አለ ሕግ
16K subscribers
3.29K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
"ተስፋችሁ አይሙት/Keep Hope Alive"
🕯ጄሲ ጃክሰን (1941 - 2026)

የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የፖለቲካ መሪ ጄሲ ጃክሰን በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጄሲ ጃክሰን በ1960ዎቹ ከአንጋፋው የሰብአዊ መብት ታጋይ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር በመሆን የጥቁር አሜሪካውያንን መብት ለማስከበር በግንባር ቀደምትነት የታገሉ እና ሲገደሉም አብረዋቸው ከነበሩ የቅርብ ረዳቶቻቸው አንዱ ነበሩ።

ጄሲ ጃክሰን በ1984 እና በ1988 ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር በዲሞክራቲክ ፓርቲ ውስጥ ጠንካራ ዘመቻ በማድረግ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ የፕሬዝዳንት ዕጩ በመሆን በታሪክ ተመዝግበዋል።

ተስፋችሁ አይሙት/Keep Hope Alive በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት ጄሲ ጃክሰን በአሜሪካ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያኖሩ ግለሰብ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ እ.ኤ.አ. በ2020 የአሜሪካ መንግስት ከህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የገንዘብ እርዳታ እገዳ ጄሲ ጃክሰን በጽኑ ተቃውመዋል።

ጃክሰን ለአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደብዳቤ በመጻፍ፣ እገዳው ፍትሃዊ እንዳልሆነና የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ገልጸው ነበር።

"ይህ [የአሜሪካ የእርዳታ እገዳ] ምንም ምክንያት የሌለው ውሳኔ ነው፤ ምክንያቱም 85 በመቶው የዓባይ ወንዝ ውኃ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ነው። ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ ከሌሎች 10 የሰሃራ በታች የአፍሪካ የዓባይ ተፋሰስ አገራት የሚመጣ ነው። ግብፅ ለወንዙ ፍሰት የምታበረክተው አስተዋጽኦ 0 በመቶ ነው። " - ጄሲ ጃክሰን


ጃክሰን የህዳሴ ግድብን በሚመለከት የኢትዮጵያን መብት ከደገፉ ጥቂት ተፅዕኖ ፈጣሪ አሜሪካውያን አንዱ የነበሩ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በግድቡ ዙሪያ ፍትሃዊ አቋም እንዲይዝ አቋም ይዘው ተናግረዋል።

😀  | @tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
10😢2😭1
ገንዘብ ሚኒስቴር ጀኔሬተር እና ትራንስፎርመር ለኢንቨስትመንት በካፒታል ዕቃነት ከቀረጥ ነፃ ከሚገቡት መካከል እንዲሆን ፈቅዷል!

ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ቅድሚያ የተፈቀዱ ካፒታል እቃዎች ዝርዝር ከመመሪያ ቁጥር 1064/2017 (የኢንቨስትመንት ማበረታቻን ለማስፈጸም የወጣ መመሪያ) ሙሉ ሰነዱን ላይ ማንበብ ትችላላች።

Source: The Ethiopian economist view
4👍2
የተከለከለው ትልቅ ትንሽ፤ ወፍራም ስስ ተብሎ ሳይሆን ሁሉም አይነት የፕላስቲክ ከረጢት መሆኑን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ፡፡
***

ባለስልጣኑ ሁሉንም አይነት የከረጢት ፕላስቲክ ይዞ የተገኘ በአዋጅ 1383/2017 መሰረት ከ2000 ብር በማያንስ እና ከ5000 ብር የማይበልጥ ገንዘብ እንደሚቀጣ አሰረድቷል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ በለስልጣን "ህግን እናውቃለን" በማለት የተከለከለው ስስ ፌስታል ብቻ ነው ከሚሉ አሳሳች አካላት ህብረተሰቡ እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ ይህን ያሳሰበው ዛሬ የፕላስቲክ ከረጢትን የሚተካ ከፕላስቲክ ውጭ ከረጢቶችን ከሚያመርቱ አካላት ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ ፕላስቲክ በአገር ኢኮኖሚ፣ጤና እና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እያደረሰ ያለውን ቀውስ አስመልክተው የውይይት መነሻ ጸሁፍ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የህግ ተከባሪነት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ጉደታ በአለም ደረጃ በፕላስቲክም ሆነ በሎሎች ምክንያቶች በሚፈጠር ብክለት ወደ 9 ሚሊዮን ሰዎች ይሞታሉ ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ብቻ ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ ውሳጥ 13 በመቶ የሚሆነው ከፕላስቲክ ቁሶች ነው ሲሉ አቶ ለሜሳ ተናግረዋል፡፡

በዓመት 80ሺህ ቶን ፕላስቲክ ይመረታል ተብሎ ይገመታል የሚሉት የባለስልጣኑ የህግ ተከባሪነት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ጉደታ ከዛ ውስጥ በዑደት ተመልሶ ለአገልግሎት የሚበቃው 5 በመቶው ብቻ ነው ይላሉ፡፡

ቀሪው ለዳግም አገልግሎት አይውልም ብለዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢት ተመልሶ ለአገልግሎት አይውልም ወይንም ሪሳይክል አይሆንም ይህን ተግባር የሚያከናውኑትም አይፈልጉትም ለዚያ ነው የፕላስቲክ ከረጢት የተከለከለው ሲሉ አቶ ለሜሳ አክለዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢት ሲቃጠል አየርን ይበክላል፣ሲጣልም አይበሰብስም ለመሬት አይሆንም ሳይበሰብስ አፈር ውስጥ 100 ዓመት ይቀመጣል ይህን ችግር ለመፍታት የፕላስቲክ ከረጢትን ማምረትም ሆነ መጠቀምን ሙሉ በሙሉ መከልከል አስፈልገዋል ተብሏል፡፡

ህጉን አላግባብ ከሚተረጉሙት ሰዎች እራሳችሁን ጠብቁ ያለው ባለስልጣኑ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል ማለት ስስ ከረጢት ማለት ሳይሆን በሪሳይክል ተመልሶ የማይቀየር ማለት እንደሆነ መታወቅ አለበት ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የትኛውም አይነት ማለትም ስስም ይሁን ወፍራም ትልቅም ይሁን ትንሽ የፕላስቲክ ከረጢትን ያመረተ ከ50 ሺህ ብር የማያንስ እና ከ200 ሺህ ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል፣ይዞ ከተገኘ ደግሞ ከ2000 ብር በማያንስ እና ከ5000 ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል ብሏል። #Sheger
5
የአፍሪካ #አህጉራዊ ነጻ #ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አተገባበር፣ የስምምነቱ መሠረታዊ ዓላማው
#AfCFTA ምንድን ነው?

የአፍሪካ አገራት የራሳቸውን ምርት ያለምንም የቀረጥ መሰናክል እርስ በእርሳቸው እንዲገበያዩ የተፈጠረ ታሪካዊ ስምምነት ነው።
ዓላማው፦ የአፍሪካን ምርቶች ማሳደግ፣ የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠር እና አህጉራዊ የንግድ ተወዳዳሪነትን መጨመር ነው።
የአገራት ብዛት፦ እስካሁን 54 አገራት ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን፣ ይህም በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ የንግድ ቀጠናዎች አንዱ ያደርገዋል።
2. የኢትዮጵያ ተሳትፎና የሕግ ማዕቀፍ
ፊርማ፦ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ መጋቢት 21/2018 በኪጋሊ ፈርማለች።
ማጽደቅ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1124/2011 አጽድቆታል።

ለትግበራው ይረዳ ዘንድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 574/2017 ጸድቋል።
መመሪያ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን በጥቅምት 04/2018 በቁጥር 4/0755/18 ባወጣው ሰርኩላር ትግበራውን በይፋ ጀምሯል።
3. የቀረጥ ቅነሳው እንዴት ይፈጸማል? (የዕቃዎች ምድብ)
ኢትዮጵያ ያቀረበቻቸው የዕቃ ዓይነቶች በሦስት ምድብ ተከፍለዋል፦
ምድብ ሀ (Category A)፦ 90% የሚሆኑ ዕቃዎች (እንደ ቆዳ ጥሬ ዕቃዎች ያሉ)። በ10 ዓመት ውስጥ ቀረጣቸው 0% ይገባል።
ምድብ ለ (Category B)፦ 7% የሚሆኑ ዕቃዎች (እንደ ጫማና ቦርሳ ያሉ ስሱ ምርቶች)። በ 8 ዓመት ውስጥ ቀረጣቸው 0% ይገባል።
ምድብ ሐ (Category C)፦ 3% የሚሆኑ ዕቃዎች (ምንም ዓይነት ቅናሽ የማይደረግላቸው)።
4. የቀረጥ ቅነሳው የጊዜ ሰሌዳ
ምድብ ሀ፦ እ.ኤ.አ ከጥር 2021 ጀምሮ በየዓመቱ እኩል እየቀነሰ ሄዶ በ2030 ሙሉ በሙሉ ነጻ ይሆናል።

ምድብ ለ፦ እ.ኤ.አ ከጥር 2026 ጀምሮ ቅነሳው ተጀምሮ በ8 ዓመታት ውስጥ (እ.ኤ.አ እስከ 2033) ሙሉ በሙሉ ነጻ ይሆናል።

ምርቱ ሙሉ በሙሉ ነጻ በሚሆንበት ዓመት ሱርቻርጅ (Surcharge) እና የሶሻል ዴቨሎፕመንት ሌቪ (Social Development Levy) አብረው ይነሳሉ።

5. ተጠቃሚ የሚሆኑ አባል አገራት (የ24ቱ ዝርዝር)
የቀረጥ ቅናሹ የሚሰራው ስምምነቱን ለሴክሬታሪያቱ አሳውቀው በይፋ በጀመሩት 24 አገራት ላይ ብቻ ነው፦


ምሥራቅ አፍሪካ፦ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን።

ምዕራብ አፍሪካ፦ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ጋምቢያ።

ሰሜን አፍሪካ፦ ግብፅ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ አልጄሪያ።

ደቡብ አፍሪካ፦ ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና Namibia፣ ዛምቢያ፣ ማላዊ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሶቶ።

ሌሎች፦ ሞሪሸስ፣ ሲሸልስ፣ ሞዛምቢክ።


6. ለቆዳ ዘርፍ SMEs የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
የአገር በቀል ምርት ምስክር ወረቀት (Certificate of Origin)፦ ምርቱ "በኢትዮጵያ የተመረተ" መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ከጉምሩክ ኮሚሽን ማግኘት ግዴታ ነው።
የታሪፍ ኮድ (HS Code)፦ ምርትዎ በየትኛው የምድብ ኮድ ውስጥ እንደሚወድቅ ማረጋገጥ።
የንግድ ሰነዶች፦ የንግድ ደረሰኝ (Invoice)፣ የይዘት ዝርዝር (Packing List) እና የጽሑፍ ውል ማዘጋጀት።

7. ተቋማዊ ኃላፊነቶች
ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፦ አገራቱን የመለየትና የንግድ ድርድሩን የመምራት ኃላፊነት።
ጉምሩክ ኮሚሽን፦ የምስክር ወረቀት የመስጠት፣ የዕቃዎችን አመዳደብ የመቆጣጠርና ቀረጡን የመቀነስ ኃላፊነት።
ገንዘብ ሚኒስቴር፦ የቀረጥ መጠኑን በየዓመቱ የማሳወቅና የማስተካከል ኃላፊነት።

8. የሂደት ቅደም ተከተል (Step-by-Step Approach)
ምርትዎን ይለዩ፦ የትኛውን የቆዳ ውጤት (ጫማ፣ ቦርሳ ወዘተ) ለመላክ እንደፈለጉ መወሰን።
ገበያ ይምረጡ፦ ከላይ ከተጠቀሱት 24 አገራት ውስጥ የተሻለ ገበያ ያለውን መምረጥ።
የአገር በቀል ምስክር ወረቀት ይውሰዱ፦ ምርቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ከጉምሩክ ያረጋግጡ።
ገዢ ያግኙ፦ የዲጂታል መሣሪያዎችን (WhatsApp, Email) በመጠቀም ከውጭ ገዢዎች ጋር ይደራደሩ።
ጭነት ይጀምሩ፦ በደንብ ቁጥር 574/2017 መሠረት የቀረጥ ቅናሹን ተጠቅመው ምርትዎን ይላኩ።
ይህ ስምምነት ለቆዳ ዘርፍ አምራቾች አዲስና ሰፊ በር የከፈተ በመሆኑ፣ አምራቾች የጥራት ደረጃቸውን በማሻሻልና ሕጋዊ ሰነዶችን በማሟላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመከራል።
ስልጠናው በጠበቃና የሕግ አማካሪ Mikias Melak ተሰጠ🙏 #ሚኪያስ_መላክ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
9👍4
በየሶስት ወሩ የሚከፈል ታክስ መክፈያ እና ማሳወቂያ ጊዜ


በገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ 1395/2017 አንቀጽ 89 እንደተደነገገው በየሶስት ወሩ የሚከፈለው ግብር ግብር ከፋዩ የሂሳብ ሪፖርት በሚያቀርብበት ወር መጨረሻ ጀምሮ ካለው ሶስት ወር ጊዜ በኋላ ባለው 30 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሰረት የሂሳብ ሪፖርታቸውን ጥቅምት/2018 ዓ.ም ያጠናቀቁ ግብር ከፋዮች የመጀመሪያውን የካቲት/2018፣ ሁለተኛውን ግንቦት/2018፣ ሶስተኛውን ነሀሴ/2018ዓ.ም ይከፍሉና አራተኛውን እና የማጠቃለያ የሂሳብ ሪፖርታቸውን እስከ ጥቅምት/2019 ዓ.ም የሚያጠናቅቁ ይሆናል፡፡
የሂሳብ ሪፖርታቸውን እ.ኤ.አ በኤፕሪል/2025 የዘጉ ድርጅቶች የመጀመሪያውን ኦገስት/2025፣ ኖቬምበር/2025 እና ፌብርዋሪ/2026 ይከፍሉና አራተኛውን እና የማጠቃለያ የሂሳብ ሪፖርታቸውን እስከ ኤፕሪል/2026 ዓ.ም የሚያጠናቅቁ ይሆናል፡፡

በየሶስት ወሩ የሚከፈለው የአመታዊ ግብሩ 25% ወይም 1/4ኘኛ ሲሆን፣ በሶስት ወር ውስጥ ከገቢያችን ላይ የተቀነሰ የቅድመ ግብር (withholding tax) ካለ ከምንከፍለው ክፍያ ላይ ተቀናሽ እናደርጋለን፡፡

ለምሳሌ፡ X PLC የሂሳብ ሪፐርቱን ያቀረበው ጥቅምት 2018ዓ.ም ቢሆን እና የከፈለው ታክስ 1,500,000 ቢሆን፤
የካቲት/2018ዓ.ም ላይ 375,000
ግንቦት/2018ዓ.ም ላይ 375,000
ሶስተኛውን ነሀሴ/2018ዓ.ም 375,000
አራተኛውን እና የመጨረሻውን ጥቅምት/2019ዓ.ም የሂሳብ ሪፖርት ያሰራ እና መከፈል ያለበት ግብር ከ2018 በጀት ከፍ ያለ ከሆነ 375,000ብር ላይ ልዩነቱን ጨምሮ፣ ከ2018 በጀት ዝቅ ያለ ከሆነ ደግሞ ከ375,000ብር ቀንሶ ልዩነቱን ብቻ ይከፍላል፡፡
መጋቢት እና ሚያዚያ ወር ላይ ዊዝሆልድ የተደረገ 150,000ብር ቢኖረው ግንቦት ላይ ከሚከፍለው ታክስ ላይ ተቀናሽ ማድረግ አለበት፡፡
ይህ ማለት 375,000 - 150,000 = 225,000ብር ይሆናል ማለት ነው፡፡
https://t.me/AleHig
3🔥1
#ከፍቺ_በኋላ_የተደረገ የንብረት ስምምነት- በፍርድ ቤት መጽደቅ አላስፈላጊነት

ከ “የቤተሰብ ህግ፥ በሰበር ችሎት” የተወሰደ
#ተጋቢዎች በትዳር ውስጥ እያሉ የሚያደርጓቸው የንብረት ስምምነቶች ወይም የጋብቻ ውል ማሻሻያዎች በሕግ ፊት ተቀባይነት እንዲኖራቸው በፍርድ ቤት መጽደቅ አስፈላጊነት ጋብቻው በፍቺ ከፈረሰ በኋላ ተጋቢዎቹ የሚያደርጓቸውን የንብረት ስምምነቶች የሚመለከት አለመሆኑን የሰበር ውሳኔዎች በዝርዝር ያስረዳሉ። ከፍቺ በኋላ የሚደረግ የንብረት ስምምነት ተጋቢዎቹ እንደገና ታርቀው ጋብቻቸውን ለመቀጠል በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ሊከሰት የሚችል ሲሆን እንዲህ ዓይነቱ ስምምነት በፍርድ ቤት እንዲጸድቅ ሕጉ በግልጽ አያስገድድም።

#ይህንን መርህ በተመለከተ በሰበር መዝገብ ቁጥር 181543 ላይ ግልጽ የሆነ የሕግ ትርጉም ተሰጥቶበታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ተጋቢዎቹ ቀደም ብለው በፍቺ ከተለያዩ በኋላ እርቅ አድርገው ጋብቻቸውን ለመቀጠል ሲስማሙ አንደኛው ወገን ከጋብቻ በፊት በውርስ ያገኘው ቤት የጋራ ንብረት እንዲሆን በውል ተስማምተዋል። የበታች ፍርድ ቤቶች ይህ ስምምነት በፍርድ ቤት ስላልጸደቀ ዋጋ የለውም በማለት ውድቅ ቢያደርጉትም የሰበር ሰሚ ችሎቱ ግን ውሳኔውን ሽሮታል። ችሎቱ በሰጠው አስገዳጅ ትርጉም የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ አንቀጽ 47 እና 73 የሚያስገድዱት የጋብቻ ውልን የማሻሻል ወይም በጋብቻ ውስጥ የመዋዋል ግዴታ በፍርድ ቤት እንዲጸድቅ ሲሆን ይህ ድንጋጌ ተጋቢዎች ጋብቻቸው በሕግ ከፈረሰ በኋላ የሚያደርጉትን ስምምነት አይመለከትም። በመሆኑም ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ የተደረገው የእርቅና የንብረት ስምምነት በፍርድ ቤት ሳይጸድቅም የጸና ሕጋዊ ውጤት ይኖረዋል።

#በተመሳሳይ ሁኔታ በአማራ ክልል የቤተሰብ ሕግ አተገባበር ላይም ተመሳሳይ አቋም በሰበር መዝገብ ቁጥር 148204 ላይ ተንጸባርቋል። ተጋቢዎች በፍርድ ቤት ከተፋቱ በኋላ ከፍርድ ቤት ውጭ ጋብቻ የማደስ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን በዚህ ስምምነት ወቅት ወፍጮን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶችን ተከፋፍለዋል። የክልሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 84 ተጋቢዎች በትዳር ውስጥ እያሉ የሚያደርጉት ውል በፍትሕ አካል መጽደቅ እንዳለበት ቢደነግግም ስምምነቱ የተደረገው ጋብቻው በፍርድ ቤት ከፈረሰ በኋላ እስከሆነ ድረስ ይህ አንቀጽ ተፈጻሚነት እንደሌለው ችሎቱ ወስኗል።

#ከፍቺ በኋላ የሚደረጉ የንብረት ስምምነቶች በአፈፃፀም ሂደት ላይም ያላቸው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው። ተጋቢዎች ከፍቺ በኋላ በሽማግሌዎች ወይም በራሳቸው ስምምነት አድርገው ንብረት ከተረካከቡና ይህንኑም በአፈፃፀም ችሎት ቀርበው ካረጋገጡ ስምምነቱ በፍርድ ቤት አልጸደቀም በሚል ምክንያት እንደገና አዲስ ክርክር ሊነሳበት አይችልም። የአፈፃፀም ትዕዛዝ የመጨረሻነት ባህሪ ስላለውና ግራ ቀኙ በስምምነቱ መሠረት ንብረት መረካከባቸውን ካረጋገጡ በኋላ ስምምነቱን መካድ አይቻልም። በተጨማሪም እንዲህ ያሉ ስምምነቶች በሰው ምስክር ሊረጋገጡ የሚችሉ ሲሆን በተለይም የሁለቱም ወገን ምስክሮች ስለ ስምምነቱ መኖርና ስለ ንብረት ክፍፍሉ ከመሰከሩ ስምምነቱ ጸንቶ ይቆያል።

#ከላይ በተጠቀሱት ሁለት መዝገቦች ከፍቺ በኋላ የሚደረግ የንብረት ስምምነት በሕግ ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በፍርድ ቤት መጽደቅ እንደ ቅድመ ሁኔታ እንዳልተቀመጠ የሰበር ችሎት ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ችሎቱ አክሎ ኣንዳለው የሕጉ ጥበቃ በትዳር ውስጥ ለሚደረጉ ውሎች ብቻ የተገደበው ተጋቢዎች በትዳር ውስጥ ባላቸው ልዩ ግንኙነት ምክንያት አንደኛው በሌላው ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል በሚል ስጋት ሲሆን ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ግን ተዋዋዮቹ እንደ ማንኛውም ነጻ ግለሰብ ስለሚቆጠሩ ስምምነታቸው በውል ሕግ መሠረት ተፈጻሚነት ይኖረዋል። ሁለቱም ውሳኔዎች የተሰጡት ፍቺ በፍርድ ቤት ከተወሰነ በኋላ ተጋቢዎች “ጋብቻውን ማደስ” በሚል እርቅ በፈጸሙበት ሁኔታ ነው። በችሎቱ ሀተታ ላይ እንደሰፈረው ተጋቢዎች ከፍቺ በኋላ ጋብቻቸውን ለማደስ በሚያደርጉት የእርቅ ስምምነት ውስጥ የግል ንብረትን የጋራ ለማድረግ ወይም ንብረት ለመከፋፈል ቢስማሙ ይህ ስምምነታቸው በፍርድ ቤት ባይጸድቅም በመካከላቸው አስገዳጅ የሆነ ሕጋዊ ውጤት ያስከትላል።

#ምንም እንኳን በሁለቱም የሰበር ውሳኔዎች ላይ የንብረት ስምምነት የተደረገው በ “ጋብቻ ማደስ” ዐውድ ቢሆንም “የጋብቻ ማደሱ” የክርክሩ ጭብጥ አልነበረም። ዳግም ጋብቻ ተመስርቷልም አልተባለም። ስለሆነም “ተጋቢዎች ጋብቻቸው በፍርድ ቤት ከፈረሰ በኋላ በሕግ ከተመለከቱት የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች (በክብር መዝገብ ሹም፣ በሃይማኖት ወይም በባህል) ውጭ አዲስ የጋብቻ ሥርዓት ሳይፈጽሙ አብረው መኖራቸው ብቻውን ጋብቻው እንደቀጠለ ያስቆጥራል የሚለው የሰበር ትርጓሜ” በፌዴሬሽን ምክር ቤት መሻሩ በውሳኔዎቹ ይዘት ላይ የሚያስከትለው ለውጥ የለም። ምክንያቱም ከችሎቱ ሀተታ እንደሚነበበው የህግ አተረጓጎሙ መነሻ ያደረገው የጋብቻ አለመኖር እንጂ መኖሩ አይደለም። በተለይም “የሕጉ ጥበቃ በትዳር ውስጥ ለሚደረጉ ውሎች ብቻ የተገደበው ተጋቢዎች በትዳር ውስጥ ባላቸው ልዩ ግንኙነት ምክንያት አንደኛው በሌላው ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል በሚል ስጋት” እንደሆነ የተገለጸው አመክንዮ የችሎቱ አቋም በ “ጋብቻ ማደስ” ተጽዕኖ ስር እንዳልወደቀ አስረጂ ነው።

#እዚህ ላይ መነሳት ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ ይህ የሰበር ችሎቱ የህግ ትርጉም ችሎቱ በሌሎች መዝገቦች ላይ “የፍቺ ውጤቶች ስምምነት” በፍርድ ቤት መጽደቅ እንዳለባቸው ከያዘው ጠንካራ አቋም ጋር እንዴት ይታረቃል? የሚለው ነው። ምናልት ይሄኛው ህጋዊ ውጤት ይኑረውም አይኑረውም ተጋቢዎች ከተፋቱ በኋላ አንድ ላይ ለመኖር ታርቀው የሚያደርጉት የንብረት ስምምነት ሲሆን ኋለኛው ግን የፍቺ ውጤት ስምምነት ነው ቢባል የችሎቱን አቋም ያስታርቀው ይሆን? ይሁን እንጂ በዚህ መልኩ ድምዳሜ ላይ መድረስ አንድን ህንጻ ፊት እና ከኋላ አይቶ “ሁለት የተለያዩ ህንጻዎች ናቸው” ስለመሆናቸው እርግጠኛ የመሆን ያክል የማያስኬድ ነው።
አብርሀም ዮሀንስ
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
11
የቤተሰብ ህግ በሰበር ችሎት

📢 አዲስ የህግ መጽሐፍ የቅድመ-ትዕዛዝ ጥሪ!

"የቤተሰብ ህግ በሰበር ውሳኔዎች" — በአቀራረቡ ለየት ያለና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ላይ ያተኮረ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለህትመት ይበቃል።

በአሁኑ ወቅት የህትመት ዋጋ መናር ስራዎችን ለህዝብ ለማድረስ ፈታኝ ቢሆንም፣ ይህ እውቀት ለባለሙያውና ለአንባቢው እንዲደርስ ለማድረግ በጣም ውስን ኮፒዎችን (ከ300-500 ብቻ) ለተመዝጋቢዎች ለማቅረብ ተዘጋጅተናል።

🎯 የምዝገባ አማራጮች እና ልዩ ጥቅሞች
መጽሐፉን በሁለት መንገድ መመዝገብ ይችላሉ፦

1. ቅድሚያ ገዢ (Early Bird):
ቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም መጽሐፉ እስኪወጣ ለሚጠብቁ ደንበኞች የሚከተሉት ልዩ የቴክኖሎጂ ጥቅሞች ለተወሰነ ጊዜ በነጻ ይሰጣሉ፦

* Desktop Application: ከቅፅ 1-28 ያሉ፣ የ7 ዳኞች ትርጉም፣ የህፃናትና ሴቶች ጉዳይን ጨምሮ ከ 10,000 በላይ የሰበር ውሳኔዎች ማጠቃለያ የያዘ። እያንዳንዱ ማጠቃለያ የክርክሩን አመጣጥ፣ ቁልፍ የህግ ትርጉም እና የፍርዱን አመክንዮ በዝርዝር የያዘ ሲሆን፤ ፈጣንና ዘመናዊ መፈለጊያ (Search) ተገጥሞለታል።


* Mobile Application: ከ10 ሺህ በላይ ውሳኔዎችን "የአንድ መስመር" ማውጫ የያዘ መተግበሪያ።
2. ኋላ ገዢ (Standard):
መጽሐፉ ሲታተም ክፍያ ፈጽመው መጽሐፉን ብቻ በአድራሻቸው የሚረከቡ።

📘 የመጽሐፉ መረጃ
* ርዕስ፦ የቤተሰብ ህግ
* የገጽ ብዛት፦ 350
* ዋጋ፦ 1,000 ብር (Delivery/ማድረሻን ጨምሮ)

📝 እንዴት ይመዘገባሉ?
ኮፒው በጣም ውስን ስለሆነ አሁኑኑ ስምዎትንና አድራሻዎትን በሚከተለው ስልክ ቁጥር ይላኩ፦

📞 ስልክ፦ 0915735560 (በText, Telegram ወይም WhatsApp)
ሲመዘገቡ የሚከተለውን መረጃ ያካትቱ፦
* ሙሉ ስም
* ስልክ ቁጥር
* አድራሻ (መጽሐፉ እንዲደርሶ የሚፈልጉበት)

* የምዝገባ አይነት፦ "ቅድሚያ ገዢ" ወይም "ኋላ ገዢ" በማለት ይጥቀሱ።

> ማሳሰቢያ፦ መጽሐፉ ለተመዝጋቢዎች ብቻ የሚሸጥ ሲሆን፣ ርክክቡም ባለዎት አድራሻ ላይ በመመስረት በቤትዎ ወይም በቢሮዎ ድረስ በነጻ ይከናወናል።
>
ይህንን መልዕክት ለሌሎች የህግ ባለሙያዎች በማጋራት ይተባበሩ!


(ከታች ምስል mobile app screenshots)
6😁1
የቤተሰብ ህግ በሰበር ችሎት ✍️

📢 አዲስ የህግ መጽሐፍ የቅድመ-ትዕዛዝ ጥሪ!

"የቤተሰብ ህግ በሰበር ውሳኔዎች" — በአቀራረቡ ለየት ያለና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ላይ ያተኮረ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለህትመት ይበቃል።

በአሁኑ ወቅት የህትመት ዋጋ መናር ስራዎችን ለህዝብ ለማድረስ ፈታኝ ቢሆንም፣ ይህ እውቀት ለባለሙያውና ለአንባቢው እንዲደርስ ለማድረግ በጣም ውስን ኮፒዎችን (ከ300-500 ብቻ) ለተመዝጋቢዎች ለማቅረብ ተዘጋጅተናል።

🎯 የምዝገባ አማራጮች እና ልዩ ጥቅሞች
መጽሐፉን በሁለት መንገድ መመዝገብ ይችላሉ፦

1. ቅድሚያ ገዢ (Early Bird):
ቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም መጽሐፉ እስኪወጣ ለሚጠብቁ ደንበኞች የሚከተሉት ልዩ የቴክኖሎጂ ጥቅሞች ለተወሰነ ጊዜ በነጻ ይሰጣሉ፦

* Desktop Application: ከቅፅ 1-28 ያሉ፣ የ7 ዳኞች ትርጉም፣ የህፃናትና ሴቶች ጉዳይን ጨምሮ ከ 10,000 በላይ የሰበር ውሳኔዎች ማጠቃለያ የያዘ። እያንዳንዱ ማጠቃለያ የክርክሩን አመጣጥ፣ ቁልፍ የህግ ትርጉም እና የፍርዱን አመክንዮ በዝርዝር የያዘ ሲሆን፤ ፈጣንና ዘመናዊ መፈለጊያ (Search) ተገጥሞለታል።


* Mobile Application: ከ10 ሺህ በላይ ውሳኔዎችን "የአንድ መስመር" ማውጫ የያዘ መተግበሪያ።
2. ኋላ ገዢ (Standard):
መጽሐፉ ሲታተም ክፍያ ፈጽመው መጽሐፉን ብቻ በአድራሻቸው የሚረከቡ።

📘 የመጽሐፉ መረጃ
* ርዕስ፦ የቤተሰብ ህግ
* የገጽ ብዛት፦ 350
* ዋጋ፦ 1,000 ብር (Delivery/ማድረሻን ጨምሮ)

📝 እንዴት ይመዘገባሉ?
ኮፒው በጣም ውስን ስለሆነ አሁኑኑ ስምዎትንና አድራሻዎትን በሚከተለው ስልክ ቁጥር ይላኩ፦

📞 ስልክ፦ 0915735560 (በText, Telegram ወይም WhatsApp)
ሲመዘገቡ የሚከተለውን መረጃ ያካትቱ፦
* ሙሉ ስም
* ስልክ ቁጥር
* አድራሻ (መጽሐፉ እንዲደርሶ የሚፈልጉበት)

* የምዝገባ አይነት፦ "ቅድሚያ ገዢ" ወይም "ኋላ ገዢ" በማለት ይጥቀሱ።

> ማሳሰቢያ፦ መጽሐፉ ለተመዝጋቢዎች ብቻ የሚሸጥ ሲሆን፣ ርክክቡም ባለዎት አድራሻ ላይ በመመስረት በቤትዎ ወይም በቢሮዎ ድረስ በነጻ ይከናወናል።
>
ይህንን መልዕክት ለሌሎች የህግ ባለሙያዎች በማጋራት ይተባበሩ!


(ከላይ ምስል mobile app screenshots)
11
👉#ሰበር #መረጃ
👉 ሰበር #ውሳኔ
👉 ሰበር #ትዕዛዝ
👉 ሰበር #መግለጫ
👉 ሰበር #ምርመራ

👉ሰበር ዝውውር
👉 ሰበር #ውጤት
👉ሰበር #ቅሌት
👉ሰበር #ሹመት

👉ሰበር የዋጋ ተመን
👉 ሰበር ስምምነት
👉 ሰበር #ቅናሽ

👉 ሰበር #እውነታ
👉ሰበር #ምስል
👉 #ሰበር_ጥቆማ
#አለሕግ #AleHig
6