Just joined the 100 subscribers on YouTube club. VIRTUAL HIGH-FIVE! https://www.youtube.com/channel/UC_GAiujz7Otwc3X4-GrhLZg
YouTube
Addis Zeybe
Welcome to the OFFICIAL Addis zeybe News YouTube Channel! Bringing you Original reporting and trusted news with rich content and impartial perspective. Our channel combines all of the news that people care about in one place. We cover it all from pop culture…
Ustaz Abubeker Ahmed made this statement on an interview he gave to the Ethiopian Press Agency on the stand Egypt is taking regarding the #GERD
በሁለተኛው የአለም ጦርነትን በተለይም የናዚ ጀርመንን የግፍ ጭፍጨፋን ባለማስቆሙ የቀድሞው ሊግ ኦፍ ኔሽንስንን ተክቶ ሰኔ 19፣ 1937 ዓ.ም የተመሰረተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 75 አመት ሊሞላው ሁለት ቀናት ይቀሩታል። በወቅቱ በአሜሪካዋ ከተማ ሳን ፍራንሲስኮ ከተገኙት 50 መስራች አገራት መካከል፣ ኢትዮጵያ አንዷ ነበረች። ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብጽ፣ ላይቤርያና ደቡብ አፍሪካ አህጉሪቷን ወክለው በወቅቱ በሳን ፍራንሲስኮ መገኘታቸው ይታወሳል::
በፎቶው ላይ እንደሚታየው በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው፣ ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩትን አቶ አክሊሉ ሃብተወልድ ፣ ምክትል የፍትህ ሚኒስተር የነበሩት አቶ አምባይ ወልደማርያም፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ብላታ ኤፍሬም ተወልደ መድህን፣ የትምህርት ሚንስቴር ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ አማኑኤል አብርሃም እንዲሁም የፋይናንስ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ምናሴ ለማ ኢትዮጵያን በመወከል በስፍራው ተገኝተው ፊርማቸውን ማሳረፋቸውን ታሪክ ያስረዳል።
@addiszeybe

Lake Tana - recognized in UNESCO's World Network of Biosphere Reserves list for its rich biodiversity and significant cultural heritage - has been battling with Emboch since 2011/12. Getu Eristu has invented a machine to help fight the water hyacinth.
Read our web story http://addiszeybe.com/…/meet-getu-the-innovator-the-carpent…
And watch the you tube video https://youtu.be/uqj0mDEgYhA

Meet Getu: The Innovator, the Carpenter, and Adversary of Emboch (Hyacinth)
Young Ethiopian entrepreneur invents a machine to combat the emboch(Hyacinth) weed infestation in Tana Lake. This is a short video about his journey and how he was motivated to take on this responsibility
Ethiopia won the bid to host the African Union by competing against strong contenders like Libya, Nigeria and Kenya. As we enter another decade of hosting the organization it is time to ask how well we are hosting the organization representing the African continent and its 1.26 Billion inhabitants. Bruck Negash did just that read his article by clicking the link http://addiszeybe.com/currentaffairs/featured/addis-ababa-and-the-african-union-meeting-the-standards-of-a-continental-capital
Addis Zeybe - Digital Newspaper
Addis Ababa and the African Union: Meeting the standards of a Continental Capital - Addis Zeybe - Digital Newspaper
Since the Sirte declaration of 1999 announced the establishment of the African Union (AU) and the end of the Organization of African Unity (OAU), Addis Ababa has hosted the African Union for the past two decades. Located around Roosevelt Street in what is…
አሃዱ ባንክ የተባለ አዲስ የንግድ ባንክ ተቋቋመ
አሃዱ ባንክ የተባለ አዲስ የንግድ ባንክ ተቋቁሟል። ባንኩ እስካለፈው ሳምንት ድረስ 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአክሲዮን ሽያጭ ያካሄደ ሲሆን አንድ ባለይዞታ መግዛት የሚችለው ትንሹ የድርሻ መጠን 40 ሲሆን በ500 ብር ነጠላ የአክሲዮን ዋጋ እንደሆነ ተገልፅዋል። አንድ ባለአክሲዮን ከፍተኛውን ድርሻ እስከ 20,000,000 ሚሊዮን ብር ሊገዛ ይችላል።
እንደ አዲስ ኢንሳይት ዘገባ በባንክ ፣ በቢዝነስ ፣ በ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በመስራት እና በግንባታ ልምድ ያላቸው አሥራ ሰባት ሰዎች አሐዱን ያስጀመሩ ሲሆን የቀድሞው የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ካሳሁን ኃይለማርያም ከባንኩ መስራቾች አንዱ ነው ። በአሁኑ ጊዜ አማራ ፣ ጎህ ቤቶች ፣ ጃኖ ፣ ዛድ ፣ አሀዱ እና ዘምዘም ባንክን ጨምሮ ከደርዘን በላይ የሆኑ ባንኮች በምስረታ ላይ ይገኛሉ። እናት ባንክ የባንኩን ኢንዱስትሪ ለመጨረሻ ጊዜ የተቀላቀለ ባንክ መሆኑ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ራስ አርኪቴክቸር በ ዶመስ የአርኪቴክቸር መፅሄት ከምርጥ 50 የምህንድስና ድርጅቶች ውስጥ ተካተተ።
ራሄል ሻውል በ1991 ከአዲስ አበባ የምህንድስና ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ስትሆን በ1994 አባ አርክቴክት በ2004 ደግሞ ራስ አርክቴክቸርን አቋቁማለች ። የራሄል ሙያ በዘመነ ኢትዮጵያ ባሕላዊና ሙያዊ ዐውድ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ራስ አርክቴክት በአገር ውስጥ አዳዲስ ሕንጻዎች እና ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ዓለም አቀፍ ትብብር በማድረግ የግንባታ ንድፍ እንዲሁም የግንባታ ክትትል ሥራዎችን ያከናውናል።
ራሄል አዲስ አበባ በሚገኘው ሮያል ኔዘርላንድስ ኤምባሲ ግምባታ ላይ በነበራት ተሳትፎ የ2007 አጋ ካን ሽልማት ተቀባይ ሆናለች።ከተገነቡ ፕሮጀክቶች መካከል ኤምባሲዎች ፣ ትምህርት ቤቶች ፣ ሆስፒታሎች ፣ ክሊኒኮች ፣ መኖሪያ ቤቶች ፣ ሆቴሎች እና ካምፓኒዎች ፣ ይገኙበታል ። ሁሉም ፕሮጀክት የአካባቢውን እውቀት ተጠቅሞ አዳዲስ ነገሮችን የመሥራትና በዚያ ለሚገኘው አውድ እና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ትኩረት የመስጠት ዓላማ ያልው ተደርጎ የተሰራ ፕሮጀክት ነው።
ራሄል ፣ ራስ አርክቴክትን በመጠቀም በወንድ ቁጥጥር ሥር ባለው የምህንድስና ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሠሩ ወጣት ሴት አርክቴክቶችን ለማበረታታት ትሰራለች ። ወጣት ባለሙያዎችን በአጠቃላይ በእውቀት በማካፈልና በተግባር ላይ በተመሠረተ ትምህርትም ታግዛለች። ዶመስ የአርኪቴክቸር መፅሄትም ይህንን ሁሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት የ2020 ምርጥ ሀምሳ የምህንድስና ድርጅቶች ውስጥ ራስ አርኪቴክትን አካትቷል።

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቋቋም የሚረዳ የሶስት አመት ጥምረት ለመፍጠር ተስማሙ
የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በኢትዮጵያ በሕፃናትና እናቶች ላይ የሚከሰተውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመከላከል በትምህርት ቤት ላይ የተመሠረተ የተመጣጠነ ምግብና የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የሦስት ዓመት ጥምረት ፈጥረዋል።
በሦስት ዓመት ውስጥ ሊከናወን የታሰበው የእርዳታ ፕሮግራም በ100 ወረዳዎች ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በ600 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የጤናና የተመጣጠነ ምግብ እንዲኖር ይደረጋል። ይህ አካሄድ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም በህጻናት ላይ የሚታየውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከአስር በመቶ ወደ ሶስት በመቶ ዝቅ ለማድረግ የያዘችውን ግብ ለማሳካት ይረዳል ተብሎ ይገመታል።
ይህ ጥምረት በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ በሶማሌና በትግራይ ክልሎች ለድርቅ ከተጋለጡ መቶ ወረዳዎች ዒላማ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ ዘይቤ ከወግ ቡና ጋር በመተባበር የህይወት ክህሎትን እና የንግድ ሥራ ችሎታን ለማዳበር የሚጠቅሙ ቪዲዮዎችን በማዘጋጅት ላይ ይገኛል። በዚህ ሳምንት ‘ፐርሰናል ብራንዲንግ’ በሚል ርዕስ የራስን ስብዕና፣ እሴት እና ማንነት መገንባት እንዴት እንደሚቻል የሚያሳየውን የመቅደላ መኩሪያ ከዙም የተቀዳ ቪድዮ እንዲመለከቱ እንጋብዛለን።
https://youtu.be/_SbTbe-xzrM
Other similar videos - ሌሎች ተመሳሳይ ቪዲዮዎች
Habit formation - ልማድ ማዳበር https://youtu.be/fg6gieITYLc
Social business during and post COVID-19 - ማኅበረሰብ አቀፍ የንግድ ሥራ በወረርሽ ወቅትና ከወረርሽኝ በኋላ https://youtu.be/iZ2CPNC9n2U

Personal Branding - የራስን ስብዕና፣ እሴት እና ማንነት መገንባት
Addis Zeybe in collaboration with Weg Coffee is presenting a Business Enlightenment Workshop series. Please watch this week zoom recorded video of Mekedela Mekuria Hailu on the topic of Personal Branding for Professionals and Business owners. [Amharic]
…
…
እስራኤል በአወዛጋቢው የዌስት ባንክ አካባቢ ተጨማሪ መሬት ለመጠቅለል ማቀዷ በቀጠናው ስጋትን ወልዷል
ቢቢሲ በትላንትናው ዕለት ይዞት በወጣው መረጃ፣ የእስራኤል መንግስት በመጪው ክረምት በአወዛጋቢው የዌስት ባንክ አካባቢ ተጨማሪ መሬትን ለመጠቅለል እየተዘጋጀ ስለመሆኑ ዘገቧል። በፈረንጆቹ አመት መጀመርያ በአሜሪካው ፕሬዚደንት አማካኝነት በቀጠናው ያለውን ውጥረት ለማብረድ በቀረበው እቅድ ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ የሚነገርለት የእስራኤል ተጨማሪ መሬትን በዌስት ባንክ የመጠቅለል አጀንዳ በትራምፕ እቅድ በጥርጥር በሚመለከቱት የፊሊስጤም ፖለቲካዊ አመራሮች ዘንድ ተቀባይነት እንደማይኖረውም ዘገባው ጨምሮ አስነብቧል። ዘገባው አክሎም በመጪው ክረምት የኔቴንያሁ መንግስት ሊያጠቃልለው እቅድ ላይ ያለው ግዛት ከዌስት ባንክ ግዛት 3% የሚያክለውን ቢሆንም በመጪዎቹ አመታት እስከ 30 በመቶ ሊደርስ ይችላል በማለት ትንታኔውን አቅርቧል።
በቀጠናው ባለፉት ጥቂት አመታት ከታየው አንጻራዊ ሰላም በኋላም በቀጣይ ወራት ከፍተኛ ውጥረት ሊኖር ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለፍልስጤም አገር የመሆንን ተስፋ የሚያጨልም እርምጃ ስለመሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል። በወቅቱ በዌስት ባንክ ከሁለት ሚልዮን በላይ ፊሊስጤማውያንና 391,000 የሚደርሱ እስራኤላውያን እንደሚኖሩ የሚገመት ሲሆን፣ የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ባሳለፍነው ሕዳር በዌስት ባንክ ያለውን የእስራኤል ሰፈራ የአለምአቀፍ ህግን የማይጻጻር አይደለም በማለት አለማቀፉን ማህበረሰብ ማስደመሙ ይታወሳል። @addiszeybe

ከላይ የቀጠለ...
የኔቴንያሁ መንግስት ሊተገበረው ያሰበውን እቅድ ተከትሎም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ካውንስል ባሳለፍነው ሳምንት እሮብ ባካሄደው ስብሰባ ላይ የህብረቱ ሊቀመንበር አንቶንዮ ጉቲሬዝ በአሜሪካ የሚደገፈውን የግዛት ማስፋፋትና መጠቅለል እቅድ በቀጠናው ያለውን የሰላም ድርድር የሚጎዳ በመሆኑ እስራኤል ይህን እቅዷን እንድትተው ጠይቀው እንደነበረ ይታወሳል። በተጨማሪም የአረብ ሊጉ ሊቀመንበር አህመድ አብል ጌይት የእስራኤል ውሳኔ የፊልስጤማውያንን የራሳቸውን ነጻ አገር የመመስረት የሶስት አስርት አመታት ህልም የሚያጨልም ሲሉ ገልጸውታል።

የአፍሪካ ህብረት በመዲናችን አዲስ አበባ የአፍሪካ የበሸታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል (African Center For Disease Control and Prevention) የተሰኘ መጠርያ የያዘ ተቋም ለመመስረት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ይገኛል። የማእከሉ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ የሚሆን ሲሆን የማእከሉ ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገልጿል። ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ 👇👇
@addiszeybe
http://am.addiszeybe.com/2020/06/26/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%8b%a8%e1%89%a0%e1%88%b8%e1%89%b3-%e1%88%98%e1%89%86%e1%8c%a3%e1%8c%a0%e1%88%aa%e1%8b%ab%e1%8a%93-%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%8b%e1%8a%a8%e1%8b%ab/

Addiszeybe
የአፍሪካ የበሸታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው | አዲስ ዘይቤ
An eye witness account from the construction site confirms to Addis Zeybe that final preparations before filling the #GERD are going as planned. Bruck Negash analyzes yesterday's development relating to the negotiations around the dam and what it may mean going forward. Click the link below for more👇👇
http://addiszeybe.com/currentaffairs/ethiopia-is-gearing-up-to-filling-the-gerd
@addiszeybe
http://addiszeybe.com/currentaffairs/ethiopia-is-gearing-up-to-filling-the-gerd
@addiszeybe
Addis Zeybe - Digital Newspaper
Ethiopia is gearing up to filling the GERD | Addis Zeybe - Digital Newspaper
Ethiopia is gearing up towards the final stages of completing and filing its much-anticipated mega-dam. According to a conversation Addis zeybe had with an eye witness at the construction site, currently working in the dam, the final preparations to the filling…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
On this weeks episode of Recap Ethiopia, Wongel Tamene summarizes the major incidents that took place in Ethiopia in the past week. Click the link below to see more 👇
https://www.youtube.com/watch?v=cTIpRsTYjPM

በሶስት ወራት ዉስጥ በአስገድዶ መድፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸዉ 40 መዝገቦች ዉስጥ 8 ዉሳኔ ማገኘታቸዉ ተገለፀ፡፡
በሶስት ወራት ዉስጥ በአስገድዶ መድፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸዉ 40 መዝገቦች ዉስጥ 8 ዉሳኔ ማገኘታቸዉ ተገለፀ፡፡ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ መሰረት ከመዝገቦቹ ዉስጥ በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው የ64 ዓመቱ ተከሳሽ በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዕድሜያቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆኑ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈፀመባቸውና ተከሳሹ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን እንደተመሰረበት እንዲሁም ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ እንዳደረገ ገልፅዋል፡፡በዚህም ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ60 አመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ከህፃንነቷ ጀምሮ ያሳደጋትን የ15 ዓመት የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከ9 ወር ጽኑ እስራት የተቀጣ ሲሆን ቅጣቱም በቂ አይደለም ተብሎ በታመነበት ኪዝ ላይ የይግባኝ ክርክራችን ይቀጥላል ሲል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባወጣው መግለጫ የተገለትፁት ኬዞች ለአብነት የተገለፁ እንጂ በሌሎች የጥቃት ፈጻሚዎች ላይ ተገቢ የህግ ቅጣት እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ ከምንጊዜም በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ለቴሌኮም ፈቃድ ለመስጠት ከአስራ ሁለት ድርጅቶች ጥያቄ ተቀበለ
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ባሳለፍነው ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓም ሁለት የቴሌኮሚኒኬሽን ፈቃድ ለመስጠት የፍላጎት ማስታወቂያ ማውጣታቸው ይታወቃል። ባሳለፍነው ሰኔ 19 ቀን 2012 በኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ድህረገጽ የወጡ መግለጫዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ባለስልጣኑ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት አስራ ሁለት የፈቃድ ጥያቄዎችን መሰብሰብ ችሏል። ባለስልጣኑ ለኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን ገበያ ተስማሚ የሆኑ አገልግሎት ሰጪዎችን ለማግኘት ሲባል የአመልካቾችን ተቋማዊ አደረጃጀት፣ የድርጅቶቹን አለማቀፋዊ ሽፋን፣ በወቅቱ አገልግሎት የሚሰጡባቸውን ሀገራት ዝርዝርና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን መጠቀሙን በግልጽ አስቀምጧል።
ባለስልጣኑ ከተረከባቸው አስራ ሁለት ጥያቄዎች መካከል ዘጠኙ ከቴሌኮም ኦፕሬተሮች እና ሁለቱ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ካልሆኑ ድርጅቶች አንዱ ደግሞ ተሟልቶ ያልቀረበ መሆኑን መግለጫው ያስረዳል። ጥያቄውን ካቀረቡ ድርጅቶች መካከል ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮምና ቮዳፎን የፈጠሩትን ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘውን ጥምረት ጨምሮ ኢቲሳላት፣ አክሲያን፣ ኤምቲኤን፣ ኦሬንጅ፣ ሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያና ቴሌኮም ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል።
ባለስልጣኑ ጨምሮም የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ማሻሻያውን ለማሳካት እና የዲጂታል ሽግግሩን ለማሳለጥ ያለውን ጽኑ አቋም ገልጾ፣ በቀጣይ ምዕራፍ የሚያደርገውን ዝግጅት ለተመራጮች የሚያሳውቅ መሆኑን በመግለጽ በውድድሩ የተሳተፉትን ሁሉ አመስግኗል። የድርጅት መረጣው ሲጠናቀቅ በመንግስት ቁጥጥር ስር የቆየውን የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል።

Despite being at the embryonic level, some e-commerce platforms are coming out and introducing themselves to the untouched potential of the market. Wongel Tamene had a talk with one of those stores. Want to find out more? Click the link below 👇http://addiszeybe.com/currentaffairs/featured/zeila-store-a-multi-store-platform-introduced-by-two-young-entrepreneurs
Addis Zeybe - Digital Newspaper
Zeila store: a multi-store platform introduced by two young entrepreneurs - Addis Zeybe - Digital Newspaper
The rapid explosion of the Internet gave rise to the concept and practice of using electronic devices for shopping, which has become a common phenomenon in the world today. Internet-based economic structures and information groups are the new business reality.…
የማኅበራዊ ሚድያ ድርጅቱ ትዊተር በኢንተርኔት መዝባሪዎች መጠቃቱን ገለጸ
ገናናው ማኅበራዊ ሚድያ ትዊተር በትላንትናው እለት በኢንተርኔት መዝባሪዎች መጠቃቱን የተለያዩ የሚዲያ ምንጮች በመዘገብ ላይ ይገኛሉ። ከቢትኮይን ጋር የተያያዘ የማታለል ሙከራ ነው የተባለው ድርጊት ራሱን ክሪፕቶፎርሄልዝ (Criptoforhealth) በማለት በሚጠራ ቡድን ስለመካሄዱ ቢቢሲ የዘገበ ሲሆን፤ በጥቃቱ የቀድሞ የአሜሪካ የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦችንና ፖለቲከኞች ገጾች መጠቃታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
ከነዚህ ግለሰቦች መካከል በመጪው የአሜሪካ ምርጫ የዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩት ሴናተር ጆው ባይደን፣ የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ፣ ታዋቂው ራፐር ካንዬ ዌስትና ባለቤቱ ኪም ካርዳሽያን እንዲሁም ታዋቂ የአለም ሃብታሞች ቢል ጌትስና ኤሎን መስክ የሚጠቀሱ ናቸው።
ጥቃቱ ከላይ የተጠቀሱት አካውንቶች በመጠቀም የተለያዩ መልክቶችን በማስተላለፍ የተደረገ ሲሆን ጥቃቱን የፈጸመው ድርጅት ወንጀሉን የፈጸመው ለበጎ ተግባር መሆኑን በሌላኛው ማኅበራዊ ሚድያ ኢንስታግራም ገልጿል። በግለሰቦቹ ገጽ ላይ የሰፈረው መልዕክት ተጠቃሚዎች በቢትኮይን ገንዘብ እንዲለግሱና ሲለግሱ የሰጡትን እጥፍ መልሰው እንደሚያገኙ የሚገልጽ እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ። እስካሁን በወንጀል ድርጊቱ ምን ያህል ገንዘብ እንዳጋበሱ ያልተገለጸ ሲሆን በድህረ ገጽ ወንጀሎች ላይ እንደሚስተዋለው ወንጀለኞቹን ለመያዝ ቀላል እንደማይሆን ይገመታል።
ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ትዊተር በሰጠው መግለጫ ድርጅቱ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ስለመሆኑ አስረድቷል። የተለያዩ አካውንቶች ትዊት እንዳያረጉ ከማድረግ አንስቶ የይለፍ ቃልን መቀየርን እስከመከልከል ድረስ የሚደርሱ የደህንነት እርምጃዎችን ስለመውሰዱም ድርጅቱ አስረድቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃምሌ ወር ተጨማሪ በረራዎችን መልሶ እንደሚጀምር አስታወቀ
በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በማለት የሚጠራው ገናናው የኢትዮጰያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ የተነሳ አቋርጧቸው የነበሩትን በረራዎች ሊጀምር ስለመሆኑ ሲምፕል ፍላዪንግ የተሰኘው መካነ ድር በዛሬው እለት አስነብቧል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ከተከሰተ ወዲህ መጋቢት 21፣2012 ጀምሮ መዳረሻዎቹን ወደ 19 ቀንሶ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአገሪቱ የተቀመጠው የመዘዋወር እገዳ መላላቱን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ መዳረሻዎችን መጓዝ እንደሚጀምር ዘገባው ገልጿል።
ባሳለፍነው ሳምንት ሃምሌ 1 ቀን 2012 ወደ ዱባይ የሚያደርገውን በረራ መልሶ የጀመረው አየር መንገዱ በተጨማሪ ወደተለያዩ ሃገራት የሚያደርጋቸውን ጉዞዎች መልሶ በመጀመር የበረራ መዳረሻዎቹን ወደ 40 ከፍ ለማድረግ መወጠኑን ዘገባው ያስረዳል።
ከአየር መንገዱ የትዊተር ገፅ መረዳት እንደሚቻለው ወደ ለንደን፣ ፓሪስ፣ ፍራንክፈርትና ብራስልስ የሚደረጉት እለታዊ በረራዎች በሃምሌ ወር መልሰው ከተከፈቱ መዳረሻዎች መካከል ይገኛሉ። አየርመንገዱ ወደ ፍራንክፈርትና ለንደን የሚያደርጋቸው በረራዎች በወረርሺኙ ምክንያት ካልተቋረጡት በረራዎች መካከል እንደሆኑ ይታወቃል።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ከመምጣቱ በኋላ እንደሌሎች የበረራ ድርጅቶች ኪሳራን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሰሞንኛው የመዘዋወር እገዳ መላላት የተሻለ ጊዜን ለአየር መንገዱ ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የምርጫ ኮሚሽን አመራሮችን እንደሾመ አስታወቀ
ሐምሌ 9 ቀን 2012 ባካሄደው 5ኛ ዘመን 8ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የትግራይ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስተኛውን ክልላዊ ምርጫ የሚያስፈፅሙ የምርጫ ኮሚሽን አመራሮችን ሹመት አፅድቋል።
በዚህም መሰረት ፣ በነሐሴ መገባደጃ ላይ ይካሄዳል የተባለውን ምርጫ እንዲያስፈጽሙ ፣ አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም (መምህር) የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሆኖው ሲሾሙ ፣ ወይዘሮ ጽጌሬዳ ዲበኩሉ ደግሞ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሰይመዋል። መረሳ ጸሃዬ (ተባባሪ ፕ/ር) ፣ ጸጋ ብርሃነ (ዶ/ር) እና አቶ መሀመድ ስዒድ ደግሞ የኮሚሽኑ አባላት ሆነዋል።