አለ ሕግ
15.9K subscribers
3.31K photos
34 videos
1.94K files
3.72K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የቀድሞው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ በድጋሚ አብሮ መኖር ወይም በድጋሚ መጋባት አዲስ ጋብቻ ከመመሥረት የተለየ አይደለም።
በመካከላቸው የትዳር ሁኔታ መኖሩ ከተረጋገጠ፣ በዚሁ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 97(1) መሠረት፣ ጋብቻ መፈጸሙን የሕግ ግምት (Legal Presumption) መውሰድ ይቻላል።
👍1413
#እንድታውቁት: ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ምጣኔን በተመለከተ

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጧል፡፡

🔗 በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት መጣኔዎች ከላይ በምስሉ ተያይዟል።

ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4👍4😁1
የተማሪዎች የሥነ ምግባር ረቂቅ መመሪያ በውስጡ ምን ምን አካቷል?

"Crazy day፣ olds day፣ Valentine day " እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር ይከለክላል።

መመሪያው በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ፣ የግል፣ በኃይማኖት ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶችና ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።

በመመሪያው የተማሪዎች መብትና ግዴታዎች ሲቀመጡ በተማሪዎች ግዴታ ስር ፀጉርን በአግባቡ መሰራት/ማሳጠር፣ ከተፈጥሯዊ ጸጉራቸው ውጪ እንዳይጠቀሙ ተቀምጧል።

የሴቶቾ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ቀሚስ ቁመት ከባት በታች መሆን ያለበት ሲሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን ልብስ መልበስ የሚለውም ተካቷል።

በመመሪያው ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ ጫት መቃም፣ ዕፆችን መጠቀም/ማዘዋወር እንደዚሁም ሞባይልና የሙዚቃ ማዳመጫዎችን ወደ ትምህርት ቤት ይዞ መምጣት ይገኙበታል።

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ኃይማኖታዊ አምልኮ ስርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማከናወንም በመመሪያው ተከልክሏል።

በመመሪያው ሀገራዊ እሴት ያልሆኑ መጤ ነገሮችን በሰውነት ላይ መነቀስ ሲከለከል፤ ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም ከመቀባትና ከመኳኳል እንደዚሁም አላስፈላጊ ጌጥ ከማድረግ ይከለክላል።

በተጨማሪም በረቂቁ  በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ ያላቸውን ድርጊቶች (Crazy Day, Gentle Day, Olds Day, Baby Day, Fruit Day, Tomato 
Day, Valentine Day, April the full, Color Day, Pyjama Day…etc) መፈጸም፤ እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር እንደማይቻል ተገልጿል።

የተከለከሉ ተግባራትን በሚፈፅመት ላይ የተለያያ የእርምት እርምጃዎች ሲቀመጡ ቀላል እርምጃ ሊያስወስዱ በሚችሉ ጥፋቶች ስር ከፀጉር ጋር የተያያዙ እና ሌሎች ቀላል ጥፋቶች ተካተዋል።

የትምህርት ቤት ፕላዝማና ኮምፒውተር ለሌላ አላማ መጠቀም፣ በአጥር መዝልና መሽሎክ፣ ከላይ የተጠቀሱ አላስፈላጊ ባህሎችን ማክበር፣ አሉታዊ ምልክቶችን መነቀስ፣ ድብድብ እንደዚሁም ኃይማኖታዊ ስርዓት መፈፀምና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በከባድ ጥፋት ውስጥ ተካተዋል።

የቅጣት እርከኑ እንደ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃና ጥፋቱ ሲለያይ ለከባድ የስነ ምግባር ግድፈት  በመደበኛ ህግ መሰረት የህግ ተጠያቂነት ይኖራል።

መመሪያው የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴ ስብጥር እንደዚሁም ተግባርና ኃላፊነትን በዝርዝር አስቀምጧል።

በተጨማሪ መመሪያው በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትን ተግባርያ ኃላፊነትም ዘርዝሮ ሲያስቀምጥ ማንኛውም ትምህርት ቤት ያለ መሸኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ መመዝገብንም ከልክሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በ  https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍105👏1
የተማሪዎች የሥነ ምግባር ረቂቅ መመሪያ በውስጡ ምን ምን አካቷል ?

➡️ " Crazy day ፣ olds day ፣ Valentine day " እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር ይከለክላል።

መመሪያው በመንግስት ፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ፣ የግል ፣ በኃይማኖት ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶችና ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።

በመመሪያው የተማሪዎች መብትና ግዴታዎች ሲቀመጡ በተማሪዎች ግዴታ ስር ፀጉርን በአግባቡ መሰራት/ማሳጠር፣ ከተፈጥሯዊ ጸጉራቸው ውጪ እንዳይጠቀሙ ተቀምጧል።

የሴቶቾ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ቀሚስ ቁመት ከባት በታች መሆን ያለበት ሲሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን ልብስ መልበስ የሚለውም ተካቷል።

በመመሪያው ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ ጫት መቃም፣ ዕፆችን መጠቀም/ማዘዋወር እንደዚሁም ሞባይልና የሙዚቃ ማዳመጫዎችን ወደ ትምህርት ቤት ይዞ መምጣት ይገኙበታል።

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ኃይማኖታዊ አምልኮ ስርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማከናወንም በመመሪያው ተከልክሏል።

በመመሪያው ሀገራዊ እሴት ያልሆኑ መጤ ነገሮችን በሰውነት ላይ መነቀስ ሲከለከል፤ ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም ከመቀባትና ከመኳኳል እንደዚሁም አላስፈላጊ ጌጥ ከማድረግ ይከለክላል።

በተጨማሪም በረቂቁ  በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ ያላቸውን ድርጊቶች ፦
• Crazy Day,
• Gentle Day,
• Olds Day,
• Baby Day,
• Fruit Day,
• Tomato Day,
• Valentine Day,
• April the full,
• Color Day,
• Pyjama Day…etc መፈጸም፤ እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር እንደማይቻል ተገልጿል።

የተከለከሉ ተግባራትን በሚፈፅመት ላይ የተለያያ የእርምት እርምጃዎች ሲቀመጡ ቀላል እርምጃ ሊያስወስዱ በሚችሉ ጥፋቶች ስር ከፀጉር ጋር የተያያዙ እና ሌሎች ቀላል ጥፋቶች ተካተዋል።

የትምህርት ቤት ፕላዝማና ኮምፒውተር ለሌላ አላማ መጠቀም፣ በአጥር መዝልና መሽሎክ፣ ከላይ የተጠቀሱ አላስፈላጊ ባህሎችን ማክበር፣ አሉታዊ ምልክቶችን መነቀስ፣ ድብድብ እንደዚሁም ኃይማኖታዊ ስርዓት መፈፀምና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በከባድ ጥፋት ውስጥ ተካተዋል።

የቅጣት እርከኑ እንደ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃና ጥፋቱ ሲለያይ ለከባድ የስነ ምግባር ግድፈት በመደበኛ ህግ መሰረት የህግ ተጠያቂነት ይኖራል።

መመሪያው የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴ ስብጥር እንደዚሁም ተግባርና ኃላፊነትን በዝርዝር አስቀምጧል።

ከዚህ ባለፈ ፦
• ትምባሆ (ሲጋራ፣ ሺሻ)
• ጫት
• አልኮል
• የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶችና ሱስ አስያዥ ዕፆች በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መገኘት፣ መጠቀም፣ መሸጥ፣ ማብቀል፣ ማምረት ወይም መለወጥ የተከለከለ እንደሆነ መመሪያው ላይ ተቀምጧል።

እንዲሁም ፦
• የአልኮል መሸጫና ማከፋፈያ ቤቶች
• የሲጋራ መሸጫ ሱቆች
• ሺሻ ቤቶች
• ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች
• ጭፈራ ቤቶች
• ቁማር ቤቶች
• የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች
• የሰውነት መታሻ (ማሳጅ) ቤቶች
• የፊልም ማጫዎቻ ቤቶች
• ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች
• ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች
• ከረንቡላ ፑል
•  ጆተኒ
• ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም እገዳ ተጥሎባቸዋል።

በተጨማሪም መመሪያው በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትን ተግባርያ ኃላፊነትም ዘርዝሮ ሲያስቀምጥ ማንኛውም ትምህርት ቤት ያለ መሸኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ መመዝገብንም ከልክሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በ  https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።

Via @TikvahethMagazine
23👏8👎2
ት/ት ሚኒስቴር❗️

ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ አይችሉም!

📌ሴት ተማሪዎች
👉የጥፍር፣
👉የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣
👉ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣
👉አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር #አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም
👉እንደ ክሬዚ ዴይ፣
👉ኦልድ ዴይ፣
👉ቤቢ ዴይ፣
👉ቶማቶ ዴይ፣
👉ከለር ዴይ፣
👉ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡

በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ ከባት በታች የሆነ ቁመት ያለው ለብሶ መገኘት አለባቸው ተብሏል፡፡ 

ከደንብ ልብስ ውጪ ቢሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን አለባበስ መልበስ ይጠበቅባቸዋል ይላል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ትምህርት ቤት ውስጥ መፈፀም የተከለከሉ ድርጊቶች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል ደግሞ የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ የትምህርት አመራር፣ ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ማህበረሰብ አካላትን መዝለፍ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽና አካላዊ ጥቃት መፈጸም ቅጣት የሚያስከትል ተግባር ነው ተብሏል፡፡

👉ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ሞባይል እና
👉የሙዚቃ ማዳመጫ መሣሪያዎችን ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል፡፡

👉በቃል፣ በምልክትም ሆነ በጽሑፍ ፀያፍ ነገሮችን መግለፅ፤ ጨዋነት የጎደላቸውን እንዲሁም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ምስሎችና ጽሑፎች በትምህርት ቤት ውስጥ ይዞ መገኘትና ማሰራጨት አይፈቀድም፡፡

👉በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የማንኛውንም ዓይነት የኃይማኖት አምልኮ ሥርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ ይከለክላል፡፡

ማንኛውም ተማሪ አገራዊ እሴት ያልሆኑና መጤ የሆኑ ነገሮችን በሰውነት ላይ ምልክት ማድረግ፤ ከአገራዊ እሴት ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ መጤ ምልክቶችን በሰውነት ላይ መነቀስ፣ ማሳየት፣ ማድረግ፣ መጠቀም ፍፁም የተከለከለ ነው ብሏል ረቂቅ መመሪያው፡፡

#ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አንድ ተማሪ በሥነ-ምግባር ጉድለት እጅ ከፍንጅ ከተያዘና የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ሆኖ ከተገኘ ውሳኔ እስኪሰጠው ከትምህርት ቤት ሊታገድ እንደሚችልም በመመሪያው ሰፍሯል፡፡

👉ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ በተለይም ከ7 እስከ 12ተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እስከ 1 ዓመት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከትምህርት ሊታገዱ ይችላልም ሲል ረቂቅ መመርያው አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ደንብ ተሰናድቷል፡፡

በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምባሆ(ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶች እና ሱስ አስያዥ ዕፆች ትምህርት ቤት አካባቢ መሸጥም ሆነ ይዞ መገኘትን ይከለክላል።

👉የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፣
👉የሲጋራ መሻጫ ሱቆች፣
👉ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣
👉ጭፈራ ቤቶች፤ ቁማር ቤቶች፤
👉የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና
👉የሰውነት መታሻ ወይም ማሳጅ ቤቶች በትምህርት ቤቶች በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ መክፈት አይቻልም፡፡

👉ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣
👉ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ፣ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና
👉የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም በትምህርት ቤት አቅራቢያ መክፈትን ከልክሏል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
      ኢትዮ-መረጃ
27👍8
8
አንቀጽ 1845 Period of Limitation) አንቀጽ 1810 Action for Invalidation

👇👇👇👇
አንቀጽ 1810፡ ልዩ እና አጭር የጊዜ ገደብ (Action for Invalidation)

ይህ አንቀጽ ውል በውስጡ ባለው ጉድለት (ስህተት፣ ማስገደድ፣ ማታለል ወይም ተመጣጣኝ ያልሆነ ግምት) ምክንያት እንዲፈርስ የሚቀርብ ክስ ላይ ያተኩራል።
👉 ዋናው ዓላማ: ለውል ማፍረስ ክሶች ልዩ የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ።
👉 የጊዜ ገደብ: በአብዛኛው ሁለት ዓመት ነው።

   👉 ጉድለቱ ከጠፋበት (ለምሳሌ ማስገደድ ካቆመ) ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት።

👉ውሉ ተመጣጣኝ ባልሆነ ግምት (Unconscionable) ምክንያት የሚፈርስ ከሆነ ደግሞ ውሉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት።

👉ውልን በጉድለት ለማፍረስ የሚቀርብ ክስ ይህን አጭር ጊዜ ማሟላት ይኖርበታል።

አንቀጽ 1845፡ አጠቃላይ እና ረዥም የይርጋ ገደብ (General Period of Limitation)✍️

ይህ አንቀጽ በአጠቃላይ የውል ግዴታዎችን ማስፈጸም፣ ውል ባለመፈጸም የተነሳ ካሳ መጠየቅ፣ እንዲሁም ውልን ማፍረስን ጨምሮ ለማንኛውም የውል ክስ የሚውል አጠቃላይ የይርጋ ጊዜ ያስቀምጣል።
👉 ዋናው ዓላማ: ለሁሉም የውል ክሶች አጠቃላይ የይርጋ ገደብ ማስቀመጥ።
👉የጊዜ ገደብ: አሥር ዓመት ነው።
👉በህግ በተለየ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር (እንደ 1810)፣ ማንኛውም የውል ክስ በ10 ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል።


አንቀጽ 1810 Action for Invalidation;
አንቀጽ 1810 በተለይ ለውል ማፍረስ ክሶች የሚቀድም የሁለት ዓመት አጭር ጊዜ ሲሆን፣ አንቀጽ 1845 ደግሞ ለሁሉም የውል ክሶች አጠቃላይ የአሥር ዓመት የመጨረሻ ገደብ ነው። ስለዚህ፣ የውል ማፍረስ ክስ የሚቀርበው በሁለት ዓመት ውስጥ (በ1810 መሰረት) ካልሆነ ግን በማንኛውም ምክንያት በአሥር ዓመት (በ1845 መሰረት) ውስጥ መሆን ይኖርበታል።

በጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
ሚኪያስ መላክ

ተዘጋጅቶ በአለሕግ አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልግሎት የቀረበ ነው።
Alternative legal enlightenment & Service

https://t.me/AleHig

https://linktr.ee/alehig

WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ #የሕግ_እውቀት #AleHig #አለሕግ #ህግ
alehig.com
28👍1
👍51🙏1