አለ ሕግ
16K subscribers
3.29K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
1085_የግል_ድርጅቶች_ሠራተኞች_ጡረታ_አፈጻጸም_መመሪያ_ቁጥር_1085_2017.pdf
406.1 KB
1085-የግል-ድርጅቶች-ሠራተኞች-ጡረታ-አፈጻጸም-መመሪያ-ቁጥር-1085-2017.pdf
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት

Alternative legal enlightenment & Service

Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
6👍4👌2
213020_2014_መጥሪያ_በቴሌግራም_ማድርስ_አይቻልም_2.pdf
447.8 KB
1. በቴሌግራም ወይም በቫይበር መጥሪያ ማድረስ ይቻላል?

በመ/መ/ቁ. 213020 ውሳኔ መሰረት መጥሪያን በቴሌግራም ወይም በቫይበር ማድረስ በሕጉ የተዘረጋው መደበኛ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት አካል እንደሆነ ተደርጎ አልተወሰደም ። 

ይሁን እንጂ እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ክስ መኖሩን ለተከሳሹ ለማሳወቅ እንደ "ተሻለ አማራጭ ዘዴ" ሊያገለግሉ እንደሚችሉ ፍርድ ቤቱ ጠቁሟል ።

2. የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 94-110 መጥሪያ የሚደርስባቸውን አራት መደበኛ ደረጃዎች (ለተከሳሹ ራሱ፣ ለሌላ ሰው፣ በፖስታ እና ምትክ መጥሪያ) በቅደም ተከተል ያስቀምጣል።

ተጠሪ ከአመልካች ጋር በቴሌግራም፣ በቫይበር እና በስልክ ግንኙነት እያላቸው፣ ይህንን ግንኙነት ለሥር ፍርድ ቤት ሳታሳውቅ "አድራሻቸውን አላውቅም" በማለት በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ ማድረጓ "ከቅን ልቦና ውጭ" ተደርጎ ተቆጥሯል ።

ተከሳሹ በውጭ አገር እንደሚኖርና በነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘዴዎች እንደሚገናኙ ለፍርድ ቤቱ ቢታወቅ ኖሮ፣ ፍርድ ቤቱ ጋዜጣ ላይ ከመለጠፉ በፊት "የተሻለ የመጥሪያ አደራረስ ዘዴን" (መረጃው ለተከሳሹ መድረሱን ማረጋገጫ የሚሆንበትን መንገድ) ተግባራዊ ለማድረግ ያስችለው ነበር ።

ውሳኔው የቴሌግራም ወይም የቫይበር መልእክት ራሱን ችሎ እንደ ሕጋዊ መጥሪያ ይቆጠራል አላለም። ነገር ግን፡ ተከሳሹን በእነዚህ መንገዶች ማግኘት እየተቻለ፣ አድራሻው እንደማይታወቅ ተቆጥሮ በጋዜጣ ጥሪ መደረጉ ስህተት እንደሆነ ወስኗል ።

ፍትሐዊ የሙግት ሂደት እንዲኖር፣ ፍርድ ቤቶች ተከሳሹ መኖሩን የሚያውቁበትን ማንኛውንም የተሻለ አማራጭ በመጠቀም መጥሪያው እንዲደርስ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል።
በመልካሙ መርጊያ
21
ለጥንቃቄ !

ከላይ ያለውን የሄለን አበራ (ስሟ የተቀየረ) በአፍዝ አደንግዝ የተፈጸመባትን የዝርፊያ ታሪክ ያነበቡ በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት እነሱም የደረሰባቸውን የሚያውቁትን በDM ሲያጋሩ አምሽተዋል።

የቀረበው ታሪክ ለሁላችንም ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው።

መሰል የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የሰዎችን ደግነት እና የኢትዮጵያዊነት የመረዳዳት ባህልን ለክፉ ዓላማቸው የሚጠቀሙ ናቸው።

ከዚህ አስደንጋጭ ድርጊት በመነሳት ራሳችንን፣ ቤተሰባችንን እንዲሁም የምናውቃቸውን ለመጠበቅ የሚረዱ አጭር የጥንቃቄ ሀሳቦችን እናግራችሁ።

ከምንም ነገር በላይ እንደየ እምነታችሁ ከቤት ስትወጡ ፈጣሪ ከክፉ እንዲጠብቃችሁ ፤ ክፉውን እንዲያርቅላችሁ ፣ መጥፎ ድርጊት ሁሉ እናተ ላይ እንዳይሰራባችሁ ፣ በሰላም ወጥታችሁ በሰላም እንድትገቡ ጸልያችሁ ይሁን።

ከዚህ ባለፈ ...

⚠️ ከማታውቁት ሰው ጋር ንክኪን አስወግዱ።

የ" አፍዝ አደንዝዝ " ድርጊትን የሚሰሩ ሰዎች የአካል ንክኪ በመጠቀም ነው።

መንገድ ላይ ሆነ ባንክ አካባቢ ወይም ሌላ ቦታ ማንም ሰው እንዲጠጋዎት አይፍቀዱ።

ትከሻዎትን፣ አንገትዎትን ወይም እጅዎትን ለመንካት የሚሞክርን ሰው በንቃት ይከታተሉ፤ ወዲያውኑ ይራቁት።

" ልብስዎ ላይ ቆሻሻ አለ" በሚል ሰበብ ሊጠርጉልዎትና ሊነካዎት የሚሞክሩ ሰዎችን ከማመን ይልቅ ይጠራጠሩ፤ ይራቁ።

⚠️ "ሎተሪ ደረሰኝ" ድራማዎችን ይለዩ።

ይህ " ሎተሪ ደረሰኝ " ድራማ በጣም የተለመደ የማጭበርበሪያ ስልት ነው። " ሎተሪ ደርሶኛል ነገር ግን መታወቂያ የለኝም " የሚል ጥያቄ ሲቀርብልዎት በፍጹም አይመኑ።

አንድ ሰው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ደርሶት የማያውቀውን ሰው መንገድ ላይ ጠልፎ "ተባበረኝ" የሚልበት አሳማኝ ምክንያት የለም።

እንዲህ አይነት ጥያቄ ሲቀርብልዎት "ፖሊስ ጣቢያ ሄደህ ጠይቅ"  በማለት ውይይቱን ያቋርጡ።

⚠️ ያሉበትን አካባቢ በፍጹም ንቃት ይከታተሉ።

ወንጀለኞች ብቻቸውን አይደሉም። በቡድን ነው የሚንቀሳቀሱት።

አንድ ሰው ሊያናግርዎት ሲሞክር ሌላው ከኋላዎ ወይም በጎንዎ እንዳይቆም ጥንቃቄ ያድርጉ።

በአቅራቢያዎ የሚጠባበቁ ባጃጆች ወይም መኪናዎች ካሉ ጥርጣሬ ይኑርዎት። ከቻሉ ታርጋውን ለማየት ይሞክሩ።

ሰው በሌለበት ወይም ጭር ባለ መንገድ ላይ ከማያውቁት ሰው ጋር ንግግር አይጀምሩ፤ በፍጹም ንግግር አያድርጉ።

⚠️ ወንጀለኞች ርህራሄያችሁን እና ንጹህ ልባችሁን ነው የሚጠቀሙት ጥንቃቄ አድርጉ።

ወንጀለኞቹ ርህራሄያችሁንና ንጹህ ልባችሁን ተጠቅመው አእምሯችሁን ይቆጣጠራሉ።

ግራ የተጋባ ወይም የተቸገረ መስሎ የሚቀርብን ሰው ለመርዳት ከመሞከርዎ በፊት ሁኔታው ምክንያታዊ መሆኑን ያረጋግጡ።

ሰው ሲያግዙ እውነት ያ ሰው ተቸግሮ መሆኑን በደምብ ያረጋግጡ።

መንገድ ላይ ያገኙት የማያውቁት ሰው ማንኛውንም የገንዘብ ወይም የንብረት ጥያቄ የሚያነሳ ከሆነ ወዲያውኑ ጥለው ይለፉ።

ድርጊቱ ተፈጽሞስ ከሆነ ? ድርጊቱን በፍጥነት ለፖሊስ ማሳወቅ ጥሩ ነው። የእርስዎ ሪፖርት ማድረግ ሌሎች ተመሳሳይ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ፍትህ እንዲያገኙ እና ወንጀለኞቹ እንዲያዙ ይረዳል።

🔅ይህ የጥንቄቄ መልዕክት ጠቃሚ መስሎ ከታያችሁ ለሌሎች አጋሩ።

ወንጀለኞች አብዛኛውን ጊዜ ደግ እና የዋህ የሚመስሉ ሰዎችን ስለሚመርጡ ንቁ መሆን ይገባል።

Stay Safe !

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA❤️

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
9👍3🔥1
ለጥንቃቄ !

ጥር 27/2018 ዓ.ም ቀን ሄለን አበራ (ለዚህ ጹሁፍ ሲባል ስሟ የተቀየረ) እንደወትሮው ሁሉ ከስራ ገበታዋ ወደ መኖሪያ ቤቷ ሀገር አማን ብላ እየተመለሰች ነው።

በድንገት ታዲያ ከዚህ በፊት በመልክ የማትለየው እና በአካል አግኝታው የማታውቀው አንድ ግለሰብ ወደ እርሷ በመጠጋት ትብብር እንድታረግለትና እንድትረዳው ይጠይቃታል።

ግለሰቡ " እባክሽ የኔ እህት ሎተሪ ደርሶኝ ነበር። ነገር ግን ገንዘቡን ለመውሰድ መታወቂያ የለኝም። በዚህ ላይ ለሀገሩ እንግዳ ነኝ " በሚል ነው በተቅለሰለሰና ግራ በተጋባ ስሜት የጠየቃት።

ታዲያ ሄለን ወትሮም በኢትዮጵያዊነት ባህልና የመደጋገፍ ብሂል ያደገች እንደመሆኗ ጥያቄውን ለማስተናገድ ሎተሪ ደረሰኝ ያላትን ሰው ለመርዳት እያናገረች ሳለ ሌላ  ከዚህ በፊት የማታውቀው ግለሰብ አንገቷ አካባቢ #በዳበሳ መልክ ይነካታል።

በዚህ ጊዜ ሄለን ሌላ ሶስተኛ ግለሰብ ከጀርባ በመዳፉ የያዘውን ይዞ መቆሙንም ልብ አላለችም።

ራቅ ብሎ ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ሁለት ግለሰቦች በባጃጅ ውስጥ ሆነው ዙሪያ ገባውን በመቃኘት በአንክሮ ይከታተሏቸዋል።

ሄለን " ሎተሪ ደረሰኝ ተባበሪኝ " ያላትን ግለሰብ ለመርዳት ከማሰብ ውጪ በጊዜው አንዳች ነገር ይገጥመኛል ብላ በጭራሽ አልገመተችም።

ሆኖም ግን በነበረው እያንዳንዱ ማለትም " ሎተሪ ደርሶኛል " ባዩ ጀምሮ አንገቷ አካባቢ ከዳበሳት ግለሰብ ጋር በነበራት የንግግር እና የንክኪ ግንኙነት ብሎም ከጀርባ ከቆመው ግለሰብ ጋር ተያይዞ ሄለን አበራ ላይ እንግዳ ነገር ተከስቶ ነበር።

አሁን ሄለን ከስራ ወደ ቤት በመመለስ እና በራሷ የምትመራው የቅድሟ ሄለን አይደለችም።

ሙሉ በሙሉ በነዚህ የተደራጁ ሰዎች ቁጥጥር ስር በመውደቋ የነሱን ትዕዛዝ ፈጻሚና አስፈጻሚ ሆነች።

በነዚሁ ሰዎች አፍዝ አደንዝዝ የድግምት መረብ በመጠለፍ ለወጠኑት ዝርፊያ መሳሪያ ለመሆንና፣ ቀጣይ የሚነግሯትን መርሀ ግብር ለመፈጸም የተዘጋጀች ሆነች።

ሄለን ያላወቀችው የሰዎቹን ድብቅ ዓላማ ነው። ዓላማቸው " ሎተሪ ደረሰኝ " ባዩ  ሲያናግራት ትኩረቷን እሱ ላይ እንድታደርግ እና ሁለተኛው ግለሰብ እጁ ላይ ባረጠበው ፈሳሽ አንገቷን እንዲያነካት ሲያመቻች ሶስተኛው ግለሰብ ከጀርባዋ የአፍዝ አደንግዝ ስራውን እንዲሰራ ነበር፤ ይህም ተሳክቶላቸዋል።

ሄለን ላይ ያሰቡትን ቀጣይ መርሀ ግብር ለመፈጸም ባጃጅ 300 ብር ተኮናትረው ለሶስት አብረዋ ገቡ።

ጉዞ ላይ ሳሉ የመጀመሪያውን " የአንገት እና የጆሮ ጌጥ ብሎም የእጅ ቀለበት ወርቅን አውለቀሽ ስጪን ? "  አሏት።

ሌሎች ሁለት ግብረአበሮቻቸው ደግሞ በሌላ ባጃጅ በጥንቃቄ ፓሊስ መኖሩን አለመኖሩንና ሌላ ሰው ሁኔታውን አየ አላየ በትኩረት ይከታተላሉ።

ሄለንም አንዳች አላንገራገረችም፤ ያሏትን ፈፀመች።

ቀጠለው " ገንዘብ አለሽ ? " የአፍዝ አደንዛዦቹ ጥያቄ ነበር።

ሄለንም " አዎን  4 ሺህ ዶላር መኖሪያ ቤቴ አለኝ" በማለት መለሰችላቸው።

" እንግዲያውስ ስጪን " ሲሉ አዘዙ።

ሄለንም ወደ መኖሪያ ቤቷ አብራቸው በመሄድ 4 ሺህ ዶላሩን ጨምሮ ሁለት አይፎን ስልክ እንዲሁም ያሏትን የወርቅ ጌጦቿን ከቁምሳጥኗ አውጥታ አስረከበቻቸው።

ይሄኔ ስልክ ተደወለ።

ከሄለን ጋር አብረዋት ካሉት ሁለቱ ግለሰቦች መካከል " ሎተሪ ደረሰኝ " ላለው ሰው ነው ስልክ የተደወለው።

ከኋላ በባጃጅ ከሚከተሏቸው ተባባሪ ዘራፊዎች የዕቅዳቸው የመጨረሻ መርሀ ግብርን ለመፈጸም ነበር የተደወለው።

" ሎተሪ የደረሰህ ግለሰብ መታወቂያ ይዘህ በመምጣት መውሰድ ትቻላለህ " ነበር የስልኩ የላውድ ላይ መልዕክት።

ይሄኔ ሚስኪኗን ሄለን በመረባቸው ያስገቡት አፍዛዥ አደንግዞች በሷ የማዘዝ መብት ባለቤትነትን በመጠቀም ዳግም በባጃጅ አንድ ሰው ብቻ ብሩን ከብሄራዊ ሎተሪ መውሰድ እንደሚችልና እሷ እንድትወስድ በአሚር አጣብቀው እንደደረሳቸው አስመስለው የሰሩትን ሎተሪ አስረከቧት።

ይሄን ሁሉ ሄለን ላይ ሲያደርጉ ከነሱ ውጪ ሌላ ሰው እንዳያገኛትና እንዳይነካት ፣ ውሀም ይጉን የትኛውንም ነገር አካሏን እንዳይነካት እጅግ ጥንቃቄ በማድረግ ነበር።

ታዲያ በመጨረሻ ሄለን በአፍዝ አደንዛዦቹ " የሎተሪ ብር አውጭልን " ብለው ትተዋት  ወርቆቿን፣ ሁለት አይፎን ስልኳን እና 4 ሺህ ዶላር ገንዘቧን አስረክባ እንደሄዱ ሳቢያን መስቀለኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነቃች።

ከሰዓታት በኋላ የቀድሞ ማንነቷን አገኘች።

ሄለን አበራ ከስራ ወደ ቤት ነበር የጉዞ አቅጣጫዋ ነገር ግን አሁን ብዙ ነገሯን በዘራፊዎች ተነጥቃ መስቀለኛ ራሷን ብታገኝ ሰዎች እስኪከቧት እሪታዋን አቀለጠችው፣ የምትይዘው የምትጨብጠው አጣች።

ሁኔታዋን የተገነዘቡና ያስተዋሏት ሰዎች ሳቢያን ፓሊስ ጣቢያ የደረሰባትን እንድታመለክት ጠቆሟት።

የሳቢያን ፓሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራን በዋናነት ወደሚከውነው የድሬዳዋ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ቡድን ወዳለበት ከዚራ ጣቢያ ይልካታል።

ሄለን የተፈጸመባትን የአፍዝ አደንግዝ ዝርፊያ በድሬዳዋ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ተመስገን ተሰማ አስረዳች።

መሠል ወንጀሎች በተለያዩ ከተሞች መፈጸማቸውን ስለሚያውቁ ቀዳሚ እርምጃቸው ከፍተኛ የመደናገጥ ባህሪ እያሳየች የነበረችውን ሄለንን ማረጋጋት ነበር።

ኢንስፔክተር ተሰማ የሄለንን ቃል ከተቀበሉ በኋላ ጊዜ ከበላይ አመራሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ የምርመራ ስራ ሂደቱን ትዕዛዝ ተቀብለው ለጉዳዩ የምርመራ ቡድን አዋቀሩ።

የተዋቀረው የወንጀል ምርመራ ቡድን ስራውን ጀመረ።

የአፍዝ አደንግዝ ዘራፊዎቹን ለመቆጣጠር ምርመራውን በመሠል ተጠርጣሪ ታራሚዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ባደረገው ምርመራ ያገኘውን ፍንጭ ተመርኩዞ ባደረገው ኦፕሬሽን ሄለን አበራን አፍዝዘው በቀን የዘረፉትን 5ቱንም ተጠርጣሪዎች ማታውኑ ተከራይተው ከነበሩበት ቤት በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

ጉዳያቸው አሁን ላይ በምርመራ ሂደት ላይ ይገኛል።

ሄለን ለወንጀል ምርመራ ቡድኑ ምስጋናዋን አድርሳለች።

በዚሁ አፍዝ አደንግዝ ሌሎች 23 መሠል ዝርፊያዎች ተፈጽሞብናል በሚል ለወንጀል ምርመራ ቡድኑ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ጉዳያቸውም በምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያን ይህን መረጃ ከድሬዳዋ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
15👍6👏2
"ተስፋችሁ አይሙት/Keep Hope Alive"
🕯ጄሲ ጃክሰን (1941 - 2026)

የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የፖለቲካ መሪ ጄሲ ጃክሰን በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጄሲ ጃክሰን በ1960ዎቹ ከአንጋፋው የሰብአዊ መብት ታጋይ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር በመሆን የጥቁር አሜሪካውያንን መብት ለማስከበር በግንባር ቀደምትነት የታገሉ እና ሲገደሉም አብረዋቸው ከነበሩ የቅርብ ረዳቶቻቸው አንዱ ነበሩ።

ጄሲ ጃክሰን በ1984 እና በ1988 ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር በዲሞክራቲክ ፓርቲ ውስጥ ጠንካራ ዘመቻ በማድረግ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ የፕሬዝዳንት ዕጩ በመሆን በታሪክ ተመዝግበዋል።

ተስፋችሁ አይሙት/Keep Hope Alive በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት ጄሲ ጃክሰን በአሜሪካ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያኖሩ ግለሰብ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ እ.ኤ.አ. በ2020 የአሜሪካ መንግስት ከህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የገንዘብ እርዳታ እገዳ ጄሲ ጃክሰን በጽኑ ተቃውመዋል።

ጃክሰን ለአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደብዳቤ በመጻፍ፣ እገዳው ፍትሃዊ እንዳልሆነና የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ገልጸው ነበር።

"ይህ [የአሜሪካ የእርዳታ እገዳ] ምንም ምክንያት የሌለው ውሳኔ ነው፤ ምክንያቱም 85 በመቶው የዓባይ ወንዝ ውኃ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ነው። ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ ከሌሎች 10 የሰሃራ በታች የአፍሪካ የዓባይ ተፋሰስ አገራት የሚመጣ ነው። ግብፅ ለወንዙ ፍሰት የምታበረክተው አስተዋጽኦ 0 በመቶ ነው። " - ጄሲ ጃክሰን


ጃክሰን የህዳሴ ግድብን በሚመለከት የኢትዮጵያን መብት ከደገፉ ጥቂት ተፅዕኖ ፈጣሪ አሜሪካውያን አንዱ የነበሩ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በግድቡ ዙሪያ ፍትሃዊ አቋም እንዲይዝ አቋም ይዘው ተናግረዋል።

😀  | @tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
10😢2😭1
ገንዘብ ሚኒስቴር ጀኔሬተር እና ትራንስፎርመር ለኢንቨስትመንት በካፒታል ዕቃነት ከቀረጥ ነፃ ከሚገቡት መካከል እንዲሆን ፈቅዷል!

ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ቅድሚያ የተፈቀዱ ካፒታል እቃዎች ዝርዝር ከመመሪያ ቁጥር 1064/2017 (የኢንቨስትመንት ማበረታቻን ለማስፈጸም የወጣ መመሪያ) ሙሉ ሰነዱን ላይ ማንበብ ትችላላች።

Source: The Ethiopian economist view
4👍2
የተከለከለው ትልቅ ትንሽ፤ ወፍራም ስስ ተብሎ ሳይሆን ሁሉም አይነት የፕላስቲክ ከረጢት መሆኑን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ፡፡
***

ባለስልጣኑ ሁሉንም አይነት የከረጢት ፕላስቲክ ይዞ የተገኘ በአዋጅ 1383/2017 መሰረት ከ2000 ብር በማያንስ እና ከ5000 ብር የማይበልጥ ገንዘብ እንደሚቀጣ አሰረድቷል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ በለስልጣን "ህግን እናውቃለን" በማለት የተከለከለው ስስ ፌስታል ብቻ ነው ከሚሉ አሳሳች አካላት ህብረተሰቡ እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ ይህን ያሳሰበው ዛሬ የፕላስቲክ ከረጢትን የሚተካ ከፕላስቲክ ውጭ ከረጢቶችን ከሚያመርቱ አካላት ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ ፕላስቲክ በአገር ኢኮኖሚ፣ጤና እና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እያደረሰ ያለውን ቀውስ አስመልክተው የውይይት መነሻ ጸሁፍ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የህግ ተከባሪነት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ጉደታ በአለም ደረጃ በፕላስቲክም ሆነ በሎሎች ምክንያቶች በሚፈጠር ብክለት ወደ 9 ሚሊዮን ሰዎች ይሞታሉ ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ብቻ ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ ውሳጥ 13 በመቶ የሚሆነው ከፕላስቲክ ቁሶች ነው ሲሉ አቶ ለሜሳ ተናግረዋል፡፡

በዓመት 80ሺህ ቶን ፕላስቲክ ይመረታል ተብሎ ይገመታል የሚሉት የባለስልጣኑ የህግ ተከባሪነት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ጉደታ ከዛ ውስጥ በዑደት ተመልሶ ለአገልግሎት የሚበቃው 5 በመቶው ብቻ ነው ይላሉ፡፡

ቀሪው ለዳግም አገልግሎት አይውልም ብለዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢት ተመልሶ ለአገልግሎት አይውልም ወይንም ሪሳይክል አይሆንም ይህን ተግባር የሚያከናውኑትም አይፈልጉትም ለዚያ ነው የፕላስቲክ ከረጢት የተከለከለው ሲሉ አቶ ለሜሳ አክለዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢት ሲቃጠል አየርን ይበክላል፣ሲጣልም አይበሰብስም ለመሬት አይሆንም ሳይበሰብስ አፈር ውስጥ 100 ዓመት ይቀመጣል ይህን ችግር ለመፍታት የፕላስቲክ ከረጢትን ማምረትም ሆነ መጠቀምን ሙሉ በሙሉ መከልከል አስፈልገዋል ተብሏል፡፡

ህጉን አላግባብ ከሚተረጉሙት ሰዎች እራሳችሁን ጠብቁ ያለው ባለስልጣኑ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል ማለት ስስ ከረጢት ማለት ሳይሆን በሪሳይክል ተመልሶ የማይቀየር ማለት እንደሆነ መታወቅ አለበት ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የትኛውም አይነት ማለትም ስስም ይሁን ወፍራም ትልቅም ይሁን ትንሽ የፕላስቲክ ከረጢትን ያመረተ ከ50 ሺህ ብር የማያንስ እና ከ200 ሺህ ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል፣ይዞ ከተገኘ ደግሞ ከ2000 ብር በማያንስ እና ከ5000 ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል ብሏል። #Sheger
5
የአፍሪካ #አህጉራዊ ነጻ #ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አተገባበር፣ የስምምነቱ መሠረታዊ ዓላማው
#AfCFTA ምንድን ነው?

የአፍሪካ አገራት የራሳቸውን ምርት ያለምንም የቀረጥ መሰናክል እርስ በእርሳቸው እንዲገበያዩ የተፈጠረ ታሪካዊ ስምምነት ነው።
ዓላማው፦ የአፍሪካን ምርቶች ማሳደግ፣ የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠር እና አህጉራዊ የንግድ ተወዳዳሪነትን መጨመር ነው።
የአገራት ብዛት፦ እስካሁን 54 አገራት ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን፣ ይህም በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ የንግድ ቀጠናዎች አንዱ ያደርገዋል።
2. የኢትዮጵያ ተሳትፎና የሕግ ማዕቀፍ
ፊርማ፦ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ መጋቢት 21/2018 በኪጋሊ ፈርማለች።
ማጽደቅ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1124/2011 አጽድቆታል።

ለትግበራው ይረዳ ዘንድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 574/2017 ጸድቋል።
መመሪያ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን በጥቅምት 04/2018 በቁጥር 4/0755/18 ባወጣው ሰርኩላር ትግበራውን በይፋ ጀምሯል።
3. የቀረጥ ቅነሳው እንዴት ይፈጸማል? (የዕቃዎች ምድብ)
ኢትዮጵያ ያቀረበቻቸው የዕቃ ዓይነቶች በሦስት ምድብ ተከፍለዋል፦
ምድብ ሀ (Category A)፦ 90% የሚሆኑ ዕቃዎች (እንደ ቆዳ ጥሬ ዕቃዎች ያሉ)። በ10 ዓመት ውስጥ ቀረጣቸው 0% ይገባል።
ምድብ ለ (Category B)፦ 7% የሚሆኑ ዕቃዎች (እንደ ጫማና ቦርሳ ያሉ ስሱ ምርቶች)። በ 8 ዓመት ውስጥ ቀረጣቸው 0% ይገባል።
ምድብ ሐ (Category C)፦ 3% የሚሆኑ ዕቃዎች (ምንም ዓይነት ቅናሽ የማይደረግላቸው)።
4. የቀረጥ ቅነሳው የጊዜ ሰሌዳ
ምድብ ሀ፦ እ.ኤ.አ ከጥር 2021 ጀምሮ በየዓመቱ እኩል እየቀነሰ ሄዶ በ2030 ሙሉ በሙሉ ነጻ ይሆናል።

ምድብ ለ፦ እ.ኤ.አ ከጥር 2026 ጀምሮ ቅነሳው ተጀምሮ በ8 ዓመታት ውስጥ (እ.ኤ.አ እስከ 2033) ሙሉ በሙሉ ነጻ ይሆናል።

ምርቱ ሙሉ በሙሉ ነጻ በሚሆንበት ዓመት ሱርቻርጅ (Surcharge) እና የሶሻል ዴቨሎፕመንት ሌቪ (Social Development Levy) አብረው ይነሳሉ።

5. ተጠቃሚ የሚሆኑ አባል አገራት (የ24ቱ ዝርዝር)
የቀረጥ ቅናሹ የሚሰራው ስምምነቱን ለሴክሬታሪያቱ አሳውቀው በይፋ በጀመሩት 24 አገራት ላይ ብቻ ነው፦


ምሥራቅ አፍሪካ፦ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን።

ምዕራብ አፍሪካ፦ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ጋምቢያ።

ሰሜን አፍሪካ፦ ግብፅ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ አልጄሪያ።

ደቡብ አፍሪካ፦ ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና Namibia፣ ዛምቢያ፣ ማላዊ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሶቶ።

ሌሎች፦ ሞሪሸስ፣ ሲሸልስ፣ ሞዛምቢክ።


6. ለቆዳ ዘርፍ SMEs የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
የአገር በቀል ምርት ምስክር ወረቀት (Certificate of Origin)፦ ምርቱ "በኢትዮጵያ የተመረተ" መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ከጉምሩክ ኮሚሽን ማግኘት ግዴታ ነው።
የታሪፍ ኮድ (HS Code)፦ ምርትዎ በየትኛው የምድብ ኮድ ውስጥ እንደሚወድቅ ማረጋገጥ።
የንግድ ሰነዶች፦ የንግድ ደረሰኝ (Invoice)፣ የይዘት ዝርዝር (Packing List) እና የጽሑፍ ውል ማዘጋጀት።

7. ተቋማዊ ኃላፊነቶች
ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፦ አገራቱን የመለየትና የንግድ ድርድሩን የመምራት ኃላፊነት።
ጉምሩክ ኮሚሽን፦ የምስክር ወረቀት የመስጠት፣ የዕቃዎችን አመዳደብ የመቆጣጠርና ቀረጡን የመቀነስ ኃላፊነት።
ገንዘብ ሚኒስቴር፦ የቀረጥ መጠኑን በየዓመቱ የማሳወቅና የማስተካከል ኃላፊነት።

8. የሂደት ቅደም ተከተል (Step-by-Step Approach)
ምርትዎን ይለዩ፦ የትኛውን የቆዳ ውጤት (ጫማ፣ ቦርሳ ወዘተ) ለመላክ እንደፈለጉ መወሰን።
ገበያ ይምረጡ፦ ከላይ ከተጠቀሱት 24 አገራት ውስጥ የተሻለ ገበያ ያለውን መምረጥ።
የአገር በቀል ምስክር ወረቀት ይውሰዱ፦ ምርቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ከጉምሩክ ያረጋግጡ።
ገዢ ያግኙ፦ የዲጂታል መሣሪያዎችን (WhatsApp, Email) በመጠቀም ከውጭ ገዢዎች ጋር ይደራደሩ።
ጭነት ይጀምሩ፦ በደንብ ቁጥር 574/2017 መሠረት የቀረጥ ቅናሹን ተጠቅመው ምርትዎን ይላኩ።
ይህ ስምምነት ለቆዳ ዘርፍ አምራቾች አዲስና ሰፊ በር የከፈተ በመሆኑ፣ አምራቾች የጥራት ደረጃቸውን በማሻሻልና ሕጋዊ ሰነዶችን በማሟላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመከራል።
ስልጠናው በጠበቃና የሕግ አማካሪ Mikias Melak ተሰጠ🙏 #ሚኪያስ_መላክ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
9👍4