አለ ሕግ
16K subscribers
3.3K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 418፣ ሦስተኛ ወገኖች ንብረቱ በሚታገድበት ወቅት ሕጋዊ ጥቅም ወይም ይዞታ እንዳላቸው ማረጋገጥ ከቻሉ፣ በንብረት እገዳው ላይ ተቃውሞ እንዲያቀርቡ ይፈቅዳል። ይህ ሥነ-ሥርዓታዊ ጥበቃ የንጹሐን ሦስተኛ ወገኖች ንብረት የሌሎችን ዕዳ ለመክፈያነት እንዳይውል ይከላከላል፤ ሆኖም ይህ ሂደት የአፈጻጸም ፍርድ ቤቱ ከአፈጻጸሙ ወሰን ውጭ ውሎችን እንዲሰርዝ ወይም አዲስ የባለቤትነት መብት እንዲሰጥ ስልጣን አይሰጠውም።
👍135
ሰበር ን በአንድ ዓረፍተ ነገር
thank you all በመጀመሪያ ታላቅ ምሴጋናዬን እያቀረብኩኝ

For Pre-Order ተመዝጋቢዎች በገባሁት ቃል መሠረት ሁለት application available አደርጋለው።
እስከዛው beta version የጫናችሁ ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኛችሁት ምላሻችሁን ስለሰጣችሁኝ ከልብ አመሠግናለው።
ስለዚህኛው Cassation Key Rules app
ጥቂት ልበል።
አፕሊኬሽኑ የሰበርን ውሳኔ በአንድ ዓረፍተ ነገር የሚያጠቃልል ማውጫ ነው። ማውጫውን አይታችሁ ዋናውን ውሳኔ ማንበብ አትርሱ። ከዚህ በታች ቅንጭብ ቀርቧል።

#​የሰበር_ውሳኔዎች_ማጠቃለያ

#​የሰበር መዝገብ ቁጥር 197368፦ በአንድ ዓይነት ጉዳይ ላይ በሌላ ፍርድ ቤት ክርክር እየተካሄደ ነው (Pending Suit) የሚለው መቃወሚያ ተፈጻሚ የሚሆነው፣ ሁለቱ ክሶች ተመሳሳይ የውል መሠረት ያላቸው ሲሆን ብቻ ነው።

#​የሰበር መዝገብ ቁጥር 197405፦ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ያለው የስረ ነገር ሥልጣን የሚመነጨው ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ሕግን ተፈጻሚ የሚያደርግ ሲሆን እንጂ፣ ተከራካሪው አካል ዓለም አቀፍ ድርጅት ስለሆነ ብቻ አይደለም።

#​የሰበር መዝገብ ቁጥር 197695፦ የሰበር ሰሚ ችሎት ሥልጣን መሠረታዊ የሕግ ስህተትን በማረም ላይ የተገደበ በመሆኑ፣ የበታች ፍርድ ቤቶች ማስረጃን መዝነው የደረሱበትን የፍሬ ነገር ድምዳሜ የመመርመር ሥልጣን የለውም።

#​የሰበር መዝገብ ቁጥር 197736፦ ፍርድ ቤቶች ዳኝነት መስጠት ያለባቸው በተጠየቀው ዳኝነት አግባብ ቢሆንም፣ በክርክር ሂደት በማስረጃ የተረጋገጠን ዝርዝር ፍሬ ነገር (ለምሳሌ የመንገድ ስፋት) መወሰን ባልተጠየቀ ዳኝነት መወሰን ተብሎ አይቆጠርም።

#​የሰበር መዝገብ ቁጥር 197790፦ በፍትሐብሔር ክርክር ውስጥ የወጥነት እና የተገማችነት መርህ ወሳኝ በመሆኑ፣ ቀደም ሲል በሌላ መዝገብ ላይ ተወስኖ የጸና ጭብጥ (ለምሳሌ የውል መቋረጥ ጥፋት) በድጋሚ ሊመረመር አይገባም።

#​የሰበር መዝገብ ቁጥር 199060፦ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን (ለምሳሌ ይርጋን) በተመለከተ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ሽሮ ውሳኔ ከሰጠ፣ ይግባኙ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መቅረብ አለበት።
በጠበቃ አብርሀም ዮሀንስ
18👍1
ምን አይነት የፕላስቲክ ማሸጊያዎች ተፈቅደዋል ?

የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፥ " በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 መሰረት የፕላስቲክ ማሸጊያ ማለት እቃዎችን ከብክለት ለመከላከል ወይንም ከሌላ ነገር ጋር እንዳይቀላቀል ለማድረግ በእቃው አምራች ጥቅም ላይ የሚውል ከፕላስቲክ የሚዘጋጅ መጠቅለያ ወይም መያዣ ነው የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል " ብሏል።

በዚህም መሰረት ፦
- የምግብ፣
- የባልትና ውጤቶችን፣
- ለላውንደሪ አገልግሎት እና ሌሎች ምርቶችን ለማሸግ የሚውሉ የፕላስቲክ ማሸጊያዎች በአዋጁ የተፈቀዱ መሆኑን ገልጿል።

የእነዚህ ማሸጊያዎች የቆሻሻ አያያዝ በአዋጁ እና አዋጁን ተከትለው በሚወጡ የማስፈፀሚያ ህጎች እንደሚተገበር አመልክቷል።

(የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 18 ቀን 2018

@tikvahethiopia
9👍3
2👍2
የቀዳሚነት መብት ጨረታ ጊዜ እና የጋራ ባለሀብት በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር መ/ቁ 215842፣ ቅጽ 28፣ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1126(1)፣ 1386-1409 እና የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 430(1)፣ 443 መሰረት ተደርጐ በአብላጫ ድምፅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል

🏠በጨረታ በሚሸጠው ንብረት ላይ የጋራ ባለሀብት በመሆኑ ምክንያት በሕግ የቀዳሚነት መብት የተጠበቀለት ወገን ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ ካልቀረበ በቀር ጨረታው ተከናውኖ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ የጨረታውን ውጤት አውቆ የሚያቀርበው የቀዳሚነት መብት ጥያቄ በጨረታው አሸናፊ መብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚኖረው አቤቱታው ተቀባይነት የሌለውም።
ዋና ዋና ነጥቦች (Key Legal Points)
#የቅድመ-ሁኔታ ግዴታ፦ የቀዳሚነት መብት ያለው ሰው መብቱን ለመጠቀም የግድ በጨረታው ሂደት ውስጥ እንደ ተወዳዳሪ መሳተፍ አለበት።
#የጊዜ ገደብ፦ ጨረታው ተጠናቆ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚቀርብ የ"እኔ እገዛለሁ" ጥያቄ በሕግ ተቀባይነት የለውም።
#የሦስተኛ ወገን መብት፦ ሕጉ የጨረታውን አሸናፊ (የገዢውን) መብትና ጥቅም ለመጠበቅ ሲል ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚመጡ ጥያቄዎችን ውድቅ ያደርጋል።
Fiker Getachew
10👍5
3