የቤተሰብ ህግ በሰበር ችሎት ✍️
📢 አዲስ የህግ መጽሐፍ የቅድመ-ትዕዛዝ ጥሪ!
"የቤተሰብ ህግ በሰበር ውሳኔዎች" — በአቀራረቡ ለየት ያለና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ላይ ያተኮረ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለህትመት ይበቃል።
በአሁኑ ወቅት የህትመት ዋጋ መናር ስራዎችን ለህዝብ ለማድረስ ፈታኝ ቢሆንም፣ ይህ እውቀት ለባለሙያውና ለአንባቢው እንዲደርስ ለማድረግ በጣም ውስን ኮፒዎችን (ከ300-500 ብቻ) ለተመዝጋቢዎች ለማቅረብ ተዘጋጅተናል።
🎯 የምዝገባ አማራጮች እና ልዩ ጥቅሞች
መጽሐፉን በሁለት መንገድ መመዝገብ ይችላሉ፦
1. ቅድሚያ ገዢ (Early Bird):
ቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም መጽሐፉ እስኪወጣ ለሚጠብቁ ደንበኞች የሚከተሉት ልዩ የቴክኖሎጂ ጥቅሞች ለተወሰነ ጊዜ በነጻ ይሰጣሉ፦
* Desktop Application: ከቅፅ 1-28 ያሉ፣ የ7 ዳኞች ትርጉም፣ የህፃናትና ሴቶች ጉዳይን ጨምሮ ከ 10,000 በላይ የሰበር ውሳኔዎች ማጠቃለያ የያዘ። እያንዳንዱ ማጠቃለያ የክርክሩን አመጣጥ፣ ቁልፍ የህግ ትርጉም እና የፍርዱን አመክንዮ በዝርዝር የያዘ ሲሆን፤ ፈጣንና ዘመናዊ መፈለጊያ (Search) ተገጥሞለታል።
* Mobile Application: ከ10 ሺህ በላይ ውሳኔዎችን "የአንድ መስመር" ማውጫ የያዘ መተግበሪያ።
2. ኋላ ገዢ (Standard):
መጽሐፉ ሲታተም ክፍያ ፈጽመው መጽሐፉን ብቻ በአድራሻቸው የሚረከቡ።
📘 የመጽሐፉ መረጃ
* ርዕስ፦ የቤተሰብ ህግ
* የገጽ ብዛት፦ 350
* ዋጋ፦ 1,000 ብር (Delivery/ማድረሻን ጨምሮ)
📝 እንዴት ይመዘገባሉ?
ኮፒው በጣም ውስን ስለሆነ አሁኑኑ ስምዎትንና አድራሻዎትን በሚከተለው ስልክ ቁጥር ይላኩ፦
📞 ስልክ፦ 0915735560 (በText, Telegram ወይም WhatsApp)
ሲመዘገቡ የሚከተለውን መረጃ ያካትቱ፦
* ሙሉ ስም
* ስልክ ቁጥር
* አድራሻ (መጽሐፉ እንዲደርሶ የሚፈልጉበት)
* የምዝገባ አይነት፦ "ቅድሚያ ገዢ" ወይም "ኋላ ገዢ" በማለት ይጥቀሱ።
> ማሳሰቢያ፦ መጽሐፉ ለተመዝጋቢዎች ብቻ የሚሸጥ ሲሆን፣ ርክክቡም ባለዎት አድራሻ ላይ በመመስረት በቤትዎ ወይም በቢሮዎ ድረስ በነጻ ይከናወናል።
>
ይህንን መልዕክት ለሌሎች የህግ ባለሙያዎች በማጋራት ይተባበሩ!
(ከላይ ምስል mobile app screenshots)
❤11
የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 418፣ ሦስተኛ ወገኖች ንብረቱ በሚታገድበት ወቅት ሕጋዊ ጥቅም ወይም ይዞታ እንዳላቸው ማረጋገጥ ከቻሉ፣ በንብረት እገዳው ላይ ተቃውሞ እንዲያቀርቡ ይፈቅዳል። ይህ ሥነ-ሥርዓታዊ ጥበቃ የንጹሐን ሦስተኛ ወገኖች ንብረት የሌሎችን ዕዳ ለመክፈያነት እንዳይውል ይከላከላል፤ ሆኖም ይህ ሂደት የአፈጻጸም ፍርድ ቤቱ ከአፈጻጸሙ ወሰን ውጭ ውሎችን እንዲሰርዝ ወይም አዲስ የባለቤትነት መብት እንዲሰጥ ስልጣን አይሰጠውም።
👍13❤5
ሰበር ን በአንድ ዓረፍተ ነገር
thank you all በመጀመሪያ ታላቅ ምሴጋናዬን እያቀረብኩኝ
For Pre-Order ተመዝጋቢዎች በገባሁት ቃል መሠረት ሁለት application available አደርጋለው።
እስከዛው beta version የጫናችሁ ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኛችሁት ምላሻችሁን ስለሰጣችሁኝ ከልብ አመሠግናለው።
ስለዚህኛው Cassation Key Rules app
ጥቂት ልበል።
አፕሊኬሽኑ የሰበርን ውሳኔ በአንድ ዓረፍተ ነገር የሚያጠቃልል ማውጫ ነው። ማውጫውን አይታችሁ ዋናውን ውሳኔ ማንበብ አትርሱ። ከዚህ በታች ቅንጭብ ቀርቧል።
#የሰበር_ውሳኔዎች_ማጠቃለያ
#የሰበር መዝገብ ቁጥር 197368፦ በአንድ ዓይነት ጉዳይ ላይ በሌላ ፍርድ ቤት ክርክር እየተካሄደ ነው (Pending Suit) የሚለው መቃወሚያ ተፈጻሚ የሚሆነው፣ ሁለቱ ክሶች ተመሳሳይ የውል መሠረት ያላቸው ሲሆን ብቻ ነው።
#የሰበር መዝገብ ቁጥር 197405፦ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ያለው የስረ ነገር ሥልጣን የሚመነጨው ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ሕግን ተፈጻሚ የሚያደርግ ሲሆን እንጂ፣ ተከራካሪው አካል ዓለም አቀፍ ድርጅት ስለሆነ ብቻ አይደለም።
#የሰበር መዝገብ ቁጥር 197695፦ የሰበር ሰሚ ችሎት ሥልጣን መሠረታዊ የሕግ ስህተትን በማረም ላይ የተገደበ በመሆኑ፣ የበታች ፍርድ ቤቶች ማስረጃን መዝነው የደረሱበትን የፍሬ ነገር ድምዳሜ የመመርመር ሥልጣን የለውም።
#የሰበር መዝገብ ቁጥር 197736፦ ፍርድ ቤቶች ዳኝነት መስጠት ያለባቸው በተጠየቀው ዳኝነት አግባብ ቢሆንም፣ በክርክር ሂደት በማስረጃ የተረጋገጠን ዝርዝር ፍሬ ነገር (ለምሳሌ የመንገድ ስፋት) መወሰን ባልተጠየቀ ዳኝነት መወሰን ተብሎ አይቆጠርም።
#የሰበር መዝገብ ቁጥር 197790፦ በፍትሐብሔር ክርክር ውስጥ የወጥነት እና የተገማችነት መርህ ወሳኝ በመሆኑ፣ ቀደም ሲል በሌላ መዝገብ ላይ ተወስኖ የጸና ጭብጥ (ለምሳሌ የውል መቋረጥ ጥፋት) በድጋሚ ሊመረመር አይገባም።
#የሰበር መዝገብ ቁጥር 199060፦ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን (ለምሳሌ ይርጋን) በተመለከተ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ሽሮ ውሳኔ ከሰጠ፣ ይግባኙ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መቅረብ አለበት።
በጠበቃ አብርሀም ዮሀንስ

❤18👍1
ምን አይነት የፕላስቲክ ማሸጊያዎች ተፈቅደዋል ?
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፥ " በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 መሰረት የፕላስቲክ ማሸጊያ ማለት እቃዎችን ከብክለት ለመከላከል ወይንም ከሌላ ነገር ጋር እንዳይቀላቀል ለማድረግ በእቃው አምራች ጥቅም ላይ የሚውል ከፕላስቲክ የሚዘጋጅ መጠቅለያ ወይም መያዣ ነው የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል " ብሏል።
በዚህም መሰረት ፦
- የምግብ፣
- የባልትና ውጤቶችን፣
- ለላውንደሪ አገልግሎት እና ሌሎች ምርቶችን ለማሸግ የሚውሉ የፕላስቲክ ማሸጊያዎች በአዋጁ የተፈቀዱ መሆኑን ገልጿል።
የእነዚህ ማሸጊያዎች የቆሻሻ አያያዝ በአዋጁ እና አዋጁን ተከትለው በሚወጡ የማስፈፀሚያ ህጎች እንደሚተገበር አመልክቷል።
(የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 18 ቀን 2018
@tikvahethiopia

❤9👍3
የቀዳሚነት መብት ጨረታ ጊዜ እና የጋራ ባለሀብት በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር መ/ቁ 215842፣ ቅጽ 28፣ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1126(1)፣ 1386-1409 እና የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 430(1)፣ 443 መሰረት ተደርጐ በአብላጫ ድምፅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል
🏠በጨረታ በሚሸጠው ንብረት ላይ የጋራ ባለሀብት በመሆኑ ምክንያት በሕግ የቀዳሚነት መብት የተጠበቀለት ወገን ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ ካልቀረበ በቀር ጨረታው ተከናውኖ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ የጨረታውን ውጤት አውቆ የሚያቀርበው የቀዳሚነት መብት ጥያቄ በጨረታው አሸናፊ መብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚኖረው አቤቱታው ተቀባይነት የሌለውም።
ዋና ዋና ነጥቦች (Key Legal Points)
#የቅድመ-ሁኔታ ግዴታ፦ የቀዳሚነት መብት ያለው ሰው መብቱን ለመጠቀም የግድ በጨረታው ሂደት ውስጥ እንደ ተወዳዳሪ መሳተፍ አለበት።
#የጊዜ ገደብ፦ ጨረታው ተጠናቆ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚቀርብ የ"እኔ እገዛለሁ" ጥያቄ በሕግ ተቀባይነት የለውም።
#የሦስተኛ ወገን መብት፦ ሕጉ የጨረታውን አሸናፊ (የገዢውን) መብትና ጥቅም ለመጠበቅ ሲል ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚመጡ ጥያቄዎችን ውድቅ ያደርጋል።
Fiker Getachew

❤10👍5