👉 ቃብድ ✍️
ቃብድ ማለት ተዋዋይ ወገኖች ውላቸው እንዲጸናላቸው ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት እና ሽያጩን ለማረጋገጥ አንዱ ወገን ለሌላኛው የሚሰጠው የማስያዣ ገንዘብ ነው።
በኢትዮጵያ የውል ሕግ ሥርዓት ውስጥ ቃብድ ከመደበኛ የውል አፈጻጸም ለየት ያሉ የሕግ ውጤቶች አሉት።
1. የቃብድ የሕግ ውጤት በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885
እንደ ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885(1) እና (2) ድንጋጌ፣ በቃብድ የታሰረ የሽያጭ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለየው በሚከተሉት ነጥቦች ነው፦
ተቃራኒ ስምምነት እስካልተደረገ ድረስ፣ ቃብድ የሰጠው ወገን የሰጠውን ቃብድ በመተው፣ ቃብድ የተቀበለው ወገን ደግሞ የተቀበለውን ቃብድ እጥፍ አድርጎ በመመለስ ውሉን በፈቃዳቸው ማፍረስ ይችላሉ።
በቃብድ የታሰረ ውል እንደ ሌሎች መደበኛ ውሎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1776 መሠረት በግዴታ እንዲፈጸም በሕግ አይገደድም።
ይልቁንም ተዋዋዮቹ ቃብዱን በመተው ወይም እጥፍ በመመለስ ከውሉ የመውጣት የመውጫ ቀዳዳ ይሰጣቸዋል።
የቅድመ ክፍያ እና የቃብድ ልዩነት
👇👇👇✍️✍️✍️
ተከራካሪዎች የከፈሉት ገንዘብ ቃብድ ሳይሆን ለሽያጭ ዋጋው ማሟያ የተደረገ የቅድመ ክፍያ ከሆነ፣ የቃብድ ሕግ እጥፍ መመለስ ወይም ትቶ መቅረት ተፈጻሚ አይሆንም።
ቃብድ ለተዋዋይ ወገኖች ውሉን የመተው መብት የሚሰጥ ቢሆንም፣ የሚከፈለው ገንዘብ ቃብድ መሆኑንም ወይም የቅድመ ክፍያ መሆኑ በግልጽ መታወቅ አለበት።
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
ሚኪያስ መላክ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak

❤7👏1
ለተከታታይ አምስት (5) ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነው።
ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናትና ከዚያ በላይ ከስራ የቀረ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውልን ማቋረጥ የሚያስችል አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰበር መዝገብ ቁጥር 249795 ላይ አንድ ሰራተኛ በተከታታይ ከአምስት (5) ቀናት በላይ ከሥራ ከቀረ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ጠቅሶ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ ነበር።
ሆኖም ሰበር ሰሚ ችሎቱ አሁን ላይ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ከስራ ማሰናበት የለበትም የሚለውን የሕግ ትርጉም ሽሮታል።
በምትኩ ከእረፍቶችና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውሉን ማቋረጥ ይቻላል በሚል ትርጉም ተሰጥቷል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።
ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia

❤13😱1
ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው እነማን ናቸው?
ማንኛውም ሰው ማንኛውንም የንግድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብሎ በታክስ ከፋይነት መመዝገብ ይኖርበታል። ለዚህም አስቀድሞ የተመዘገበ ካልሆነ በስተቀር በታክስ ሕግ መሠረት ታክስ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ሰው በባለሥልጣኑ ዘንድ ለመመዝገብ ማመልከት አለበት፡፡
• ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው …
በንግድ ወይም በሙያ ሥራ (መቀጠርን ሳይጨምር) የተሰማራ ግለሰብ፣
ቤት በማከራየት ገቢ የሚያገኝ ግለሰብ፣
ተቀጣሪ፣
የመንግሥት የልማት ድርጅት፣
የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤት፣
መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
የሃይማኖት ተቋማት፣
የንግድ ማህበር፣
በኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆነ ኩባንያ በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት፣
የወጪ መጋራት ተጠቃሚዎች፣
በጋራ ሃብትነት ያልተመዘገበ ሃብት ያላቸው ሰዎች፣
ባለ ልዩ መብት፣
በመንግሥታት መካከል የሚደረግ ስምምነት በጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ ስምምነት የሚቋቋም ድርጅት እንዲሁም
የኩባንያ አክሲዮን ባለድርሻ ናቸው።

❤2
በመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደ
--------------------
(ዜና ፓርላማ) ሚያዝያ 19፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመረጃ ነጻነት አዋጅ ላይ ከአስረጅዎች ጋር ተወያይቷል።
የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቱ አለነ በውይይቱ መክፈቻ እንዳሉት በመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ ግልጽ ያልሆኑ ሐሳቦችን በጥያቄ ተነስተው በኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ የሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያ የሚሰጥበት መሆኑን አመላክተው ውይይቱን በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ወይዘሮ ስመኝ ውቤም የአዋጁን አስፈላጊነት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግሥትና በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች መሠረት መረጃን ሕዝቡ እንዲያገኝ ታስቦ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱም የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አዝመራ አንዴሞ፣ የቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ እና ሌሎች የዕንባ ጠባቂው የሥራ ኃላፊዎች ተግኝተዋል።
(በ ጋሹ ይግዛው)
www.hopr.gov.et

Telegram
House of Peoples' Representatives of FDRE
የህዝብ ተወካይ የህዝብ አገልጋይ
#የደቦ #ፍርድ ከጎዳና እስከ ዲጂታል አደባባይ #ለሕግ የበላይነት የፈጠረው ስጋት
በሀገራችን እየተለመደ የመጣው #የደቦ_ፍርድ (Mob Justice) ከጎዳና እስከ ዲጂታል መድረኮች ፍትሕን ከችሎት አውጥቶ አደባባይ ላይ በመጣል የሀገርን ገጽታና የዜጎችን ደኅንነት ከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሎ ይገኛል፡፡ በማንኛውም ሥልጡን ማኅበረሰብ ውስጥ ፍትሕ የሚሰጠው በሕግ በተቋቋሙ የፍርድ አካላት እንጂ በቲክቶክ የዲጂታል ፍረጃ ወይም በጎዳና ስሜታዊ ስብስብ አይደለም፡፡
አለሕግ ስንል፤ አወ ሕግ ስላለ ነው፡፡ ሕግ ባለበት ሀገር ደግሞ ፍትሕ የማግኘት መብት የሁሉም ሰው ነው፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 መሠረት፣ የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤት እንጂ የቲክቶክ መንደር ወይም የሰፈር ቡድን አይደለም፡፡
ችሎት ማለት ዝም ብሎ አዳራሽ ወይም ወንበር አይደለም፤ ችሎት የሥልጣን፣ የጥበብ እና የውሳኔ መፍለቂያ ነው። በሕግ ቋንቋ ችሎት ማለት፡-
1. ክርክር የሚሰማበትና የሚደመጥበት፣
2. ማስረጃ የሚመዘንበትና እውነታው የሚመረመርበት፣
3. በዳኞች አማካኝነት የመጨረሻ ሕጋዊ ውሳኔ የሚሰጥበት የተቀደሰ ሥርዓት ነው፡፡
በሕገ-መንግሥታችን አንቀጽ 20 መሠረት፣ ማንኛውም ሰው ጥፋተኛነቱ በሕግ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደ ንጹሕ የመቆጠር መብት አለው፡፡ ሆኖም ዛሬ ወንጀለኛን ማጋለጥ በሚል ሰበብ፤ የግል ቂም በቀልንና ጥላቻን ለመወጣት የሚደረጉ የዲጂታል ስም ማጥፋት ዘመቻዎች ንጹሕ ዜጎችን ለከፋ ሥነልቦናዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እየዳረጉ ነው፡፡ በተለይ በቲክቶክ እና መሰል መድረኮች ላይ ፎሎወር እና ላይክ ለማግኘት ብቻ ፖሊስ ምርመራ ሳይጀምር ሰዎችን ማዋረድና እንደወንጀለኛ መቁጠር እንዲሁም ለጥቃት ማጋለጥ በራሱ ከባድ ወንጀል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ብዙዎች በቡድን ስንሆን አንጠየቅም ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፤ ይህ ግን ትልቅ የሕግ ስህተት ነው፡፡ በወንጀል ሕጋችን መሠረት በቡድን/በደቦ ነው የፈጸምኩት የሚል ምክንያት ከቅጣት አያድንም፡፡
• የጸጥታ አካላት ተጠርጣሪዎችን ሲይዙ የሚያሳዩት ከሥነምግባር ውጭ የሆነ አያያዝ ማኅበረሰቡ ሕግን በእጁ እንዲያጠናቅቅ በዝምታ የሚሰጥ ግብዣ ይመስላል፡፡ ሕግ የሚከበረው ሕግን አክብሮ በማስከበር ነው፡፡
• ወንጀለኛን ለሕግ አሳልፎ መስጠት እንጂ፣ በእራሳችን እርምጃ መውሰድ እና ራስን እንደ ዳኛ አድርጎ መቁጠር ሌላ የከፋ ወንጀል ነው፡፡ ዛሬ በሌላው ላይ የሚፈረደው የደቦ ፍርድ፣ ነገ የእኛንም በር ማንኳኳቱ አይቀርም፡፡
መደብደብ፤ መግደል፤ ማኅበራዊ ሚዲያዎች/በዲጂታል ስም ማጥፋት እና ለአሉታዊ ነገር ግለሰቦችን ማነሳሳት በቡድን/በደቦ በዘመቻ ስለተፈፀመ ተጠያቂነትን አያስቀርም
1. በኢፌዴሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 15 ፤20 ፤ 24 እና 37 መሰረት ማንኛውም ሰው በሕግ ካልተደነገገ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡ ጥፋተኛነቱ በሕግ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደ ንጹሕ ይቆጠራል፡፡ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው፡፡ ክርክሩ ወይም ጉዳይ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ለማስወሰን መብት አለው፡፡
2. በወንጀል ህጋችን አንቀጽ 538 እና ተከታዮቹ መሰረት በሰው ሕይወትና አካል ላይ የሚፈጸሙ በቡድን የታገዙ ጥቃቶች ከባድ ቅጣት ያስከትላሉ፡፡
3. የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ 958/2008 መሰረት በዲጂታል መድረክ የሰውን ስም ማጥፋትና የሐሰት መረጃ ማሰራጨት በጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡
4. የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ አዋጅ 1185/2012 መሰረት በማስረጃ ያልተደገፈ ማንኛውም ሰው ወንጀለኛ እያሉ መሰየም ዘመቻ ከባድ የወንጀል ተጠያቂነት አለው፡፡
ያለ ሕግ የበላይነት ፍትሕ የለም፤ ያለ ፍትሕ ደግሞ ሰላም የለም! የፍርድ ቤት መዶሻን በእጃችን ከመያዝ እንቆጠብ። መንግሥት የሕግ ማስከበር ቁርጠኝነቱን በተግባር ሊያሳይ፣ ማኅበረሰቡም ለሕግ ተገዥነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡
በዚህች ምድር ስንኖር ያለ ሕግ ፍትሕ የለም፤ ያለ ሕግ የበላይነት ፍትሕ የለም፤ ያለ ፍትሕ ደግሞ ሰላም የለም!
በእውነት ዓምድ እንቁም!
ሚኪያስ መላክ
በፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤት
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
አለሕግ alehig.com አለ ሕግ
0920666595
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
https://t.me/AleHig

❤12🥰1
ከ6 ዓመት በላይ ሲሰራበት የነበረውን እና ለስራ የተሰጠውን ተሽከርካሪ የሸጠው ሾፌር በእስራት ተቀጣ፤ የተሽከርካሪው ሠሌዳና ቀለም ተቀይሮ ተገኝቷል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የሠሌዳ ጥቁር ኮድ 1-37226 አ/አ ሚኒባስ አሽከርካሪ የሆነው አሽናፊ ታደሰ ለስራ የተሰጠውን ተሽከርካሪ ይዞ መጥፋቱ ያሳሰባቸው የመኪናዋ ባለንብረት ወ/ሮ አስራት በየነ ጉዳዩን ለፖሊስ ያሳውቃሉ፡፡
ፖሊስ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ባሰባሰበው መረጃ ሾፌሩ መኪናውን በ280ሺ ብር ሸጦ ከሀገር ለመውጣት ጥረት ሲያደርግ ጅግጅጋ ከተማ ላይ በቁጥጥር አውሎታል፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካራማራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ንብረቱን ለማስመለስ ባደረገው ጥረት መኪናውን የገዛውን ያብስራ አበራን በቁጥጥር ማዋሉን አስታውቋል፡፡
መኪናውን የገዛው ግለሰብ ከዚህ በፊት ሰማያዊ በነጭ የነበረውን የተሽከርካሪውን ቀለም ሙሉ በሙሉ ነጭ በማስቀባት እንዲሁም ኮድ 1-37226 አ/አ የነበረውን ሰሌዳ ወደ ኮድ 3-ኦሮ 93124 በመቀየር የኋላ ወንበር ሙሉ በሙሉ በመፍታትና የመኪናውን ዕቃ መጫኛ በመንቀል ተሽከርካሪው ሌላ ይዘት እንዲኖረው በማድረግ ሻሽመኔ ከተማ ዲዳ ቦቄ በሚባል መንደር በአንድ መኖሪያ ግቢ ውስጥ መኪናውን ደብቆ ተገኝቷል፡፡
ግለሰቡ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረ በአሁኑ ወቅት ግልጋሎት የማይሰጥ መኪናን ሰሌዳ በመለጠፍ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ታውቋል፡፡
ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡ ለአቃቤ ህግ በመላክ ዋናው ወንጀል ፈፃሚ በሆነው አሽናፊ ታደሰ ክስ እንደ እንዲመሰረት አድርጓል፡፡
የአሽናፊ ታደሰን ጉዳይ የተመለከተው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ፈጣን ችሎት ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ግለሰቡ በ4 ዓመት ከ11 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡ ተሽከርካሪውን የገዛው ያብስራ አበራ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት በማረፊያ ቤት የሚገኝ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መኪናዋን የሸጠው ግለሰብ ለ6 ዓመት በረዳት እና ለአንድ ዓመት በሾፌርነት በሸጣት መኪና ላይ ሲሰራ እንደነበር ታውቋል፡፡
የተሰረቀ ንብረት የሚገዙ ግለሰቦች ለወንጀል መስፋፋት መንስኤ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሰረቀ ንብረት በሚያሻሽጡ እና በሚገዙ ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ የጀመረውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡ https://www.addispolice.gov.et/Q

❤7👏6🔥1
ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ሰላምታ ይድረስዎ፣
በ1958 ዓ.ም የተመሰረተው እና ስልሳኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከምስረታው ጀምሮ ለሕግ ባለሙያዎች መብት መጠበቅ፣ ለሕግ ሙያ መዳበር እንዲሁም ለማኅበረሰብ ነጻ የሕግ አገልግሎት እየሰራ የተለያዩ ታሪካዊ ሁነቶችን በማለፍ 60 ዓመታትን ተጉዟል። ማኅበራችን፣ የተመሠረተበትን 60ኛ ዓመት ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ያከብራል።
እርስዎም፣ በእለቱ በመካከላችን ተገኝተው የማኅበራችንን ሥልሳኛ ዓመት አብረን እንድናከብር ከዚህ ጋር በተያያዘው የጥሪ ደብዳቤ በማክበር ጠርተኖታል መገኘት የሚችሉ ከሆነ የደብዳቤውን ዝርዝር በማየት እስከ ሚያዝያ 20 ድረስ እንዲያሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን።
ለሕግ ሙያ እና ለሕግ ስርዓት መዳበር የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሕግ ባለሙያዎችን እናክብር!
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115530122 ወይም በ0925171651 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
የኢትዮጲያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር

❤9👍6