የቀዳሚነት መብት ጨረታ ጊዜ እና የጋራ ባለሀብት በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር መ/ቁ 215842፣ ቅጽ 28፣ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1126(1)፣ 1386-1409 እና የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 430(1)፣ 443 መሰረት ተደርጐ በአብላጫ ድምፅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል
🏠በጨረታ በሚሸጠው ንብረት ላይ የጋራ ባለሀብት በመሆኑ ምክንያት በሕግ የቀዳሚነት መብት የተጠበቀለት ወገን ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ ካልቀረበ በቀር ጨረታው ተከናውኖ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ የጨረታውን ውጤት አውቆ የሚያቀርበው የቀዳሚነት መብት ጥያቄ በጨረታው አሸናፊ መብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚኖረው አቤቱታው ተቀባይነት የሌለውም።
ዋና ዋና ነጥቦች (Key Legal Points)
#የቅድመ-ሁኔታ ግዴታ፦ የቀዳሚነት መብት ያለው ሰው መብቱን ለመጠቀም የግድ በጨረታው ሂደት ውስጥ እንደ ተወዳዳሪ መሳተፍ አለበት።
#የጊዜ ገደብ፦ ጨረታው ተጠናቆ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚቀርብ የ"እኔ እገዛለሁ" ጥያቄ በሕግ ተቀባይነት የለውም።
#የሦስተኛ ወገን መብት፦ ሕጉ የጨረታውን አሸናፊ (የገዢውን) መብትና ጥቅም ለመጠበቅ ሲል ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚመጡ ጥያቄዎችን ውድቅ ያደርጋል።
Fiker Getachew

❤10👍5
በፍሪላንስ እና በዲጂታል ገቢ ላይ ግብር ሊጣል ነው !
ገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ባዘጋጀው የገቢ ግብር ረቂቅ ደንብ፤ በኢትዮጵያ ነዋሪ ሆነው በዲጂታል አማካኝነት እና በፍሪላንስ (Freelance) ወይም በርቀት (Remote) የሥራ ዘዴ ገቢ በሚያገኙ ግለሰቦች ላይ የገቢ ግብር ተፈጻሚ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል።
ማንኛውም በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር ምንጮች በዲጂታል ይዘት ፈጠራ ወይም በማንኛውም የፍሪላንስ ሥራ የሚያገኘው ገቢ (በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት) ግብር ይከፍላል ብሏል።
የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ያገኙትን የገቢ መጠን በሚመለከት ትክክለኛ እና የተሟላ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ይህንን ግዴታ ባልተወጡ ግብር ከፋዮች ላይ ታክስ የሚወሰነው በሚኒስቴሩ መመሪያ መሠረት በግምት ይሆናል።
በተጨማሪም ክፍያ የሚያመቻቹ ኩባንያዎች የዲጂታል ስራ የፈጣሪዎችን ስም ዝርዝር፣ አድራሻ፣ የሲም ካርድ መረጃ፣ የአይፒ (IP) አድራሻ እና የተከፈለውን የገንዘብ መጠን በየሩብ ዓመቱ ለታክስ ባለሥልጣኑ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።
በዚሁ መመሪያ ባንኮች ለኪሳራ የያዙት የመጠባበቂያ ሂሳብ በብሔራዊ ባንክ መሥፈርት መሠረት የተሰላ ከሆነ፣ 80 በመቶው በተቀናሽ ወጪ እንዲያዝላቸው ተደንግጓል።
የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ የሚወሰነው የታክስ ባለሥልጣኑ በየሦስት ዓመቱ በሚያደርግ የገበያ ጥናት እንደሚወሰን በአዲሱ ደንብ ተካቷል።
ከመንግሥት ቦንዶችና ግምጃ ቤት ሰነዶች የሚገኝ ወለድ ወይም ትርፍ፣ እንዲሁም የአየር መንገድ የውጭ ብድር ወለድና የአውሮፕላን ኪራይ (ሮያሊቲ) ክፍያዎች ከግብር ነፃ ተደርገዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ረቂቅ ደንቡ ከመጽደቁ በፊት አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መጋቢት 1/2018 ዓ.ም. ስድስት ኪሎ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ወይም በተቋሙ infopr@mofed.gov.et የኢሜይል አድራሻ መላክ እንደሚችሉ አስታውቋል።
መረጃው #የሪፖርተር_ጋዜጣ ነው።
አዲስ አበባ
የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia

❤11👍5😡3