በፍሪላንስ እና በዲጂታል ገቢ ላይ ግብር ሊጣል ነው !
ገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ባዘጋጀው የገቢ ግብር ረቂቅ ደንብ፤ በኢትዮጵያ ነዋሪ ሆነው በዲጂታል አማካኝነት እና በፍሪላንስ (Freelance) ወይም በርቀት (Remote) የሥራ ዘዴ ገቢ በሚያገኙ ግለሰቦች ላይ የገቢ ግብር ተፈጻሚ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል።
ማንኛውም በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር ምንጮች በዲጂታል ይዘት ፈጠራ ወይም በማንኛውም የፍሪላንስ ሥራ የሚያገኘው ገቢ (በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት) ግብር ይከፍላል ብሏል።
የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ያገኙትን የገቢ መጠን በሚመለከት ትክክለኛ እና የተሟላ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ይህንን ግዴታ ባልተወጡ ግብር ከፋዮች ላይ ታክስ የሚወሰነው በሚኒስቴሩ መመሪያ መሠረት በግምት ይሆናል።
በተጨማሪም ክፍያ የሚያመቻቹ ኩባንያዎች የዲጂታል ስራ የፈጣሪዎችን ስም ዝርዝር፣ አድራሻ፣ የሲም ካርድ መረጃ፣ የአይፒ (IP) አድራሻ እና የተከፈለውን የገንዘብ መጠን በየሩብ ዓመቱ ለታክስ ባለሥልጣኑ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።
በዚሁ መመሪያ ባንኮች ለኪሳራ የያዙት የመጠባበቂያ ሂሳብ በብሔራዊ ባንክ መሥፈርት መሠረት የተሰላ ከሆነ፣ 80 በመቶው በተቀናሽ ወጪ እንዲያዝላቸው ተደንግጓል።
የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ የሚወሰነው የታክስ ባለሥልጣኑ በየሦስት ዓመቱ በሚያደርግ የገበያ ጥናት እንደሚወሰን በአዲሱ ደንብ ተካቷል።
ከመንግሥት ቦንዶችና ግምጃ ቤት ሰነዶች የሚገኝ ወለድ ወይም ትርፍ፣ እንዲሁም የአየር መንገድ የውጭ ብድር ወለድና የአውሮፕላን ኪራይ (ሮያሊቲ) ክፍያዎች ከግብር ነፃ ተደርገዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ረቂቅ ደንቡ ከመጽደቁ በፊት አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መጋቢት 1/2018 ዓ.ም. ስድስት ኪሎ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ወይም በተቋሙ infopr@mofed.gov.et የኢሜይል አድራሻ መላክ እንደሚችሉ አስታውቋል።
መረጃው #የሪፖርተር_ጋዜጣ ነው።
አዲስ አበባ
የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia

❤11👍5😡3
የሕዝብ ጠበቃ!
በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የዓቃቤ ሕግ ሥልጣንና ኃይል እጅግ ከፍተኛ ሲሆን፣ በሕዝብና በመንግሥት ስም ወንጀለኞችን የመክሰስና ፍትሕ የማስፈን ታላቅ ኃላፊነት ያለበት አካል ነው። የጥበቃ ኃይል በደንበኛው መብት ላይ፣ የዳኛ ኃይል ደግሞ በመጨረሻው ውሳኔ ላይ ትኩረት ሲያደርጉ፤ የዓቃቤ ሕግ ኃይል ግን ወንጀልን የመመርመርና ክስ የመመሥረት ሰፊ ሥልጣን ላይ ያርፋል። አንድ ግለሰብ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ በሚጠረጠርበት ጊዜ፣ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት መሆኑን የመወሰን የመጨረሻው ቃል የዓቃቤ ሕግ በመሆኑ፣ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ቢልክም እንኳ ዓቃቤ ሕግ ማስረጃው በቂ አይደለም ካለ ክሱን የመዝጋት ወይም ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ የማዘዝ ሥልጣን አለው። ተከሳሹ በምን ዓይነት የሕግ አንቀጽ መከሰስ እንዳለበት የመመደብ ኃይሉም ሌላው ወሳኝ ነጥብ ሲሆን፣ ለምሳሌ አንድን ድርጊት "በአጋጣሚ በሰው መግደል" ወይም "በታሰበበት ሰው መግደል" ብሎ መለየቱ በቅጣቱ መጠን ላይ መሠረታዊ ልዩነት ያመጣል።
ዓቃቤ ሕግ ከፖሊስ ጋር በቅርበት ቢሠራም፣ በሕግ ረገድ ግን የፖሊስን የምርመራ ሂደት የመቆጣጠርና የመምራት ከፍተኛ ኃይል የተሰጠው አካል ነው። ፖሊስ የትኛውን ማስረጃ መሰብሰብ እንዳለበትና የትኛው ምስክር መጥራት እንደሚገባው መመሪያ ከመስጠት ባለፈ፣ የምርመራ ሂደቱ በሕግ አግባብ መከናወኑንና የተጠርጣሪው መብት አለመጣሱን የማረጋገጥ ኃላፊነት የዓቃቤ ሕግ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በቅርብ ጊዜ በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ቦታ እየያዘ የመጣው የጥፋተኝነት ድርድር (Plea Bargaining) የዓቃቤ ሕግን ሚና "የፍትሕ ስምምነት ፈጣሪ" ያደርገዋል። ዓቃቤ ሕግ ከተከሳሹ ጋር በመደራደር፣ ተከሳሹ ጥፋቱን አምኖ ሌላ ትልቅ ወንጀል ያደረሰን ሰው አሳልፎ እንዲሰጥ በማድረግ ክሱን ሊቀንስለት ወይም ሊተውለት የሚችልበት ይህ ልዩ ሥልጣን የፍትሕ ሂደቱን ለማቀላጠፍ ይረዳል።
ዓቃቤ ሕግ የግለሰብ ጠበቃ ሳይሆን የሕዝብና የመንግሥት ጠበቃ በመሆኑ፣ ፍርድ ቤት ውስጥ ወንጀሉ መፈጸሙን የማስረዳት ሸክም (Burden of Proof) በእርሱ ላይ ይወድቃል። ዓቃቤ ሕግ በቂ ማስረጃ አቅርቦ የወንጀሉን መፈጸም ካላስረዳ በስተቀር ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ አይገደድም፤ ይህም የሕዝብን ጥቅም የመወከል ኃላፊነቱን ያሳያል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለሕዝብ ጥቅም ተገቢ አይደለም ብሎ ካመነም፣ ውሳኔው እንዲታረም እስከ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ድረስ ይግባኝ የመጠየቅና የመከራከር ኃይል አለው። ይሁን እንጂ ይህ ሰፊ ሥልጣን አላግባብ እንዳይሠራበት ሕጉ እንደ ገለልተኝነት፣ የበላይ ኃላፊ ቁጥጥርና የፍርድ ቤት ፈቃድ ያሉ የሥልጣን ገደቦችን አስቀምጧል። ለምሳሌ ዓቃቤ ሕግ ለተከሳሹ የሚጠቅም ማስረጃ ካገኘ ያንን የመደበቅ መብት የሌለው ሲሆን፣ ለፍትሕ ሲባል ማቅረብ ይኖርበታል።
ዓቃቤ ሕግ በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ እንደ በር ጠባቂ (Gatekeeper) የሚቆጠር ሲሆን፣ አንድ ሰው ወደ ፍርድ ቤት ገብቶ ፍትሕ እንዲያገኝ ወይም ከሕግ ተጠያቂነት እንዲያመልጥ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። የዓቃቤ ሕግ ጥንካሬ የፍትሕ ሥርዓቱን ጥንካሬ የሚያሳይ ሲሆን፣ ድክመቱ ደግሞ የሕግ የበላይነት መላላትን ያመለክታል፤ ስለዚህ ሥልጣኑ ሁልጊዜም በሕግና በገለልተኝነት መርሕ የተገደበ መሆን አለበት። ክስ የመመሥረት ሥልጣን በፍርድ ቤት ሂደት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንዳለውና ዓቃቤ ሕግ የሕዝብ ጠበቃ ሆኖ እንዲያገለግል ሕጉ የጣለበት ኃላፊነት የፍትሕ ሥርዓቱ የጀርባ አጥንት ነው።
ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig

❤24👎1👏1🥱1
EBS ቴሌቪዥነ በቅርቡ በሞት በተለየዉ ወንድማችን በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ይቀርብ የነበረዉን የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም በተመለከተ ለማስቀጠል ተክቶ ማን ያጋፍር ሲሉ ጠይቀዋል። ጠቁሙ ተብሏል።
በመሆኑም ካለዉ የሕዝብ ተወዳጅነት የዘርፉ ብቃትና ችሎታ አንፃር አርቲስት ሸዋፈራዉ ደሳለኝ አጋፋሪ ሆኖ ቢያስቀጥል የተሻለ ነዉ የሚል እምነት አለን። እናንተ ምን ትላላችሁ?❓
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
በመሆኑም ካለዉ የሕዝብ ተወዳጅነት የዘርፉ ብቃትና ችሎታ አንፃር አርቲስት ሸዋፈራዉ ደሳለኝ አጋፋሪ ሆኖ ቢያስቀጥል የተሻለ ነዉ የሚል እምነት አለን። እናንተ ምን ትላላችሁ?❓
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
🤮49👎40❤28👍1🔥1
ዜና ሹመት ፣ #ሕግ አዋቂው ፣ #የሕግ #ሰው #ዮናስ_አለማየሁ
አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ተቋም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ ደንብ ቁጥር 193/2017ዓ.ም ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባ ከተደረገበት ግዜ ጀምሮ አቶ ዮናስ አለማየሁ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ መሆኑ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ዮናስ አለማየሁ ከየካቲት 25/2018ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመሶብ አገልግሎት ዋና ስራ-አስፈፃሚ ሆነው እንዲያገለግሉ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል።
የአዲስ መሶብ ስትራቴጂክ እና ጠቅላላ ካውንስል እንዲሁም መላው ሰራተኛ አቶ ዮናስ አለማየሁ ተቋሙን ከማደራጀት ጀምሮ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ላበረከቱት አስተዋፅዖ እና ለሰጡት አመራር ከልብ እያመሰገነ የሃገር አቀፉን የመሶብ ስርዓት እንዲመሩ በተመደቡበት ሃላፊነት ውጤታማ የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።
Addis MESOB
The New Horizon of Service !

❤24👏2👍1
በፍርድ ቤት በክርክር ላይ ባለጉዳይ ተከራካሪ ወገኖች ነገሩን በእርቅ ለመጨረስ ተስማምተው እርቁም በጹሑፍ ተደርጎ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ተረጋግጦ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ ከተደረገ የእርቅ ስምምነት እንደ ፍርድ ተወስዶ አፈፃፀም ክስ ሊቀርብበት የሚችል ሲሆን ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በተከራካሪ ወገኖች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር እንደ መደበኛ ዉል ዉል እንዲፈርስ አዲስ ክስ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ ,, የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 386 ; 392 ,,,, ቅፅ 28 ሰ/መ/ቁ 143086,,,
Ethio law
Ethio law
❤10
🥇ጋብቻው በየትኛውም ዓይነት የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓት ቢፈጸም በጋብቻ ላይ ፍቺ ለመወሰን ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ ነው።
🥈አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ለረጅም ጊዜያት ተለያይተው ቢኖሩም፤ ሌላ ትዳር ቢመሰርቱም ጋብቻቸው በፍርድ ቤት እስካልፈረሰ ድረስ በሕግ አግባብ ባልና ሚስት እንደሆኑ ይቆጠራሉ።
🥉ፍቺ ለመጠየቅ ጋብቻ መኖሩን ማስረዳት ቀዳሚ ግዴታ ነው። በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ጋብቻ አለ ለማለት የጋብቻ ምስክር ወረቀት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል። የጋብቻ ምስክር ወረቀት በሌለ ጊዜ የሰው ምስክሮችን በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል።
4⃣በሕግ አግባብ 2 ዓይነት ፍቺ አለ። 1ኛው. የስምምነት ፍቺ ሲሆን 2ኛው. አንደኛው ተጋቢ የፍቺ አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ የሚያሰጥበት ፍቺ ነው። ሁለቱም የግዴታ ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ መሆን አለባቸው።
5⃣ጋብቻ በሁለቱ ተጋቢዎች ፍላጎት እና ነፃ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ አንደኛው ተጋቢ ፍቺውን አልፈልግም ቢል ወይም ፍርድ ቤት ባይቀርብም ፍርድ ቤቶች የፍቺ ውሳኔ ከመስጠት የሚከለክላቸው አይደለም።
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹

❤23