ብዙዎች ህግ የለም ብለው በደመነፍስ ሲመሩ፣ እኔ ግን በዚያው ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆኖ የሚታየውን ሕግ መኖሩን ለማሳየት #እየሞከርኩ ነው።በብዙዎች ዘንድ #ሕግ የለም" የሚል ተስፋ መቁረጥ በነገሰበት፣ ገንዘብ ካለህ ሕግ አያስፈልግህም የሚል የተሳሳተ ብሂል በሰፈነበት ሁኔታ ውስጥ ቆሜ፣ እኔ ግን አንድ እውነትን ለማረጋገጥ ደጋግሜ እተጋለሁ። አዎ፣ #እየሞከርኩ ነው‼️
አለሕግ እና ሕግ አለ✅
ብዙዎች ህግ የለም ብለው በደመነፍስ ሲመሩ፣ እኔ ግን በዚያው ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆኖ የሚታየውን ሕግ መኖሩን ለማሳየት #እየሞከርኩ ነው።
ሕግ መኖሩ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ሕጉ ለሁሉም እኩል መሆኑን እና ማንም ከሕግ በላይ አለመሆኑን በተግባር ለማሳየት የፍትህ ስርዓቱ ላይ የራሴን አሻራ ለማሳረፍ እተጋለሁ። ይህ ጥረቴ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገሬ መፃኢ እድል እና ለልጆቻችን የሚተርፍ የፍትህ መሠረት ለመጣል ነው።
ሕግ መኖሩን እያወቁ፣ ነገር ግን እንደሌለ በማስመሰል የሰውን ንብረትና ሀብት ለዘረፉ፣ "ሕግ አለ!" ብዬ ፊት ለፊት እጋፈጣቸዋለሁ። የኔ ሙከራ እንደ አንድ ተራ ጠበቃ የሙያ ግዴታን መወጣት ብቻ አይደለም።
እኔ እየሞከርኩ ያለሁት፦
✔️ ለተገፉት ድምፅ ለመሆን፣
✔️ለተካዱት እውነትን ለማውጣት፣
✔️ ለተጭበረበሩት መብታቸውን ለማስከበር ነው።
የእነሱ ህመም ህመሜ፣ ስብራታቸው ስብራቴ ሆኖ ከጎናቸው እቆማለሁ። የተሰበረውን ፍትህ ለመጠገን እኔው ራሴ ተሰብሬም ቢሆን የቆሙለትን ዓላማ ዳር ለማድረስ እጥራለሁ።
በዚህ ሂደት ውስጥ መረጃ የፍትህ ዋስትና መሆኑን ለማስረፅ እሰራለሁ። ያለ መረጃ የሚጮህ ድምፅ ሰሚ እንደማያገኝ አውቃለሁና፣ እውነትን በመረጃ ደግፌ ለማቅረብ እና እያንዳንዱ የፍትህ ሂደት በስርዓትና በሕግ እንዲመራ ለማሳመን ሌት ተቀን #እየሞከርኩ ነው።
አዎ፣ ዛሬም ነገም #እየሞከርኩ ነው! #አለሕግ የሚለውን ድምፅ በ "ሕግ አለ" ለመተካት፣ በሀገሬ ላይ የሕግ የበላይነት እንዲነግስ እንደ አንድ ዜጋ የድርሻዬን እወጣለሁ። ግፍና መካድ በጊዜያዊነት ቢያሸንፉም፣ በመጨረሻ ግን ሕግና ስርዓት ማሸነፋቸው አይቀሬ ነው።
አዎ! ሕግ አለ!! ‼️🙏
#እየሞከርኩ ነው ‼️✅🙏✍️✍️✍️
#ሚኪያስ_መላክ
#Mikias_Melak
በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና ህግ አማካሪ
https://t.me/AleHig
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_እውቀት #የሕግ_መረጃ
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
alehig.com
❤47👍14👏5🙏3🖕1
ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 236212
ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁጥር 50835 “በአንድ መዝገብ ላይ የተሠጠ ውሳኔ ከተፈፀመ በኋላም ቢሆን በውሳኔው መብቱ የተነካበት 3ኛ ወገን በሌላ መዝገብ ላይ ክስ አቅርቦ መብቱን ማስከበር ይችላል “ በሚል እንዲሁም
በሰ/መ/ ቁጥር 67127 “በፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል የሚል ሰው በዚያው መዝገብ ላይ የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ መብቱን ማስከበር ከሚችል በቀር ዉሳኔዉ በአፈጻጸሙ ከተቋጨ በኋላ በሌላ መዝገብ ላይ አዲስ ክስ ማቅረብ አይችልም፤ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የቀረበ ክስ ተቀብሎ ውሳኔ መስጠትም መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነው” በሚል የተሰጡት አስገዳጅ ውሳኔዎች ተሻሽለዋል፡፡
ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት በመዝገብ ቁጥር 236212፡
“አንድ ሰዉ መብቱን የሚነካ ዉሳኔ የተፈጸመ እንደሆነ አዲስ ክስ በማቅረብ መብቱን ማስከበር የሚችለዉ፣ ከአቅም በላይ ወይም በቂ በሆነ ምክንያት ዉሳኔዉ ከመፈጸሙ በፊት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ስለመኖሩ ማወቅ ባለመቻሉ ወይም በተመሳሳይ ምክንያት መቃወሚያ ማቅረብ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው” ተብሎ ተሻሽሎ ተተርጉሟል፡፡
የውሳኔውን ሙሉ ይዘት በቴሌግራም ቻናላችን እንደሚከተለው አያይዘናል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጅያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

❤23👍2
የDNA ምርመራ ወጪን ማን መክፈል አለበት?
"እናትነት እውነት፤ አባትነት እምነት።"
ታኅሳሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
#አንድን ወንድ ለአንድ ሕጻን አባቱ ነው ተብሎ ይወሰንልኝ በማለት በፍርድ ቤት ውሳኔ ለማሰጠት በማያሻማ ሁኔታ ወንድየው ለሕጻኑ አባት መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
#በትዳር ወይም ሳይጋቡ እንደባልና ሚስት በመኖር ግንኙነት ውስጥ ለሚወለዱ ልጆች ሕጉ ባልየው አባት ነው ተብሎ የሕግ ግምት እንደሚወሰድ ደንግጓል። የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 126 እና 130 /1/ን ይመለከቷል።
#የአባትነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ ብዙውን ጊዜ አከራካሪ የሚሆነው ከትዳር ወይም ሳይጋቡ እንደባልና ሚስት ከመኖር ግንኙነት ውጪ ለሚወለዱ ሕጻናት ነው።
የምርመራውን ወጪ ማን መሸፈን አለበት?
#በፍርድ ቤት ክርክር በየትኛውም አግባብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲቀርብለት የጠየቀውን ለማስረጃ ለማስቀረብ የጠየቀ ወገን ወጪን መሸፈን እንዳለበት ግልጽ ነው።
#በመሆኑም የDNA Test /የዘረመል ምርመራ/ እንዲደረግለት የጠየቀ ወገን ለምርመራው የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹

❤11👍6
ነገር ግን እነዚህን የወራሹን ጥፋቶች ሟች ግልጽ በሆነ ጽሑፍ ይቅርታ ያደረለገት እንደሆነ ከውርስ መነቀሉ ይቀርልታል።
#ሟች ተወላጅ ልጁን ከውርስ ለመንቀል የሚፈልግ ቢሆን በኑዛዜው ላይ በምን ምክንያት እንደነቀለው በግልጽ ማመላከት እንዳለበት በፍትሐ ብሔር ሕጉ ቁጥር 938 /1/ ላይ ላይ “ተናዛዡ ከርስት ከውርስ ለመንቀል የደረሰበትን ምክንያት በኑዛዜው ውስጥ ካልገለጸ በቀር ልጁን ወይም ወደ ታች የሚቈጠር ተወላጁን ከውርስ ቢነቅል አይጸናም።” በማለት ይደነግጋል።
#ሟች ተወልጃ ልጁን ከውርስ ለመንቀል የሚችልባቸው ምክንያቶች ምን ምን እንደሆኑ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 838 ላይ በግልጽ ተመልክተዋል። እነሱም፦
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 838 ያልተገባ ስለ መሆን (1) ወንጀሎች ወይም ቅጣቶች
#ሟቹን ለመውረስ የማይገባ ነው ተብሎ የወራሽነትን መብት የሚያጣው
1️⃣ሟቹን ወይም የሟቹን ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጅ ወይም ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች አንዱን ወይም የሟቹን ባል ወይም ሚስት አስቦ በመግደል የተፈረደበት።
2️⃣ከነዚሁ ሰዎች መካከል አንደኛውን ለመግደል በመሞከር የተቀጣ።
3️⃣በሐሰት በወንጀል ወይም በሐሰት ምስክርነት ይህ በሐሰት መወንጀል በሐሰት መመስከር ከነዚሁ ሰዎች መካከል በአንደኛው ላይ የሞት ፍርድ ወይም ከአስር ዓመት የበለጠ የጽኑ እስራት ቅጣትን ለማስተካከል የሚያሰጋ ሁኖ የተቀጣ ማኛውም ሰው ነው።
በሁሉም ምክንያቶች ወራሹ በወንጀል ተከሶ ቅጣት የተጣለበት መሆን አለበት።
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 840 (3) ሌሎች ምክንያቶች
#በተለይ ሟቹን ለመውረስ የማይገባ ነው ተብሎ
ሀ. የሟቹን ሰውነት ሁኔታ ምክንያት በማድረግ አውራሹ ከመሞቱ በፊት በአሉት በሦስት ወር ውስጥ ኑዛዜ እንዲያደርግ እንዳይለውጥ ወይም እንዳይሽር የከለከለ።
ለ. አስቦ ያለሟቹ ፈቃድ የሟቹን የመጨረሻ ኑዛዜ ያበላሸ እንይገኝ ያደረገ ያጠፋ ወይም ጉዳዩን በማወቅ በሐሰት ኑዛዜ የተጠቀመ የወራሽነት መብት ያጣል።

❤15👎2
👉በአንድ ንብረት ላይ ንብረቱ በማንኛውም መልኩ ወደ ሌላ ሰው እንዳይተላለፍ የእግድ ትዕዛዝ በፍርድ ቤት የሚሰጠው በክርክር ሂደት ረቺ የሚሆነው ወገን ለፍርድ አፈፃፀም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲያስችለው
ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 154 እና ተከታታይ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡
👉በዚህ አግባብ በፍርድ ቤት የሚሰጠው የዕግድ ትዕዛዝም በየትኛውም አካል ሊከበር ይገባል፡፡
👉በሌላ በኩል ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት
የተሰጠ ፍርድ ሊፈፀም የሚችለው በፍርድ ባለዕዳውና በሕግ አግባብ እንዳይያዙ ከሚጠቀሱት ንብረቶች ውጪ ባሉት ንብረቶች/መብቶች ላይ ስለመሆኑ በቁጥር 378 እና ተከታዩቹ የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡
👉 አንድ ሰው በሕግ አግባብ ለሌላ ሰው ሊያስተላልፍ የሚችለው መብትም በህግ
አግባብ ገደብ ያልተደረገበትንና ያለውን ንብረት ወይም መብት ስለመሆኑ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም፡
👉በሌላ በኩል የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ኔት ከፍርድ ቤት የተሰጠ የዕግድ ትዕዛዝ እያለ በተዋዋይ ወገኖች የተፈጸመውን የሽያጭ ውል ከመነሻውም ቢሆን ውጤት አልባ የሆነውን ውል የመዘገበ በመሆኑ ውልን መሠረት በማድረግ የሚጠይቅ መብት ተፈጸሚ ሊሆን አይችልም፡፡
👉የሰ.መ.ቁ. 206060 ሕዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም

❤8👍2
የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ የተደረገው ማሻሻያ ምንድነው?
- ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ መግለጫ
***
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሟላ የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርም መደረግ ከጀመረበት ሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ፤ የውጭ ምንዛሬ ገበያን ለማጎልበት የሚያስችሉ የተለያዩ የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያዎችን ሲያደርግ ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅትም የውጭ ምንዛሬ ገበያን የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ በውጭ ምንዛሬ መመሪያ ላይ የሚከተሉትን ማሻሻያዎች ማድረጉን ያሳውቃል።
1. የአገልግሎት ላኪዎች ከወጪ ንግድ የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ በሪቴንሽን ሂሳባቸው ያለ ምንም የጊዜ ገደብ እንዲይዙ ተፈቅዷል።
2. ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ ላላቸው ደንበኞቻቸው ለውጭ ሀገር ክፍያ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ጨምሮ የሚያገለግል ዓለምአቀፍ ካርድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ተፈቅዷል።
3. ማንኛውም የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ ያለው የባንክ ደንበኛ ህጋዊ ሰነዱን ሂሳብ ለከፈተበት ባንክ በማቅረብ፤ የውጭ ምንዛሬ ሂሳቡን በመጠቀም ለትዳር አጋርና ለልጆቹ የትምህርት፣ የህክምናና የጉዞ ወጪ ክፍያ ማድረግ ይችላል።
4. ማንኛውም ለትርፍ የተቋቋመ ድርጅት የውጭ ምንዛሬ ምንጩ ከወጪ ንግድ የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ ሳይጨምር በዕርዳታ/ስጦታ ወይም ከሌላ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ የተገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ የተንቀሳቃሽ፣ የቁጠባና የጊዜ ገደብ የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ መክፈት ይችላል።
5. ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የውጭ ምንዛሬ የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ይጠየቁ የነበረው አነስተኛ 100 የአሜሪካ ዶላር እንዲቀር ተደርጓል።
6. ድርጅቶች የመቀነስ ካፒታላቸውን ሁኔታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስመዝግበው ከሀገር ውጭ በሌላ ሀገር መቀነስ ካፒታላቸውን ፈሰስ ማድረግ እንዲችሉ ተፈቅዷል።
7. ማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ ወደ ሀገር ይዞ የተመለሰውን የትኛውንም ያህል መጠን ያለው የውጭ ምንዛሬ ያለ ጉምሩክ ሰነድ በባንኮችና ህጋዊ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ቢሮዎች በኩል ወደ ብር መመንዘር ወይም ወደ የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ በማስገባት ተቀማጭ ማድረግ ይችላል።
8. ኢትዮጵያውያን ህጋዊ ሰነድ ለባንክ በማቅረብ መጠኑ ከ3,000 የአሜሪካ ዶላር ያልበለጠ የውጭ ምንዛሬ ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ዘመዶቻቸው እገዛ እንዲውል ከሀገር ወደ ውጭ ማስተላለፍ የሚችሉበት ሥርዓት ተፈቅዷል።
9. ባንኮች የፎርዋርድ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ ማካሄድ እንዲችሉ ተፈቅዷል።
10. የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስተሮች፣ ኤምባሲዎችና በሀገር ውስጥ የሚሰሩ ዓለምአቀፍ ተቋማት የተራድኦ ድርጅቶችን ጨምሮ ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ በባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ።
11. ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚያመጡት የውጭ ብድር (በገንዘብና በዓይነት) እና የሰፕላየር ብድርን የማጽደቅ ሥራ የውጭ ምንዛሬ መመሪያ መስፈርቶችን በተከተለ መልኩ ሙሉ በሙሉ በባንኮች እንዲከናወን ተፈቅዷል።
12. ማንኛውም በወጪ ንግድ ላይ የተሰማራ ላኪ ድርጅት ከማንኛውም የውጭ አካል የቅድመ ክፍያ ስምምነት ላይ በመድረስ እና በሁለቱ ወገኖች የተደረገውን የስምምነት ሰነድ ለላኪው ድርጅት ደንበኛ ባንክ በማቅረብ የቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላል።
13. በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለወደፊት የወጪ ንግድ ክፍያ እንደ ቅድመ ክፍያ የሚቆጠረው (ሀ) ስምምነቱ ገዢውን ለማመልከት ታስቦ “ቅድመ ክፍያው ለወደፊት ወጪ ወይም ገቢ ንግድ የሚውል” ወደ (ለ) ወደፊት ወደ ውጭ የሚላኩ ሸቀጦችን ዘርዝሮ ወይም የደረሰኝ ቁጥሩ ከተጠቀሰ ወይም የግብይት የውል ስምምነት ሰነድ ቁጥር በሚላከው የውጭ ምንዛሬ ደረሰኝ ላይ ከተጠቀሰ ይሆናል።
14. ባንኮች ከካፒታላቸው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ለግሉ ዘርፍ የውጭ ሀገር ብድር ዋስትና መስጠት እንዲችሉ ተፈቅዷል።
15. ባንኮች የውጭ ተቋም በሚሰጠው የማረጋገጫ ደብዳቤ እና ደንበኛው በሚያቀርበው ጥያቄ ላይ በመመስረት በአንድ ጉዳይ እስከ 20,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም ከተመጣጣኝ የሌላ ሀገር ገንዘብ ያልበለጠ የውጭ ምንዛሬ ለህክምናና ለትምህርት ያለ ቢዛ እና የአውሮፕላን ትኬት ቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላሉ።
16. ያለምንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን ሰነድ ለባንካቸው በማቅረብ እንዲሁም ባንኮች በመመሪያው መሰረት የቀረበው ሰነድ መሟላቱን በማረጋገጥ በትርፍ ክፍፍል መልክ ያገኙትን የውጭ ምንዛሬ ከሀገር ማስወጣት እንዲችሉ ተፈቅዷል።
17. የውጭ ምንዛሬ ግብይት ቢሮዎችን የገንዘብ ፍላጎት ካፒታል የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፈቃድ አሰጣጥ ወቅት የሚያዘው ተቀማጭ ገንዘብ፤ (አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ በሥራ ላይ ለሆኑ ቢሮዎች 30 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ቢያንስ ስድስት ወራት በሥራ ላይ ላሉ ቢሮዎች 15 ሚሊዮን ብር) ተመላሽ ያደርጋል።
18. የውጭ ምንዛሬ ግብይት ቢሮዎች በእጃቸው የሚይዙት ጥሬ የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ ቀደም ሲል ከነበረው የካፒታላቸው 10 በመቶ ወደ 25 በመቶ ተሻሽሏል። ከዚህ በላይ የሆነ ትርፍ የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ ለባንኮች መሸጥ አለባቸው።
19. ሁሉም የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች አስፈላጊውን ሰነድ በመጠየቅ ለቪዛ፣ ለፓስፖርትና ለፈቃድ እድሳት ጥሬ የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል።
#EBC

❤8
የፌዴራል_የመጀመሪያ_ደረጃ_ፍርድ_ቤት_የንግድ_ችሎቶች_ሥርዓተ_ችሎት.pdf
3.7 MB
Federal First Instance Court Commercial Bench Proceedings Code
❤2
ለጋብቻ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና ሰርተፊኬት መያዝ ግድ ሊሆን ነው ተባለ።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ ፣ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና ሰርተፊኬት ሳይዝ ማንም ሰው ወደ ጋብቻ እንዳይገባ የሚያደርግ አሰራር ሊጀምር መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ተናግሯል።
ይህንን አሰራር በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት መደረጉን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሸገር ኤፍ ኤም ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጄንሲ በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት የትዳር ፍቺ ከአለፉት አመታት አንፃር 54 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethmagazine

👏8❤4
DIRECTIVE-NO.-FXD042026.pdf
976.9 KB
Foreign Exchange Directive No. FXD/04/2026
Ethiopia’s FX Liberalization: What Changes, Who Benefits, and What to Watch✍️
የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ የተደረገው ማሻሻያ 🙏
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
Ethiopia’s FX Liberalization: What Changes, Who Benefits, and What to Watch✍️
የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ የተደረገው ማሻሻያ 🙏
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
❤6
ፍትህ ከሕግ በላይ ነው
ፍትህ ሲባል ብዙዎቻችን ወደ ፍርድ ቤትና ወደ ሕግ መጻሕፍት እናመራለን። ነገር ግን በጥንታውያን ስቶይኮች እይታ ፍትህ (Dikaiosyne) ከዚህ እጅግ የሰፋ ትርጉም አለው። ፍትህ ማለት ለእያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ክብር መስጠት እና ለሰው ልጆች ሁሉ አንድነትና ደኅንነት መሥራት ማለት ነው። ይህ እሴት እኛን ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚያስተሳስረን ብቸኛው የሞራል ሰንሰለት ነው።
በስቶይክ ፍልስፍና ፍትህ በአራት ዋና ዋና መርሆች ላይ ይቆማል፦
1. ማኅበራዊ አንድነት፦ ከልዩነት በላይ የሆነ ሰውነት
ስቶይኮች ሁላችንም የአንድ ትልቅ ዓለማቀፋዊ ማኅበረሰብ አካል ነን ብለው ያምናሉ። ፍትህ የሚጀምረው ሰዎችን በዘር፣ በቋንቋ ወይም በደረጃ ሳይሆን በሰውነታቸው ብቻ ክብር ስንሰጥ ነው።
ልምምዱ፦ ማንኛውንም ሰው ስናገኝ፣ ጥበቃውንም ይሁን ሥራ አስኪያጁን፣ በእኩል ትህትና እና አክብሮት ማነጋገር የፍትሃዊነት መጀመሪያ ነው።
2. ቅንነት እና ታማኝነት፦ ማንም በማያይበት ቦታ ትክክለኛ መሆን
ፍትህ ማለት ማንም በማያይህ ቦታ እንኳን ሳይቀር ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ነው። ለገቡት ቃል ታማኝ መሆን እና በስራም ሆነ በግል ግንኙነት ሰውን አለማታለል የፍትሃዊ ሰው መታወቂያ ነው። ሁልጊዜም "ይህ ተግባሬ ለሌላው ሰው ጥቅም ይኖረዋል ወይስ ጉዳት?" ብሎ መጠየቅን ይጠይቃል።
3. የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፦
ፍትህ ማለት ከመጥፎ ነገር መራቅ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ለጋራ ደኅንነት በጎ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው። ያለንን እውቀት፣ ጊዜ ወይም ገንዘብ ለሌሎች ማካፈል የፍትህ አካል ነው። በቀን ቢያንስ ለአንድ ሰው የሚሆን ትንሽ መልካም ነገር ማድረግ የዓለምን የፍትህ ሚዛን ይጠብቃል።
4. ደግነት፦ የፍትህ ለስላሳው ገጽታ
በስቶይክ ፍልስፍና ደግነት የፍትህ አንዱ ዘርፍ ነው። ፍትሃዊ ሰው ለሌሎች ስህተት ይቅር ባይ ነው፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው እንደ እውቀቱ መጠን እንደሚንቀሳቀስ ይረዳልና። የፍትህ ዓላማ በዙሪያችን ያሉትን የሰዎች ክበቦች ወደ ውስጥ በማምጣት፣ መላው የሰው ልጅ እንደ ቤተሰብ እንዲሰማን ማድረግ ነው።
እነዚህን አራት ታላላቅ እሴቶች በአንድ ላይ ስናያቸው የሕይወት መሪ መመሪያዎቻችን ይሆናሉ።
"ፍትህ ማለት 'ማንም በማያይህ ቦታ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ነው' የሚለው ስቶይካዊ መርህ ዛሬ ላይ በስራም ሆነ በማኅበራዊ ሕይወታችን ምን ያህል እየተገበርነው ነው?
#ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

❤12👍9🥰1👏1