አለ ሕግ
16K subscribers
3.3K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
👉 #የሰነድ #ማስረጃ አቀራረብ በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145 ሥር
#በፍትሐብሔር #ክርክር ሂደት ውስጥ የሰነድ ማስረጃዎችን በወቅቱ እና በሥነ-ሥርዓቱ መሠረት ማቅረብ ለፍትህ መከበር ወሳኝ ነው። ብዙ ጊዜ ግልጽነት የሚጎድለውን የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 አተገባበር እና ከሌሎች ድንጋጌዎች ጋር ያለውን ቁርኝት እንደሚከተለው እንመልከተው።
🔍 የሰነድ ማስረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ
በመሠረቱ ማንኛውም ተከራካሪ ወገን ሊያቀርባቸው የሚፈልጋቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ከክስ ወይም ከመልስ ጋር አያይዞ የማቅረብ ግዴታ አለበት (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 137, 223 እና 234)። ነገር ግን ማስረጃው በእጁ ያልሆነና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲቀርብለት የሚፈልግ ከሆነ በቁጥር 145 መሠረት ይጠይቃል።
👉 ቁጥር 145 መቼ እና እንዴት ተግባራዊ መሆን አለበት?
ቅድመ-ዝግጅት፦ አንድ ተከራካሪ ማስረጃውን በራሱ አቅም ማቅረብ ካልቻለ፣ ፍርድ ቤቱ ማስረጃው ለክርክሩ አስፈላጊ መሆኑን አምኖበት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ይሰጣል።
ከጭብጥ በፊት፦ ይህ ሂደት የግድ የክስ መስማት ሂደቱ ከመጀመሩ እና ጭብጥ ከመያዙ በፊት ሊከናወን ይገባል።
የመሰማት መብት፦ ፍርድ ቤቱ በቁጥር 145 መሠረት ያስቀረበው ማስረጃ ለሌላኛው ወገን ሊደርሰው ይገባል። ለምሳሌ፡ ከሳሽ ያስቀረበው ሰነድ ለተከሳሽ ደርሶት፣ ተከሳሹ በሰነዱ ላይ ተመስርቶ የመከላከያ መልሱን ሊያደራጅ ይገባል።

👉 ማስረጃ በወቅቱ ባይቀርብ የሚመጣው ችግር
ማስረጃዎች በጊዜው (በመጀመሪያው ቀጠሮ ወይም ከዚያ በፊት) ሳይቀርቡ ቀርተው፣ ክርክሩ ተጠናቆ ለፍርድ በሚያዝበት ወቅት እንዲቀርቡ ከታዘዘ የሚከተሉት ችግሮች ይፈጠራሉ፡
👉ተከራካሪ ወገኖች በማስረጃው ላይ የመከራከር እና አስተያየት የመስጠት ዕድል ያጣሉ።
አዲስ ማስረጃ በገባ ቁጥር አዲስ ጭብጥና ክርክር እየተነሳ የፍርድ ሂደቱ ይንዛዛል።
የተገኘው ውጤት የፍትሃዊነት ሚዛኑን ሊስት ይችላል።

👉 ዋና ዋና ነጥቦች
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 137፦ ማንኛውም የጽሁፍ ማስረጃ ከመጀመሪያው የችሎት ቀጠሮ በፊት ወይም በዕለቱ መቅረብ እንዳለበት ያዝዛል።
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 256፦ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በጊዜው ያልቀረበ ማስረጃ ካለ፣ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት መቅረብ እንደሚችል ቢደነግግም፣ ይህም ቢሆን የተቃራኒ ወገንን የመሰማት መብት በጠበቀ መልኩ ሊሆን ይገባል።
ጭብጥ አመሰራረት፦ እንደ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 249 ድንጋጌ፣ ትክክለኛ ጭብጥ ለመያዝ የሰነድ ማስረጃዎችን አስቀድሞ መመርመር ለፍርድ ቤቱ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ክርክር ወደ ኋላ እንዳይመለስ፣ ሂደቱ እንዳይጓተት እና ፍትህ እንዳይዛባ፤ በ145 መሠረት የሚቀርቡ ማስረጃዎች ክስ መስማት ከመጀመሩ በፊት ቀርበው ተከራካሪዎች ሊያውቋቸው ይገባል። ማስረጃ ሳይቀርብ ወይም ሳይመረመር የሚሰጥ ውሳኔ የህግ መሠረት የለውም።
#EthiopianLaw #LegalAwareness #CivilProcedure #Justice #Ethiopia #የህግምክር #ፍትሐብሔር
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
17👍3
ታናሸ ወንድም የሚከበርበትና የሚፈራበት,የታዛዥነት ስሜት ሊፈጠርበት የሚችልበት ሁኔታ የለም-
የውርስ ድርሻዬን በ 3(ሶስት) ዓመት ውስጥ ከስሼ ያልጠየቅኩትና ይርጋ ያገደኝ ታናሽ ወንድሜን በማክበርና በመፍራት ነው ብሎ መከራከር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፌደራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 166214 በሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ/ም ገዢ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
በ ዘወልድ ምክረ ህግ
9
ሰበር መዝገብ 244308 (1).docx
46.5 KB
ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ!
መዝገብ ቁጥር 244308
Click Ethiopian Laws
ከዚህ ቀደም በሰበር መዝገብ ቁጥር 43600 የተሰጠው ውሳኔ መሰረት በማድረግ በከተማ ክልል ያለን ይዞታ ለማስመለስ የቀረበ የመፋለም ክስ በይርጋ አይታገድም በሚል በሰበር መዝገብ ቁጥር 210477 የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ ተቀይሯል፡፡
Click Ethiopian Laws
ከከተማ መሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ አለአግባብ ከያዘ ሰው ላይ ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በአስር ዓመት ይርጋ ይታገዳል ተብሎ ተተርጉሟል፡፡
ይህንን ትርጉም የቀድሞው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ የአሁኑ ጠበቃ አቶ አልማው ወሌ ትችት ሰጥተውበታል። ሁለቱም ዶክመንቶች እነሆ
*Click Ethiopian Laws*
10
የመኪና ሽያጭ ውል፡ የጽሁፍ ስምምነት ብቻ በቂ ነው ወይስ ምዝገባ ያስፈልገዋል?
​የመኪና ሽያጭ ውል በጽሁፍ መደረጉ ብቻ ገዢውን የመኪናው ህጋዊ ባለቤት አያደርገውም። መኪና በህግ አግባብ "ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት" ተብሎ የሚመደብ በመሆኑ፣ የባለቤትነት መብት ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ህጋዊ በሆነ መንገድ ተላልፏል የሚባለው በህግ የተቀመጠው አሰራር ሲጠናቀቅ ብቻ ነው።
​በኢትዮጵያ ህግ፣ በተለይም በአዋጅ ቁጥር 681/2002 መሰረት፡
የባለቤትነት መታወቂያ (ሉብሬ)፡ የተሽከርካሪ ባለንብረት በስሙ የተዘጋጀ የባለቤትነት መታወቂያ መያዝ ግዴታ ነው።
የምዝገባ ሂደት፡ ተሽከርካሪን አስመልክቶ የሚደረግ የባለቤትነት መብት ማስተላለፍ ህጋዊ የሚሆነው በአዋጁ አንቀጽ 6 እና 7 ላይ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት፣ ገዢው ተሽከርካሪውን በራሱ ስም ሲያስመዘግብ ብቻ ነው።
​ስለሆነም፣ በሻጭ እና በገዢ መካከል የሚደረግ የጽሁፍ ውል የውል ግዴታዎችን ለመመስረት የሚያገለግል እንጂ፣ የባለቤትነት መብትን በራሱ አያስተላልፍም።
የባለቤትነት መብት መተላለፉን የሚያረጋግጠው በባለስልጣን መስሪያ ቤት (የትራንስፖርት ቢሮ) የሚከናወነው የባለቤትነት ምዝገባ ነው።
👍135