ዲቦ ዘፈንም እናቴም አበሩብን....ዝም ጭጭ እንዳልን እሷን ጥበቃ ያዝን።
አባቴ ትሄድባቸዋለች ካላቸው ደብሮች ያልበረበረው አልነበረም....ቤተልሄሙ ሲቀረው ጊቢውን....ቤተመቅደሱን....የክርስትና ቤቱ ውስጥ ሳይቀር አገላብጦ ፈትሿል.....የዘበኛ ቤት እና መቃብር ስፍራም አልቀረውም....
የአባቴ አይኖች ለመጀመሪያ ጊዜ እንባ ሲያረግዙ ያየሁት ያኔ ነው....."አስካል መጣች....?"...ብሎ የጠየቀው እኔና አፍ ያልፈታችውን እህቴን ነበር....ደብሩን አዳርሶ ሲመለስ ቤት እንደሚያገኛት ጭላንጭል ተስፋ ነበረችው....እንዳልተመለሰች ሲያውቅ እንዴት አንገቱን ደፍቶ እንደተንሰቀሰቀ ሳስታውስ አሁን ድረስ እንባዬን መቆጣጠር ያቅተኛል....እናቴ አንጀቴን ከምታላውሰው በላይ ሆዴ ተገለባበጠለት.....
እሷ ከሄደችበት ቀን ጀምሮ የአባቴን ድምፅ ያለ ገደብ እንሰማው ጀመር....
ዝምታው የሸኛት መለጎሙ ያስኮበለላት እንደመሰለው ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም....በሚያሳብቅ ሁኔታ ማውራት እኛን ማጫወት ጀመረ....አንድም አለመኖሯ እንዳያጎለን እየተጋጋጠ ....ደግሞም ያስኮበለላት ዝምታው እኛ ልጆቹንም እንዳያሳጣው የሰጋ መሰለኝ.....
እናቴ ጥላን ሄዳለች....ምክንያቷ ምንም ይሁን ምን ውጤቱ መሄዷ ነው....እንደ እኔ እንደ እኔ እኛን መተው ባይቀላት እግሯን አታነሳም ነበር....ብዙ የማላውቃቸው ነገሮች መሄጀ ቀኗን እንደወሰኑላት ግልፅ ነው....ምን አልባት ብዙ መከፋት....ውጤቱ ግን ጥሎ መሄድ ነው....ምን አልባት ብዙ እንባ...ውጤቱ ግን አሁንም መሄድ ነው....ምክንያት ከቅጣት ቢያድን አዳምና ሄዋን ከገነት አይባረሩም ነበር አይደል....እንደዛ....የእናቴ ምክንያት ምንም ይሁን ምን ከልቤ ላለመባረር አላዳናትም....
እናቴ ጥላኝ ሄዳለች....
ከማህፀኗ ያወጣችኝ ጥላኝ ከሄደች ማህፀን የማይመርጥ አክሱሙን ተሸክሞ የሚዞር ዮናስ መሄዱ ምን ይገርማል.....
*
አንድ ሁለት እያለ ወራትን ቆጠርኩ.....የእናቴ የውሀ ሽታ መሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቀመኝ.....ሰው ሲርቀኝ ሳይሆን ሲቀርበኝ የምደነግጥ አይነት ሰው አረገኝ....ነካክቶ 'ሂድ ሂድ ብረር ብረር' የሚለው በበዛበት ዘመን የእናቴ መሄድ በማንም መሄድ እንዳልደነግጥ አረገኝ....በዚህ በኩል ደግሞ የአዲስ አበባ ስፋት ጠቀመኝ....ከዮናስ ጋር በአጋጣሚ እንኳን ተገናኝተን አናውቅም... ግዛቱ የመሰሉኝ ሰፈሮችም ቀስ በቀስ ዮናስ ዮናስ መሽተታቸውን ቀነሱ...
ከእርሱ ጋር የማሳልፋትን ቅዳሜ ለአባቴ ቡና በማፍላት ማሳለፍ ጀመርኩ...የእርሱ "አፈቅርሻለሁ" ትርክት በአባቴ እውነተኛ ምርቃት ተተካ...
**
ከሀኒ ጋር በትርፍ ጊዜያችን ብቻ ሳይሆን እንዲሁ ገርበብ ባለ ጊዜያችን መገናኘት የበፊት ልምዳችን ነው...ምሳ ሰአት አብሮ መብላት...አልያም ከስራ ስንወጣ አብረን መሄዱ አስር አስር ፍቅረኛ እንኳን ብንይዝ የማይቀየር ህጋችን ነው....ዮናስ የውሀ ሽታ ከሆነ በኃላ ደግሞ ብሶብናል...
እንዳልኳችሁ ነው...ባገኘናት ሽንቁር መገናኘት ለምደናል...አንዱ ሽንቁር ደግሞ ምሳ ሰአት ነው....የዛሬው ሽንቁራችን ላይ ድንኳን ሰባሪ እንደነበር ያወቅኩት ከደረስኩ በኃላ ነው...ሀኒ ከሆነ ሰው ጋር ናት...
"መክብብ እባላለሁ..."....ብሎ እጁን ለትውውቅ ከዘረጋበት ቀን ጀምሮ የሆነ ነገሩ ውስጤ ቀርቷል...እንደተነገረኝ ከሆነ መክብብ እሳት የላሰ ጠበቃ ነው...እድሜው ከሰላሳ መግቢያ አካባቢ የሚሆን...ቁመቱ ብቅል አውራጅ የሚባል አይነት ባይሆንም ዘለግ ያለ...ግርማ ሞገስ ያለው...ፊቱ የሀብታም ወዝ ያለው...እጁ ከጥጥ የሚለሰልስ....አናቱ ላይ የደፋው ጥቁር ኮፍያ ፊቱ ላይ ካጀበው ፂሙ ጋር ተደምሮ የሆነ ዘፈን ላይ የማውቀው የትግርኛ ዘፋኝ የሚመስል....ለሰላምታ ገርበብ ያደረገው ከንፈሩ ውስጥ ተአምር የሚመስሉ ባዘቶ ጥርሶቹን ያየ እንደ እኔ ቆሞ አይሄድም..... እፍፍፍፍ ሚያስብለኝ አይነት ውበት ያለው ....
አላለቀም....
✍ሸዊት
@AmbaBooks|📚

❤19🥰6❤🔥1👍1
📖 የመፅሐፍ ዳሰሳ
📚ዳርክ ሳይኮሎጂ 📚
📝ደራሲ: ዊሊያም ኩፐር
👤ትርጉም: ፍሉይ አለም
📜ዘውግ: dark psychology and manipulation
📆ዓ.ም: 2018
📑የገፅ ብዛት: 344
💰ልጥፋ ዋጋ: 790br
#ታድናለህ_ወይም_ትታደናለህ
ይሄ #ዳርክ_ሳይኮሎጂ የተሰኘው መጽሐፍ ማንም እንደፈለገ እንዳይጫወትብህ የሚረዳ አስተሳሰብህን የሚቀይርና በሕይወትህ እንዴት በጥበብ መጫወት እንዳለብህ የሚያስተምር መጽሐፍ ነው።
የዋህነት በዘመናችን ትልቅ ወንጀል ነው። ቅን መሆን ብቻውን ዋጋ የለውም ሰዎች ደግነትህን እንደ ድክመት ይቆጥሩታል ግልጽነትህን ተጠቅመው ያጠቁሃል። ይህ የ #ዳርክ_ሳይኮሎጂ መጽሐፍም የተከለከለውን እውቀት በመግለጥ ዓለም እንዴት እንደምትሰራ ያሳይሃል።
መጽሐፉ የሥነ-ልቦና ጨዋታ ምሥጢሮች በመበታተን ሰዎች አንተን ለመቆጣጠር የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች ያሳይሃል። እውቀቱ በእጅህ ሲገባ ከአሻንጉሊትነት ወደ መሪነት ትሸጋገራለህ።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የምትማራቸው የኃይል ሕጎች
#ማኑፕዩሌሽን (Manipulation) ሰዎች ሳያውቁት ወደ ፈለግከው አቅጣጫ እንዴት እንደምትዘውራቸው
#የማታለል_ጥበብ (Deception) እውነተኛ ዓላማህን በመደበቅ ጠላቶችህን እንዴት እንደምታዘናጋ እና እንደምትጥላቸው
#ስሜታዊ_ጫና (Emotional Blackmail) የሰዎችን ፍርሃት ፍቅር እና ድክመት በመጠቀም እንዴት ተጽዕኖ እንደምትፈጥር
#የአዳኞች_ሥነ_ልቦና ናርሲሲስቶች እና ሳይኮፓቶች የሚጠቀሙበትን ስልት ቀድሞ በመረዳት እንዴት ጥቃታቸውን ማክሸፍ እንደምትችል።
ይህ መጽሐፍ ለደካሞች የተዘጋጀ አይደለም። እውነቱን ለመጋፈጥ ለሚደፍሩ የሕይወታቸውን ዙፋን ለሌሎች አሳልፈው ለመስጠት ፈቃደኛ ላልሆኑ እና ጨለማውን ተረድተው ብርሃኑን ለመቆጣጠር ለሚፈልጉ ብቻ ነው።
አቅራቢ:- 📚@ambabooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ

❤17👍3🙏2
✨✨ፍቅር ቅብ-8✨✨
እጁን ከዘረጋበት ቅፅበት ጀምሩ...ስሜ እስኪጠፋኝ ድረስ ልቤ ደንግጦለታል...
"እድል ትባላለች..."...ብላ ሀኒ ስሜን ስታስታውሰኝ በልቤ አመስግኛታለሁ...
"እንደዚች አይነት ቆንጆ ጓደኛ እንዳለሽ ነግረሺኝ አታውቂም...."...ከማለቱ እንደመሽኮርመም ነገር አረገኝ...
"ኧረ መሽኮርመም ካካካ...."...አንዴ ከተጀመረ ማቆሚያ የሌለው ሳቋ ተከተለ...
"ካካካካ ቆ...ቆንጆ ትርጉሙ ተቀየረ መሰለኝ ካካካካ"....ይሄን ስትል ንዴቴ ጣሪያ ነካ.....እንደደበረኝ እንድታውቅልኝ ፊቴን በመዘፍዘፍ ምልክት ሰጠኃት.. በአይኔም ላወራት ሞከርኩ...እሷ ወይ ፍንክች....
"መኬ ግን ጨምረሀል...ቆንጆ ምናምን ካካካ"
"ቆንጆ ናት...እውነቴን ነው..."....ይሄን ያለው እኔን እኔን እያየ ስለነበር የድብርት ፊቴን ፈታሁለት....
"ኧረ መፋጠጥ...እሺ ልነሳላችሁ..."....ይሄን ስትልም ሳቋ አፍኗት ነበር....
"ወሬ አለብሽ..."...ካላት በኃላ አስተናጋጇን በምልክት ጠራት...
"ወሬ አይደለም ይሄ...በት በት ጀምረህልኛል እ...ብትበረታ ነው ጥሩ...ፀጉርህም ወደማለቁ ነው ካካካካ...."
"ቆይ ውበት ማድነቅ አይቻልም..."...አስተናጋጇን ከሸኘን በኃላ መለሰላት...
"ይቻላል...በደንብ ይቻላል...ግን በእኔ ፊት ስታደንቅ ለመጀመሪያ ጊዜህ ነው ብዬ ነው...."
"ለምን አልተደነቅኩም መሰለብሽ..."...ሲላት ሀይለኛ የቃላት ጦርነት እንደሚጀመር ገባኝና ደራሽ ጥይት እንዳያገኘኝ በውስጤ መፀለይ ጀመርኩ።
"ለምን ይከነክነኛል...አይን እንደሌለህ የገባኝ እኮ እድልን ቆንጆ ስትል ነው...ለዚህ ይታዘናል እንጂ አይቀናም..."...የፈራሁት አልቀረልኝም...ለእርሱ የተተኮሰ ጥይት ሽራፊው ደረሰኝ....
ከዚህ ንግግር በኃላ ምግባችን መጣ...ቀጣይ ጥይት ሳይተኮስ በፊት እጄን ልታጠብ በሚል ከመሀላቸው ተነሳሁ...እውነቱን ለመናገር እጄን መታጠብ ሳይሆን መስታወት ማየት ነበር ዋና አላማዬ...ፊቴን በአእምሮዬ መሳል ራሱ ከበደኝ...ሀኒ ምን ሆነች...?...ጠየቅኩ ራሴን።እኔን በማላውቀው ሰው ፊት ማጥላላት ከመቼ ጀምሮ...በእርግጥ እነርሱ በደንብ ይተዋወቃሉ...ከዩንቨርስቲ ጀምሮ...ግን ይሄ እኔን ለማጥላላት በቂ ምክንያት አይደለም...ስደነቅ በእኔ ፈንታ ኩራት የሚሰማት ጓደኛዬ የት ገባች...?ይቺን ሀኒ አላውቃትም...ከማላውቃቸው ሁለት ሰዎች ጋር ያለሁ ያህል ተሰማኝ....
ፊቴን ብቻ በደንብ አይቼ እጄን ውሀ ሳላስነካ ተቀላቀልኳቸው...የቃላት ጦርነቱ በርዶ የደራ ጨዋታ ላይ ደረስኩ...ከመቼው አልኩኝ በሆዴ...መቼስ ስለ እኔ ውበት እንዳይወራ ሆን ብላ ነው ወሬውን ያደራችው አልኩ ደግሜ።..
ወይ ጦጣ መሆን...ቼክም አላደርግ አሉኝ...የእርሷስ ይቅር እሱ ግን ውበቴን ትቶ ምን አባቱ ነው የሚያወራው...ከእኔ ውበት የሀኒ ወሬ በለጠበት...?
"እሺ ቢያንስ ምግቡን ደጅ አታስጠኑት..."...አልኩ አምልጦኝ...
"ማለት ቢያንስን ምን አመጣው...አንቺን ደጅ አስጠናንሽ እንዴ....?"...ሀኒ ናት...አሁን በደንብ ገባኝ...የጥይቷ ኢላማ በትክክል እኔ እንደነበርኩ...እየተፈጠረ ያለው ነገር ጭራሽ ሀገር የማይሰጥበት እንቆቅልሽ ሆነብኝ....
"አይ እንደዛ ማለቴ ብዬ ሳይሆን ከበረደ አያስበላም ብዬ ነው..."
"ልክ ነሽ...እጄን ታጥቤ ልምጣ..."...አለ ባኮፍያው...ይሄን አጋጣሚ ከሀኒ ጋር ለማውራት ልጠቀምባት እያሰብኩ "ጠብቀኝ መኬ እኔም እመጣለሁ"...ስትል ከጥያቄዬ እየሸሸች እንደሆነ ፍንትው አለልኝ።
ከምንም የማልቆጠርበት ቦታ ላይ የተቀመጠች አሻንጉሊት የሆንኩ መሰለኝ...ምን ብዬ ተነስቼ መሄድ እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ...
ብዙም አልቆዩም እያሽካኩ መጡ...
"ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ሳቅ...ንገሩኝና እኔም ልሳቅ..."...አልኩኝ ልቀላቀላቸው በማሰብ።
"ካካካካካካ...."....አሽካካች...ሳቂልኝ አላልኳትም አይደል...በገነኩ...ይሄን ጊዜ ባለኮፍያው አብሯት አልሳቀም...
"ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ...."...አሁንም ወሬው ላይ የለሁበትም...
"ምን ትዝ አለሽ...አያልቅብሽ..."...ምን አልባት ስለ ጊቢ ትውስታቸው ልታወራ ነው ብዬ ባልጠራም ለወሬ ቀላወጥኩ...
"ድሮ ታች ክላስ ስንስቅ አስተማሪዎቻችን ንገሩንና እኛም እንሳቅ የሚሏት ነገር...ካካካ"...ያማታል እንዴ...አሁን ይሄ ከእርሱ ጋር ነው ሊታወስ የሚገባው ወይስ ከእኔ ጋር...እንዳልኳችሁ ነው...ይቺን ሀኒ አላውቃትም...የማይናገረውን መብላት ጀመርኩ።
አላለቀም.....

👍16❤8
📖 የመጽሐፍ ዳሰሳ (Book Review)
📘 መጽሐፍ፦ አልወለድም
✍️ ደራሲ፦ አቤ ጉበኛ
📅 የታተመበት ዓመት፦ 1955 ዓ.ም
👤 ስለ ደራሲው
አቤ ጉበኛ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ፍፁም ደፋር፣ እውነትን የማይፈራ እና የጭቆና ስርአትን በብዕሩ በግልፅ የተቃወመ ታላቅና ታሪካዊ ፀሐፊ ነው። በንጉሱም ሆነ በደርግ ዘመን ስለ እውነት በመፃፉ ምክንያት እስር እና እንግልት የደረሰበት የህዝብ ድምፅ ነበር።
📝 ስለ መጻሕፉ
«አልወለድም» በኢትዮጵያ ስነ-ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ እጅግ ደፋር የተቃውሞ መጽሐፍ ነው። ታሪኩ የሚጀምረው ገና በእናቱ ማህፀን ውስጥ ሆኖ በዓለም ላይ ያለውን ግፍ፣ ጭቆና፣ ድህነት እና የባለስልጣናትን ግብዝነት የተመለከተ ህፃን "በዚህች ክፉ ዓለም ላይ አልወለድም!" ብሎ አሻፈረኝ ማለቱን ተከትሎ ነው። መጽሐፉ ስርአቱን በምሳሌያዊ መንገድ ክፉኛ ይተቻል።
📊 የመጽሐፉ ውጤት (Book Result)
መጽሐፉ እንደወጣ በወቅቱ የነበረው የፊውዳል ስርአት ወዲያውኑ እንዲታገድ እና እንዳይሸጥ አድርጎታል። ደራሲው አቤ ጉበኛም ወደ ጎሬ (ኢሉባቡር) በግዞት እንዲጋዝ ተደርጓል። ነገር ግን መጽሐፉ በምስጢር በሰዎች እጅ እየተቀባበለ በመነበብ በታሪክ ትልቅ ቦታ አግኝቷል።
አቅራቢ:- 📚@ambabooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
📘 መጽሐፍ፦ አልወለድም
✍️ ደራሲ፦ አቤ ጉበኛ
📅 የታተመበት ዓመት፦ 1955 ዓ.ም
👤 ስለ ደራሲው
አቤ ጉበኛ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ፍፁም ደፋር፣ እውነትን የማይፈራ እና የጭቆና ስርአትን በብዕሩ በግልፅ የተቃወመ ታላቅና ታሪካዊ ፀሐፊ ነው። በንጉሱም ሆነ በደርግ ዘመን ስለ እውነት በመፃፉ ምክንያት እስር እና እንግልት የደረሰበት የህዝብ ድምፅ ነበር።
📝 ስለ መጻሕፉ
«አልወለድም» በኢትዮጵያ ስነ-ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ እጅግ ደፋር የተቃውሞ መጽሐፍ ነው። ታሪኩ የሚጀምረው ገና በእናቱ ማህፀን ውስጥ ሆኖ በዓለም ላይ ያለውን ግፍ፣ ጭቆና፣ ድህነት እና የባለስልጣናትን ግብዝነት የተመለከተ ህፃን "በዚህች ክፉ ዓለም ላይ አልወለድም!" ብሎ አሻፈረኝ ማለቱን ተከትሎ ነው። መጽሐፉ ስርአቱን በምሳሌያዊ መንገድ ክፉኛ ይተቻል።
📊 የመጽሐፉ ውጤት (Book Result)
መጽሐፉ እንደወጣ በወቅቱ የነበረው የፊውዳል ስርአት ወዲያውኑ እንዲታገድ እና እንዳይሸጥ አድርጎታል። ደራሲው አቤ ጉበኛም ወደ ጎሬ (ኢሉባቡር) በግዞት እንዲጋዝ ተደርጓል። ነገር ግን መጽሐፉ በምስጢር በሰዎች እጅ እየተቀባበለ በመነበብ በታሪክ ትልቅ ቦታ አግኝቷል።
አቅራቢ:- 📚@ambabooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
❤12👍1
🔥 እስኪ ዛሬ ትንሽ የተለየ ውይይት እናድርግ!
አንድ አስፈላጊ ጉዳይ አለኝ፤ የእናንተንም አስተያየት ማወቅ እፈልጋለሁ። 👀
በግልጽና በነፃነት ሀሳባችሁን ለመጋራት ዝግጁ ናችሁ? 🤔
ከሆነ፣ ከስር Comment ላይ
👇 «አዎ፣ ፈቃደኛ ነኝ» ብላችሁ ጀምሩ!
ጉዳዩን ቀጥሎ እንከፍተዋለን… 🔥

❤17🔥6
📚 የሳጥናኤል_ጎል_በኢትዮጵያ_ቁጥር_5📚
📝ደራሲ:- ፍስሐ ያዜ
📜ይዘት:-
📖የገፅ ብዛት:- 379
📅 ዓ.ም :- 2018
🖨 ዕትም :- —-
🪝Type :- #pdf #የሳጥናኤል_ጎል_በኢትዮጵያ_ቁጥር_5
🔔 አዘጋጅ :- @AmbaBooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
📝ደራሲ:- ፍስሐ ያዜ
📜ይዘት:-
📖የገፅ ብዛት:- 379
📅 ዓ.ም :- 2018
🖨 ዕትም :- —-
🪝Type :- #pdf #የሳጥናኤል_ጎል_በኢትዮጵያ_ቁጥር_5
🔔 አዘጋጅ :- @AmbaBooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
❤5
የሳጥናኤል_ጎል_ኢትዮጵያ_ቁጥር_5_AmbaBooks.pdf
116 MB
📚 የሳጥናኤል_ጎል_በኢትዮጵያ_ቁጥር_5📚
📝ደራሲ:- ፍስሐ ያዜ
📜ይዘት:-
📖የገፅ ብዛት:- 379
📅 ዓ.ም :- 2018
🖨 ዕትም :- —-
🪝Type :- #pdf #የሳጥናኤል_ጎል_በኢትዮጵያ_ቁጥር_5
🔔 አዘጋጅ :- @AmbaBooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
📝ደራሲ:- ፍስሐ ያዜ
📜ይዘት:-
📖የገፅ ብዛት:- 379
📅 ዓ.ም :- 2018
🖨 ዕትም :- —-
🪝Type :- #pdf #የሳጥናኤል_ጎል_በኢትዮጵያ_ቁጥር_5
🔔 አዘጋጅ :- @AmbaBooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
❤6🥰4
📚 ልዑሉ 📚
📝ደራሲ:- ኒኮሎ ማኬቬሊ
📜ይዘት:- -_-_
👤ትርጉም ፦ አና ፍራንክ
📖የገፅ ብዛት:- 152
📅 ዓ.ም :- 2005
🖨 ዕትም :- 58.6MB
🪝Type :- #pdf #ልዑሉ
🔔 አቅራቢ :- @AmbaBooks
አሰቃቂው መጽሐፍ!
ከ500 ዓመት በፊት ይሄ መጽሐፍ እንዲቃጠል እና እንዲታገድ የሃይማኖት አባቶች ፈርደውበት ነበር! መፍረድ ብቻ ሳይሆን ይሄንን መጽሐፍ ያነበበ ማንኛውም ሰው እንዲገደል ትዕዛዝ ተስጥቶ ነበር
ነገር ግን በአንድ ሰው ምክንያት አፈትልኮ በመውጣቱ ብዙ ሺ ሰዎች በአንድ ጊዜ አንብበውታል።በምስጢር የተለያዩ ቦታዎችና ሃገሮች ላይ ተዳርሷል።ዛሬም ድረስ አንዳንዶች ጭካኔ የተሞላበት መጽሐፍ ነው ይሉታል።አብዛኛዎቹ ደግሞ የሰውን ልጅ ባህሪ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አስደናቂ መጽሐፍ ነው ይሉታል።ብቻ አሁን ላይ ሚሊየን ኮፒ ተሸጧል።ዋሽግተን ፖስት ላይ በየሳምንቱ ከሚነበቡ መጽሐፎች ዝርዝር ውስጥ በ1ኛ ደረጃ ተቀምጧል

❤7👍1
ልዑሉ (The Prince)AmbaBooks.pdf
58.6 MB
📚 ልዑሉ 📚
📝ደራሲ:- ኒኮሎ ማኬቬሊ
📜ይዘት:- -_-_
👤ትርጉም ፦ አና ፍራንክ
📖የገፅ ብዛት:- 152
📅 ዓ.ም :- 2005
🖨 ዕትም :- 58.6MB
🪝Type :- #pdf #ልዑሉ
🔔 አቅራቢ :- @AmbaBooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
📝ደራሲ:- ኒኮሎ ማኬቬሊ
📜ይዘት:- -_-_
👤ትርጉም ፦ አና ፍራንክ
📖የገፅ ብዛት:- 152
📅 ዓ.ም :- 2005
🖨 ዕትም :- 58.6MB
🪝Type :- #pdf #ልዑሉ
🔔 አቅራቢ :- @AmbaBooks
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
❤4
🥳📚 ትልቅ የምስራች አለን!
በብዙዎቻችሁ ጥያቄ እና ጉጉት የተጠበቀው…
📖 «ጥሪ ወደ ሞት»
የመፅሐፉ PDF ቅጂ በቅርቡ በቻናላችን ይለቀቃል! 🔥
👀 ይህን መፅሐፍ ለረጅም ጊዜ ስትጠይቁን የነበራችሁ ቤተሰቦቻችን፣ ትንሽ ታገሱ! ❤️
🔔 PDF ሲለቀቅ እንዳያመልጣችሁ ቻናሉን ይከታተሉ!

❤23👍8🙏4🥰2👎1🔥1
📚 የኢትዮጵያ ስልጣኔ 📚
📝ደራሲ:-በላይ ግደይ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 132
📅 ዓ.ም :- 1983
⬇️size :- 9 MB
👆አቅራቢ:- @ambabooks
👇 ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
📢 @AMBABOOKS
📢 @AMBABOOKS
📢 @AMBABOOKS
❤️ React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
📝ደራሲ:-በላይ ግደይ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 132
📅 ዓ.ም :- 1983
⬇️size :- 9 MB
👆አቅራቢ:- @ambabooks
👇 ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
📢 @AMBABOOKS
📢 @AMBABOOKS
📢 @AMBABOOKS
❤️ React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
❤2👍1🙏1
Forwarded from አምባ መጻሕፍት ማቆያ 📚
የኢትዮጵያ_ስልጣኔ_ከበላይ_ግደይ_@AmbaBooks.pdf
9.1 MB
📚 የኢትዮጵያ ስልጣኔ 📚
📝ደራሲ:-በላይ ግደይ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 132
📅 ዓ.ም :- 1983
⬇️size :- 9 MB
👆አቅራቢ:- @ambabooks
━━━━━━━━━━
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📚 ዋና ቻናል ➤ @ambabooks
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️ ከወደዱት React ያድርጉ
📝ደራሲ:-በላይ ግደይ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 132
📅 ዓ.ም :- 1983
⬇️size :- 9 MB
👆አቅራቢ:- @ambabooks
━━━━━━━━━━
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📚 ዋና ቻናል ➤ @ambabooks
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️ ከወደዱት React ያድርጉ
👍1😘1
Forwarded from አምባ መጻሕፍት ማቆያ 📚
📚የኢትዮጵያ ታሪክ📚
📝ደራሲ:- ብላቴን ጌታ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 329
📅 ዓ.ም :- 1920
⬇️size :- 18.6 MB
👆አቅራቢ:- @ambabooks
👇 ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
📢 @AMBABOOKS
📢 @AMBABOOKS
📢 @AMBABOOKS
❤️ React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
📝ደራሲ:- ብላቴን ጌታ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 329
📅 ዓ.ም :- 1920
⬇️size :- 18.6 MB
👆አቅራቢ:- @ambabooks
👇 ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
📢 @AMBABOOKS
📢 @AMBABOOKS
📢 @AMBABOOKS
❤️ React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
❤2❤🔥2😘1
Forwarded from አምባ መጻሕፍት ማቆያ 📚
የኢትዮጵያ ታሪክ@AmbaBooks.pdf
18.6 MB
📚የኢትዮጵያ ታሪክ📚
📝ደራሲ:- ብላቴን ጌታ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 329
📅 ዓ.ም :- 1920
⬇️size :- 18.6 MB
👆አቅራቢ:- @ambabooks
━━━━━━━━━━
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📚 ዋና ቻናል ➤ @ambabooks
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️ ከወደዱት React ያድርጉ
📝ደራሲ:- ብላቴን ጌታ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 329
📅 ዓ.ም :- 1920
⬇️size :- 18.6 MB
👆አቅራቢ:- @ambabooks
━━━━━━━━━━
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📚 ዋና ቻናል ➤ @ambabooks
📖 ማቆያ ➤ @amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤ @amba_treka
🎓ትምህርት➤@yetmhrt_pdf
🎵 ሙዚቃ ➤ @ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️ ከወደዱት React ያድርጉ
❤3❤🔥2🥰1
Forwarded from አምባ ትረካ
📖የጦርነት ጥበብ 📚 the art of war📖
📝ደራሲ: ሰን ዙ
👤ትርጉም: ደሳለኝ ማስሬና ስማቸው ተበጀ
⏱️ቆይታ: 3:59:12 ⏳
ትረካ ሙሉ ክፍል
🎧 ትረካውን ለማዳመጥ አይርሱ!
📢 @AMBA_TREKA
📢 @AMBA_TREKA
❤️ React ያድርጉ!
📝ደራሲ: ሰን ዙ
👤ትርጉም: ደሳለኝ ማስሬና ስማቸው ተበጀ
⏱️ቆይታ: 3:59:12 ⏳
ትረካ ሙሉ ክፍል
🎧 ትረካውን ለማዳመጥ አይርሱ!
📢 @AMBA_TREKA
📢 @AMBA_TREKA
❤️ React ያድርጉ!
❤2🥰1
Forwarded from አምባ ትረካ
Audio
📖የጦርነት ጥበብ 📚 the art of war📖
📝ደራሲ: ሰን ዙ
👤ትርጉም: ደሳለኝ ማስሬና ስማቸው ተበጀ
⏱️ቆይታ: 3:59:12 ⏳
ትረካ ሙሉ ክፍል
👇 ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
📢 @AMBA_TREKA
📢 @AMBA_TREKA
❤️ React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
📝ደራሲ: ሰን ዙ
👤ትርጉም: ደሳለኝ ማስሬና ስማቸው ተበጀ
⏱️ቆይታ: 3:59:12 ⏳
ትረካ ሙሉ ክፍል
👇 ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
📢 @AMBA_TREKA
📢 @AMBA_TREKA
❤️ React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ
❤3