ADIL CREATIVE TECH Am©
92 subscribers
154 photos
8 videos
1 file
153 links
🌐 WELCOME TO ADIL CREATIVE TECH !!!

💻 Technology | Software | AI | Tutorials
📱 Apps • Websites • Digital Skills
🌍 Learn • Create • Innovate

Admin - @Yonail_Typography

© Main Channel: https://t.me/ADIL_CREATIVE
Download Telegram
Google ለብዙ አመታት ሲጠበቅ የነበረውን የGmail address መቀየር የሚቻልበትን አሰራር ለመላው አለም ይፋ አድርጓል።

ስለዚህ በልጅነታችሁ እንደ አጋጣሚ የሰጣችሁትን የGmail address ከዛሬ ጀምሮ መቀየር ትችላላችሁ።
ለምሳሌ momloveyouxyz@gmail.com የነበረውን ወደ hanaabraham1234@gmail.com መቀየር ትችላላችሁ።

ይህንንም ለማድረግ የስልካችሁ settings በመግባት Google services — Manage your Google account —- Personal info —- Email —- Google account Email — change Google account Email

ድጋሜ መቀየር ከፈለጋችሁ 1 አመት መጠበቅ ይኖርባችኋል። ስለዚህ ጥንቃቄ አድርጉ።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
📱 OnePlus ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ገበያ ሊወጣ ነው
OnePlus በይፋ ከአውሮፓ እና ከሰሜን አሜሪካ ገበያ መውጣቱን አስታውቋል። ከእንግዲህ በኋላ በእነዚህ ገበያዎች አዲስ የOnePlus ስልኮች አይቀርቡም።
ነገር ግን አሁን ያሉ የOnePlus ተጠቃሚዎች የከሽያጭ በኋላ አገልግሎት (After-sales Support)፣ የጥገና አገልግሎት እና የሶፍትዌር ዝመናዎችን እንደቀድሞው ያገኛሉ።
በተጨማሪም OnePlus ስልኮች ላይ የነበረው OxygenOS በቀጣዮቹ ወራት ColorOS በመባል ይተካል።
የOnePlus እናት ኩባንያ የሆነው Oppo በአሜሪካ ገበያ ለመግባት እቅድ እንደሌለው ገልጿል፤ በተቃራኒው ግን በአውሮፓ ገበያ ላይ በተለይ በFlagship ስልኮች ላይ የበለጠ ትኩረት ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
1
Separate Sound

ስልካችሁን ከheadset ወይም ከearpad ጋር connect አድርጋች ነገር ግን የፈለጋችሁትን አፕሊኬሽን ስትከፍቱ በስልካችሁ speaker ወይም በheadset ማዳመጥ እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

ለምሳሌ YouTube ስትከፍቱ በearpad TikTok ስትከፍቱ ግን በspeaker

ይህን ለማድረግ የስልካችሁ settings ከገባችሁ በኋላ Sound and vibration የሚል ውስጥ ትገባላችሁ።
ታች ላይ Separate app sound የሚል ምርጫ አለ። እሱን ትከፍቱና turn on ታደርጉታላችሁ።
ከተዘረዘሩት አፕሊኬሽኖች ውስጥ በስልኩ speaker ወይም በbluetooth እንዲከፈት የምትፈልጉትን አፕሊኬሽኖች ትመርጣላችሁ። ከዛ ስልክ speaker ከሆነ Phone በbluetooth ከሆነ ደግሞ Bluetooth device አድርጋችሁ መውጣት ነው።

ይህን በምታደርጉበት ጊዜ ሁለት ሰው በ1 ጊዜ በስልካችሁ የተለያየ ነግር መስማት ይችላል። ለምሳሌ እናንተ TikTok እያያችሁ ሌላ ሰው ደግሞ ሙዚቃ መስማት ይችላል።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
ኢንስታግራም በሜታ ስማርት መነጽሮች የሚሰሩ አስነዋሪ ቪዲዮዎችን ሊያግድ ነው

ኢንስታግራም በሜታ ስማርት መነጽሮች (Smart Glasses) ሰዎችን በድብቅ በመቅረጽ የሚሰሩ ትንኮሳዎችንና አስነዋሪ የቪዲዮ ይዘቶችን ለማገድ መወሰኑን አስታወቀ። የኢንስታግራም ኃላፊ አዳም ሞሴሪ እንደገለጹት፣ መድረኩ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው እየቀረጹ ለትንኮሳ፣ መንገድ ላይ ሴቶችን ለማስቸገር (pickup) እና የሱቅ ሰራተኞችን ኢላማ ለሚያደርጉ የ"ፕራንክ" ቪዲዮዎች የሚጠቀሙባቸውን ይዘቶች በሙሉ ያስወግዳል። ይህ እርምጃ የተወሰደው የመነጽሩ ካሜራ በግልጽ አለመታየት የሰዎችን ግላዊነት ለሚጋፉ፣ ንጹሃንን ለኀፍረት ለሚዳርጉና ለተለያዩ የዲጂታል ጥቃቶች የሚያጋልጡ "ትሮል" አካውንቶች ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ ነው።

በዚህ አዲስ ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት ኢንስታግራም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተከታዮች የነበሯቸውን ሁለት ታዋቂ የ"ፒክ-አፕ አርቲስት" አካውንቶችን የትንኮሳ ፖሊሲ ጥሰዋል በሚል በቋሚነት የዘጋ ሲሆን፣ ሰዎችን ለወሲባዊ ትንኮሳ የሚያጋልጡ ይዘቶችም እንዲወገዱ አድርጓል። ሜታ የመነጽሩን የግላዊነት ስጋት ለመቀነስ በሚቀርጽበት ጊዜ የሚበራው ትንሽ ነጭ መብራት ከተሸፈነ ካሜራው በራሱ ጊዜ እንዳይሰራ የሚያደርግ የቴክኖሎጂ ማስተካከያ ማድረጉን ገልጿል። ኩባንያው ይህንን እርምጃ የወሰደው ቴክኖሎጂው ለሌሎች ሰዎች ስጋት እንዳይሆንና የማህበራዊ ሚዲያ ፈጣሪዎች የሰዎችን ሰብአዊ ክብርና የግል ነፃነት እንዲያከብሩ ለማስገደድ ነው።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
⚡️ ትልቅ ዜና ከቴሌግራም! 🚀

​ፓቬል ዱሮቭ እንዳስታወቀው፣ ቴሌግራም በዚህ ክረምት ለሁሉም ከ 1 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች የሚሆን አዲስ ናቲቭ (በአፑ ውስጥ የተገነባ) Non-custodial Gram Wallet ሊለቀቅ ነው።

​ይህ ዋሌት የሚከተሉትን ድንቅ ገጽታዎች ይዞ ይመጣል፦

🔹 ሙሉ ቁጥጥር (Non-custodial): ሚስጥራዊ ቁልፍዎ (Private Key) እና ዲጂታል ንብረትዎ ሙሉ በሙሉ በእርስዎ እጅ ብቻ ይሆናል።

🔹 ዜሮ ክፍያ (Zero-Fee): የ Gram ክሪፕቶፕቶ ሳንቲም ትራንዛክሽኖች ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ በቅጽበት ይከናወናሉ።

🔹 ቀጥታ በአፕ ውስጥ: ተጨማሪ ቦት ወይም ውጫዊ አፕሊኬሽን መጠቀም ሳያስፈልግ በቀጥታ በቴሌግራም አፕ ውስጥ ይገኛል።

​ይህ በክሪፕቶ ታሪክ ውስጥ ትልቁ የዋሌት ዝርጋታ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል! 🌐

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
በቅርቡ ይፋ የሆነውን የሳምሰንግ አዲስ ታጣፊ ስልክ Galaxy Z Fold 8 Review

ስልኩ አጠቃላይ rating 8.9 / 10 ከፍተኛ ነጥብ ያገኘ ሲሆን ዘንድሮ ሳምሰንግ የDesign ለውጥ ካደረገባቸው ስልኮች ቀዳሚው ነው።
ስልኩን ከቀደሙት የFold ስልኮችና ከUltra series የበለጠ ተመራጭ አድርጎታል ብሏል።

⚫️አዲስ Aspect Ratio (Passport Shape): የቀደሙት የFold ስልኮች ረዥምና ጠባብ ነበሩ። Z Fold 8 ግን አጭርና ሰፊ (Wider) ሆኖ ተሰርቷል።
⚫️የውጪ ስክሪን (Cover Screen): 5.5-inch AMOLED (10:16 aspect ratio) ሲሆን እንደ ፓስፖርት ሰፋ ያለ በመሆኑ ስልኩን ሳትከፍቱት መልእክት ለመጻፍ እና ካርታ ለማየት በጣም ይመቻል።
⚫️የውስጥ ስክሪን (Main Display): 7.6-inch AMOLED (4:3 aspect ratio) አለው። ይህም ቪዲዮዎችን ሲያዩ የሚፈጠረውን ጥቁር ፍሬም (Letterboxing) ይቀርፋል።
ለGamingና ለMultitasking በጣም ምቹ ነው።
⚫️Flex Titanium & Anti-Glare Coating: በስክሪኑ ስር Titanium alloy የተጨመረበት ሲሆን የስክሪኑ መታጠፊያ መስመር ከበፊቱ በበለጠ እንዳይታይ አድርጎታል። አዲሱ Anti-glare coating ደግሞ የፀሐይ ብርሃን ነጸብራቅን ይከላከላል ተብሏል።
⚫️ቀላልና ቀጭን፦ ስልኩ በታሪክ ቀላል የተባለው የFold ስልክ ሲሆን ክብደቱ 201 ግራም ብቻ ነው። ሲታጠፍ 9.7mm ውፍረት አለው።
ADIL CREATIVE TECH Am©
በቅርቡ ይፋ የሆነውን የሳምሰንግ አዲስ ታጣፊ ስልክ Galaxy Z Fold 8 Review ስልኩ አጠቃላይ rating 8.9 / 10 ከፍተኛ ነጥብ ያገኘ ሲሆን ዘንድሮ ሳምሰንግ የDesign ለውጥ ካደረገባቸው ስልኮች ቀዳሚው ነው። ስልኩን ከቀደሙት የFold ስልኮችና ከUltra series የበለጠ ተመራጭ አድርጎታል ብሏል። ⚫️አዲስ Aspect Ratio (Passport Shape): የቀደሙት የFold ስልኮች…
🚀 ዋና ዋና specificationና Performance
⚫️Processor: በቅርቡ የወጣው Snapdragon 8 Elite Gen 5 ቺፕሴት ተገጥሞለታል።
⚫️RAM & Storage: እስከ 16GB RAM እና 1TB Storage
⚫️Battery: 4,800mAh
⚫️Brightness: የሁለቱም ስክሪኖች Peak Brightness እስከ 3,000 nits ይደርሳል።
⚫️Durability: IP48 Dust & Water resistance Gorilla Glass Victus 2 እና 3 ተጠቅሟል።

ደካማ ጎኖች (Cons):
ስልኩ በጣም ውድ የሚባል ሲሆን ዋጋውም ከ1,900 ዶላር ጀምሮ ይሸጣል ተብሏል።
ሌላው Dedicated Zoomና Telephoto Camera የለውም። 50MP Main + 50MP Ultra-wide ብቻ ነው ያለው።
እንደ MagSafe ያሉ Magnetic accessories ለመጠቀም ተጨማሪ Case ያስፈልገዋል።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Breaking

Google በgemini omni አማካኝነት በነፃ እስከ 10 የሚደርስ video Generate ማድረግ እንደምችሉ አስታውቋል።

Gemini ክፍቱና የ+ ምልክቱን ነክታችሁ Video የሚለውን በመምረጥ የፈለጋችሁትን አይነት video create ማድረግ ትችላላችሁ።

ይህ ዕድል የሚቆየው እስከ august 4 ድረስ ብቻ ነው።
ሞክሩት።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
የናይኪ አዲሱ 'ሃይፐርስላይድ' (Nike Hyperslide)

ናይኪ ከሃይፐር አይስ (Hyperice) ጋር በመተባበር "Nike Air Zoom Hyperslide" የተባለ አዲስ የቤት ውስጥ ነጠላ ጫማ ይፋ አድርጓል። ይህ ጫማ ከስፖርት በኋላ የእግርን ጡንቻ ለማዝናናት እና ድካምን ለመቀነስ በሙቀት እና በንዝረት የታጀበ ቴክኖሎጂን ይጠቀማል። ተጠቃሚዎች ሦስት የሙቀት እና የንዝረት ደረጃዎችን በስልክ መተግበሪያ ወይም በጫማው ላይ ባሉ ቁልፎች ማስተካከል የሚችሉ ሲሆን፣ ባትሪው በUSB-C ቻርጅ ተደርጎ ለአንድ ሰዓት ያህል ያገለግላል። በ249 ዶላር ለገበያ የቀረበው ይህ ምርት፣ ለጤና ማገገሚያ የሚውል በመሆኑ በጤና ቁጠባ ፈንድ (FSA/HSA) መግዛት የሚቻል ሲሆን፣ በምቾቱ የሚታወቀውን የናይኪ ኤር ዙም (Air Zoom) ሶል በመጠቀም በተለያዩ ቀለማት እና መጠኖች ተዘጋጅቷል።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
Channel name was changed to «ADIL CREATIVE TECH Am©»
ኬንያ ከTether ጋር በመተባበር USDTን ለSettlement የመጠቀም ሙከራ ጀመረች።

የኬንያው ግዙፍ የአክሲዮንና የሴኩሪቲስ ገበያ Nairobi Securities Exchange (NSE) በአለም አቀፍ ደረጃ በUSDT Stablecoin የሚታወቀው Tether ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩን ይፋ አደረገ። ይህ ትብብር 26.4 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል ባለው የኬንያ የካፒታል ገበያ ውስጥ ክፍያዎችን (Settlement) በUSDT ለመፈጸም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ነው።

ከዚህ ቀደም የኬኒያ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች በNSE ገበያ ውስጥ Stock፣ Bondና ሌሎች Financial Assets ሲገዙ በFiat Currency ወይም በኬንያ ሽልንግና በአሜሪካን ዶላር ብቻ በኩል የነበረው የSettlement ሂደት ቀናት ይወስድ ነበር። Tether USDTን በመጠቀም ግን አጠቃላይ ሂደቱን በBlockchain ቴክኖሎጂ አማካኝነት በሰከንዶች ውስጥ በዝቅተኛ የTransaction Fee ለማከናወን ያስችላል።

ይህ ስምምነት የዶላር እጥረት በሚያጋጥምበት በአፍሪካ ገበያ ውስጥ USDTን እንደ Settlement Currency መጠቀም የውጭ ኢንቨስተሮች በቀላሉ ወደ ኬንያ ገበያ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ በር ይከፍታል ተብሏል።

ይህ ሙከራ የሚካሄደው በኬንያ Capital Markets Authority (CMA) የቁጥጥር ማዕቀፍ ስር ሲሆን የደህንነት እና ህጋዊነት መስፈርቶችን የጠበቀ መሆኑ ይረጋገጣል።
ADIL CREATIVE TECH Am©
ኬንያ ከTether ጋር በመተባበር USDTን ለSettlement የመጠቀም ሙከራ ጀመረች። የኬንያው ግዙፍ የአክሲዮንና የሴኩሪቲስ ገበያ Nairobi Securities Exchange (NSE) በአለም አቀፍ ደረጃ በUSDT Stablecoin የሚታወቀው Tether ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩን ይፋ አደረገ። ይህ ትብብር 26.4 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል ባለው የኬንያ የካፒታል ገበያ ውስጥ ክፍያዎችን (Settlement)…
NSE ባወጣው መግለጫ "ይህ አጋርነት የኬንያን የካፒታል ገበያ ወደ አዲሱ Digital Economy እና Web3 ማስገቢያ ትልቅ እርምጃ ነው። የTrading እና Settlement ሂደቶችን በማዘመን አጠቃላይ የገበያችንን Liquidity ያሳድጋል።" ብሏል።
Tether በበኩሉ "አፍሪካ ለCrypto እና Stablecoin አጠቃቀም በጣም ፈጣን እድገት የምታሳይ አህጉር ናት። ከNSE ጋር መስራታችን USDTን Trading ብቻ ሳይሆን ለሀገር አቀፍ የካፒታል ገበያ infrastructure ደረጃ ለመጠቀም መንገድ ይከፍታል።" ማለቱን CoinMarket ዘግቧል።

ጎረቤታችን ኬንያ የDigital finance ህጎና ስርዐቶችን በማውጣት ከቴክኖሎጂው እየተጠቀመች ሲሆን እኛ ሃገር ግን ዜጎች ጭራሽ በቴክኖሎጂው ተጠቅመው ሃብት እንዳያፈሩ የተለያዩ ክልከላዎች እየወጡ ነው።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
ጠቃሚ ዌብሳይቶች ዝርዝር

⚫️ https://web3.university
A massive hub of free tutorials about blockchain development
⚫️https://medscape.com
Primarily for professionals, but offers free, high-level clinical information and drug interaction checkers.
⚫️ https://linuxjourney.com
Linux learning platform
⚫️ https://www.iconfinder.com/
Millions of icons that you can use for your projects
⚫️ https://zoom.earth/
Live satellite weather maps that look strangely satisfying
⚫️ https://brilliant.org
Interactive, visual lessons in math, science, and computer science
⚫️https://chess.com
learn, play, and watching competitive chess at all skill levels
⚫️https://www.edge.org/
Intellectual discussions and debates from leading thinkers and scientists

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
ADIL CREATIVE TECH Am© pinned «ጠቃሚ ዌብሳይቶች ዝርዝር ⚫️ https://web3.university A massive hub of free tutorials about blockchain development ⚫️https://medscape.com Primarily for professionals, but offers free, high-level clinical information and drug interaction checkers. ⚫️ https://linuxjourney.com…»
Google messages ስትጠቀሙ RCS On ማድረጋችሁ ምን ይጠቅማችኋል?
⚫️Message ስትልኩ ብር አይቆርጥባችሁም።
ነገር ግን Data ማብራት ይጠበቅባችኋል።
የምትልኩለት ሰው Google messages የሚጠቀምና Online መሆን አለበት።
⚫️የGemini AI እዛው Google messages ላይ መጠቀም ትችላላችሁ።
⚫️ የድምፅ መለዕክት፣ ፎቶ፣ location፣ GIFና Sticker መላላክ ትችላላችሁ።
⚫️End-to-End encrypted ነው። ያ ማለት የምትልኩትን መልዕክት ማንኛውም service provider (ቴሌ ወይም ሳፋሪኮም) የማየት እድል የላቸውም። ግን ሁለታችሁም Google messages ከተጠቀማችሁና E2EE on ከሆነ ብቻ ነው።
⚫️Message የላካችሁለት ሰው የላካችሁትን መልዕክት ማየቱና አለማየቱን ማዎቅ ትችላላችሁ። እንዲሁም type በሚያደርግበት ጊዜ Typing....ይላችኋል።

እዚ ጋ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባችሁ RCS on አድርጋችሁ Message ስትልኩ እናንተ data ካላበራችሁ message error ይላችኋል። የምትልኩለት ሰውም Online ካልሆነ የላካችሁት message አይገባለትም።

ይህን ነገር ለማስተካከል የምትልኩለት ሰው profile ላይ ገብታችሁ "Only send SMS and MMS messages" የሚለውን On ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
ሰበር ዜና!!
የYouTube የMonitization መስፈርት ጭማሪ ተደረገበት

YouTube የዩትዩብ ክሬተሮች ከቻናላቸው ገንዘብ ለማግኘት (Monetized) ለመሆን የሚያስፈልገውን የWatch Hours መስፈርት በእጥፍ ማሳደጉን ይፋ አደረገ።

ከዚህ ቀደም አንድ ቻናል Monetize ለመሆን ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 4,000 Watch Hours1,000 Subscribers እንዲሁም በshorts በ90 ቀናት ውስጥ 10 Million እይታ ማሟላት ይጠበቅበት ነበር።
አሁን በተሻሻለው ህግ መሰረት ግን የMonetization ማመልከቻ ለማስገባት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 8,000 Watch Hoursና 20 Million የshorts ዕይታ ማሟላት ይኖርባቸዋል። የSubscribers መስፈርት ከ1,000 Subscribers ጭማሪ አልተደረገበትም።

ይህም ተግባራዊ የሚሆነው ከFebruary 1 ጀምሮ ነው።

ይህ አዲስ መመሪያ በተለይም ገና በማደግ ላይ ላሉ Small Creators ትልቅ መሰናክል የሚፈጥር ሲሆን Monetized ለመሆን የሚወስደውን ጊዜ በእጥፍ ያራዝመዋል። ሆኖም ግን አስቀድመው Monetized የሆኑ ቻናሎች ላይ ተግባራዊ አይደሩግም ተብሏል።

✍️YouTube መስራት የጀመራችሁ ወይም ለመጀመር ያሰባችሁ ምን ተሰማችሁ?

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE
የGemini ዕለታዊ የተጠቃሚ ቁጥር 1 Billion መድረሱን የGoogle CEO Sundar Pichai አስታወቀ።

ይህም 1B የተጠቃሚ ቁጥር የደረሰ 14ኛው የGoogle product መሆን ችሏል።

Follow: ADIL CREATIVE TECH for more tips

© 2026 @AdilCreativeTech | Powered by ADIL CREATIVE