የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ29ኛ እስከ 38ኛ ሳምንት ውድድር መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፥
የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከኢትዮጵያ ዋንጫ መልስ ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም ይጀምራል። በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም እና በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረጉትን ከ29ኛ እስከ 38ኛ ሳምንት ያሉትን የአስር ሳምንት(ቀሪ የሊጉ ሙሉ ፕሮግራም) መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል።
33ኛ እና 34ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ዋንጫን ታሳቢ በማድረግ ሊሻሻል ይችላል። እንዲሁም የ37ኛ እና 38ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም የክለቦችን ውጤት መሰረት በማድረግ ሊሻሻል ይችላል።

❤4
ጊዮርጊሳውያን ፡ የትም ፡ ቢሆኑ ፡ ልባቸው ፡ ከክለባቸው ፡ ጋር ፡ ነው፡፡የክለባችን ፡ ቀንደኛ ፡ ደጋፊ ፡ እና ፡ የቁርጥ ፡ ቀን ፡ ወዳጃችን ፡ የሆነው ፡ ሚድሮክ ፡ ኢንቨስትመንት ፡ ግሩፕ ፡ ዋና ፡ ስራ ፡ አስፈጻሚ ፡ የሆኑት ፡ አቶ ፡ ጀማል ፡ አህመድም ፡ ከጊዮርጊሳውያን ፡ አንዱ ፡ ናቸው፡፡
አቶ ፡ ጀማል ፡ ከሚድሮክ ፡ ዋና ፡ መስሪያ ፡ ቤት ፡ ይሄን ፡ መልእክት ፡ አስተላልፈውልናል፡፡ከጨዋታ ፡ ጅማሮ ፡ እስከ ፡ ፍጻሜው ፡ በሚድሮክ ፡ ጽህፈት ፡ ቤት ፡ የመስታወት ፡ ግድግዳ ፡ ላይ ፡ የክለባችን ፡ አርማ ፡ እንዲሁም ፡ "ሆ ፡ ብሎ ፡ ተነሳ" ፡ የሚለው ፡ ዝማሬ ፡ መልእክት ፡ እየተላለፈ ፡ ለደጋፊዎቻችን ፡ እና ፡ ለተጫዋቾቻችን ፡ ሞራል ፡ እና ፡ የመነቃቃት ፡ መልእክት ፡ ሲተላለፍ ፡ ውሏል፡፡
አቶ ፡ ጀማል ፡ በቦታው ፡ ባይገኙም ፡ በብልሃት ፡ ከኛ ፡ ጋር ፡ ቡድኑን ፡ ሲያበረታቱ ፡ እና ፡ ሲደግፉ ፡ ውለዋል፡፡
እናመሰግናለን ፡ አቶ ፡ ጀማል
እናመሰግናለን ፡ ሚድሮክ ፡ ኢንቨስትመት ፡ ግሩፕ

❤10
የድል ቀን የማሸነፍ ቀን
የአሸናፊዉ ክለባችን ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ስትመጡ ልታረጉት ሚገቡት ነገሮች
1. ያለ ማሊያ ስለማይገባ ሁላችሁም በዉቡ ቢጫ እና ቀይ ማሊያችን ደምቃቹ ኑልን።
2. ቲኬት ስላለቀ እና በር ላይ ስለማይሸጥ ሁላችሁም ስክሪንሹት ያረጋችሁበትን QR CODE ይዛቹ ኑ እምቢ ላላቹ በ @esportgetticket_bot ላይ Start ብላቹ share contact ላይ የቆረጣችሁበትን ስልክ ከገባ የሚመጣላቹ ዝርዝር ላይ ticket 1 ስትነኩት ይመጠላችኋል።
3. የስታዲየም በር ከ5 :30 ጀምሮ ክፍት ነዉ 8 ሰአት ላይ ደሞ ይዘጋል።
4. በተቻለ መጠን መጠጥ ሳትጠጡ ኑ ከድላችን በኋላ ሚከለክለን ምንም ነገር ስለሌለ እንደርስበታለን።
5. ለቲኬተሮች ,ለፀጥታ ሀይሎች እና ለስቲዋርድ አባላቶች ትብብሯን ያሳዩ ሁሌም ምንታወቅበት ጨዋነታችን ዛሬም ማስመስከር አለብን።
6. ሙሉ 90 ደቂቃዉን የተቃራኒ ተጨዋቾችን በሚያፈዘዉ እና በሚያምርብን ዉብ ዝማሬዎቻችን ጀግኖቹን ተጨዋቾቻችንን ማጀገን አለብን።
7. ያዉ ዛሬም እንደለመድነዉ ጎሎችን ማግባታችን አይቀርም በዛ ደስታ መሀል ክለባችን ሊያስቀጡ ሚችሉትን ማለትም ወደ ሽቦ መምጣት እና ወንበር ላይ መቆም ክለባችንን ስለሚያስቀጣ ከወዲሁ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
8. የሚዘጋጁ ሞዛይክ ስለሚኖር በቦታችሁ ላይ ተቀመጡልን ድባቡንም ልዩ ለማረግ ስላለብን።
9. አያሆሆ ማታ ነዉ ድሌ ✌️
10. ከጨዋታዉ መጠናቀቅ በኋላ ልዩነታችን ሜዳ ላይ መሆኑን አሳይተን ወደ ቤታችን ስንመለስ በፍፁም ሰላም መሆን አለበት የናፈቀንን የክለባችን ጨዋታ ከሸገር ሳይወጣ እዚ ደርሰናል ልናጣዉም አይገባንም።
ለጨዋ ደጋፊ ይሄን መንገር አይገባንም ያዉ ለማስታወስ ብቻ ነዉ ✌️
ድል ለኢትዮጵያ አርማዉ እና ለ31 ጊዜ ሻምፒዮናዉ አርበኛዉ ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ✌️✌️✌️✌️

❤8
በተጨማሪ ያለ ማሊያ መጥታቹ ስከርቭ ብቻ አርጎ መግባት ስለማይቻል ሁላችሁም ካለአስፈላጊ ንትርክ ለመራቅ ያለ ማሊያ መምጣት አይቻልም።
❤7
ቅዱስ ጊዮርጊስ vs ሲዳማ ቡና
🗓 አርብ ሚያዝያ 23 /2018 ዓ.ም
⏱ 8⃣ ሰአት
🏟 አዲስ አበባ ስቴድየም
💵 ቲኬቱን በዚህ ሊንክ ይቁረጡ http://ticket.ethiosport.pro

👌5❤3🥰1
የዜና መግለጫ
ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አራት የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾችን አስመጣ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ እየተወዳደረ ለሚገኝበት የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎውን በተሻለ ውጤትና ብቃት ለማጠናቀቅና በሊጉ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲጨርስ ይረዳው ዘንድ የአይቮሪኮስት፣ የኮንጎ ብራዛቪል እና ሁለት የጋና ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾችን አስመጥቷል፡፡
ለክለባችን ለመጫወት ወደ ሀገራችን የመጡት ተጨዋቾች፡-
1. ኬልቪን ኤዶ ዶሴህ
ኬልቪን ኤዶ ዶሴህ 1.90 ቁመት ያለው የ23 ዓመት ጋናዊ ወጣት ተከላካይ ነው፡፡ ኬልቪን ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ከመምጣቱ በፊት በጋና እንዲሁም በአልባኒያ ዋናው ሊግ ተጫውቷል፡፡
2. ካርተር አሂሮ
ካርተር አሂሮ አይቮሪኮስታዊ የ29 ዓመት የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ነው፡፡ ካርተር በአይቮኮስቱ ታላቅ ክለብ አሴክ ሚሞሳስን ጨምሮ በኮንጎ፣ ቤሩትና ኦማን ሊጎች ልምድ ያካበተ ተጨዋች ነው፡፡
3. ክሪስት ቶሉንጋ
ሌላው አዲስ ፈረሰኛ ሆኖ ወደ ሀገራችን የገባው የኮንጎ ብራዛቪል ተወላጅ የሆነው ክሪስት ቶሉንጋ ነው፡፡ ክሪስት የ20 ዓመት ወጣት የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ሲሆን ለሀገሩ ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ክሪስት ወደ ሀገራችን ከመምጣቱ በፊት በሀገሩ ለሚገኘው ዲያብሌስ ኖይሪስና ለአልጄሪያው ፓራዱ ክለቦች ተጫውቷል፡፡
4. አልፍሬድ ሜንሳህ
የ26 ዓመቱ ጋናዊ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አልፍሬድ ሜንሳህ ሌላው የክለባችን አዲሱ ተጨዋች ነው፡፡ አልፍሬድ በአልባኒያ፣ በኮሶቮ እና በጋና ፕሪምየር ሊግ ለተለያዩ ክለቦች ተጫውቷል፡፡
ተጨዋቾቹ በዛሬው እለት ያደረጉትን የህክምና ምርመራ በስኬት ያጠናቀቁ ሲሆን የምዝገባ ሂደታቸውን በማጠናቀቅ ከቡድናችን ጋር ልምምድ ይጀምራሉ።
ክለባችን የ2018ዓ.ም የፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመንን በተሻለ ደረጃ ላይ ሆኖ ለማጠናቀቅ ያሉንን ወጣት ተጨዋቾች በልምድ እንዲያግዙ እነዚህን ተጨዋቾች ያስመጣ ሲሆን ሁሌም ከቡድናችን የማይለዩት ደጋፊዎችም በአንድ ልብ ሆነው እንደለመዱት ከተጨዋቾቻችን ጎን በመሆን ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እንጠይቃለን፡፡
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ፤ ህዝብ ግንኙነት ክፍል፤