አለ ሕግ
16K subscribers
3.3K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ሰበር መዝገብ 244308 (1).docx
46.5 KB
ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ!
መዝገብ ቁጥር 244308
Click Ethiopian Laws
ከዚህ ቀደም በሰበር መዝገብ ቁጥር 43600 የተሰጠው ውሳኔ መሰረት በማድረግ በከተማ ክልል ያለን ይዞታ ለማስመለስ የቀረበ የመፋለም ክስ በይርጋ አይታገድም በሚል በሰበር መዝገብ ቁጥር 210477 የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ ተቀይሯል፡፡
Click Ethiopian Laws
ከከተማ መሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ አለአግባብ ከያዘ ሰው ላይ ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በአስር ዓመት ይርጋ ይታገዳል ተብሎ ተተርጉሟል፡፡
ይህንን ትርጉም የቀድሞው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ የአሁኑ ጠበቃ አቶ አልማው ወሌ ትችት ሰጥተውበታል። ሁለቱም ዶክመንቶች እነሆ
*Click Ethiopian Laws*
10
የመኪና ሽያጭ ውል፡ የጽሁፍ ስምምነት ብቻ በቂ ነው ወይስ ምዝገባ ያስፈልገዋል?
​የመኪና ሽያጭ ውል በጽሁፍ መደረጉ ብቻ ገዢውን የመኪናው ህጋዊ ባለቤት አያደርገውም። መኪና በህግ አግባብ "ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት" ተብሎ የሚመደብ በመሆኑ፣ የባለቤትነት መብት ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ህጋዊ በሆነ መንገድ ተላልፏል የሚባለው በህግ የተቀመጠው አሰራር ሲጠናቀቅ ብቻ ነው።
​በኢትዮጵያ ህግ፣ በተለይም በአዋጅ ቁጥር 681/2002 መሰረት፡
የባለቤትነት መታወቂያ (ሉብሬ)፡ የተሽከርካሪ ባለንብረት በስሙ የተዘጋጀ የባለቤትነት መታወቂያ መያዝ ግዴታ ነው።
የምዝገባ ሂደት፡ ተሽከርካሪን አስመልክቶ የሚደረግ የባለቤትነት መብት ማስተላለፍ ህጋዊ የሚሆነው በአዋጁ አንቀጽ 6 እና 7 ላይ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት፣ ገዢው ተሽከርካሪውን በራሱ ስም ሲያስመዘግብ ብቻ ነው።
​ስለሆነም፣ በሻጭ እና በገዢ መካከል የሚደረግ የጽሁፍ ውል የውል ግዴታዎችን ለመመስረት የሚያገለግል እንጂ፣ የባለቤትነት መብትን በራሱ አያስተላልፍም።
የባለቤትነት መብት መተላለፉን የሚያረጋግጠው በባለስልጣን መስሪያ ቤት (የትራንስፖርት ቢሮ) የሚከናወነው የባለቤትነት ምዝገባ ነው።
👍135
#ጥንቃቄ

" ውጭ ሀገር እንልካችኋል " የሚሉ ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸውን ዘራፊዎች ተጠንቀቁ።

በሀገራችን ወጣቱ ያለበትን የኑሮ ፈተና እንዲሁም ዜጎች አሁን ላይ ካለው የኑሮ ክብደት አንፃር ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ሲሉ በፍጥነት ገንዘብ ለማግኘት የሚያደርጉትን ከፍተኛ የህይወት ትግል እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ድሃውን ለመዝረፍ የተሰማሩ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያው ላይ እንደ አሸን ፈልተዋል።

" ውጭ አገር እንልካለን " በሚሉ አጭበርባሪዎች ያላችሁን በላባችሁ ያገኛችሁርን ፣ ተበድራችሁ የመጣችሁትን እንዳታጡ ጥንቃቄ አድርጉ።

ያስተውሉ ፦

1. ንግድ ፍቃድና ቢሮ ስላላቸው ብቻ አትመኗቸው።

አንዳንዶቹ ለጥቂት ወራት ቢሮ ተከራይተውና የሰው ፍቃድ ወይም የራሳቸውን ፍቃድ ይዘው የብዙዎችን ገንዘብ ሰብስበው ይሰወራሉ። ስለሆነም የድርጅቶቹን ማንነት በደምብ #አጣሩ

2. ገንዘብ በባንክም ቢሆን በጭራሽ እንዳታስገቡ። በካሽ እጅ በእጅ ስጡን ካሉ በፍጹም እንዳታምኗቸው።

" ቪዛ ተመትቷል"  በሚል ማታለያ በባንክ አካውንታቸው ብር እንድታስገቡ ካደረጉ በኋላ ስልካቸውን ዘግተው  የሚጠፉ አሉ። አልያም በካሽ እጅ በእጅ ስጡን ካሉ ገንዘባችሁን ይዘው ለመሰወር ብቻ ነው።

በሕጋዊ መንገድ ሳትሄዱ ምንም ክፍያ አትፈጽሙ።

3. የቲክቶክ፣ በፌስቡክ ፣ ቴሌግራም ወይም ሌሎች ሚዲያዎች ላይ የሚተላለፉ የተጋነኑ ማስታወቂያዎችን አትመኑ።


• " በአጭር ቀን እንልካችኋለን " ፣
• " ያለ ስልጠና እንልካችኋለን "  ፣
• " ያለ ምንም ትምህርት እና ክህሎት ትሄዳላችሁ "
• " ከፍተኛ ደመወዝ  ታገኛላችሁ " የሚሉ ማባበያዎች የሌቦች ወጥመድ ናቸው።

4. ታዋቂ ሰዎችን ታዋቂ ብቻ ስለሆኑ አትመኑ። እነሱ አሉ ማለት  ብቻ እውነት ነው ማለት አይደለም።

አርቲስቶች ወይም ታዋቂ ሰዎች ስለተከፈላቸው ብቻ ማስታወቂያ ሊሰሩ ይችላሉ፤ የእነሱ መኖር የድርጅቱን ታማኝነት አያረጋግጥም። ስለዚህ ስለ ድርጅቱ በደምብ አጣሩ።

5. ዋና ፓስፖርታችሁን አሳልፋችሁ አትስጡ።


" ቪዛ ለማስመታት " ወይም " ሂደት ለመጀመር " በሚል ሰበብ ዋና ፓስፖርታችሁን ተቀብለው ለወራት ሊያንገላቷችሁ እና ሊያስፈራሯችሁ ይችላሉ። የፓስፖርት ፎቶ ኮፒ ብቻ መስጠት ይበቃል፤ ዋናው ፓስፖርት ጉዞው ተረጋግጦ አሻራ እስኪሰጥ ድረስ በእጅዎ መቆየት አለበት።

ማንኛውንም ክፍያ ከመፈጸማችሁ በፊት ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የሥራ ስምሪት ቢሮ በመሄድ የድርጅቱን ትክክለኛነት አረጋግጡ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
15
1
Ethiopia’s defence was led by the Ministry of Justice and Addis Law Group LLP, a U.S.-based law firm founded by lawyers of Ethiopian origin, including Zewdineh Beyene (PhD). After four years of proceedings, the tribunal handed down a mixed ruling. The tribunal found that Ethiopia had not "expropriated the investment" and had "acted within its rights" to protect the environment and the city’s water supply. But it also found that the government had failed to meet the standard of "fair and equitable treatment." #Arbitration #Ethiopia #Turkey #Hague #ICJ

Read more - https://shorturl.at/nzstp
7
Income Tax Amn updated PP(3).pptx
395.2 KB
የገቢ ግብ አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሰረት የተዘጋጀ ማሰልጠኛ ሰነድ
3
መንግስት በሚያስተዳድርው ይዞታ ላይ በመንግስት ዕውቅናም ሆነ ሳያውቅ በይዞታው ላይ ግንባታ መፈጸም የንብረት ባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍና በዚህ አግባብ የሚቀርብ ክርክር ተባይነት የሌለው ስለመሆኑ
የፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ መ/ቁ 217447 ቅፅ 28.
👍2