አለ ሕግ
16K subscribers
3.3K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
EBS ቴሌቪዥነ በቅርቡ በሞት በተለየዉ ወንድማችን በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ይቀርብ የነበረዉን የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም በተመለከተ ለማስቀጠል ተክቶ ማን ያጋፍር ሲሉ ጠይቀዋል። ጠቁሙ ተብሏል።

በመሆኑም ካለዉ የሕዝብ ተወዳጅነት የዘርፉ ብቃትና ችሎታ አንፃር አርቲስት ሸዋፈራዉ ደሳለኝ አጋፋሪ ሆኖ ቢያስቀጥል የተሻለ ነዉ የሚል እምነት አለን። እናንተ ምን ትላላችሁ?
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
🤮49👎4028👍1🔥1
ዜና ሹመት ፣ #ሕግ አዋቂው ፣ #የሕግ #ሰው #ዮናስ_አለማየሁ
አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ተቋም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ ደንብ ቁጥር 193/2017ዓ.ም ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባ ከተደረገበት ግዜ ጀምሮ አቶ ዮናስ አለማየሁ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ መሆኑ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ዮናስ አለማየሁ ከየካቲት 25/2018ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመሶብ አገልግሎት ዋና ስራ-አስፈፃሚ ሆነው እንዲያገለግሉ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል።

የአዲስ መሶብ ስትራቴጂክ እና ጠቅላላ ካውንስል እንዲሁም መላው ሰራተኛ አቶ ዮናስ አለማየሁ ተቋሙን ከማደራጀት ጀምሮ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ላበረከቱት አስተዋፅዖ እና ለሰጡት አመራር ከልብ እያመሰገነ የሃገር አቀፉን የመሶብ ስርዓት እንዲመሩ በተመደቡበት ሃላፊነት ውጤታማ የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።
Addis MESOB
The New Horizon of Service !
24👏2👍1
በፍርድ ቤት በክርክር ላይ ባለጉዳይ ተከራካሪ ወገኖች ነገሩን በእርቅ ለመጨረስ ተስማምተው እርቁም በጹሑፍ ተደርጎ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ተረጋግጦ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ ከተደረገ የእርቅ ስምምነት እንደ ፍርድ ተወስዶ አፈፃፀም ክስ ሊቀርብበት የሚችል ሲሆን ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በተከራካሪ ወገኖች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር እንደ መደበኛ ዉል ዉል እንዲፈርስ አዲስ ክስ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ ,, የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 386 ; 392 ,,,, ቅፅ 28 ሰ/መ/ቁ 143086,,,
Ethio law
10
🥇ጋብቻው በየትኛውም ዓይነት የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓት ቢፈጸም በጋብቻ ላይ ፍቺ ለመወሰን ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ ነው።
🥈አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ለረጅም ጊዜያት ተለያይተው ቢኖሩም፤ ሌላ ትዳር ቢመሰርቱም ጋብቻቸው በፍርድ ቤት እስካልፈረሰ ድረስ በሕግ አግባብ ባልና ሚስት እንደሆኑ ይቆጠራሉ።
🥉ፍቺ ለመጠየቅ ጋብቻ መኖሩን ማስረዳት ቀዳሚ ግዴታ ነው። በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ጋብቻ አለ ለማለት የጋብቻ ምስክር ወረቀት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል። የጋብቻ ምስክር ወረቀት በሌለ ጊዜ የሰው ምስክሮችን በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል።
4⃣በሕግ አግባብ 2 ዓይነት ፍቺ አለ። 1ኛው. የስምምነት ፍቺ ሲሆን 2ኛው. አንደኛው ተጋቢ የፍቺ አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ የሚያሰጥበት ፍቺ ነው። ሁለቱም የግዴታ ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ መሆን አለባቸው።
5⃣ጋብቻ በሁለቱ ተጋቢዎች ፍላጎት እና ነፃ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ አንደኛው ተጋቢ ፍቺውን አልፈልግም ቢል ወይም ፍርድ ቤት ባይቀርብም ፍርድ ቤቶች የፍቺ ውሳኔ ከመስጠት የሚከለክላቸው አይደለም።
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹
23
ሕግና ኢኮኖሚክስ
የውል ሕግ ኢኮኖሚክስ (Economics of Contract Law) ትኩረት የሚያደርገው ሕጉ እንዴት የሀብት ክፍፍልን ውጤታማ እንደሚያደርግ እና በሰዎች መካከል የሚደረጉ ግብይቶች ዝቅተኛ ወጪና ከፍተኛ ጥቅም እንዲኖራቸው እንዴት እንደሚረዳ ሲሆን፣ ይህ ዘርፍ ሕግና ኢኮኖሚክስ (Law and Economics) በሚባለው ሰፊ የጥናት መስክ ውስጥ ይመደባል። የውል ሕግ ሰዎችን ለማስገደድ ብቻ ሳይሆን፣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡ መተማመንን በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል፤ በተለይም ግብይቶች በተመሳሳይ ጊዜ የማይከናወኑ ከሆነ (ለምሳሌ ዛሬ ተከፍሎ ዕቃው ከሳምንት በኋላ የሚደርስ ከሆነ) ሕጉ ውልን አስገዳጅ በማድረግ ሻጩ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመጠራጠር ስጋት ያስቀራል። በተጨማሪም ወገኖች ስለ ግብይቱ ያላቸውን መረጃ በግልጽ እንዲለዋወጡ በማድረግ የመረጃ አለመመጣጠን (Information Asymmetry) የሚያስከተለውን ኪሳራ ከመቀነሱም በላይ፣ ሕጉ ቀድመው የተዘጋጁ ውሎችን (Default Rules) በማቅረብ ወገኖች ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ነገር ረጅም ጊዜ እንዳይደራደሩና የግብይት ወጪያቸው (Transaction Costs) እንዲቀንስ ይረዳቸዋል።

በውል ሕግ ኢኮኖሚክስ ውስጥ በጣም አነጋጋሪው ጽንሰ-ሐሳብ "ውጤታማ ውል ማፍረስ" (Efficient Breach) ሲሆን፣ ይህም አንዳንድ ጊዜ ውልን ከመፈጸም ይልቅ ማፍረስ ለጠቅላላው ኢኮኖሚ የተሻለ ጥቅም የሚሰጥበትን ሁኔታ ያብራራል። አንድ ወገን ውሉን አፍርሶ ለሌላኛው ወገን የሚገባውን የካሳ መጠን (Compensatory Damages) ከከፈለ በኋላም ትርፋማ ሆኖ የሚቀጥል ከሆነ፣ ያ ውል መፍረሱ በኢኮኖሚክስ እይታ ውጤታማ ይባላል፤ ምክንያቱም ሀብቱ ይበልጥ ዋጋ ወደሚሰጠው አካል እንዲሄድ በማድረጉ ሁሉም ወገኖች ተጠቃሚ ይሆናሉ። ለምሳሌ አንድ ሰው ለሌላው ዕቃ በ 100 ብር ለመሸጥ ተስማምተው ሳለ ሌላ ሶስተኛ ሰው መጥቶ ያንኑ ዕቃ በ 150 ብር ለመግዛት ቢፈልግ፣ ሻጩ የመጀመሪያ ውሉን አፍርሶ ለመጀመሪያው ገዢ የደረሰበትን 20 ብር የጉዳት ካሳ ከከፈለ በኋላ 130 ብር ትርፍ ይኖረዋል፤ በዚህም የመጀመሪያው ገዢ ጉዳት ተክሷል፣ ሻጩ ትርፍ አግኝቷል፣ ዕቃውም የበለጠ ዋጋ ወደሚሰጠው ሁለተኛው ገዢ ተላልፏል።

ሕጉ ውል ሲፈርስ የሚጥላቸው የተለያዩ የካሳ ዓይነቶች ወገኖች ለወደፊቱ እንዴት ዓይነት ተግባር ሊፈጽሙ እንደሚገባ ማበረታቻ (Incentive) የመስጠት ግብ አላቸው። ውሉ ቢፈጸም ኖሮ ተበዳዩ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም የሚሰጠው Expectation Damages እና ተበዳዩ በውሉ በመተማመን ላወጣው ወጪ የሚካሰው Reliance Damages እንደየሁኔታው ኢኮኖሚያዊ ግባቸውን ይመታሉ። በተጨማሪም ሕጉ ስጋትን (Risk) ዝቅተኛ ወጪ ለሚያወጣው ወገን የመጫን መርሕ ይከተላል፤ ለምሳሌ ግንባታ በዝናብ ቢስተጓጎል አስቀድሞ የመከላከል አቅሙ ያለው ተቋራጩ በመሆኑ፣ ሕጉ ስጋቱን በእርሱ ላይ መጫኑ ተቋራጩ የተሻለ ጥንቃቄ እንዲያደርግና የኢኮኖሚ ኪሳራን እንዲቀንስ ያነሳሳዋል።

ይህ የውል ሕግ ኢኮኖሚክስ ከፍትሐዊነት ባሻገር ውጤታማነትን (Efficiency) የሚፈልግ የሕግ ፍልስፍና ሲሆን፣ ግጭቶችን በመቀነስና መተማመንን በማዳበር የአገርን የኢኮኖሚ ዕድገት በከፍተኛ ሁኔታ ይደግፋል። ሀብት ይበልጥ ዋጋ ወደሚሰጠው አካል እንዲሄድ በማመቻቸትና ወገኖች ያላቸውን አቅም በቁጠባና በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ በማበረታታት፣ የውል ሕግ ለንግድና ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ የሕግ ከባቢን ይፈጥራል። ይህ ዘርፍ በሰዎች መካከል የሚደረጉ ግብይቶች በግልጽነትና በብቃት እንዲከናወኑ በማድረግ ረገድ ያለው ፋይዳ በቀላሉ የሚታይ አይደለም።
ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ African Leadership Excellence Academy

አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
17👏2🙏1
If you are ever called as a Witness in Court, these are the first questions you will hear

“Witness, tell the court your name.”
“My name is …”

“Where do you live?”
“I live at …”

“What do you do for a living?”
“I am a …”

Do you know the defendant in this case?”
“Yes, I do.”

“How do you know him?”
“He is my neighbor / friend / colleague…”

“Do you remember what happened on the day of the incident?”
“Yes.”

“Tell the court what happened.”

If you have ever attended a court session, you would notice that witnesses are usually asked questions like these before they begin to explain what happened. This stage of the trial is called Examination-in-Chief.

Examination-in-Chief simply means the stage where a lawyer questions the witness he or she brought to court so that the witness can tell the judge what they know about the case.

The purpose is simple. To allow the witness explain what they saw, heard, or experienced.

During Examination-in-Chief, the lawyer usually asks simple and open questions such as:
• “What happened next?”
• “Where were you when it happened?”
• “Who was there with you?”
• “What exactly did you see?”
• “Can you identify the person you saw that day?”

One important rule in this stage is that the lawyer should not ask leading questions. In other words, the lawyer should not suggest the answer to the witness.

For example:
“The defendant slapped you, didn’t he?”
Instead, the proper way is:
“What did the defendant do?”

This allows the witness to tell the story in their own words, which helps the court hear the facts directly from the person who experienced them.
After the lawyer finishes the Examination-in-Chief, the opposing lawyer will then question the witness. That stage is called Cross-Examination.

So the next time you hear a lawyer say in court:
“Witness, tell this Honourable Court what happened…”

You are watching Examination-in-Chief in action.

Have you ever witnessed a court proceeding before?

©️Confidence Aribibia
I remain your favorite Lawyer💕

Please note we now have a backup page Legal Talk with #Confidence_Aribibia

አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
24👍3
አዲስ የተመዘገበ ሰው የግብዓት ታክስ ተቀናሽ
*******************************
(1) ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ አዲስ የተመዘገበ ሰው በተመዘገበበት ቀን በእጁ በሚገኙ እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ለማከናወን በሚውሉ የንግድ ዕቃዎች ወይም የካፒታል ዕቃዎች ላይ የከፈለው የግብዓት ታክስ ተቀናሽ እንዲደረግለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

 ሀ) የተመዘገበው ሰው የንግድ ዕቃዎቹን ወይም የካፒታል ዕቃዎቹን ከተመዘገበበት ቀን በፊት ባለው የመጨረሻ ቀን በእጁ የያዘ ከሆነ፣
 ለ) የተመዘገበው ሰው የንግድ ዕቃዎቹን ወይም የካፒታል ዕቃዎቹን ያገኘው ተቀናሽ በሚደረግ ግዥ ከሆነ፣
 ሐ) ተቀናሽ የሚደረገው ግዥ የተፈጸመው፡-
(1)የንግድ ዕቃዎችን በሚመለከት፣ ከተመዘገበበት ቀን በፊት ባለው የ6 ወር ጊዜ ውስጥ ከሆነ፣
(2)የካፒታል ዕቃዎችን በሚመለከት፣ ከተመዘገበበት ቀን በፊት ባለው የ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ከሆነ፣ እና
 መ) የተመዘገበው ሰው የታክሱን ባለስልጣን በሚያረካ አኳኋን ተቀናሽ ለሚደረገው ግዥ የግብአት ታክስ የከፈለ መሆኑን እና የከፈለውን ታክስ መጠን የሚያሳይ የታክስ ደረሰኝ ወይም ሌላ የሰነድ ማስረጃ ካቀረበ::

(2).ከላይ በተገለፀው መሠረት የሚደረገው የግብአት ታክስ ተቀናሽ የተመዘገበው ሰው ከተመዘገበበት ቀን ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያ የሂሳብ ጊዜ መቅረብ አለበት፡፡

(3).የአዋጁ አንቀጽ 29 እና 30 ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፀው ተፈጻሚ በሚሆንበት ሁኔታ የተመዘገበው ሰው የግብአት ታክስ ተቀናሽ ማግኘት የሚችለው በተመዘገበበት ቀን በእጁ የሚገኙ የንግድ ዕቃዎችን በገዛበት ጊዜ ለከፈለው የግብአት ታክስ ይሆናል፡፡

(4).የአዋጁ አንቀጽ 29 እና 30 ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለፀው መሠረት የተመዘገበው ሰው በተመዘገበበት ቀን በእጁ የሚገኙ የካፒታል ዕቃዎችን በሚመለከት ለተመዘገበው ሰው ተቀናሽ የሚደረገው የግብአት ታክስ የሚሰላው በሚከተለው ቀመር መሠረት ይሆናል፡-

ሀ=ሐ-ለ/ሐ
ለዚህ ቀመር አፈጻጸም፡-
ሀ) የተመዘገበው ሰው የካፒታል ዕቃዎቹን በገዛበት ጊዜ የከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ፣
ለ) በገቢ ግብር አዋጅ መሠረት የሚወሰነው ይህ ሰው በተመዘገበበት ቀን የካፒታል ዕቃዎቹ ያላቸው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ፣ እና
ሐ) ለካፒታል ዕቃዎቹ የተደረገው የመጀመሪያው ወጪ፡፡
5.የአዋጁ አንቀጽ 29 (5) ድንጋጌ በዚህ አንቀጽ መሠረት ተቀናሽ የሚደረገውን የግብዓት ታክስ በሚመለከት ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
15
Almaw Wolie, Case Comment on Cassation File Number 236212 - Ethiolex
https://ethiolex.com/almaw-wolie-case-comment-on-cassation-file-number-236212/

የሕገ-መንግሥት መብት ድል ወይስ የሥነ-ሥርዓት አጣብቂኝ?፤ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ባለሰባት ዳኞች ሰበር ሰሚ ችሎት
በሰ/መ/ቁ 236212 ጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለውጥ ላይ የቀረበ ሂሳዊ ትንታኔ
በአቶ አልማው ወሌ
6
13
👉 #የሰነድ #ማስረጃ አቀራረብ በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145 ሥር
#በፍትሐብሔር #ክርክር ሂደት ውስጥ የሰነድ ማስረጃዎችን በወቅቱ እና በሥነ-ሥርዓቱ መሠረት ማቅረብ ለፍትህ መከበር ወሳኝ ነው። ብዙ ጊዜ ግልጽነት የሚጎድለውን የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 አተገባበር እና ከሌሎች ድንጋጌዎች ጋር ያለውን ቁርኝት እንደሚከተለው እንመልከተው።
🔍 የሰነድ ማስረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ
በመሠረቱ ማንኛውም ተከራካሪ ወገን ሊያቀርባቸው የሚፈልጋቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ከክስ ወይም ከመልስ ጋር አያይዞ የማቅረብ ግዴታ አለበት (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 137, 223 እና 234)። ነገር ግን ማስረጃው በእጁ ያልሆነና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲቀርብለት የሚፈልግ ከሆነ በቁጥር 145 መሠረት ይጠይቃል።
👉 ቁጥር 145 መቼ እና እንዴት ተግባራዊ መሆን አለበት?
ቅድመ-ዝግጅት፦ አንድ ተከራካሪ ማስረጃውን በራሱ አቅም ማቅረብ ካልቻለ፣ ፍርድ ቤቱ ማስረጃው ለክርክሩ አስፈላጊ መሆኑን አምኖበት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ይሰጣል።
ከጭብጥ በፊት፦ ይህ ሂደት የግድ የክስ መስማት ሂደቱ ከመጀመሩ እና ጭብጥ ከመያዙ በፊት ሊከናወን ይገባል።
የመሰማት መብት፦ ፍርድ ቤቱ በቁጥር 145 መሠረት ያስቀረበው ማስረጃ ለሌላኛው ወገን ሊደርሰው ይገባል። ለምሳሌ፡ ከሳሽ ያስቀረበው ሰነድ ለተከሳሽ ደርሶት፣ ተከሳሹ በሰነዱ ላይ ተመስርቶ የመከላከያ መልሱን ሊያደራጅ ይገባል።

👉 ማስረጃ በወቅቱ ባይቀርብ የሚመጣው ችግር
ማስረጃዎች በጊዜው (በመጀመሪያው ቀጠሮ ወይም ከዚያ በፊት) ሳይቀርቡ ቀርተው፣ ክርክሩ ተጠናቆ ለፍርድ በሚያዝበት ወቅት እንዲቀርቡ ከታዘዘ የሚከተሉት ችግሮች ይፈጠራሉ፡
👉ተከራካሪ ወገኖች በማስረጃው ላይ የመከራከር እና አስተያየት የመስጠት ዕድል ያጣሉ።
አዲስ ማስረጃ በገባ ቁጥር አዲስ ጭብጥና ክርክር እየተነሳ የፍርድ ሂደቱ ይንዛዛል።
የተገኘው ውጤት የፍትሃዊነት ሚዛኑን ሊስት ይችላል።

👉 ዋና ዋና ነጥቦች
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 137፦ ማንኛውም የጽሁፍ ማስረጃ ከመጀመሪያው የችሎት ቀጠሮ በፊት ወይም በዕለቱ መቅረብ እንዳለበት ያዝዛል።
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 256፦ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በጊዜው ያልቀረበ ማስረጃ ካለ፣ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት መቅረብ እንደሚችል ቢደነግግም፣ ይህም ቢሆን የተቃራኒ ወገንን የመሰማት መብት በጠበቀ መልኩ ሊሆን ይገባል።
ጭብጥ አመሰራረት፦ እንደ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 249 ድንጋጌ፣ ትክክለኛ ጭብጥ ለመያዝ የሰነድ ማስረጃዎችን አስቀድሞ መመርመር ለፍርድ ቤቱ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ክርክር ወደ ኋላ እንዳይመለስ፣ ሂደቱ እንዳይጓተት እና ፍትህ እንዳይዛባ፤ በ145 መሠረት የሚቀርቡ ማስረጃዎች ክስ መስማት ከመጀመሩ በፊት ቀርበው ተከራካሪዎች ሊያውቋቸው ይገባል። ማስረጃ ሳይቀርብ ወይም ሳይመረመር የሚሰጥ ውሳኔ የህግ መሠረት የለውም።
#EthiopianLaw #LegalAwareness #CivilProcedure #Justice #Ethiopia #የህግምክር #ፍትሐብሔር
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
17👍3
ታናሸ ወንድም የሚከበርበትና የሚፈራበት,የታዛዥነት ስሜት ሊፈጠርበት የሚችልበት ሁኔታ የለም-
የውርስ ድርሻዬን በ 3(ሶስት) ዓመት ውስጥ ከስሼ ያልጠየቅኩትና ይርጋ ያገደኝ ታናሽ ወንድሜን በማክበርና በመፍራት ነው ብሎ መከራከር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፌደራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 166214 በሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ/ም ገዢ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
በ ዘወልድ ምክረ ህግ
9