አለ ሕግ
15.9K subscribers
3.31K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ማስታወቂያ

ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህግ ጉዳዮች ጸሃፊ I እና የህግ ጉዳዮች ጸሃፊ II የፅሁፍ ፈተና ወስዳችሁ ለቃል ፈተና የተመረጣችሁ ስማችሁ በዚህ ዝርዝር የተጠቀሰው ለህግ ጉዳዮች ጸሃፊ I ጠዋት 2:30 እንዲሁም ለህግ ጉዳዮች ጸሃፊ II ከሰዓት 7:30 ማክሰኞ ቀን 26/05/2018 ዓ.ም ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ለቃል ፈተና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
8
የንብረት ህግ.pdf
579.8 KB
የንብረት ሕግ ማብራሪያ
Vacancy Announcement.pdf
482.6 KB
📢 The Ethiopian Lawyers Association (ELA)
5👍3
EFAA INVITATION FOR EXPRESSION OF INTEREST.docx
21.7 KB
EFAA Invitation for Expression of Interest – Baseline Financial & Compliance Audit
The Ethiopian Federal Advocates Association (EFAA) invites qualified and licensed audit firms to submit their Expression of Interest to conduct a Baseline Financial and Compliance Audit of the Association.
📅 Submission Deadline: February 8, 2026 (5:30 PM)
📧 Submission Email: info@efaa.et
🔗 Full details available in the attached Invitation Document.
EFAA encourages eligible firms to apply.
8
3
1
#በሰበር መዝገብ ቁጥር 236212 የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358 በተመለከተ በሰበር ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የህግ ትርጉም
#ሰበር መዝገብ ቁጥር፦ 236212
#ቀን፦ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም
#ዳኞች፦ ቴዎድሮስ ምህረት፣ ብርሃኑ አመነው፣ ገበየሁ ፈለቀ፣ ተሾመ ሽፈራው፣ ደረጀ አያና፣ ደጀኔ አያንሳ እና ብርቅነሽ እሱባለው (ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት ሙሉ ችሎት)
#አመልካቾች፦ 1ኛ. ወ/ሮ ዘምዘም መሐመድ፣ 2ኛ. አቶ ፍቃዱ ዳባ
#ተጠሪዎች፦ 1ኛ. አቶ ሙሉጌታ ደጀኑ፣ 2ኛ. ወ/ሮ እህተማሪያም በዛብህ
የጉዳዩ አመጣጥ
የክርክሩ መነሻ በቀድሞው ወረዳ 23 ቀበሌ 15 ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 033 የሆነ ቤት ነው። ጉዳዩ በተለያዩ መዛግብት ላይ የተካሄዱ ክርክሮችን ውጤት የሚመለከት ነው፦
#በመ/ቁ. 00867 ላይ በተደረገ ክርክር ቤቱ ለተጠሪዎች እንዲረከቡ ተወስኖ ነበር።
#በሌላ በኩል፣ በመ/ቁ. 68979 ላይ በተደረገ ክርክር 2ኛ አመልካች ቤቱን እንዲረከብ ተወስኖ በአፈጻጸም ተረክቧል።
#ተጠሪዎች 2ኛ አመልካች ቤቱን የተረከበበት የውሳኔ መዝገብ (መ/ቁ. 68979) እንዲሰረዝላቸው አዲስ ክስ አቅርበዋል።
#የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መጀመሪያ ላይ "በሌላ መዝገብ ላይ የተሰጠ ውሳኔ እንዲሰረዝ የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የለውም" በማለት ውድቅ ቢያደርገውም፣ ጉዳዩ በሰበር መዝገብ ቁጥር 104920 ታይቶ ወደ ስር ፍርድ ቤት እንዲመለስ ተደርጓል።
#በመጨረሻም የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በመ/ቁ. 00867 መብታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ፣ አመልካቾች ቤቱን እንዲያስረክቡ ወስኗል። ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ቢሽረውም፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽንቷል።
#የሰበር ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም
"አንድ ሰው መብቱን የሚነካ ውሳኔ ከተፈጸመ በኋላ አዲስ ክስ በማቅረብ መብቱን ማስከበር የሚችለው፣ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በቂ እና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ ውሳኔው ከመፈጸሙ በፊት መብቱን የሚነካ ውሳኔ ስለመኖሩ ማወቅ ባለመቻሉ የመቃወም አቤቱታ (በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት) ማቅረብ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።"
ይህ የሕግ ትርጉም የሚከተሉትን ዝርዝር ነጥቦች ያካትታል፦
1. ሶስተኛ ወገን መብቱን ለመከላከል ያለው ዋናው መንገድ ውሳኔው ከመፈጸሙ በፊት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ ማቅረብ ነው።
2. ውሳኔው መብቱን እንደሚነካ እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው በቸልተኝነት ሳይጠቀምበት ቀርቶ፣ ውሳኔው ከተፈጸመ በኋላ አዲስ ክስ ማቅረብ አይቻልም።
3. አዲስ ክስ ለማቅረብ ውሳኔው ከመፈጸሙ በፊት መቃወሚያውን ለማቅረብ ያልቻለበትን "አሳማኝ ምክንያት" ወይም "ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ" የማስረዳት ግዴታ አለበት።
ችሎቱ ይህንን የሕግ ትርጉም ለመስጠት የተገደደው ቀደም ብለው በሰበር ሰሚ ችሎት ይሰጡ በነበሩ ውሳኔዎች መካከል የነበረውን ግልጽ ቅራኔ ለመፍታት ነው።
#የቀድሞው የመጀመሪያ አቋም (ሰ/መ/ቁ. 50835)፦ አንድ ውሳኔ ከተፈጸመ በኋላም ቢሆን በውሳኔው መብቱ የተነካበት ሦስተኛ ወገን በሌላ መዝገብ አዲስ ክስ አቅርቦ መብቱን ማስከበር ይችላል የሚል ነበር።
#የቀድሞው ሁለተኛ አቋም (ሰ/መ/ቁ. 67127)፦ አንድ ሰው መብቱን የሚነካ ውሳኔ መኖሩን ሲያውቅ በዚያው መዝገብ ላይ የመቃወም አቤቱታ (በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት) ማቅረብ ከሚችል በቀር፣ ውሳኔው በአፈጻጸም ከተጠናቀቀ በኋላ አዲስ ክስ ማቅረብ አይችልም የሚል ነበር።
#ችሎቱ መሠረት ያደረጋቸው የሕግ መርሆዎች
ችሎቱ መፍትሔ የሰጠው መሰረታዊ ጭብጥ "በአንድ መዝገብ በተሰጠ ውሳኔ መብቴ ተነክቷል የሚል ሦስተኛ ወገን፣ ውሳኔው ከተፈጸመ በኋላ በሌላ መዝገብ አዲስ ክስ ማቅረብ ይችላል ወይ?" የሚለውን ነው። ችሎቱ ለውሳኔው የሚከተሉትን ነጥቦች በምክንያትነት ጠቅሷል፦
#የውሳኔዎች አስገዳጅነት ወሰን
እንደ አጠቃላይ መርህ፣ ፍርድ ውጤት የሚኖረው በተከራካሪ ወገኖች ላይ ብቻ ነው (Res inter alios judicata)። በኢትዮጵያ ሕግም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 መሠረት አንድ ውሳኔ መቃወሚያ የሚሆነው ተከራካሪዎቹ አንድ ሲሆኑ ነው።
#ፍትሕ የማግኘት መብት እና ሥነ ሥርዓታዊ ውጤታማነት
ችሎቱ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 37(1) የተደነገገውን ፍትሕ የማግኘት መብት እና የሥነ ሥርዓት ሕጉን ወጪና ጊዜ ቆጣቢነት መርሆዎችን አገናዝቧል። ሰዎች በቂ ማስታወቂያ ሳይሰጣቸው እና ሳይሰሙ በመብታቸው ላይ የተሰጠ ውሳኔ እንዲገደዱ ማድረግ ፍትሐዊ አይደለም።
#የሕጉ ክፍተት እና አማራጭ መፍትሔዎች
የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 ሦስተኛ ወገን ውሳኔው ከመፈጸሙ በፊት የመቃወም አቤቱታ እንዲያቀርብ ቢፈቅድም፣ ውሳኔው ከተፈጸመ በኋላ ያለውን ሁኔታ በግልጽ አይደነግግም።
#አዲስ ክስ የማቅረቢያ ቅድመ ሁኔታ
አንድ ሰው መብቱን የሚነካ ውሳኔ ስለመኖሩ በቸልተኝነት ሳይሆን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በቂ በሆነ ሁኔታ ሳያውቅ ቀርቶ ውሳኔው ከተፈጸመ፣ አዲስ ክስ ማቅረብን መከልከል ፍትሕ የማግኘት መብትን ይጥሳል። ሆኖም ይህ መብት ያልተገደበ ሳይሆን በበቂ ምክንያት ውሳኔውን ማወቅ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ የሚፈቀድ ነው።
#የችሎቱ ውሳኔ
#በሰ/መ/ቁጥር 50835 እና በሰ/መ/ቁጥር 67127 ላይ የተሰጡት ተቃራኒ አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች ተሻሽለዋል።
#አንድ ሰው መብቱን የሚነካ ውሳኔ ከተፈጸመ በኋላ አዲስ ክስ ማቅረብ የሚችለው፣ ከአቅም በላይ በሆነ ወይም በቂ በሆነ ምክንያት ውሳኔው ከመፈጸሙ በፊት መብቱን የሚነካ ውሳኔ መኖሩን ማወቅ ባለመቻሉ የመቃወም አቤቱታ (በቁጥር 358 መሠረት) ማቅረብ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
#ጉዳዩን በመሰረታዊነት እንዲወስን መዝገቡ አምስት ዳኞች ወደሚሰየሙበት ችሎት ተመልሷል።
#የተጠቀሱ የሕግ ድንጋጌዎች እና የሰበር ውሳኔዎች
#የሕግ ድንጋጌዎች
የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 37(1)፤ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 5፣ 5(4)፣ 36፣ 40(2)፣ 41፣ 43፣ 358፣ 360(2)፣ 418፣ 421፣ 455፤ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 27(1/2)።
#የተሻሻሉ/የተለወጡ የቀድሞ የሰበር ውሳኔዎች፦
#ሰ/መ/ቁ. 50835 (ቅጽ 12)፦ "ውሳኔ ከተፈጸመ በኋላም ሦስተኛ ወገን አዲስ ክስ ማቅረብ ይችላል" የሚል አቋም የነበረው።
#ሰ/መ/ቁ. 67127 (ቅጽ 13)፦ "ውሳኔ ከተፈጸመ በኋላ አዲስ ክስ ማቅረብ አይቻልም" የሚል አቋም የነበረው።
#ሌሎች የተጠቀሱ መዛግብት፦ ሰ/መ/ቁ. 122926፣ 104920፣ 56795፣ 40229፣ 93998፣ 181236፣ 210077፣ 53607
በጠበቃ እና የሕግ አማካሪ አብርሀም ዮሀንስ
30
ኬንያ በወር ከ30 ሺህ ሽልንግ በታች የሚያገኙ ዜጎቿን ከገቢ ግብር ነፃ ልታደርግ ነው።

የኬንያ የገንዘብና የኢኮኖሚ እቅድ ሚኒስትር ጆን ምባዲ በወር ከ30 ሺህ የኬንያ ሽልንግ (36ሺ ገደማ) በታች የሚያገኙ ዜጎች ከገቢያቸው ከሚከፍሉት ግብር ነፃ እንደሚደረጉ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በኬንያ ከሚከፍሉት ግብር ነፃ የነበሩት ከ24ሺ ሽልንግ በታች የነበሩት ነበሩ። አሁን ይህንን ጣሪያ ወደ 30 ሺ ለማሳደግ ነው በመንግሥት በኩል እቅድ የተያዘው።

ሚኒስትሩ ከገቢ ግብር ነፃ የማድረጉ ሃሳብ ከፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መምጣቱን ገልጸው ከግብሩ ነፃ ማድረጉ ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኙ ሰዎችን ጫና ያቃልላል በማለት እነዚህ ሰዎች ደመወዛቸውን ለመሰረታዊ አገልግሎቶች ካወጡት በኋላ ለቁጠባ የሚቀራቸው ጥቂት ወይም ምንም አልነበረም ብለዋል።

ሚኒስትሩ በኬንያ ከ3 ሚሊየን በላይ ደመወዝተኞች መኖራቸውን ገልጸው ከነዚህ ውስጥ 1.5 ሚሊየኑ በወር 30ሺህ ሽልንግና ከዛ በታች የሚያገኙ መሆናቸውን አስታውሰዋል። "እነዚህን ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኙ ዜጎች ታክስ ማድረግ ፍትሃዊ አይደለም" ሲሉ ነው የተናገሩት።

የገንዘብ ሚኒስትሩ ጆን ምባዲ እስከ 30ሺህ ሽልንግ የሚያገኙትን ከታክስ ነፃ ከማድረግ በተጨማሪ ከ30ሺህ-50ሺህ ሽልንግ በወር ለሚያገኙ የሚከፍሉት የገቢ ግብር በ5 በመቶ በመቀነስ ወደ 25% ዝቅ እንደሚደረግላቸውም በመግለጽ በአጠቃላይ 1.7 ሚሊየን ሰዎች ከታክስ ማሻሻያው እንደሚጠቀሙ አስታውቀዋል።

መረጃው የዘ ኬንያ ታይምስ ነው።

Source: tikvahethmagazine
#ethiopianbusinessdaily
👏1611😁6👍2
ብዙዎች ህግ የለም ብለው በደመነፍስ ሲመሩ፣ እኔ ግን በዚያው ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆኖ የሚታየውን ሕግ መኖሩን ለማሳየት #እየሞከርኩ ነው።
በብዙዎች ዘንድ #ሕግ የለም" የሚል ተስፋ መቁረጥ በነገሰበት፣ ገንዘብ ካለህ ሕግ አያስፈልግህም የሚል የተሳሳተ ብሂል በሰፈነበት ሁኔታ ውስጥ ቆሜ፣ እኔ ግን አንድ እውነትን ለማረጋገጥ ደጋግሜ እተጋለሁ። አዎ፣ #እየሞከርኩ ነው‼️
አለሕግ እና ሕግ አለ
ብዙዎች ህግ የለም ብለው በደመነፍስ ሲመሩ፣ እኔ ግን በዚያው ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆኖ የሚታየውን ሕግ መኖሩን ለማሳየት #እየሞከርኩ ነው።
ሕግ መኖሩ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ሕጉ ለሁሉም እኩል መሆኑን እና ማንም ከሕግ በላይ አለመሆኑን በተግባር ለማሳየት የፍትህ ስርዓቱ ላይ የራሴን አሻራ ለማሳረፍ እተጋለሁ። ይህ ጥረቴ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገሬ መፃኢ እድል እና ለልጆቻችን የሚተርፍ የፍትህ መሠረት ለመጣል ነው።

ሕግ መኖሩን እያወቁ፣ ነገር ግን እንደሌለ በማስመሰል የሰውን ንብረትና ሀብት ለዘረፉ፣ "ሕግ አለ!" ብዬ ፊት ለፊት እጋፈጣቸዋለሁ። የኔ ሙከራ እንደ አንድ ተራ ጠበቃ የሙያ ግዴታን መወጣት ብቻ አይደለም።

እኔ እየሞከርኩ ያለሁት፦
✔️ ለተገፉት ድምፅ ለመሆን፣
✔️ለተካዱት እውነትን ለማውጣት፣
✔️ ለተጭበረበሩት መብታቸውን ለማስከበር ነው።

የእነሱ ህመም ህመሜ፣ ስብራታቸው ስብራቴ ሆኖ ከጎናቸው እቆማለሁ። የተሰበረውን ፍትህ ለመጠገን እኔው ራሴ ተሰብሬም ቢሆን የቆሙለትን ዓላማ ዳር ለማድረስ እጥራለሁ።

በዚህ ሂደት ውስጥ መረጃ የፍትህ ዋስትና መሆኑን ለማስረፅ እሰራለሁ። ያለ መረጃ የሚጮህ ድምፅ ሰሚ እንደማያገኝ አውቃለሁና፣ እውነትን በመረጃ ደግፌ ለማቅረብ እና እያንዳንዱ የፍትህ ሂደት በስርዓትና በሕግ እንዲመራ ለማሳመን ሌት ተቀን #እየሞከርኩ ነው።

አዎ፣ ዛሬም ነገም #እየሞከርኩ ነው! #አለሕግ የሚለውን ድምፅ በ "ሕግ አለ" ለመተካት፣ በሀገሬ ላይ የሕግ የበላይነት እንዲነግስ እንደ አንድ ዜጋ የድርሻዬን እወጣለሁ። ግፍና መካድ በጊዜያዊነት ቢያሸንፉም፣ በመጨረሻ ግን ሕግና ስርዓት ማሸነፋቸው አይቀሬ ነው።
አዎ! ሕግ አለ!! ‼️🙏
#እየሞከርኩ ነው ‼️🙏✍️✍️✍️
#ሚኪያስ_መላክ
#Mikias_Melak
በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና ህግ አማካሪ
https://t.me/AleHig
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_እውቀት #የሕግ_መረጃ
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
  alehig.com
47👍14👏5🙏3🖕1
6
ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 236212

ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁጥር 50835 “በአንድ መዝገብ ላይ የተሠጠ ውሳኔ ከተፈፀመ በኋላም ቢሆን በውሳኔው መብቱ የተነካበት 3ኛ ወገን በሌላ መዝገብ ላይ ክስ አቅርቦ መብቱን ማስከበር ይችላል “ በሚል እንዲሁም
በሰ/መ/ ቁጥር 67127 “በፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል የሚል ሰው በዚያው መዝገብ ላይ የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ መብቱን ማስከበር ከሚችል በቀር ዉሳኔዉ በአፈጻጸሙ ከተቋጨ በኋላ በሌላ መዝገብ ላይ አዲስ ክስ ማቅረብ አይችልም፤ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የቀረበ ክስ ተቀብሎ ውሳኔ መስጠትም መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነው” በሚል የተሰጡት አስገዳጅ ውሳኔዎች ተሻሽለዋል፡፡

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት በመዝገብ ቁጥር 236212፡

“አንድ ሰዉ መብቱን የሚነካ ዉሳኔ የተፈጸመ እንደሆነ አዲስ ክስ በማቅረብ መብቱን ማስከበር የሚችለዉ፣ ከአቅም በላይ ወይም በቂ በሆነ ምክንያት ዉሳኔዉ ከመፈጸሙ በፊት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ስለመኖሩ ማወቅ ባለመቻሉ ወይም በተመሳሳይ ምክንያት መቃወሚያ ማቅረብ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው” ተብሎ ተሻሽሎ ተተርጉሟል፡፡

የውሳኔውን ሙሉ ይዘት በቴሌግራም ቻናላችን እንደሚከተለው አያይዘናል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጅያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት
23👍2
የDNA ምርመራ ወጪን ማን መክፈል አለበት?
"እናትነት እውነት፤ አባትነት እምነት።"
ታኅሳሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
#አንድን ወንድ ለአንድ ሕጻን አባቱ ነው ተብሎ ይወሰንልኝ በማለት በፍርድ ቤት ውሳኔ ለማሰጠት በማያሻማ ሁኔታ ወንድየው ለሕጻኑ አባት መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
#በትዳር ወይም ሳይጋቡ እንደባልና ሚስት በመኖር ግንኙነት ውስጥ ለሚወለዱ ልጆች ሕጉ ባልየው አባት ነው ተብሎ የሕግ ግምት እንደሚወሰድ ደንግጓል። የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 126 እና 130 /1/ን ይመለከቷል።
#የአባትነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ ብዙውን ጊዜ አከራካሪ የሚሆነው ከትዳር ወይም ሳይጋቡ እንደባልና ሚስት ከመኖር ግንኙነት ውጪ ለሚወለዱ ሕጻናት ነው።
የምርመራውን ወጪ ማን መሸፈን አለበት?
#በፍርድ ቤት ክርክር በየትኛውም አግባብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲቀርብለት የጠየቀውን ለማስረጃ ለማስቀረብ የጠየቀ ወገን ወጪን መሸፈን እንዳለበት ግልጽ ነው።
#በመሆኑም የDNA Test /የዘረመል ምርመራ/ እንዲደረግለት የጠየቀ ወገን ለምርመራው የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹
11👍6
ነገር ግን እነዚህን የወራሹን ጥፋቶች ሟች ግልጽ በሆነ ጽሑፍ ይቅርታ ያደረለገት እንደሆነ ከውርስ መነቀሉ ይቀርልታል።
#ሟች ተወላጅ ልጁን ከውርስ ለመንቀል የሚፈልግ ቢሆን በኑዛዜው ላይ በምን ምክንያት እንደነቀለው በግልጽ ማመላከት እንዳለበት በፍትሐ ብሔር ሕጉ ቁጥር 938 /1/ ላይ ላይ “ተናዛዡ ከርስት ከውርስ ለመንቀል የደረሰበትን ምክንያት በኑዛዜው ውስጥ ካልገለጸ በቀር ልጁን ወይም ወደ ታች የሚቈጠር ተወላጁን ከውርስ ቢነቅል አይጸናም።” በማለት ይደነግጋል።
#ሟች ተወልጃ ልጁን ከውርስ ለመንቀል የሚችልባቸው ምክንያቶች ምን ምን እንደሆኑ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 838 ላይ በግልጽ ተመልክተዋል። እነሱም፦
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 838 ያልተገባ ስለ መሆን (1) ወንጀሎች ወይም ቅጣቶች
#ሟቹን ለመውረስ የማይገባ ነው ተብሎ የወራሽነትን መብት የሚያጣው
1️⃣ሟቹን ወይም የሟቹን ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጅ ወይም ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች አንዱን ወይም የሟቹን ባል ወይም ሚስት አስቦ በመግደል የተፈረደበት።
2️⃣ከነዚሁ ሰዎች መካከል አንደኛውን ለመግደል በመሞከር የተቀጣ።
3️⃣በሐሰት በወንጀል ወይም በሐሰት ምስክርነት ይህ በሐሰት መወንጀል በሐሰት መመስከር ከነዚሁ ሰዎች መካከል በአንደኛው ላይ የሞት ፍርድ ወይም ከአስር ዓመት የበለጠ የጽኑ እስራት ቅጣትን ለማስተካከል የሚያሰጋ ሁኖ የተቀጣ ማኛውም ሰው ነው።
በሁሉም ምክንያቶች ወራሹ በወንጀል ተከሶ ቅጣት የተጣለበት መሆን አለበት።
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 840 (3) ሌሎች ምክንያቶች
#በተለይ ሟቹን ለመውረስ የማይገባ ነው ተብሎ
ሀ. የሟቹን ሰውነት ሁኔታ ምክንያት በማድረግ አውራሹ ከመሞቱ በፊት በአሉት በሦስት ወር ውስጥ ኑዛዜ እንዲያደርግ እንዳይለውጥ ወይም እንዳይሽር የከለከለ።
ለ. አስቦ ያለሟቹ ፈቃድ የሟቹን የመጨረሻ ኑዛዜ ያበላሸ እንይገኝ ያደረገ ያጠፋ ወይም ጉዳዩን በማወቅ በሐሰት ኑዛዜ የተጠቀመ የወራሽነት መብት ያጣል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
©ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማናቸውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
📍አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ🇪🇹
15👎2