Legal Aid
1.47K subscribers
612 photos
6 videos
53 files
144 links
⚖️ Legal Aid: Your essential hub for legal professionals and students! Stay updated on new laws, landmark judgments, vacancies, and key insights. Join us to empower your legal journey and connect with the community! 📚"
Download Telegram
ገበን ፈፂሙ ተባሂሉ ዝተጠርጠረ ሰብ ምርመራ መዝገቡ ተፃርዩ ናብ ዓቃቢ ሕጊ ምስ ሓለፈ ዓቃቢ ሕጊ ኣብዚ ጉዳይ ተጠርጣሪ ካብ ዝክሰስ ምስክር ተዝኮን ነቲ ፈፃመ ገበን የርድእ እዩ ኢሉ እንተኣሚኑ ምስክር ክኮን ንምግባር ዝክልክል ሕጊ ከም ዘየለ ፌደራል ሰበር ሰማዒ ቤት ፍርዲ ኣብ ቅፅ12 ሰ/መ/ቁ57988 መገደዳይ ናይ ሕጊ ትርጉም ሂብሉ እዩ።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዳኝነት ሥልጣን (Jurisdiction) ላይ በርካታ አስገዳጅ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። ዋና ዋና ውሳኔዎችና አቋሞች የሚከተሉት ናቸው፦

1. የሥልጣን ጥያቄ በማንኛውም የክርክር ደረጃ እንደሚነሳ !!

ሰበር ሰሚ ችሎት በተለያዩ መዛግብት (ለምሳሌ ቅፅ-9 በመ.ቁ. 36730) ላይ እንደገለጸው፣ የአንድ ፍርድ ቤት የቁሳዊ (Material) የዳኝነት ሥልጣን ጉዳይ የመሠረታዊ ሕግ ስህተት የሚታይበትና በማንኛውም የክርክር ደረጃ (በይግባኝም ሆነ በሰበር) ሊነሳ የሚችል ጉዳይ ነው። ተከሳሹ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ባያነሳው እንኳ፣ ፍርድ ቤቱ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሲባል በራሱ ተነሳሽነት ሊመረምረው ይገባል የሚል አቋም አለው።

2. የአካባቢያዊ ሥልጣን እና የፍትሕ መጓደል !!

ችሎቱ በአካባቢያዊ (Local) ሥልጣን ላይ ያለው አቋም ከቁሳዊ ሥልጣን የተለየ ነው። የሰበር ችሎቱ የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 9 እና 21ን መሠረት በማድረግ የሚከተሉትን ነጥቦች ያጸናል፦

• ተከሳሹ በመጀመሪያው የክርክር ደረጃ ላይ መቃወሚያ ካላቀረበ፣ የአካባቢያዊ ሥልጣን ጥያቄው እንደታለፈ (Waived) ይቆጠራል።

• በአካባቢያዊ ሥልጣን ጉድለት ምክንያት ብቻ አንድ ውሳኔ አይሻርም፤ ውሳኔው ሊሻር የሚችለው ተከሳሹ በጊዜው ተቃውሞ አቅርቦ ሳይቀበሉት ሲቀርና ይህም በውሳኔው ላይ "የፍትሕ መጓደል" (Failure of Justice) ማስከተሉ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

3. የፌዴራል እና የክልል ፍርድ ቤቶች የሥልጣን ክፍፍል

በቅርብ ጊዜ በወጡ የሰበር ውሳኔዎች (ለምሳሌ:- ቅፅ-21 በመ.ቁ. 144242 እና መሰል መዛግብት) ላይ ችሎቱ የሚከተሉትን መርሆዎች አስቀምጧል፦

• የፌዴራል ጉዳይ ሆኖ ሳለ በክልል ፍርድ ቤት ከታየ፣ ይህ የቁሳዊ ሥልጣን ጥሰት ስለሚሆን ውሳኔው መሠረታዊ የሕግ ስህተት እንዳለበት ይቆጠራል።
• ልዩ ሥልጣን ለተሰጣቸው አካላት (ለምሳሌ ለአስተዳደር ጉባዔዎች ወይም ለልዩ ፍርድ ቤቶች) የተሰጠ ጉዳይን መደበኛ ፍርድ ቤት አይቶት ቢወስን፣ ተከሳሹ መቃወሚያ ባያነሳም ውሳኔው በሥልጣን ጉድለት ይሻራል።

4. የውጭ አገር ዜጎችን የሚመለከት ሥልጣን

በአገር አቀፍ ደረጃ ያለን የዳኝነት ሥልጣን በተመለከተ፣ የሰበር ችሎቱበቅፅ-23 በመ.ቁ. 146955 እና መሰል መዛግብት ላይ እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳዩ እንዲታይ የሚያደርግ በቂ ግንኙነት (ለምሳሌ ውሉ የተፈጸመበት ወይም ጉዳቱ የደረሰበት ቦታ ኢትዮጵያ ከሆነ) ካለ፣ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን እንዳላቸው ይወስናል።

ማጠቃለያ፦

ተከሳሹ መቃወሚያ ባያነሳም እንኳ የቁሳዊ ሥልጣን (ለምሳሌ የፌዴራል ጉዳይን ክልል ፍርድ ቤት ማየቱ) ካልተከበረ ውሳኔው በሰበር ሊሻር ይችላል። ነገር ግን የአካባቢያዊ ሥልጣን (ለምሳሌ የአዲስ አበባ መሆን ሲገባው አዳማ መታየቱ) ከሆነ ተከሳሹ በጊዜው ካልተቃወመ ውሳኔው ጸንቶ ይቆያል።
2👍2
⚖️ ወሳኝ የሰበር ዉሳኔ መ.ቁ 208644
• በወንጀል ጉዳይ የሚቀርበው ማስረጃ በማስረጃነት እንዳይቀርብ በህግ በልዩ ሁኔታ ካልተከለከለ በቀር ስለ ድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያረጋግጥ የሚችል ማናቸውም ማስረጃ ሊቀርብ ይቻላል.
* አንድን የቀረበ የወንጀል ክስ ለማረጋገጥ የሚያስችሉትን ማስረጃዎች የመለየት እና የመወሰን ስልጣኑ የዓቃቤ ሕግ በመሆኑ ክሱን ያረጋግጡልኛል ያላቸውን ማስረጃዎች እስካቀረበ ድረስ የቀረቡት ማስረጃዎች በእርግጥም ክሱን በህግ በተቀመጠው የማስረዳት ደረጃ የሚያረጋግጡ መሆን ያለመሆናቸው ከሚመዘን በቀር አንድን የማስረጃ አይነት ለይቶ “ካላቀረብክ” ተብሎ የሚገደድበት የህግ አግባብ የለም.
*ብዙ ጊዜ ፍርድ ቤቶች የግል ተበዳይ በምስክርነት ካልቀረበ እንዲሁም በአካል ላይ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች የሕክምና ማስረጃ ካልቀረበ የሚል የተሳሳተ አቋም በመያዝ ትዕዛዝ ይሰጣሉ.

የኢ.ፌ .ዴ .ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 19(5) እና የወንጀል ህግ ሥነሥርዓት ቁጥር133,134, 137,141,149
👍31
የምስራች፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዳኞች አዲስ የጥቅማጥቅም መመሪያ ጸደቀ!
####
​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የፍትህ አካላት ሲጠባበቁት የነበረው የጥቅማጥቅም ማሻሻያ በይፋ ስራ ላይ መዋሉ ተረጋግጧል። ይህ መመሪያ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የፍርድ ቤት የስራ ኃላፊዎችን፣ ዳኞችን እና በጉባኤው የሚተዳደሩ ባለሙያዎችን ሁሉ የሚያካትት ነው።
​ የካቲት 16/2018 ዓ.ም በተካሄደው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት አስተዳደር ዋና ጉባኤ 6ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ስብሰባ።
​በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አንዷለም አምባዬ አቅራቢነት በጉባኤው ፀድቋል
​መመሪያው በዞን እና በሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች ለሚገኙ ሁሉም የፍትህ አካላት ተሰራጭቷል።
​ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/06/2018 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ መሰረት፣ ክፍያው ከየካቲት ወር መጀመሪያ ጀምሮ ታስቦ የሚፈጸም ይሆናል።
​የዳኞችን እና የባለሙያዎችን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል፣ የፍትህ ስርዓቱ በነጻነት እና በብቃት እንዲሰራ ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
​"ፍትህ በነጻነት እንድትሰፍን የዳኞች ጥቅማጥቅም መከበር መሰረታዊ እርምጃ ነው!"
#ደቡብ_ኢትዮጵያ #የፍትህ_ስርዓት #የዳኞች_ጥቅማጥቅም #ኢትዮጵያ #SouthEthiopia #JudiciaryReform #EthiopiaNews
👍31👏1
ውሳኔ ለመስጠት በሚል ጉቦ በመቀበል የተጠረጠረች የፍርድ ቤት ዳኛ ተከሰሰች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳሪክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆነችውን ቴዎብስትያ ጌታቸው (የቀድሞ ስሟ ቃልኪዳን) ላይ የሙስና ወንጀል ክስ መሰረተ።

ተከሳሿ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና ቁጥር (2) ስር የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፏን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ ዝርዝር ክስ አቅርቧል።

ተከሳሽ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ 1ኛ የቤተሰብ ችሎት ዳኛ ሆና ስትሰራ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በስራ ኃላፊነቷ የተሰጣትን ሥልጣንና የተጣለባትን አደራ ወደ ጎን በመተው ውሳኔ ለመስጠት ጉቦ ጠይቃ የተቀበለችውን ገንዘብ እንዳስቀመጠች እጅ ከፍንጅ መያዟን በክሱ ዝርዝር ላይ ተገልጿል።

በዚህ መሰረት ተከሳሿ የማይገባትን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በሁለት ተከራካሪ ግለሰቦች መካከል በችሎት በነበረው የባልና ሚስት ንብረት ክርክር ላይ አመልካች ንብረቱ በግሌ ያፈራሁት ነው በሚል ያቀረበችውን አቤቱታ ተጠሪ ያመነ በመሆኑ ክስ መስማት ሳያስፈልግ ውሳኔ ለመስጠት በየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ይዛ እያለ፣ በቀጠሮ ቀን አመልካች በችሎት ስትቀርብ ተከሳሽ አመልካችን "የአንቺ ጉዳይ በቢሮ ነው የሚታየነው" በማለት በቢሮ እንድትቀርብ ማድረጓ በክሱ ላይ ተመላክቷል።

በዚህ መልኩ ተከሳሿ በቢሮ ባለጉዳይዋን እንድትቀርብ ካደረገች በኋላ ጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለማስጠት 600 ሺህ ብር እንድትከፍላት የጠየቀቻት እና አመልካችም ይህንን ያህል ገንዘብ የመክፈል አቅም እንደሌለት ስትገልጽላት 'እስበሽበት ነይ" በማለት በሚቀጥለው ቀን በቢሮ እንድትቀርብ የቀጠረቻት መሆኑ በክስ ዝርዝሩ ላይ ሰፍሯል።

በዚህም አመልካች ጉዳዩን ባለቤቷ ለሆነው ግለሰብ በማሳወቋ ባለቤቷም ምንም አይነት ገንዘብ እንዳትከፍል በመምክር አመልካች በቀጠሮ ቀን በድጋሚ በቢሮ ስትቀርብ ተከሳሽ የጠየቅችውን ገንዘብ አመጣሽ ወይ ብላ በመጠየቅ አመልካችም ገንዘቡን መክፈል እንደማትችል በምትጠልጽበት ጊዜ ተከሳሽ ዳኛ በመጨረሻም 100 ሺህ ብር እንድትከፍል በመጠየቅና የተጠቀሰውን ገንዘብ ለመቀበል በመስማማት በየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የግል ተበዳይ ገንዘቡን ይዛ ስትመጣ ውሳኔው እንደሚሰጣት መናገሯ ተጠቅሷል።

ከዚህም በኋላ አመልካችም አስቀድማ ለህግ አስከባሪ አካላት ባሳወቀችው መሰረት በመጋቢት 01 ቀን 2018 ዓ.ም የተጠየቀውን 100 ሺህ ብር ለተከሳሽ በቢሮዋ በመስጠት ተከሳሽም ገንዘቡን ተቀብላ ባስቀመጠችበት ቅጽበት እጅ ከፍንጅ የተያዘች መሆኑን በመጥቀስ፤ ተከሳሿ ያላትን የዳኝነት ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም ስልጣንን ያለአአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽማለች ሲል ዐቃቤ ሕግ ክሱን አቅርቧል።

በተጨማሪም በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 113 ንዑስ ቁጥር (1) መሰረት በአማራጭነት ሌላኛውን ማለትም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 11 ንዑስ ቁጥር (2) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ የወንጀል ድርጊቱን አካትቶ ዝርዝር ክስ አቅርቦባታል።

ተከሳሿች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ቀርባ የተመሰረተባት የክስ ዝርዝር እንዲደርሳት ተደርጓል።

በታሪክ አዱኛ
4
''የግል ሆስፒታሎች/ማህበራት ህዝባዊ ድርጅት ሆነው በሙስና አዋጅ 881/2007 ስር ይገባሉ"!!

የጥያቄዎ ዋና ይዘት በኢትዮጵያ ውስጥ የሙስና ወንጀል ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥረሰ 881/2007 ወይም ተመሳሳይ አዋጅ) አንድ ድርጅት ህዝባዊ ድርጅት (Public Organization) ሆኖ ይቆጠራል ወይስ አይቆጠርም በሚለው ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠውን የሰበር ውሳኔ መረዳት ነው።

ይህ ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 881/2015 (የሙስና ወንጀሎች አዋጅ) አንቀጽ 2(5) ላይ የተመሰረተ ነው።

አዋጁ ህዝባዊ ድርጅትን እንዲህ ይገልጻል፡-

ከአባላት ወይም ከህዝብ በማንኛውም መንገድ ገንዘብ፣ ንብረት ወይም ሌላ ሃብት የሚሰበስብና የሚያስተዳድር የግል ዘርፍ አካል (ኩባንያ ወይም ድርጅት)።
ይህ ማለት ብዙ የግል ኩባንያዎች፣ ማህበራት፣ ኮኦፕራቲቭስ ወይም ሆስፒታሎች (በተለይ ከህዝብ ገንዘብ የሚሰበስቡ) በዚህ ህግ ስር ሊገቡ ይችላሉ።

ይህም በግል ዘርፍ የሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎችን (ብልሹ ግንኙነት፣ ስልጣን መጠቀም፣ ገንዘብ መቀበል ወዘተ) ለመቆጣጠር ያለመ ነው።

* የሰበር ውሳኔ ምሳሌዎች እና አቀራረብ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። በተለይ አንዳንድ ውሳኔዎች (በተለይ ሆስፒታል ወይም ተመሳሳይ ድርጅቶችን በተመለከተ) በአብላጫ ድምጽ ድርጅቱን ህዝባዊ ድርጅት ብሎ ይቆጥራል።

ይህም ማለት በዚህ ህግ ስር ሰራተኞቹ/አስተዳዳሪዎቹ በሙስና ወንጀል ሊጠየቁ ይችላሉ።

* የውሳኔው ዋና ይዘት (ከኦፊሴላዊ ማጣቀሻ በመውጣት)
- ጉዳዩ፡ በሐረር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጀመረ የወንጀል ክርክር (የሙስና ወንጀል ክስ)። ተጠሪዎች (እነ ቤተልሄም ጌቱ አለሙ እና ሌሎች) በሆስፒታሉ አስተዳደር ውስጥ የተሰማሩ ሲሆኑ፣ የተከሰሱት በአዋጅ 881/2015 መሰረት የሙስና ወንጀሎች (እምነት ማጉደል፣ ብልሹ ግንኙነት ወዘተ) ነው።

- የሰበር ውሳኔ፡ በአብላጫ ድምጽ (majority) ሆስፒታሉ/ማህበሩ ከአባላት እና ከህዝብ በተሰበሰበ ገንዘብ/አክሲዮን የተቋቋመ በመሆኑ ህዝባዊ ድርጅት ተብሎ ተቆጥሯል። ስለዚህ አስተዳዳሪዎቹ/ሠራተኞቹ በዚህ አዋጅ ስር በሙስና ወንጀል ሊጠየቁ ይችላሉ።

- የልዩነት ሀሳብ (Dissenting Opinion)፡ አንድ ዳኛ ተቃውሞ ሰጥቷል። አዋጁ በግል ዘርፍ ላይ ቢያተኩርም፣ ህዝባዊ ድርጅት ለመሆን በምንጭ (source) እና ዓላማ (purpose) መሞከር አለበት ብሎ ተከራክሯል። ሆኖም አብላጫው ችሎት ውሳኔውን ተቀብሏል።
5
⚖️ ​በስርቆት ወንጀል አንድ ተከሳሽ "ሰርቋል" ለመባል ንብረቱን መንካት፣ መቁረጥ...ወዘተ ብቻውን በቂ ነውን? ወይንስ ንብረቱ የግድ ወደ ተከሳሹ ይዞታ መግባት አለበት?
*

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 230945 ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል።
🔍 የይዞታ ለውጥ (Possession) እና ስርቆት
​በወንጀል ህግ አንቀፅ 665 መሠረት፣ ስርቆት የሚፈፀመው አንድን ዕቃ አንስቶ በመውሰድ (Taking away) እና በራስ ይዞታ ስር በማድረግ ነው። ይህ ማለት፦
​ንብረቱ ከባለቤቱ ቁጥጥር መውጣት አለበት። ​ንብረቱ ወደ ወንጀል አድራጊው ይዞታ መግባት አለበት።
📍 የሰበሩ ክርክርና ውሳኔ
​በዚህ መዝገብ ላይ ተከሳሹ የኤሌክትሪክ ፖል (ምሶሶ) ብረትን በመጋዝ ሲቆራርጥ እጅ ከፈንጅ ተይዟል።
​የበታች ፍርድ ቤቶች እይታ፦ ብረቱን ለመስረቅ መቁረጥ መጀመሩ "ፍፃሜ ያገኘ ስርቆት" ነው በሚል ጥፋተኛ አድርገውት ነበር።
​የሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም፦ ተከሳሹ ብረቱን እየቆረጠ እንጂ አንስቶ አልወሰደም። ንብረቱ ገና ከምሶሶው ተለይቶ ወደ ተከሳሹ ቁጥጥር (ይዞታ) አልገባም።
💡 ዋናው የህግ ነጥብ
​ድርጊቱ በቆረጣ ላይ እያለ መቋረጡ፣ የይዞታ ለውጥ (Change of Possession) እንዳልተከናወነ ያሳያል። በመሆኑም፦
​ንብረቱ ወደ ተከሳሹ እጅ ካልገባ ድርጊቱ "የስርቆት ሙከራ" (Attempt) እንጂ ፍፃሜ ያገኘ ወንጀል ሊባል አይችልም።
​በመሆኑም ተከሳሹ በወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1) እና 669(1)(ለ) መሠረት በስርቆት ሙከራ ብቻ ሊቀጣ ይገባል ሲል ወስኗል።

📢 ማጠቃለያ፦ አንድን ንብረት ለመስረቅ መሰናዳት ወይም ንብረቱን ለመውሰድ የሚያስችል ተግባር ላይ እያሉ መያዝ (ለምሳሌ፡ መቁረጥ፣ መፍታት...) ነገር ግን ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሎ አለመውሰድ በህጉ በ"ሙከራ" ደረጃ የሚያስቀጣ ተግባር ነው።
6
የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ስራ አስኪያጅ ተከሰሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ማስታወቂያ በማስነገር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እናስረክባለን በማለት ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ከተበዳዮች የሰበሰበው ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ስራ አስኪያጅ የሆነው ዳንኤል ዮሐንስ ክስ ተመስርቶበታል።

ተከሳሽ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32 ቁጥር 1 ሀ እና ለ እንዲሁም አንቀጽ 35፣ 38 እንዲሁም የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀፅ 10 ቁጥር 1 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ነው ክስ የተመሰረተበት።

ተከሳሽ ለጊዜው ካልተያዙ ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን ኮምፒውተርን ወይም የኮምፒውተር ስርዓትን በመጠቀም አሳሳች ዳታ በማሰራጨት፣ የራሳቸውን በመሰወር ወይም መግለፅ የሚገባቸውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት በመጠቀም፣ ሌላውን ሰው አታልለው የተበዳይን ጥቅም የሚጎዳ ድርጊት እንዲፈፀም ለማድረግ በማሰብ ወንጀል ለመፈፀም ባደረጉት ስምምነት መሰረት የወንጀል ድርጊት መፈጸማቸውን ዐቃቤ ሕግ በክስ ዝርዝሩ ላይ አመልክቷል።

በዚህም ተከሳሽ በ2013 ዓ.ም በመጀመሪያ ሄሎ ታክሲ እና ሄሎ መኪና የተባሉትን ድርጅቶች ካቋቋመ በኋላ ድርጅቱ የታክሲ ሥራን ለማዘመን ዘመናዊ መኪኖችን ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች እና ከውጭ ሀገር በማስመጣት እንዲሁም በመገጣጠም በመንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣን (ሚኒስቴር) ባወጣው መመሪያ መሰረት አሁን ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ለታክሲ ፈላጊዎች ዘመናዊ ታክሲ በዱቤ እናቀርባለን በሚል አሳሳች መረጃዎችን አሰራጭተዋል ብሏል በክሱ።

በመረጃው መሰረት ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች ተከሳሽ እና የተከሳሽ ድርጅት በተለያዩ በመንግሥት፣ በግል እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን ማስታወቂያዎችን በመመልከት ወደ ድርጅቱ የሄዱ የግል ተበዳዮች በዱቤ ሰርታችሁ ትርፋማ የምትሆኑበትን ታክሲ ገንዘቡን በከፈላችሁት በ3 ወር ውስጥ እናስረክባቸዋለን በማለት 60 ሺህ ብር ለመመዝገቢያ፣ ከመኪናው ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ ወይም 247 ሺህ 500 ብር በድርጅቱ አካውንት ላይ ገቢ እንዲያደርጉ በማድረግ የግል ተበዳዮች እምነት እንዲጥሉባችው ለማድረግ እና በረቀቀ መንገድ ወንጀሉን ለመፈፀም እንዲያመቻቸው ውል በማርቀቅ እና በድርጅቱ በተረቀቀው ውል ላይ እንዲፈርሙ ማድረግ የሚል በክሱ ላይ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የመኪኖቻችውን ሻንሲ እና ሞተር ቁጥር ስለመጣ ፈርማችሁ ውሰዱ በማለት ከሄሎ ታክሲ ከሚል ድርጅት የሞተር እና ሻንሲ ቁጥር ላይ ፈርመው እንዲወስዱ ካደረገ በኋላ ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ተቀብሎ መኪናውን ሳያስረክብ ድርጅቱን ዘግቶ መሰወር በክሱ ላይ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ነው።

እንዲሁም ተከሳሽ ግርማይ ገ/ሚካኤል ከተባለው (አስካል የተባለውን ድርጅት በማቋቋም በድርጅቱ ስም በ2002 ዓ.ም በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዲታደሙ ወደ ደቡብ አፍሪካ እልካቸዋለሁ በማለት ብር በመቀበል ተሰውሮ በኢንተርፖል የተያዘ) ለጊዜው ካልተያዘው ግብረ-አበር ጋር በመሆን ከዚህ በፊት ከላይ የፈፀሙትን እና ከላይ የተገለፀውን ወንጀል በሰፊው ለመፈፀም በሕጋዊ፣ በንግድ እና ውል ሽፋን ስም በተለምዶ የነጭ ኮሌታ ሳይበር አታላዮች የሚፈፅሙት ወንጀል ለመፈፀም እንዲያመቻቸው ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለውን ድርጅት በተሽካርከሪዎች አስመጪነት፣ በተሽካርከሪዎች መለዋወጫ፤ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን እና ጌጣጌጦች አስመጪነት እና የተሽካርከሪዎች ከአካላት እና ተሳቢዎች አስመጪነት 7 ሚሊየን ብር ካፒታል በማቋቋም ከአዲስ አበባ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ በግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ ያወጡ መሆኑ፤ ድርጅታችን የኤሌክትሪክ መኪኖችን በቀጥታ ከቻይና ቢዋይዲ ኩባንያ በማስመጣት በጠቅላላ ዋጋ 1 ሚሊየን 900 ሺህ ብር ለደንበኞች በ50 በመቶ ወይም 950 ሺህ ብር ቅድሚያ ክፍያ እና ቀሪው የ50 በመቶ በዱቤ ሽያጭ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለደንበኞች በማስረከብ ላይ ይገኛል፤ ማንኛውም ተቋም ያላደረገውን ቀሪውን 950 ሺህ ብር 50 በመቶ ያለወለድ በ5 ዓመት ውስጥ ከፍለው የሚጨርሱበት አሰራር በመዘርጋት የመኪና ባለቤት ሊያደርጋችሁ ተዘጋጅቷል፤ ስለዚህ ተመዝግበው በ3 ወር ውስጥ የመኪና ባለቤት ይሁኑ የሚሉ ማስታወቂያዎችን በማሰራት።

በኦሮሚያ ባህል ማዕከል፣ በስካይ ላይት ሆቴል፣ በመስቀል አደባባይ እና በወዳጅነት አደባባይ እንዳስረከቡ የሚያሳይ ቪድዮ እና ፎቶ በመልቀቅ እና በማሳየት እስካሁን ከ450 በላይ መኪኖችን ለተመዝጋቢዎች ያስረከበ መሆኑን፤ አሁንም ለደንበኞቻችን ለማስረከብ ወደ 400 መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ እያጓጓዝን እናገኛለን፤ ኑ እና ከፍለው ቀሪውን 950 ሺህ ብር ያለወለድ እየከፈሉ የመኪና ባለቤት ይሁኑ፤ ለመኪናው ለ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን፤ ድርጅታችን ከፀሐይ ኢንሹራንስ ጋር የኢንሹራንስ ውል ገብቷል፣ ከባንክ ጋር አገናኝተናል” በማለት የተለያዩ ማስታወቂያዎችን በታዋቂ ግለሰቦች፣ ታዋቂ አርቲስቶችን፣ ቲክቶከሮችን፣ የመንግሥት እና የግል ሚዲያዎችን እንዲሁም የራሳቸውን ሚዲያ ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ማስታወቂያውን በማሰራጨት በርካታ ሰዎች በተከሳሽ እና በተከሳሽ ድርጅት የተሰራጨውን ትርፋማ የምትሆኑበትን ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እናቀርባለን የሚል አማላይ እና አሳሳች ማስታወቂያዎችን በመመልከት በርካታ ግለሰቦች ወደ ድርጅቱ ሄደው በመመዝገብ ቅድመ ክፍያ 950 ሺህ ብር ከከፈሉ በኋላ በማስታወቂያ ላይ ከተነገረው ገንዘብ 950 ሺህ ብር በተጨማሪ (ተጨማሪ እሴት ታክሲ) በሚል 285 ሺህ ብር እና ለቦሎ እና ለታርጋ ተብሎ ከ130 ሺህ ብር እንዲከፍሉ አድርገዋል ሲል ዐቃቤ ሕግ በክሱ ዝርዝር ላይ አመልክቷል።

በአጠቃላይ 1 ሚሊየን 365 ሺህ ብር በማስከፈል በ3 ወር ውስጥ መኪና እናስረክባለን በማለት በተከሳሽ እና በተከሳሽ ድርጅት በተረቀቀው ውል ላይ እንዲፈርሙ በማድረግ እንዲሁም በ3 ወር ውስጥ መኪና አስረክባቸዋለሁ በማለት ከ1 ሺህ 430 በላይ ግለሰቦችን በመመዝገብ ከእያንዳንዱ ተመዝጋቢ ከብር 950 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 86 ሚሊየን ብር በላይ ሰብስበው 100 መኪኖችን ለራሱ፣ ግብረ-አበሩ እና የጥቅም ተጋሪ ለሆኑ ግለሰቦች ብቻ አስረክቦ ሳለ በሚዲያዎች ከ520 በላይ መኪኖችን አስረክበናል በማለት አሳሳች መረጃዎችን በመናገር ግለሰቦች ቀርበው እንዲመዘገቡ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ሲያደርግ ነበረ በሚል 19 ተደራራቢ ክሶች ተመስርተውበታል።

የክስ መዝገቡን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ነው።

በመቅደስ ከበደ
3
vacancie for lawyers
👎21
የ2 ጠበቆች ወግ

አንዲት ደምበኛዬ ታስራ ላገኛት የፌደራል ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ነበረብኝ፤ ጠበቃ ነኝ ብዬ ልገባ ስል ፖሊሱ እንደ ምስኪን ተኮልኩለው መንገድ ዳር እየጠበቁ ያሉትን ጠበቆች እያሳየኝ "ወደዛ ሂድና ጠብቅ " አለ እያመናጨቀኝ። ሌላውም ፖሊስ ይመጣና ወደዛ ራቅ በሉ እያለ ሊያባርርም ይሞክራል።
ከየት የመጣ ልምድ እንደሆነ አላውቅም ብቻ ጠበቃ ለነሱ እንደ አንድ የፍትህ አጋር አይደለም፤ እንደሰው እንኳን የማይታይ ጠላት ነው የሚመስላቸው (እርግጥ ነው ከዐቃቤ ህጎችም ጋር የ inferiority complex እንዳለባቸውና ለመታዘዝ እንደሚያቅማሙ አውቃለሁ) ጠበቆች ላይ የሚያሳዩት ባህሪ ግን ከትግስት በላይ ነው።

እንደ አጋጣሚ ከሰሞኑ ግርግር ጋር በተያያዘ የታሰሩ አርቲስቶችንም እያየኋቸው ነበር፤ እውነት ነው የማንም ታራሚ ክብር መነካት የለበትም። ግን (እነሱ እንግዲ ታሳሪ ናቸው፤) እንዲያው እንዴት ከእነሱ ያነሰ መስተንግዶ ሊሰጠን ይገባል?🥺(ቱ! ከጨነቀው ሰው ጋር አነካኩኝ)

እየተነጫነጭኩ ወጥቼ ስሄድ ስክን ያለውን ጠበቃ ወዳጄን አገኘሁት። በጣም አንባቢና የተረጋጋ አዋቂ ሰው ነው፤ በዚህ ጉዳይ ግን መረጋጋት አልቻለም። በአንድ ወቅት ከቅንጅት ፓርቲ አመራሮች እስር ጋር በተያያዘ አንድ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ፍ/ቤት ገብቶ ያስተዋለውን አስታውሶኝ ተብሰከሰክን። "የኢትዮጵያ ጠበቆች ፖሊስ እንኳን ሲፈልግ የሚያባርራቸው፣ ፍ/ቤት ውስጥ እንደተከሳሽ የሚገላምጧቸው ምስኪኖች ናቸው" ነበር ያለው።

ፍርሀተኞች ስለሆንን ነው አለኝ ወዳጄ፤ የሳንቲም ሽርፍራፊ እንጂ መብት፣ ክብር የሚባለው ነገር የማይገባን ሆነናል።

የሌሎች አገሮች የጥብቅና ማህበራት እንዴት መብታቸውን እንደሚያስከብሩ ታውቃለህ? ሲል ጠየቀኝ፤ አላውቅም አልኩት፤ ያብራራልኝ ጀመር።

አሜሪካ (ABA Standards) በአሜሪካ ጠበቃ Officer of the Court (የችሎት መኮንን) ነው። በሕገ-መንግሥቱ 6th Amendment መሠረት፣ አንድ ጠበቃ ደንበኛውን በፈለገው ሰዓት የማግኘት መብቱ የማይገረሰስ ነው። ፖሊስ ጠበቃን ካገተ ወይም ካመናጨቀ "Civil Rights Violation ተብሎ በከባድ ካሳና በሥራ ስንብት ይጠየቃል።
እንግሊዝ (Bar Council) በእንግሊዝ የጠበቆች ማኅበር (Bar Council) እጅግ ኃያል ነው። አንድ ፖሊስ በጠበቃ ላይ ተገቢ ያልሆነ ግፊት ካሳየ፣ ማኅበሩ ወዲያውኑ ምርመራ እንዲከፈት የማድረግና ፖሊሱን ከሥራ እስከማባረር ያለ ተጽዕኖ አለው።

ደቡብ አፍሪካ (LSSA)- የደቡብ አፍሪካ የጠበቆች ማኅበር (Law Society of South Africa) የመንግሥት የፍትህ አካላት በጠበቆች ላይ የሚያሳዩትን ማንኛውንም ንቀት በሕግ ይፋለማል።
ፈረንሳይ፣ ኬኒያ.....
ጠበቃ እዛ አገር የፍትህ ምሰሶ እንጂ የፖሊስ ሲሳይ አይደለም።

ጠበቃ ነኝ ብለህ ፖሊስ ጣቢያ ስትደርስ፣ ዘበኛው ፖሊስ እንደፈለገ የሚሾፍርህ ከሆነና ዛሬ አይገባም ብሎ እንደ ደጅ ጠኚ ካንገላታህ፣ የፍትህ ሥርዓታችን ገደል ገብቷል ማለት ነው። እኛ ጠበቆች የሰው መብት እናስከብራለን እያልን እንፎክራለን እንጂ፣ የራሳችንን መብት እንኳ በፖሊስና በሬጅስትራር ፊት ማስከበር አቅቶን ከኩሊ ያልተሻለ ሚና ነው ያለን።

ተበሳጨው፤ ጎራውና... ማለትም ቃጣኝ
.
ብቻ ግን ከአዲሱ የጠበቆች ማኅበር ምን ይጠበቅበታል? Hailu Hasena
አዲሱ ማኅበር የቢሮ ጉዳይ ላይ ብቻ ከመመሰጥ፣ የጠበቃውን ሞራልና ክብር የሚያስመለስ "National Protocol በአስቸኳይ መቅረጽ አለበት። ፖሊስ ዛሬ ሰኞ ስለሆነ ግባ ምናምን.. የሚልበት ሳይሆን፣ ጠበቃው በመታወቂያው ብቻ እንደ የፍትህ አካል የሚከበርበት አሠራር ካልተዘረጋ ሙያው መሳለቂያ መሆኑ አይቀርም።

የራሱን መብት ሳያስከብር፣ የሌላውን ላስከብር የሚል ጠበቃ ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል!

ጓዶች ብታምኑም ባታምኑም ተደፍረናል ተንቀናል💪☹️
👉 Lawyer Fikerslase Mitiku እንዳጋራን እንደወረደ የተወሰደ ነው🙏👏
👉 የኢፌዴሪ ፍትህ ሚ/ርና ፌዴራል ፖሊስ ትኩረት ቢሰጡት ጥሩ ነው። አብዛኛው ፖሊስ ይሁን ዐቃቤ ህግ ጠበቆችን ይሁን ህ/ቡን አክባሪ ናቸው አንዳንዶቹ ግን ለጠበቃ ያላቸው አመለካከት ትክክል አይደለም እሱም ነገ ጠበቃ እንኳን ባይሆኑ ተገልጋይ መሆናቸው አይቀርም⚖️⚖️
👍6
የሕግ ትምህርት የመማር ፍላጎት ላላችሁ የሚሆን መረጃ:

​በኢትዮጵያ የሕግ ትምህርት ቤቶች ኮንሶርቲየም በ2013 ዓ.ም (2021 እ.ኤ.አ) በወጣው የተሻሻለው ብሔራዊ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት፣ ወደ ሕግ ትምህርት ቤት (LL.B ፕሮግራም) ለመግባት የተቀመጡ መስፈርቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ።

​በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ተማሪ ለውድድር ብቁ ለመሆን ዝቅተኛውን መስፈርት ማሟላት ይኖርበታል። ይህም የመጀመሪያ ሴሚስተር የዩኒቨርሲቲ ውጤት (GPA) ለወንድ ተማሪዎች 3.0 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፣ ለሴት ተማሪዎች፣ ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ከታዳጊ ክልል ለመጡ ተማሪዎች ደግሞ 2.75 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል። በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ውጤት 50% እና ከዚያ በላይ መሆኑ ለብቁነት የግድ ነው።

የቅበላ ነጥብ አያያዝን (Weighting) በተመለከተ ደግሞ ምደባው በውድድር ላይ የተመሰረተ ሆኖ የውጤት ድርሻው 50% ከዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ሴሚስተር GPA፣ 30% ከሕግ ትምህርት ቤት የመግቢያ ፈተና፣ እንዲሁም 20% ከብሔራዊ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የሚሰላ ይሆናል። ለአዎንታዊ ድጋፍ (Affirmative Action) የሚገባቸው ተማሪዎች ደግሞ ተጨማሪ 5% እድል ይሰጣቸዋል።

​ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው ነጥብ፣ ተማሪዎች ቁጥራቸው አነስተኛ በሚሆንበት ጊዜ ትምህርት ቤቶቹ መስፈርቱን ዝቅ ሊያደርጉ ቢችሉም፣ በማንኛውም ሁኔታ ውጤቱ ለወንድ ተማሪዎች ከ 2.8 እንዲሁም ለሴት፣ ለአካል ጉዳተኛና ከታዳጊ ክልል ለመጡ ተማሪዎች ከ 2.6 በታች ዝቅ ሊል አይችልም።

በአጠቃላይ ዝቅተኛውን መስፈርት ማሟላት ብቻውን ወደ ሕግ ትምህርት ቤት ለመግባት ዋስትና አይሆንም። ቅበላው በተቋማቱ የመቀበል አቅም እና በውድድር ላይ የተመሰረተ መሆኑን ማወቅ ይገባል።

​ለተከታታይ ትምህርት (Continuing Education) ፕሮግራም ደግሞ የመግቢያ መስፈርቱ የሚወሰነው በእያንዳንዱ የሕግ ትምህርት ቤት የቅበላ ኮሚቴ (Admission Committee) ነው። ኮሚቴው መስፈርቶቹን ሲያወጣ የጾታ ስብጥርን እና ለመደበኛው ፕሮግራም የተቀመጡ የመግቢያ መስፈርቶችን አግባብነት ባለው መልኩ ግምት ውስጥ ያስገባል።

ለሕግ ትምህርት ፍላጎቱ ላላችሁ ሁሉ ይህ መረጃ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የቀረበ ነው።

https://t.me/Aid432
5
‎መጋቢት 22/5018 ዓ.ም

‎ክፍት የሥራ ማስታወቂያ፤

‎ዕለተ ማክሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
‎( የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዝብ ግንኙነት)
‎በጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውስጥ በአሉት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ የዋና ሬጅስትራር እና ረዳት ዳኛ መስፈርቶችን ወይም ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟሉትን የሕግ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለማሾም በወጣው ማስታወቂያ መሠረት በመመዝገብ እንድወዳደሩ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ንዑስ ዳኝነት አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ይጋብዛል ።

‎@ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዝብ ግንኙነት
‎ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
‎ ዲላ፤
ሐሰተኛ ሰነድ በመፍጠር ወይም በመገልገል ወንጀል ላይ የተሰጠ አዲስ የሰበር ውሳኔ
​የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅርቡ (ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም) በመዝገብ ቁጥር 247213 በሰጠው ውሳኔ፣ በሀሰተኛ ሰነድ ክስ ሂደት ውስጥ ሊሟሉ ስለሚገቡ ማስረጃዎች አጽንኦት ሰጥቷል።
​የውሳኔው ፍሬ ሀሳብ፡-
አንድ ሰው ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቷል ወይም ተገልግሎበታል ተብሎ ክስ ሲቀርብበት፣ ተከሳሹ "ሰነዱ ሀሰተኛ አይደለም/ትክክለኛ ነው" የሚል ክርክር ካቀረበ፤ ዐቃቤ ህግ የሚከተሉትን በግልጽ የማስረዳት ግዴታ አለበት፡-
​ሰነዱ ሀሰተኛ መሆኑን፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሰነዱ ራሱ ፎርጂድ (Fake) መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ።
​የተከሳሹን ሚና፡ ያንን ሀሰተኛ ሰነድ የፈጠረው ወይም ያዘጋጀው ወይም የተገለገለበት ተከሳሹ ራሱ መሆኑን ማረጋገጥ።
​የህጉ መሰረት (አዋጅ ቁ. 881/2007 አንቀጽ 23)፡
በሙስና ወንጀሎች አዋጅ መሰረት አንድ ሰው ጥፋተኛ የሚባለው፡-
​መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ሰነድን አስመስሎ ከሰራ፣
​እውነተኛውን ሰነድ ከለወጠ/ከደለዘ (ፊርማ፣ ቁጥር፣ ይዘት በመቀየር)፣ ወይም
​ሰነዱ ሀሰተኛ መሆኑን እያወቀ ከተገለገለበት ነው።
📌 ማጠቃለያ፡ ሰነዱ ሀሰተኛ ስለመሆኑ እና ተከሳሹ ስለማዘጋጀቱ በተገቢው ማስረጃ ሳይረጋገጥ በደፈናው የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የለውም።
📖 ዋቢ መዛግብት፡ ሰ/መ/ቁ 247213፣ 241756 እና 245579
" ማንኛውም ሰው በችሎት ውስጥ ሆነ ከችሎቱ ውጭ ማንኛውም በደቡብ ፍ/ቤት ዳኛን ሲጠራ ለሴት "ክብርት ዳኛ" ለወንድ " ክቡር ዳኛ" በማለት መጥራት አለበት!! "

(የደ/ኢ/ክ/ጠ/ፍ/ቤት የክልሉ ፍ/ቤቶች የችሎት ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 04/2017 አንቀጽ 16/2 )