#Update ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያና በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤቶች ሕንፃ ውዝግብ ላይ የእግድ ውሳኔ አስተላለፈ
በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (ኢትዮጵያ ቻምበር) እና በአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) መካከል በሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የንግድ ምክር ቤቶች ሕንፃ ላይ በቀረበው የይገባኛል ውዝግብ ላይ፣ የቂርቆስ ምድብ 1ኛ ፍ/ብሄር ችሎት የእግድ ዉሳኔ አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት በሰጠው ውሳኔ መሰረት፣ ኢትዮጵያ ቻምበር ቀደም ሲል ይዞ የነበረውን የቢሮ ክፍል በአስቸኳይ ለአዲስ ቻምበር እንዲያስረክብ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ይህን ውሳኔ የሰጠው፣ ኢትዮጵያ ቻምበር ቀደም ሲል የፍርድ ቤቱን ብይን በመጣስ፣ አዲስ ቻምበር ይዟቸው የነበሩ ክፍሎችን በኃይል እንደያዘ አዲስ ቻምበር ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ነው።
ፍርድ ቤቱ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሳለፈው ብይን፣ ተከሳሽ (ኢትዮጵያ ቻምበር) ሕንጻውን ለልማት ከማዋሉ በፊት ለአዲስ ቻምበር ምትክ ክፍሎችን አስቀድሞ ማዘጋጀትና ለፍርድ ቤቱ ማሳወቅ እንደነበረበት አመልክቶ ነበር።
የኢትዮጵያ ቻምበር ይህንን ትዕዛዝ በመጣስ የክፍሎቹን ቁልፎች ሰብሮ መግባቱ በአዲስ ቻምበር በኩል መገለጹን ተከትሎ፣ ፍርድ ቤቱ ኢትዮጵያ ቻምበር ክፍሎቹን በአስቸኳይ ለከሳሽ (አዲስ ቻምበር) እንዲያስረክብ በድጋሚ በጥብቅ አዟል።
Read More
Source: capitalethiopia
#Ethiopianbusinessdaily

❤25😁2
በገቢ_ግብር_አዋጅ_ማሻሻያ_ላይ_የገንዘብ_ሚኒስቴር_የሰጠው_ማብራሪያ_.pdf
4.5 MB
ከገንዘብ ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ - የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ…
✍1
የንግድ ስራ ከተቋረጠ በኋላ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር የሚከፈልበት ሁኔታ
በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 እና በደንብ ቁጥር 410/2010 በመመሪያ ቁጥር 146/2011 የንግድ ስራ ከተቋረጠ በኋላ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር ስለሚከፈልበት ሁኔታ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ተመሰርቶ ይሆናል:-
👉🏾 ታክስ ከፋዩ የንግድ ስራ ከተቋረጠ በኋላ የሚሸጣቸው እቃዎች የተሸጡበትን ዋጋ ማረጋገጥ የማይቻል ከሆነ እቃው የተገዛበት ዋጋ ወደ ሽያጭ ተቀይሮ ግብሩ ይወሰናል ፡፡
👉🏾 ታክስ ከፋዩ እቃውን የሸጠው የሒሳብ መዝገብ ለሚይዝ ታክስ ከፋይ ከሆነ እቃው የተሸጠበት ዋጋ ገዢው በሚያዘጋጀው የግዥ ማረጋገጫ ሰነድ (Purchase Voucher) መሰረት ይወሰናል ፡፡
👉🏾 የንግድ ስራ ካቋረጠ በኋላ የንግድ እቃ የሚሸጥ ታክስ ከፋይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰብስቦ የመክፈል ግዴታ አለበት ፡፡
👉🏾 ታክስ ከፋዩ ድርጅቱን ሲዘጋ በእጁ ያሉትን እቃዎች ቆጥሮ ለታክስ ባለስልጣኑ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
👉🏾 ታክስ ከፋዩ ድርጅቱን ከዘጋ በኋላ በሸጣቸው እቃዎቹ የመዝገብ ዋጋ (Book Value) ከተሸጠበት ዋጋ ላይ ተቀንሶ በሚገኘው ልዩነት ላይ የሚሰላ ይሆናል ፡፡
❤14👍5👏1
የቀድሞው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ በድጋሚ አብሮ መኖር ወይም በድጋሚ መጋባት አዲስ ጋብቻ ከመመሥረት የተለየ አይደለም።
በመካከላቸው የትዳር ሁኔታ መኖሩ ከተረጋገጠ፣ በዚሁ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 97(1) መሠረት፣ ጋብቻ መፈጸሙን የሕግ ግምት (Legal Presumption) መውሰድ ይቻላል።

👍14❤13
#እንድታውቁት: ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ምጣኔን በተመለከተ
የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጧል፡፡
🔗 በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት መጣኔዎች ከላይ በምስሉ ተያይዟል።
ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@TikvahethMagazine
የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጧል፡፡
ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤4👍4😁1
የተማሪዎች የሥነ ምግባር ረቂቅ መመሪያ በውስጡ ምን ምን አካቷል?
⚫ "Crazy day፣ olds day፣ Valentine day " እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር ይከለክላል።
መመሪያው በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ፣ የግል፣ በኃይማኖት ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶችና ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።
በመመሪያው የተማሪዎች መብትና ግዴታዎች ሲቀመጡ በተማሪዎች ግዴታ ስር ፀጉርን በአግባቡ መሰራት/ማሳጠር፣ ከተፈጥሯዊ ጸጉራቸው ውጪ እንዳይጠቀሙ ተቀምጧል።
የሴቶቾ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ቀሚስ ቁመት ከባት በታች መሆን ያለበት ሲሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን ልብስ መልበስ የሚለውም ተካቷል።
በመመሪያው ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ ጫት መቃም፣ ዕፆችን መጠቀም/ማዘዋወር እንደዚሁም ሞባይልና የሙዚቃ ማዳመጫዎችን ወደ ትምህርት ቤት ይዞ መምጣት ይገኙበታል።
በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ኃይማኖታዊ አምልኮ ስርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማከናወንም በመመሪያው ተከልክሏል።
በመመሪያው ሀገራዊ እሴት ያልሆኑ መጤ ነገሮችን በሰውነት ላይ መነቀስ ሲከለከል፤ ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም ከመቀባትና ከመኳኳል እንደዚሁም አላስፈላጊ ጌጥ ከማድረግ ይከለክላል።
በተጨማሪም በረቂቁ በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ ያላቸውን ድርጊቶች (Crazy Day, Gentle Day, Olds Day, Baby Day, Fruit Day, Tomato
Day, Valentine Day, April the full, Color Day, Pyjama Day…etc) መፈጸም፤ እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር እንደማይቻል ተገልጿል።
የተከለከሉ ተግባራትን በሚፈፅመት ላይ የተለያያ የእርምት እርምጃዎች ሲቀመጡ ቀላል እርምጃ ሊያስወስዱ በሚችሉ ጥፋቶች ስር ከፀጉር ጋር የተያያዙ እና ሌሎች ቀላል ጥፋቶች ተካተዋል።
የትምህርት ቤት ፕላዝማና ኮምፒውተር ለሌላ አላማ መጠቀም፣ በአጥር መዝልና መሽሎክ፣ ከላይ የተጠቀሱ አላስፈላጊ ባህሎችን ማክበር፣ አሉታዊ ምልክቶችን መነቀስ፣ ድብድብ እንደዚሁም ኃይማኖታዊ ስርዓት መፈፀምና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በከባድ ጥፋት ውስጥ ተካተዋል።
የቅጣት እርከኑ እንደ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃና ጥፋቱ ሲለያይ ለከባድ የስነ ምግባር ግድፈት በመደበኛ ህግ መሰረት የህግ ተጠያቂነት ይኖራል።
መመሪያው የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴ ስብጥር እንደዚሁም ተግባርና ኃላፊነትን በዝርዝር አስቀምጧል።
በተጨማሪ መመሪያው በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትን ተግባርያ ኃላፊነትም ዘርዝሮ ሲያስቀምጥ ማንኛውም ትምህርት ቤት ያለ መሸኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ መመዝገብንም ከልክሏል።
ትምህርት ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በ https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።

👍10❤5👏1
የተማሪዎች የሥነ ምግባር ረቂቅ መመሪያ በውስጡ ምን ምን አካቷል ?
➡️ " Crazy day ፣ olds day ፣ Valentine day " እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር ይከለክላል።
መመሪያው በመንግስት ፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ፣ የግል ፣ በኃይማኖት ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶችና ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።

በተጨማሪም በረቂቁ በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ ያላቸውን ድርጊቶች ፦
• Crazy Day,
• Gentle Day,
• Olds Day,
• Baby Day,
• Fruit Day,
• Tomato Day,
• Valentine Day,
• April the full,
• Color Day,
• Pyjama Day…etc መፈጸም፤ እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር እንደማይቻል ተገልጿል።
የተከለከሉ ተግባራትን በሚፈፅመት ላይ የተለያያ የእርምት እርምጃዎች ሲቀመጡ ቀላል እርምጃ ሊያስወስዱ በሚችሉ ጥፋቶች ስር ከፀጉር ጋር የተያያዙ እና ሌሎች ቀላል ጥፋቶች ተካተዋል።
የትምህርት ቤት ፕላዝማና ኮምፒውተር ለሌላ አላማ መጠቀም፣ በአጥር መዝልና መሽሎክ፣ ከላይ የተጠቀሱ አላስፈላጊ ባህሎችን ማክበር፣ አሉታዊ ምልክቶችን መነቀስ፣ ድብድብ እንደዚሁም ኃይማኖታዊ ስርዓት መፈፀምና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በከባድ ጥፋት ውስጥ ተካተዋል።
የቅጣት እርከኑ እንደ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃና ጥፋቱ ሲለያይ ለከባድ የስነ ምግባር ግድፈት በመደበኛ ህግ መሰረት የህግ ተጠያቂነት ይኖራል።
መመሪያው የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴ ስብጥር እንደዚሁም ተግባርና ኃላፊነትን በዝርዝር አስቀምጧል።
ከዚህ ባለፈ ፦
• ትምባሆ (ሲጋራ፣ ሺሻ)
• ጫት
• አልኮል
• የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶችና ሱስ አስያዥ ዕፆች በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መገኘት፣ መጠቀም፣ መሸጥ፣ ማብቀል፣ ማምረት ወይም መለወጥ የተከለከለ እንደሆነ መመሪያው ላይ ተቀምጧል።
እንዲሁም ፦
• የአልኮል መሸጫና ማከፋፈያ ቤቶች
• የሲጋራ መሸጫ ሱቆች
• ሺሻ ቤቶች
• ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች
• ጭፈራ ቤቶች
• ቁማር ቤቶች
• የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች
• የሰውነት መታሻ (ማሳጅ) ቤቶች
• የፊልም ማጫዎቻ ቤቶች
• ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች
• ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች
• ከረንቡላ ፑል
• ጆተኒ
• ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም እገዳ ተጥሎባቸዋል።
በተጨማሪም መመሪያው በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትን ተግባርያ ኃላፊነትም ዘርዝሮ ሲያስቀምጥ ማንኛውም ትምህርት ቤት ያለ መሸኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ መመዝገብንም ከልክሏል።
ትምህርት ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በ https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
Via @TikvahethMagazine

❤23👏8👎2
ት/ት ሚኒስቴር❗️
ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ አይችሉም!
📌ሴት ተማሪዎች
👉የጥፍር፣
👉የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣
👉ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣
👉አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር #አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም
👉እንደ ክሬዚ ዴይ፣
👉ኦልድ ዴይ፣
👉ቤቢ ዴይ፣
👉ቶማቶ ዴይ፣
👉ከለር ዴይ፣
👉ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡
በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ ከባት በታች የሆነ ቁመት ያለው ለብሶ መገኘት አለባቸው ተብሏል፡፡
ከደንብ ልብስ ውጪ ቢሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን አለባበስ መልበስ ይጠበቅባቸዋል ይላል ረቂቅ መመሪያው፡፡
ትምህርት ቤት ውስጥ መፈፀም የተከለከሉ ድርጊቶች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል ደግሞ የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ የትምህርት አመራር፣ ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ማህበረሰብ አካላትን መዝለፍ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽና አካላዊ ጥቃት መፈጸም ቅጣት የሚያስከትል ተግባር ነው ተብሏል፡፡
👉ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ሞባይል እና
👉የሙዚቃ ማዳመጫ መሣሪያዎችን ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል፡፡
👉በቃል፣ በምልክትም ሆነ በጽሑፍ ፀያፍ ነገሮችን መግለፅ፤ ጨዋነት የጎደላቸውን እንዲሁም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ምስሎችና ጽሑፎች በትምህርት ቤት ውስጥ ይዞ መገኘትና ማሰራጨት አይፈቀድም፡፡
👉በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የማንኛውንም ዓይነት የኃይማኖት አምልኮ ሥርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ ይከለክላል፡፡
ማንኛውም ተማሪ አገራዊ እሴት ያልሆኑና መጤ የሆኑ ነገሮችን በሰውነት ላይ ምልክት ማድረግ፤ ከአገራዊ እሴት ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ መጤ ምልክቶችን በሰውነት ላይ መነቀስ፣ ማሳየት፣ ማድረግ፣ መጠቀም ፍፁም የተከለከለ ነው ብሏል ረቂቅ መመሪያው፡፡
#ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አንድ ተማሪ በሥነ-ምግባር ጉድለት እጅ ከፍንጅ ከተያዘና የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ሆኖ ከተገኘ ውሳኔ እስኪሰጠው ከትምህርት ቤት ሊታገድ እንደሚችልም በመመሪያው ሰፍሯል፡፡
👉ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ በተለይም ከ7 እስከ 12ተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እስከ 1 ዓመት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከትምህርት ሊታገዱ ይችላልም ሲል ረቂቅ መመርያው አስቀምጧል፡፡
በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ደንብ ተሰናድቷል፡፡
በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምባሆ(ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶች እና ሱስ አስያዥ ዕፆች ትምህርት ቤት አካባቢ መሸጥም ሆነ ይዞ መገኘትን ይከለክላል።
👉የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፣
👉የሲጋራ መሻጫ ሱቆች፣
👉ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣
👉ጭፈራ ቤቶች፤ ቁማር ቤቶች፤
👉የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና
👉የሰውነት መታሻ ወይም ማሳጅ ቤቶች በትምህርት ቤቶች በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ መክፈት አይቻልም፡፡
👉ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣
👉ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ፣ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና
👉የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም በትምህርት ቤት አቅራቢያ መክፈትን ከልክሏል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
ኢትዮ-መረጃ

❤27👍8