ነገረ ካካ
(አሌክስ አብርሃም)
ይች ምስሏን ከታች የምትመለከቷት ቆንጆ ሴት ጆኒ ዲፕ የተባለ ታዋቂ የፊልም ተዋናይ የቀድሞ ባሏ ጋር ተካሳ ችሎት ስትመላለስ ነበር! (ያው ነገሩን ታውቃላችሁ) ታዲያ የጓዳ ገመናቸውን እያወጡ ሲጠዛጠዙ ሚስኪን ባሏ ምን አለ? "ከሁሉም ከሁሉም የሚያሳዝነው ሆነ ብላ ለሞላ ሽንት ቤት ...አልጋየ ላይ... እኔ በምተኛበት በኩል ካካ ብላ እንደደህና ነገር ካካዋን አንሶላ ለበስ አድርጋ አሰቀምጣልኝ ታውቃለች" አለ! ዓለም በሙሉ ይሄን ሲሰማ አፍንጫውን ይዞ "ምኗ ካካም ናት ...ይድፋሽ እቴ" አለ! በኋላ እሷ "አይ ውሻችን ነው ካካ ያለበት እኔ አይደለሁም " ብላ ካደች! ...ጆኒ ዲፕ ታዲያ በስልኩ ያነሳውን የካካ ፎቶ(ምን ሲሆን ፎቶ አነሳው እስቲ?) መዝረጥ አድርጎ "አሁን ማን ይሙት ይሄ ካካ ምኑ ነው የውሻ የሚመስለው ወገኖቸ? የራሷ ነው! " አለ ! የጆኒ አድናቂዎች በሙሉ "ይሄማ የራሷ ነው ቁርጥ እናቱን" አሉ! በአጭሩ የዚች አገር ባለስልጣናት ምንም ቢሽቀረቀሩና ወሬ ቢያሳምሩ ወደፊት ለህግ ሲቀርቡ ክሳቸው ከዚህም የሚያስፀይፍ ይመስለኛል "አገር ላይ በመፀዳዳት" የኛ አይደለም ቢሉም ቆሻሻ ስራቸውን እየደበረውም ቢሆን ፎቶ አንስቷል ህዝቡ!

❤3
ልብ የሚነኩ 10 አረፍተ ነገሮች
1. ሰዎች እንዴት ሊይዙህ እንደሚገባ የምታስተምራቸው አንተው ነህ።
ሰዎች የሚያደርጉት አንተ የፈቀድክላቸውን ብቻ ነው። አንድ ሰው የሚያደርግብህን ነገር ካልወደድከው፣ እስከዛሬ ምን ስትቀበል እንደነበር እራስህን መርምር።
2. "ለችግሩ ያለህ አረዳድ ነው ችግሩ።"
አብዛኛው ስቃይ የሚመጣው እየሆነ ስላለው ነገር ለራስህ ከምትነግረው ታሪክ ነው። ክስተቱ በራሱ ገለልተኛ ነው። ህመሙን የሚፈጥረው ያንተ ትርጓሜ ነው። አመለካከትህን ቀይር፣ ልምድህንም ትቀይራለህ።
3. "የተጣበቅከው ምን ማድረግ እንዳለብህ ስላላወቅክ ሳይሆን፣ ምን ማድረግ እንዳለብህ እያወቅክ ለማድረግ ፈቃደኛ ስላልሆንክ ነው።"
ይህ አረፍተ ነገር የማመካኛ ጨዋታን ያቆማል። በጥልቅ ስታስብ፣ ቀጣዩን እርምጃህን ታውቀዋለህ። አንተ ዝም ብለህ የሌለ ቀላል መልስ ተስፋ እያደረግክ ነው።
4. "የሌሎች ሰዎች ስለ አንተ ያላቸው አስተያየት ያንተ ጉዳይ አይደለም።"
ስለ አንተ ያላቸው ሀሳብ የሚኖረው በነሱ አይምሮ ውስጥ ነው፤ ባንተ ውስጥ አይደለም። ልትቆጣጠራቸውም ሆነ ልትቀይራቸው አትችልም። ህይወትህን የሚቀርጸው ብቸኛው አስተያየት ያንተ የራስህ ብቻ ነው።
5. "የምትሆነው በተደጋጋሚ የምትናገረውን ሳይሆን በተደጋጋሚ የምታደርገውን ነው።"
ይህ አረፍተ ነገር በሀሳብ እና በተግባር መካከል ያለውን ክፍተት ይደፍናል። ልማዶችህ በተግባር የሚታዩ ማንነቶችህ ናቸው። ማንነትህ የሚወሰነው በግብህ ሳይሆን በየዕለት ውሳኔዎችህ ነው።
6. "ለመግባት የምትፈራው ዋሻ የምትፈልገውን ሀብት ይዟል።"
የምትፈልገው ነገር ሁሉ ያለው የምትሸሸው ነገር ማዶ ላይ ነው። ያ አስቸጋሪ ውይይት። ያ አስፈሪ እድል። ያ ምቾት የማይሰጥ እድገት። ትልቁ ስኬትህ ከትልቁ ፍርሃትህ ጀርባ ተደብቋል።
7. "ካሳመመህ አካባቢ ሆነህ ልትድን አትችልም።"
አንዳንድ ጊዜ ችግሩ ያለው አንተ ጋር አይደለም፤ ባለህበት ቦታ ነው። መርዛማ ግንኙነቶች፣ አሉታዊ አካባቢዎች እና መጥፎ ልማዶች አንተ ስለፈለግክ ብቻ አይለወጡም። አንዳንድ ጊዜ ለማደግ መልቀቅ አለብህ።
8. "ዛፍ ለመትከል ምርጡ ጊዜ ከ20 አመት በፊት ነበር። ሁለተኛው ምርጥ ጊዜ አሁን ነው።"
ይህ አረፍተ ነገር "ጊዜው አልፏል" የሚለውን ሰበብ ያፈርሳል። መቼ እንደጀመርክ መቀየር አትችልም። እንደገና መቼ እንደምትጀምር ግን መቀየር ትችላለህ። የህይወትህን ቀሪ ዘመን ለመጀመር ከዛሬ የተሻለ ቅርብ ጊዜ የለም።
9. "ለመጀመሪያው ሀሳብህ ተጠያቂ አይደለህም፤ ለሁለተኛው ሀሳብህና ለመጀመሪያው ተግባርህ ግን ተጠያቂ ነህ።"
በድንገት የሚመጣው ሀሳብህ ካለፈው ልምድህ የሚመነጭ ነው። ምላሽህ ግን ከምርጫህ የሚመጣ ነው። ወደ አእምሮህ ብልጭ የሚለውን ነገር መቆጣጠር አትችልም፤ ነገር ግን በዛ ሀሳብ ምን እንደምታደርግበት መቆጣጠር ትችላለህ።
10. "የምትፈልገው ነገር ሁሉ ያለው ከጽናት ማዶ ነው።"
ተሰጥኦ አይደለም። እድል አይደለም። ትውውቅም አይደለም። ጽናት ነው። በየቀኑ የሚደጋገሙ ትናንሽ ድርጊቶች ተጠራቅመው አስደናቂ ውጤቶችን ይፈጥራሉ። አብዛኛው ሰው ከስኬቱ አፍ ላይ ሆኖ ያቆማል።

❤4
Forwarded from Admas (Adme Logy)
እንደቆመብኝ ዓለም አይቶኝ ቢሆንስ ?
(አሌክስ አብርሃም)
ይሄ የተረገመ ኮሮና ሳያጠፋፋን በፊት አንድ ሶሪያዊ ጓደኛ ነበረኝ …ከመሬት ተነስቶ
ኢትዮጲያን ይወዳል …በተገናኘን ቁጥር ግብፅን ተባብረን እንረግማለን እናማለን ! አገሩ
የዩኒቨርስቲ መምህር ነበር ፣ወሬን እሱ ያውራት! ስንትና ስንት መከራ አልፎ ነው አሜሪካ
የገባው ግን ሁልጊዜ ሳቅ ከፊቱ ላይ አይጠፋም አወራሩ ራሱ የሆነ ድራማ ነው
የሚመስለው ….
‹‹ሚስቴ ጋር የተለያየነው የጋብቻው ቀን ማታ ነው ›› አለኝ
‹‹አግብተህ ነበር ?››
‹‹ታዲያ! ያውም አይኖቿ እንደዳይመንድ የሚያንፀባርቁ ….ሳቋ ልብህን እንደሳሙና
አኩረፍርፎ የሚጨርስ …የእጆቿ ጣቶች እንደባህር እንጉዳይ የሚስልከለኩ ….ከንፈሯ …
የሚሳም ሳይሆን እንደአቮካዶ ጁስ በወፍራሙ ፉት የሚባል ዓይነት ….››
አገላለፁ አማሎኝ ‹‹እህት አላት ?›› ልል አስቤ ከአፌ ላይ መለስኩትና
‹‹እድለኛ ነህ ›› አልኩት
‹‹አይደለሁም ባክህ !››
‹‹ምነው? ››
‹‹የጋብቻችን ቀን ማታ … ከተማችን ውስጥ አለ ወደሚባል ኢንተርናሽናል ሆቴል ነበር
የሄድነው …እዛ ነው ክፍል የተያዘልን …ሰፊ ይሄን አዳራሽ የሚያክል ክፍል ! በአበባ በተሞላ
ክፍላችን ውስጥ ገብተን …የጓጓሁለትን ሰውነቷን በምኞት እየተቃጠልኩ አያለሁ !
ጫማወቿን ስታወልቅ በሂና የተዋቡ በወርቅ አልቦ ተተሸቆጠቆጡ ከአንተ የእጅ ጣት
የረዛዘሙ ውብ የእግር ጣቶቿ ….ሽፍንፍኗን ከፀጉሯ ላይ ስታነሳው ወገቧ ላይ የሚገማሸር
ከክረምት ጨለማ የጠቆረ ውብ ፀጉሯ ….የሙሽራ ቀሚሷን ስትከፍተው የወርቅ ሃብል
የሚጫወትበት የብርሃን ሜዳ የመሰለ ሰፊ ደረቷ ….ግራና ቀኝ ሙሉ ጨረቃቃ የመሳሰሉ
ክብ ጡቶቿ …ከተፈጠረች እህል ቀምሳ ታውቃለች ወይ የሚያስብል እንዲህ በአንድ አጅ
መዳፍህ የምትከበው ውብ ሽንጥ ….ወረድ ስትል በእቅፍ የማትደርሰው ኩርት ያለ ዳሌ ….
ምራቄን ዋጥኩና ‹‹እና ምን ተፈጠረ ?›› አልኩት
‹‹በቃ ያደረገችውን የወርቅ ጌጣጌጥ ሁሉ አወላልቃ ራቁቷን ስትሆን …ወርቅኮ ውበት
ይቀንሳል አልኩ …ወርቁን ስታወላልቅ ውበቷ ወጣ ….በቃ እሷን ፈዝዠ ስመለከት የራሴን
ልብስ ማውለቅ ረስቸ ነበር ….ወላሂ ! ስልምም እያለች ‹‹አውልቅ እንጅ ›› ስትለኝ
የድምፅዋ ፍስስስ ማለትና መለስለስ እንኳን ልብስ ቆዳን ማውለቅ ያስመኛል .... የአልጋ
ልብስና አንሶላውን ገለጥ ሳደርገው የገነት በር የተከፈተ ነበር የሚመስለው …ሽቶው …በቃ
በሽቶ የታጠበ አንሶላ በለው ….በባህላችን እንደዛ ነው ….ቀስ ብላ በነዛ ረዣዥምና ውብ
እግሮቿ ወደአልጋው ሳብ ሳብ ሳብ እያለች …ስትመጣ በቃ እንደዚህና እንደዛ ጠረጴዛ …
ነበር ርቀታችን ….. ፈገግ ብየ ስመለከታት ጅስሜ ሁሉ እንደእሳት እየነደደ ወንድነቴ ሁሉ
ከተፈጠረ እንደዛ ቁሞ አያውቅም …እንኳን ሌላ ጆሮየ ቁሞ ነበር …ፀጉሬ ቁሞ ነበር ….
ድንገት አልጋው ጋ ልትደርስ አንድ ሁለት እርምጃ ሲቀር ያለንበት ሆቴል ምድር በሚያናጋ
ፍንዳታ ወደፍርስራሽነት ተቀየረ …. የማስታውሰው እነዛ ውብ አበቦች በአየር ላይ ሲንሳፈፉ
ነው .... ክፍሉ በአቧራ ብናኝና በሚፈነጣጠር እቃ ሲሞላ ነው …በቃ !!›› ብሎ ትክዝ አለ
‹‹ምን ተፈጠረ ከዛ …ባለቤትህ ….?››
‹‹እኔጃ ! የነቃሁት ከምንኖርበት ከተማ ውጭ ቃሬዛ ላይ ተሸክመውኝ ሲሮጡ ነበር …
ከተማችን በጦርነት እየተናጠች ነው …ከሳምንት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት
ካምፕ ገባን …ሚስቴ ትኑርም ትሙትም አላወቁም አላገኟትም …ከሶስት ዓመት በኋላ እዚህ
ያሉ ቤተሰቦቸ ጋር መጣሁ …ፈለኩ አስፈለኩ በቃ አልተገኘችም …. የአላህ ....ህልም ነበር
የምትመስለው ! ከሁሉም ግን እስካሁን ሳስበው የሚያስቀኝ ....›› ወዲያው ከትካዜው
ወጥቶ መሳቅ ጀመረ
‹‹የሚያስቀኝ ምን መሰለህ? …ከፍንዳታው በኋላ ሲያገኙኝ …እንደዛ እንደቆመብኝ ይሆን ?
….እያልኩ እስቃለሁ …ሃሃሃሃሃሃሃሃ ›› ጎርናና ሳቁ አካባቢውን ሞላው ...የነበርንበት ኮፊሾፕ
ውስጥ የነበሩት ሁሉ ዙረው አዩን ...ማን ያምናል ያሳቀውን ነገር ቢሰማ …
‹‹…አስበኸዋል ? አልጀዚራ ፍንዳታውን ሲዘግብ እኔ ራቁቴን ከፍርስራሽ ውስጥ እንትኔን
ሚሳኤል አስመስየ ተጎትቸ ስወጣ ….የአላህ ! ጦርነት ክፉ ነው ...አገርህንም አንተንም
ከነገመናህ ነው ለአለም የሚያሰጣህ ››
@Alexabrha

😁9❤4👍1
አስፈሪወቹ ሌሊቶች!
የሆነ ጊዜ የሚከራይ ቤት ስፈልግ አንድ ክልፍልፍ ደላላ "ግራውንድ ፕላስ 2 " ቪላ አጠገብ ያለች ቆንጆ የብሎኬት ቤት አሳየኝ። ለታክሲ ቅርብ፣ ፅድት ያለች በዚያ ላይ ዋጋዋ የማይታመን ርካሽ! ቤት። እድሌን አመስግኘ ወዲያው ተስማማሁ። መስኮቷን ስከፍት ፊት ለፊት የተንጣለለው ውብ ቤት ይታየኛል። መሀል አዲስ አበባ እንደዛ ሰፊ ግቢ ውብ ህንፃ...ዙሪያውን ያለ ደካማ መንደርተኛ እያየሁ "ወይ አዲስ አባባ የኑሮ ልዮነት..." እያልኩ እሁድ ገብቸ እስከማክሰኞ አለሜን ቀጨሁ።
ማክሰኞ እኩለ ሌሊት አካባቢ ነበር ድንገት ከአልጋየ የሚያነጥር ድምፅ እንደሰፌድ ቆሎ አንቀርቅቦ ያስነሳኝ። መድፍ ነበር የመሰለኝ። ደንግጨ ብነሳ ሀድራው ደርቷል ጭብጨባው፣ ጉሪያው፣ ከበሮው.... ሌላ ነገር ነው። በተለይ ከበሮው የአደዋ ዘማችን ነጋሪት ያስንቃል...ይነዝራል!
ድዝዝ ድዝዝ ድዝዝ ...
ጨብ ጨብ ጨብ
እሰይ እስይ እሰይ እሰይ
ሁርርርርር፣ ሁይይይ፣ አሀይ ..... እህህህህህህ !
ግርጭው ብርጭው አፍከኸከት ግራጭገት
አጉዛራ
ቀወዢራ
ጆቢጃራ
እሁይይይይ ....ደግሞ በጎች በመሀል ይጮሃሉ! ባኣኣኣኣ! ዜማውን ሁሉ እስካሁን አስታውሰዋለሁ።
መስኮቴን በቀስታ ከፍቸ ባጮልቅ ያ ቪላ ቤት ዙሪያውን በቆሙ የቤት መኪኖች ተጥለቅልቆ ሰፈሩ በከርቤ ጭስ ታፍኗል። በሩ ላይ ነጠላ ያደገደጉ ሰወች ቁመዋል፣ መብራቱ ፀሐይ ይመስላል። እንዳለ በሩ ቄጤማ ተጎዝጉዞበታል። ህልም ነበር የሚመስለው። በኋላ ስሰማ የታዋቂ ጠንቋይ ቤት ሆኖ ተገኘ። የተከራየሁት ቤት ለሰባት ወር ባዶውን እንደከረመ አንዲት ያለሁበት ግቢ ልብስ የምታጥብ ልጅ ነገረችኝ።
ድምጿን ቀንሳ በፍርሃት "ጥሩ አይደለም የገባው ሁሉ ተጥመልምሎ ነው የሚወጣው ቶሎ ልቀቅ ይሄን ቤት...ከአንተ በፊት ተከራይቶ የነበረው ልጅ፣ ሌሊት አያለሁ ብሎ በመስኮት ብቅ ሲል አፉ ወደግራ አፍንጫው ወደቀኝ ተጠነጋግሮ እግሩም ተጥመልምሎ ቁጭ! " አለችኝ....። አንች ለምን አልተጥመለመልሽም ልላት ፈልጌ ከአፌ መለስኩት። ውስጤ ቢፈራም "ሳለ መድሃኒያለም ለጠንቋይማ ርስቴን አለቅም" ብየ ጧት ጧት አፌና አፍንጫየ አለመጣመሙን በእጀ እየዳሰስኩ መኖሬን ቀጠልኩ። አንድ ቀን ጧት ቁርሴን ስበላ በአጋጣሚ ወደአፌ የላኩት ማንኪያ አፌን ሳተው። የደነገጥኩት መደንገጥ። መስተዋት ፊት ቁሜ ሳይግን አልተጣመምኩም። ነፍሴ መለስ አለች።
እና ማክሰኞና ሐሙስ "ላይቭ ባንድ በሚያቀርበው ጭፈራ እየተዝናናሁ መኖር አዝናኝ ሆነልኝ። አንድ ሐሙስ እንደውም ፀጥ ብሎብኝ ማዛጋት ጀምሮኝ ማንን ልጠይቅ ስል? ያችው ልብስ አጣቢ "ግንቦት ገባ፣ በዚህ ወር ሁልጊዜ ሰውየው የሆነ ቦታ ስለሚሄድ ሰላም እናድራለን" አለችኝ። እውነትም ጠንቋዮ ሙሉ ግንቦትን ጠፍቶ ሰኔ ላይ ተመለሰ። ሰፈሩም ትንሽ ዘና ብሎ ከረመ። በሳምንትም በወርም ከመንደርተኛው አንዱ ጠንቋዮን የተሳፈጠ ይጣመማል የሚል ወሬ ስለነበር እነዛ ሌሊቶች አስጨናቂ ነበሩ። ጠንቋይ እንዲህ ተፈሪ መሆኑን ያኔ ነው ያወኩት። በሹክሹክታ በሚደርሰን ስጋት ብዙ አስፈሪ ሌሊቶች የምናሳልፍ ህዝቦች ነን።
እንግዲህ በሳምንት ሁለት ቀን ማክሰኞና ሐሙስ ሌሊት እንዲቹ ሲቀወጥ ያድራል። የገረመኝ ይሄ አይደለም! ብዙ ባለሀብትና ታዋቂ ሰው የሚሰግድለትን፣ ስንቱን ሐብት በሐብት ያደረገ ነው የሚባለው ይሄ ጠንቋይ ለማየት ስመኝ አንድ ቀን በሁለት ሰወች ታጅቦ ሲወጣ አየሁት! ...(ጠንቋይ ከዛ በፊት አይቸ ስለማላውቅ ፤ የሆነ ፍጥረት ነበር የጠበኩት) ....ምን ገጠመኝ? መናኛ ሙሉ ልብስ ለብሶና ከዘራውን ይዞ የሚያዘግም ሽማግሌ። ያችው ወሬ ወዳድ ልብስ አጣቢ እየተጣደፈች መጥታ ነበር "ወጣልህ ና እየው" ያለችኝ። ...እና ምን አለችኝ?
"ጡረታውን ሊቀበል እየሄደኮ ነው"
ጡረታ?
"አወ ...ወታደር ነበር...ቢሞት ጡረታውን አያሳልፍም ከቤት የሚወጣውም በዚቹ ቀን ነው" 😀
By Alex abrham

ስማቸውን ጥለው የሚሄዱ ኤክሶች!
(አሌክስ አብርሃም)
ኪያ ደወለችና " ገሲ አይንሽን አላይም ከዚህ በኋላ ብሎኝ ሄደ" ብላ አለቀሰች። ገሲ ገጣሚ ወዳጀ ገሰሰ ነው። በፍቅር አንድ አመት ቆይተው ነበር።
"እንዴ ለምን ?"
"እኔጃ በቃ አያምነኝም ፣ የሰው ወሬ እየሰማ ይበሳጫል!" ማልቀሷን ቀጠለች።
"ለዛ ነው ሰሞኑን የተለየሁሽ ለት ...ሴት ሞልቷል ባገሩ ፣ ቃልሽን የበላሽ... የጉም ጅብ ፣ የፀሐይ ቀበሮ የሚል ግጥም አከታትሎ ሲለጥፍ የነበረው? አልኩና ሁለቱንም ለማስታረቅ ቀጠርኳቸው። ልክ እንደገብረመድህን ፍልጥ ይዤ መሄድ ነበር የቀረኝ። ትዝ ይለኛል ቦታው ሁሉ ብሔራዊ የነበረች ኮፊ ሾፕ ፎቅ ላይ።
"ምን አጣላችሁ ደግሞ ?" አልኩ
ገጣሚ ወዳጀ ስካርቩን አስተካከለና "ተወኝማ አብርሽ! ሁልጊዜ የምትጠራኝ በሌላ ወንድ ስም ነው...ዳኒ ትለኛለች፣ ሳሚ ትለኛለች፣ ኬ ትለኛለች ኤም ትለኛለች አሹ ትለኛለች መረረኝ አልበዛም? ምንድነው ይሄ ሁሉ ወንድ ? ምንድነው? አፏ ላይ እኔ የለሁም።" አለ በብስጭት።
"አፍ ላይ ምን ታደርጋለህ? አንተኮ ልቧ ውስጥ ነህ ገሴ!" ብየ ወደደረቷ ስጠቁም ትልልቅ ጡቶቿን አይቶ ትንሽ ተረጋጋ። ወዲያው ጣልቃ ገባችና በችኮላ እጇን እጁ ላይ ጣል አድርጋ እንባ የሞሉ አይኖቿን አይኖቹ ላይ እያንከባለለች በሚያሳዝን ድምፅ ....
"አልተረዳኸኝምኮ ግርምሽ... " ከማለቷ አበደ፣ ስካርቩን ጣለ!
"ግርምሽ ደግሞ ማነው? ያለዛሬም አልሰማሁት። ማነው....?"

❤2😁1
‹‹ሥራ ካለው ቦርጭ አለው››
"ላግባ እንዴ ለምትል ላጤ ሴት ካገባችና ( እስካሁን) ደስተኛ በሆነ ትዳር ውስጥ ከምትገኝ ባለትዳር ሴት የቀረበ ምክረ ሃሳብ "
(ርእስ ነው)
++++++
እንግዲህ ካገባሁ ሁለት አስርት ዓመታት ልደፍን ትንሽ ቀረኝ።
ወቅቱ የሰርግ ነው፣ እኔም ቢከርምም ሙሽርነቴ በጥር ነበርና፣
እነሆ ስለትዳር ሃቅ ሃቁን መስማትን ለምትፈልጉ እንስቶች
እቅጭ እቅጩን ፣ ነጭ ነጩን
ሳላሞካሽ፣ ሳልቀባባ፣
እንደሚከተለው እመክራለሁ።
ቅድመ-ጋብቻ
------
ምርጫ ተትረፍርፎልሽ "ማንን ላግባ" በሚል የግርታ ጉም ተጋርደሽ ከሆነ
ከዚህ በታች ያለው ሊጠቅምሽ ይችላልና አንብቢው፡፡
እቱ ገላ!
ከሁሉ በፊት ይህንን እወቂ!
አንድ)
ለትዳር ብቁ የሆነ ወንድ…
ስራ ካለው ቦርጭ አለው።
ብር ካለው መላጣ ነው።
ታታሪና ቤቴ ቤቴ ባይ አባወራ ሰላላ እግሮችና ነጋሪት ሆድ እንጂ ጡንቻና ሲክስ ፓክ ይለውም።
አብላጫው ወንድ ገንዘብ በበሩ ሲገባ ፀጉሩ በመስኮት ይወጣል።
ፀጉሩ ያላፈገፈገ፣ ባለሞዴል አቋም እና ሃላፊነት የሚሰማው ወንድ በአንድነት ባል ሆነው ሲመጡ ካየን ቆይተናል።
ስለዚህ ምርጫሽ ላይ ተጠንቀቂ።
‹‹ሲክስ አብ›› አይተሽ፣ በባትና ደረቱ ተማርከሽ ስታለከልኪ፣ አጇኳሚው ላይ እንዳትወድቂ።
ሁለት )
አበባ እየገዛ እሾህ ከሚሆንብሽ፣ ቫኬሽን እያዞረሽ ዓይኑ ሌላ ከሚቀላውጥ ወንድ ይልቅ ሮማንቲክ ባይሆንም፣ ገና እምቦቃቅላ ሳለሽ የትራስ ጨርቅሽን የቬሎ የራስ ልብስ አስመስለሽ ያገባሽው የእቃቃ ባልሽ አይነት ባይሆንም ፣
( እንደ አቅሙ) የሚያስፈልግሽን ነገር ሳትጠይቂው የሚያደርግልሽን ሰው ባል ካደረግሽ መለስተኛ ገነት ገባሽ። ይሄን ስልሽ አበባ ሰጥቶ ማር፣ ቫኬሽን አዙሮ ታማኝ የሆነ ወንድ የለም ማለቴ አይደለም፡፡ ግን ብዙ አይደሉም፡፡ ካሉም አግብተዋል፡፡
ስለዚህ….አብዛኛው አይነት ገጥሞሽ በብልጥልጥና ጊዜያዊ ብልጭልጭ ነገር ተታለሽ ይህን ከሳትሽ ዘላቂ ሲኦል ወረድሽ።
እሺ…መምረጡንስ መረጥኩ…ግን ለመሆኑ ትዳር ግን እንዴት ነው? ካልሽ ደግሞ የሚከተለውን ተመልከች።
አንድ)
ትዳር ነጋ ጠባ የምትሳሳሚበትና ፍትፍት እየተጎራረስሽ" ፍቅርዬ ወዬ ወዬ" የምትባባይበት ሮማንቲክ ኮሜዲ አይደለም።
ዘጠና በመቶው ሎጅስቲክ ፣ አሰልቺ የቀን ተቀን ኑሮን መግፊያ መስተጋብር፣ ደሞዝ አልባ ስራ ነው።
እውነቱን ፍርጥርጥርጥ አድርጌ ልንገርሽ?
የት ነህ)የት ደረስክ) ልጆቹ ምግብ በሉ?) አምፖሉን መግዛት እንዳትረሳ) ዳይፐር ይዘህ ና) እናትህ ዛሬም ይመጣሉ) ቀዩን ሸሚዜንን የት ከተትሽው) እራት ዛሬም ምስር ነው) ሁሌ እርጥብ እየበላሽ እንዴት ልትከሺ ነው)
ዓይነት ነገር ይበዛዋል።
ከዚያ ግን አልፎ አልፎ በፊት፣ ገና አፍላ ፍቅር ላይ ሳላችሁ እንደሚያደርገው አየት፣እቅፍ፣ ሳም፣ ውድድ ሲያደርግሽ ነፍስ ትዘሪያለሽ።
የሆነ ሰውዬ ሚስትና የሆኑ ልጆች እናት ከመሆንሽ በፊት ማን እንደነበርሽ ትዝ ይልሻል።
ሴክሲ ሴክሲ ያጫውትሻል።
እንኳን አገባሁ ትያለሽ።
ወዲያው ግን በፍቅር ድግስ ልባችሁ ጠፍቶ ደክማችሁ በተንጋለላችሁበት፣
"አከራያችን ደጋግሞ ሲደውል ነበር። አላነሳሁለትም። ይሄ አሳማ! ጨምሩ ሊላለን ነው መሰለኝ። ?"ሲልሽ ወደ ፈዛዛው ፣ ደብዛዛው፣ ለዛዛው መደበኛ ትዳርሽ ተስፈንጥረሽ ትመለሻለሽ።
ሁለት)
ካልተጣላችሁ ትፋታላችሁ!
ይሄን ስልሽ ደግሞ ዘወትር በነገር ተቋሰሉ፣ ነጋ ጠባ ጠበኛ ሁኑ እያልኩሽ አይደለም፡፡ ግን የሚዋደድ ባልና ሚስት አልፎ አልፎ ካልተጋጨ፣ ቀን እየዘለለ ካልተደባበረ፣ ተደባብሮ ካልታረቀ፣ ታርቆ እንደገና ካልተደባበረ….ነገር አለ!
ተጣላችሁ ማለት ትፋታላችሁ ማለት አይደለም፡፡
ይልቁንም ነገርን እያድበሰበሱ በሆድ ይፍጀውና በችዬው ልኑር በከመሩት ቁጥር ክብደቱ ከመጠን ያልፍና ወገብም ቅስምን ሰብሮ ባልጠበቁት ሰአት ትዳሩን ይበትነዋል፡፡
እንደ ተቀበረ ቦንብ የት ጋር ነበር ሳይባል ፈንድቶ ሁለታችሁንም ይበታትናችኋል፡፡
ስለዚህ መሰረታዊ ባልሆነ ነገር ጊዜያዊ ጠብ ብትጣሉ አትሸበሪ፡፡
ይልቅ ካልተጣላችሁ..ለመጣላት እንኳን ግድ ካልሰጣችሁ … ያኔ….እሱን ፍሪ!
ሶስት)
ባልሽን ሳታቋርጪ ስትነተርኪው ምንም ካልመለሰልሽ የምትይውን ማዳመጥ ካቆመ ቆይቷል።
አለ አይደል….አንቺ ሳይከፍል ስለረሳው የልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ ስትለፈልፊ እሱ አርሴናል እኔ ሳልሞት ዋንጫ ይበላ ይሆን ብሎ እያሰበ፣ አውራ ዶሮ ግን ከረቫት ቢያደርግ ምን ትመስል ይሆን በሚል የቂል ሃሳብ ራሱን እያዝናና ነው።
ይሄ ደግሞ ክፋት አይደለም፡፡ ወንድነት ነው፡፡ አንቺ ፊትሽ እንዳይጨማደድ ሞይስቸራይዘር እንደምትለቀለቂው እሱም ይሄን ሲያደርግ ራሱን እየጠበቀ ነው- በወንድኛ!
፪) ባልሽ ምን አንጀትሽን ቢበጥሰው….(እመኚኝ ደህና የሚባለው ባል እንኳን ደጋግሞ ይበጥሰዋል) አፀፋውን ልመልስ ብለሽ ካንቋሸሽው፣ በሰው መሃል ካዋረድሽና ካሳንሽው፣ ወይ ደግሞ ሲደክም በማበርታት ፈንታ ልግመኛ ካልሽው፣ ሲከፋው እንደማፅናናት ሆድ ብሶት ሳለ ማጭድ ካቀበልሽው፣ ሲጎድልበት ከተሳለቅሽበት፣ ሲወድቅ ከረገጥሽው፣ ለሸረኛና አሽሟጣጭ ሰው አሳልፈሽ ከሰጠሽው፣
እንደው ባጠቃላይ ባሌ ነው ብለሽ የመረጥሽውን ሰው እንደልቤ አልሆነልኝም ብለሽ የወንድነት ክብሩን ከነካሽው፣ የአባወራ ማእረጉን ግፍፍ አድርገሽ ካኮሰስሽው
እቱ ገላ! ሁሉ ነገር ማክተሙ ነው።
በቃ ምን ልበልሽ?
ባልሽን እንዲህ ያለ ነገር (በተለይ ደጋግመሽ ) ከሰራሽው
የጎጆሽን ስርና መሰረት ነቀነቅሽው።
አራት)
ባልሽ ( ልክሽ ባይሆንም፣ አንቺ ለራስሽ የማትመርጪው ነገር ቢሆንም፣ ባትወጂውም) አስቦ ስጦታ ቢጤ ሲያመጣልሽ፣ ያላሰብሽውን ሸክም ሲያቀልልሽ አቅፎ በማመስገን ፋንታ ቆሌውን ከገፈፍሽው ….ቢፋቅ ቢፋቅ የማይደበዝዝ ደማቅ ስህተት ሰራሽ።
አለ አይደል…
ስጦታውን እያየሽ…
ሲያስጠላ!
ምን ሆነህ ነው ይሄን የገዛኸው?
ርካሽ ነው አይደል?
አንድ ነገር ሲፈጽምልሽ ፣
ድሮስ ማን ሊሰራልህ ነበር?
ምናምን እያልሽ ቅስሙን አትስበሪው፡፡
ለምን አትይም?
ወንድ ልጅ ከውጪ ሲታይ የአዞ ቆዳ ይኑረው እንጂ ውስጡ እምቡጥ ነው፡፡
ጥሩ የሰራ ሲመስለው፤ ከምንም በላይ ጎሽ መባልን፣ በሚስቱ መመስገንን፣ ከባለቤቱ አበጀህ የኔ አንበሳን የሚሉ ቃላትን ይናፍቃል።
ይሄንን በፌኒዝምኛ ስታወራርጅው ባይጥምሽም ዋጭው።
ስለዚህ የባልሽን ስጦታና ድርጊት እንዳልወደድሽው ወይ እና እንዳልተስማማሽ መንገር ቢኖርብሽ እንኳን የተሻለ ጊዜና ሁኔታ ምረጪ።
እንዴት ልበልሽ…በክፉ ቃላት ሰብረሽው ትዳርሽን ከማመስ ይልቅ ያምራል ብሎ የገዛልሽን የስልሳ ዓመት ባልቴት የሚያስመስልሽን ዥንጉርጉሩን ገርዳሜ ቀሚስ ለአንዲት ቀን ለብሰሽ ከአይኑ ብትሰውሪውና ቆይተሽ በመላ…እኔ የምወደው ቀሚስ እኮ እንዲህ ያለ ነው ብትይው አይሻልም?
ከፋሽ እንዴ?
አይክፋሽ።
እመኚኝ ይህንን ሁሉ ቀድመሽ በማወቅሽ በኃላ ከሚመጣ የከፋ የልብ ስብራት ትድኛለሽ።
ልደምድምልሽ።
ምን መሰለሽ?
ትዳር እንከን አልባ ሰውን ፍልጎ በማግባት የሚቆም ለደስታና ለጨዋታ ብቻ የተሰራ ተቋም አይደለም።
እንዳይጎረና የሚማሰል ወጥ፣ እንዳይደርቅ የሚኮተኮት የአትክልት ስፍራ፣ እንዳይታመም የሚከተብ ሕይወት ያለው ነገር ነው፡፡

ስለዚህ እንከን አልባ ሰው በመፈለግና ያገባሽውን ሰው እንከን ለማጥፋት በከንቱ ከመዳከር ይልቅ ከእንከኑ በላይ እወደዋለሁ ከምትይው ሰው ጋር ተጣምሮ ለመኖር የሚወሰንበት ጉዳይ መሆኑን አምነሽ ግቢበት።
አለ አይደል…
ይህችን እስስት ዓለም ብቻዬን ከምፋለማት አብሮኝ ቢሆን ሸክሜን ያቀለዋል የምትይውን፣ ሲከፋኝ ጀርባዬን በመዳፉ ቸብ ቸብ ያደርግልኛል፣ ሳለቅስ እምባዬን ይጠርግልኛል የምትይውን ሰው ባል አድርጊ።
ይሄው ነው። ከዚህ የረቀቀ፣ የተወሳሰበ ጉዳይ የለውም።
ውይ…ረስቼው…
እቱ ገላ!
አደራሽን ይህችን እንዳትዘነጊ! ከትዳር በፊት ያለውን ነገር ስታደርጊ…በገርልፍሬንድ ማእረግ ሚስት ሆነሽ እንዳትገኚ! በእጮኝነት ዘመንሽ የሚስትነት ሃላፊነትን አትረከቢ፡፡
በ ህይወት እምሻው

❤1
የአሜሪካ ቪዛ ነገር በጣም ከባድ እየሆነ ነው። "ገነት አደረጉት እንዴ " እየተባለ ነው። በተለይ ተጋብተው ቪዛ ለሚጠይቁ "ባልና ሚስቶች" ጠበቅ አድርገውታል። ብዙወች የውሸት ስለሚጋቡ በትክክል ባልና ሚስት መሆናችሁን ለመለየት የማያደርጉት ነገር የለም! ለየብቻ ጥያቄ መጠየቅና መልሳችሁ ከተለያየ ቻው ማለት ሁሉ ጀምረዋል ነው የሚባለው(እንተዋወቃለን ወይ በኤምባሲ?😀)
ትላንት ራት የበላችሁት የት ነበር? ምን በላችሁ? ዓይነት! ይሄ እንኳን ችግር የለውም! ባል ክትፎ ሚስት ፒዛ! ሰው የተለያየ ነገር ሊበላ ይችላል።
አስባችሁታል ግን "ለመጨረሻ ጊዜ እንትን ...ማለት የተቃቀፋችሁት መቸ ነው?" ብትባሉ
ባል... ሰኞ ማታ
ሚስት... ማክሰኞ ማታ!
ጠያቂ ...ሰኞስ?
ሚስት .... ሰኞ እናቴ ቤት ነው ያደርኩት
ጠያቂ ወደባል ዙሮ ... ለሰራተኛችሁም ነው ቪዛ የምትፈልጉት?😀 (ፈረንጅ አያሸሙር)

❤2
የሚገርመኝ ነገር ነበር
ኢትዮጵያ ውስጥ በአንዳንድ የገጠር አካባቢወች ይደረጋል...ስም ሁሉ አለው ጠፋኝ እንጅ! ጭራሽ ዛሬ ህንድ አካባቢ ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርጉ አየሁ። አንዲት ላም ከወለደች በኋላ ጥጃዋ በሆነ ምክንያት ከሞተች ወተቷ ይደርቃል። ጠባችም አልጠባችም ጥጃዋ በአካባቢው ካለች ግን ሰውነቷ ወተት ማምረት ይቀጥላል። (የተፈጥሮ ተዓምር፣ የእናትና ልጅ ትስስር) ስለዚህ ባለቤቶቹ የሞተችዋን ጥጃ ቆዳዋን በሳር(ጭድ) ይሞሉና እንዲህ ጥጃ አስመስለው እናቷ አጠገብ ያቆሟታል። ሚስኪን ላም ገና ለገና ልጀ ታድጋለች ብላ በሰው ስትታለብ ትኖራለች። ትልሳታለች ታሸታታለች...ምን ልላችሁ ነው? ለመሆኑ ዋጋ እየከፈላችሁለት ያለው ነገር በህይወት አለ? ፍቅራችሁ አለ? እምነታችሁ አለ? ህልማችሁ አለ? ወይስ አለ እያሉ ባቆሙላችሁ የሞተ ነገር ለሌሎች ዕድሚያችሁ፣ ገንዘባችሁ፣ ጤናችሁ እየታለበ ነው?

ነገሩ እንደአደንዛዢ እፅ ነው...ልጆች ወይም ወጣቶች ተደብቀው የወደቀች ሲጋራ ጫት ወይም ቤት ውስጥ ጠላ መቀማመስ ይጀምራሉ...ተደብቀው "ይሳሳሙ "ይሆናል። መደበቅ የይሉኝታና የአክብሮት ስሜት አለው። የምሰራው ልክ አይደለም ሌሎች አይዮብኝ የሚል ፀፀት አለው።
ከፍ ሲሉ ሲጋራው ተራ ይሆንባቸዋል ፤ ወደመጠጥና ሽሻ ቤት ይሄዳሉ፣ መደበቁን ይተውታል። ያም አያረካቸውም ወደከባድ መጠጦች፣ ወደአደንዛዢ እፅ ይሄዳሉ፣ ሴተኛ አዳሪወች ጋር ባለጌ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ፣ ወሲብ ፣ማርገዝ ፣ወልዶ መጣል፣ ማስወረድ ወዘተ ተራ ነገር ይሆንባቸዋል። ጥርሳቸው መልካቸው ሰውነታቸው በቁማቸው መፈራረስ ይጀምራል ...እንኳን ምክርና ይሉኝታ ሞት ከሱሳቸው በላይ አያስፈራቸውም። ቤተሰብ ፣ ዕምነት ሕዝብ ተራ ይሆንባቸዋል። ከሞት አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው ወደሞት ያዘግማሉ። እንደውም "ኖርማል ሰው" ሲመለከቱ ጤነኛ አይመስላቸውም። ለሱሳቸው ይዋሻሉ፣ ማንንም አሳልፈው ይሰጣሉ፣ ይሰርቃሉ፣ ይገድላሉ።
አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ሱስ በዚያ ደረጃ ላይ ነው። ጥበብ፣ ውይይት አሽሙር፣ ቅኔ ፣ የሰከነ ሐሳብ ፣ ይሉኝታ ሞራል፣ ትምህርት የሚባለውን ጉዳይ አልፏል። ተራ ስድድቦችንም ዘሏል። ወሲብ ነክ ጉዳዮች፣ አደባባይ ላይ የማይታዮ ገመናወችን መዘርገፍ ተራ ነገር ሁኗል። ራስን ማ*ፋት የሚያስቅ ቀልድ ሁኗል፣ ስለመገዳደል ካልተወራ ሬሳ ካላየ፣ ያዛጋዋል። የለየለት ፖርኖግራፊ እና የቆሸሸ የግል ገመና ገበያ ሆኗል። በየሚሴንጀርና ቴሌግራም እንደቆሸሸ የከተማ ወንዝ ዝሙት ሲፈስ ውሎ ያድራል፣ ገምቷል ሸቷል። በውስጥ የተራቆተው ከላይ ተከናንቦ እየተስለመለመ ብቅ ይላል። ከፈጣሪ እስከነብያት ከአገር እስከህዝብ ከማንነት እስከተፈጥሮ ስብዕና የማይዘለፍ የማይንቋሸሽ የለም።
ብዙ ሺወች ከየመንደሩ የከረፋ ባህሪያቸውን ተሸክመው አደባባይ ወጥተዋል። የመላ ከተማው ቆሻሻ ተሰብስቦ እንደሚጣልበት ቆሸ ቆሻሻ መጣያ ሆኗል። ቤተሰብ እንኳን የሚፀየፋቸው ሰወች ሺህ ሚሊየን ሰው አስከትለው አደባባይ ውለዋል። የታዳሚው አእምሮ የቆሻሻ ሱስ ይዞት ቆሻሻ ያነፈንፋል። ቆሻሻው ላይ ሚሊየን ዝንቦች ያርፋሉ። "ማን ብዙ ዝንብ አለው " የሚለው ሐሳብ ኩራት ሆኗል። ድግሪ ያለው ዝንብ፣ ማስተርስ ያለው ዝንብ፣ ፒኤች ዲ የተሸከመ ዝንብ፣ ሐብት ያለው ዝንብ፣ ስልጣን ያለው ዝንብ፣ ሐይማኖተኛ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ዲያስፖራ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ቆንጆ ነኝ የምትል ዝንብ... ዝንባዊ ማንነት የሚኮራበት ሆኗል። "ለመኖር ስል ዝንብ ሆንኩ" ይልሃል።
ንቦች ቆሻሻ ላይ ያበቀለ አበባ ፍለጋ አፍንጫቸውን ይዘው በቆሻሻ ክምር ላይ ክንፋቸው እስኪዝል ይበራሉ! የጨነቀው አየሩ ያፈነው ጨዋ ትውልድ በዚህ ቆሻሻ ታፍኖ እየተጨነቀ ነው። አየሩ ቆሽሿል... የሰው አዕምሮ ቆሽሿል፣ ቃላት ቆሽሸዋል። ንቦች የሚሰሩት ጥቂት ማርም ቢሆን ዝንብ ይሰፍርበታል። ዝንብ በቆሻሻና በማር መካከል ያለው ልዮነት አይገባውም። ሱሱ ግን አሁንም አልቆመም ነገ የከፋ ቆሻሻ ሊያዋልድ እያማጠ ነው።

❤5
Alex abrham
ቻይናዊው ሻወር እየወሰደ እያለ፣ ድንገት ቤቱ በእሳት ይያያዛል... ራቁቱን በመስኮት ዘሎ ይወጣል። ትንሽ እንደተረጋጋ ሚስቱ የሚቃጠለው ቤት ውስጥ መቅረቷን ያስታውሳል፤ ነገር ግን "እንግዲህ ቀኗ ካልደረሰ መውጣቷ አይቀርም" ብሎ ችላ ይላታል።
ወዲያው ግን አንድ በጣም አስደንጋጭ ነገር ትዝ ይለውና፣ በአስደናቂ ጀግንነት ድጋሚ ዘሎ ወደሚቃጠለው ቤት ይገባል። ሚስቱንም አንከብክቦ ይዟት ይወጣል።
በኋላ ላይ ጋዜጠኞች ተሰብስበው፦ "እንዴት በዚህ ድፍረት ወደሚቃጠለው ቤት ገብተህ ሚስትህን ልታተርፋት ቻልክ? ስታገኛትስ በምን ሁኔታ ላይ ነበረች?" ብለው ጠየቁት።
ስሜቱን በራሱ ቋንቋ እንስማው...
我不能把手机和妻子单独留在家里。我一直担心她会拿起我的手机偷看信息。当我急匆匆地冲进家门时,果然不出所料,她正一边被浓烟包围着剧烈咳嗽,一边在翻看我的手机。最终,我把她和手机一起救了出来。
አቻ ትርጉም ከትንሽ ቅመም ጋር
"ስልኬንና ሚስቴን ብቻቸውን እቤት ውስጥ መተው ፈጽሞ አልችልም! 'የተላላኩትን መልዕክት እያነበበች ይሆን?' የሚለው ስጋት እረፍት ነሳኝ። ዘልዬ እቤት ውስጥ ስገባ ልክ እንደፈራሁት፤ በጭስ ተከባ የቀሚሷ ጫፍ በእሳት እየተቀጣጠለና እያሳለች ስልኬን ስትፈትሽ አገኘኋት! በጨዋነት ስልኬን ተቀብየ ልወጣ ስሞክር 'ዢዋን ማናት? ለምንስ የልብ ኢሞጂ ላክህላት?' እያለች በዚያ ጭስ ውስጥ መጨቃጨቅ ጀመረች። ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ፣ ከነስልኩ አንጠልጥዬ ይዣት ወጣሁ።"
ክፉ ጊዜ ላይ ነን እ? 😁

👍1
አሜሪካ ሄጀ ወያላ ልሁን የሚል ኮሜንት እንዳትሰጡ!
(አሌክስ አብርሃም)
ባለፈው አንድ መኪና ከፊቴ ቆመና የ "STOP" ምልክቱን ዘረጋ። ሁላችንም ከኋላ ተደርድረን ቆምን። ልክ እንደስኩል ባስ አይነት ግን ትንሽ ቫን ነገር ነው። እና በሩ ተከፍቶ አንድ ውሻ ሮጦ ወጣና ቁማ ወደምትጠብቀው ሴት ጋር ሄዶ በደስታ ይቦርቅ ጀመር። አቅፋ ሳመችው። ውሾች ልክ እንደትምህርት ቤት ውለው ሲመለሱ የሚመላለሱበት የውሻ ሰርቪስ ነው። Doggy Daycare Bus” ወይም “Puppy School Bus” እየተባለ ይጠራል።
ውሾቹ የት ነው የሚውሉት? ብየ ጎግል ሳደርግ
እነዚህ ውሾች የሚሄዱት ባለቤቶቻቸው ስራ ሲሄዱ "Doggy Daycare" ወደሚባሉ ቦታዎች ነው። እዚያ ቀኑን ሙሉ ብቻቸውን ቤት ውስጥ ከመቀመጥ ይልቅ እንደልጆች ጧት ከየቤታቸው በሰርቪስ ሄደው ከሌሎች ውሾች ጋር ይጫወታሉ፣ ዋና ይዋኛሉ፣ እንቅልፍ ይተኛሉ፣ እንዲሁም አንዳንድ የስነ ምግባር ስልጠናዎችን ያገኛሉ።
ባለቤቶች ጠዋት ወደ ስራ ከመሄዳቸው በፊት ውሻቸውን ማቆያ ቦታ ድረስ መውሰድ ስለሚደክማቸው፣ ይህ የባስ አገልግሎት ትልቅ እፎይታ ሆኖላቸዋል። አስባችሁታል "ውሻሽ የት ነው የሚማረው?" ምናምን ሲባባሉ!
ወደቲክቶክ ስመለስ አንዲት መንግስት ቤት 20 ዓመት የሰራች ሴትዮ ከኮየ ፈጨ በሰልፊ ቪዲዮ ቅሬታዋን እያቀረበች ነው። "ለሚመለከተው አድርሱልኝ... 56 ቁጥር ባስ ቀረችብኝ ይሄው ሕዝቡ ተሰልፎ እየጠበቀ ... ከስራ አረፈድን " እያለች።