አለ ሕግ
15.9K subscribers
3.31K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሰው ምስክር ለማስረዳት የሚችሉበት የህግ መሠረት ባለመኖሩ ገዥ ቤቱን ገዝቼዋለሁ በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ በሻጭ ሚስት ላይ ህጋዊ ውጤትን የሚያስከትል አይሆንም ሰ/መ/ቁ 224476 በቀን 05/02/2017ዓም የተወሰነ
==========================
የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለዉ ልዩ ባህርይ አንፃር ንብረቱን ከአንድ ወደ ሌላ ሰዉ በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ ዉሉ በህግ አግባብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ካልተመዘገበ ውሉ ፈራሽ እንደሚሆንና የፍ/ሕ/ቁ አንቀጽ 2878 ን ዋቢ በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 153664 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት ሲሆን በተያዘው ጉዳይም ተጠሪው ይህ አከራካሪ ቤት ከአመልካችዋ ባለቤት ላይ በግዢ ያገኙት መሆናቸውን ከመግለጽ በቀር፤ ቤቱን በግዢ ስለማግኘታቸውና በህግ አግባብ ባለው አካል ዘንድ የግዢና የሽያጭ ውሉ የተመዘገበበት የሰነድ ማስረጃ ተጠሪው በሥር ፍርድ ቤት ያላቀረቡ በመሆኑና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሰው ምስክር ለማስረዳት የሚችሉበት የህግ መሠረት ባለመኖሩ አመልካቹ ቤቱን ገዝቼዋለሁ በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ በአመልካችዋ ላይ ህጋዊ ውጤትን የሚያስከትል አይሆንም
18🔥1
ለተወደዳችሁ የፌደራል ጠበቆች በሙሉ:-
በከሳሽ 7ቱ ጠበቆች እና በተከሳሽ ገንዘብ ሚ/ር መካከል በከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ. 344295 ባለው የተጨማሪ እሴት ታክስ መመሪያ ቁጥር 1104/2017 ክለሳ ክርክር ፍ/ቤቱ መመሪያው በ7ቱ ጠበቆች ላይ ሳይፈጸም ታግዶ እንዲቆይ ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ትእዛዝ መስጠቱ ይታወቃል::🧓🏾

ገንዘብ ሚ/ር በዚህ ትእዛዝ ቅር ተሰኝቻለሁ በማለት ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የነበረ ሲሆን ጠቅላይ ፍ/ቤቱም በፍ/መ/ቁ. 294176 ጥር 08 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ትእዛዝ በማጽናት የመመሪያው አፈጻጸም 7ቱን ጠበቆች አስመልክቶ ታግዶ እንዲቆይ ወስኖአል::
ጠበቃ ሀይሉ ሀሰና
👍297🥰5😁2🤔2
🥰1
ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ ደንብ!!
➤በግሌ የአደጋ ምላሽ ፈንደ መኖሩ ተገቢ ነው!! በተጠቃሚ ላይ ብቻ ያተኮረ ክፍያ ሆነ!ነዳጅ፣ ቴሌኮም አገልግሎት፤ የባንክ ብድር፤ ተጠቃሚዎች ላይ ያተኮሩ ሆኑ! ያው የሚቀየር ነገር ባይኖርም ማወቁ አይከፋም።

🦜ይህ ደንብ መሆን ነበረበት ወይስ አዋጅ?

➤የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ
👉የትሌኮም አገልግሎት ለድምፅና ዳታ ከማጠቀው 5% በጣም ብዙ ነው!
👉አክሲዮን ትርፍ( Dividend ) 15% ታክስ ይደረግ ተብሎ አሁን ደግሞ 1% ይክፈሉ ተብሏል::

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው አዲስ ደንብ ቁጥር 576/2018 መሰረት የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ ጽህፈት ቤት በይፋ ተቋቁሟል።

በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ላይ በወጣው ዝርዝር መሰረት የሚከተሉት አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ተጥሏል፡

1. ​​የባንክ ብድር፡ ከሚሰጠው የብድር መጠን ላይ 1%

2. ​የኢንሹራንስ አረቦን (Premium)፦ከሚሰበሰበው ክፍያ ላይ 1%

3. ​ዲጂታል የባንክ አገልግሎት፦ ደንበኞች ከሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ላይ 5%

4. ​የአየር መንገድ ትኬት (የሀገር ውስጥ)፦ በእያንዳንዱ ትኬት ላይ 100 ብር

5. ​የነዳጅ ሽያጭ፦ በአንድ ሊትር ነዳጅ ላይ 1 ብር

6. ​የቴሌኮም አገልግሎት (ድምጽና ዳታ)፦ ከሚገዛው የአየር ሰዓት ወይም የአገልግሎት ዋጋ ላይ 5%

7.​ ፓስፖርትና ቪዛ፦ ለእያንዳንዱ አገልግሎት 200 ብር

8. ​የንግድ ፈቃድ (ማውጣትና ማደስ)፦ በእያንዳንዱ አገልግሎት 200 ብር

9. ​የአክሲዮን ትርፍ (Dividend)፦ ከሚያገኘው የትርፍ ድርሻ ላይ 1%

10. ​ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ፦ ከአገልግሎት ክፍያው ላይ 5%

መንግስት ይህንን ፈንድ ያቋቋመው እንደ ድርቅ፣ ጎርፍ እና መሰል አደጋዎች ሲከሰቱ ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት ለመውጣት እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መሆኑን ይገልጻል። አተገባበሩ ግን በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባለው ማህበረሰብ ላይ የኢኮኖሚ ጫና ማሳረፉ አይቀሬ ነው።
Via #Menur_Reshid #አለሕግ
👍119👎1🍾1
ማስታወቂያ

ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህግ ጉዳዮች ጸሃፊ I እና የህግ ጉዳዮች ጸሃፊ II የፅሁፍ ፈተና ወስዳችሁ ለቃል ፈተና የተመረጣችሁ ስማችሁ በዚህ ዝርዝር የተጠቀሰው ለህግ ጉዳዮች ጸሃፊ I ጠዋት 2:30 እንዲሁም ለህግ ጉዳዮች ጸሃፊ II ከሰዓት 7:30 ማክሰኞ ቀን 26/05/2018 ዓ.ም ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ለቃል ፈተና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
8
የንብረት ህግ.pdf
579.8 KB
የንብረት ሕግ ማብራሪያ
Vacancy Announcement.pdf
482.6 KB
📢 The Ethiopian Lawyers Association (ELA)
5👍3