የዓረና ፓርቲ ሊቀ መንበር ዓምዶም ገብረስላሴን ጨምሮ ዛሬ ብቻ ከ20 በላይ ሰዎች ታሰሩ
ጳጉሜን 2፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በትግራይ ክልል 'ጥምረት ለስር ነቀል ለውጥ” በሚል የተሰባሰቡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬ እለት ከጠሩት ሠላማዊ ሰልፍ ጋር ተያይዞ ከጠዋት ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከወጣበት ሰዓት ድረስ ቢያንስ ከ20 የሚበልጡ ሰዎች ታስረዋል ተባለ።
የሠልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል እና የውድብ ናፃነት ትግራይ (ውናት) ምክትል ሊቀ መንበር አለምሰገድ አረጋይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት “ሰልፉን የሚያስተባብሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎቹ የተውጣጡ የኮሚቴ አባላቶች በሙሉ ከሁለት አስተባባሪዎች በስተቀር ታስረዋል”።
እንደ መረጃ ምንጮቹ ከሆነ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ብቻ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራርና አባላት ብቻ ዓምዶምን ጨምሮ 13 ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ ስድስት የቀድሞ የትግራይ ሠራዊት (ቲዲኤፍ) ሰዎች፣ አራት ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ንፁሃን ሰዎች በአጠቃላይ ከ20 በላይ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል።
ሰላማዊ ሰልፉ የተጠራበት ሮማናት አደባባይ አካባቢ “ከሰልፈኞች ቁጥር ያለተናነሰ የፀጥታ ኃይል” መኖሩ የተገለፀ ሲሆን አሁንም በሰልፈኞች እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ግብግብ ቀጥሏል።

❤2👎1
የሐረሪ ክልል ፖሊስ በከተማው የደረሰውን የእሳት አደጋ መነሻና ኪሳራ እያጣራሁ ነው አለ
ጳጉሜን 2፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በሐረሪ ክልል በተለምዶ ሸዋበር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ለጳግሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም አጥቢያ ከለሊቱ 10:00 ሰአት ገደማ ሸዋበር የሸቀጣሸቀጥ መደብር በተባለ ስፍራ እስካሁን "ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ" የእሳት አደጋ ደርሷል።
አደጋው ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይዛመት መደረግ ተችሏል ያለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን "ከአደጋው ጋር በተገናኘ መንስኤውን እና የወደመውን ንብረት ግምት" ፖሊስ እያጣራ ይገኛል ብሏል። የምርመራው ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

👍1
በመቀሌ የተቃውሞ ሰልፍ ከ120 በላይ ሰዎች ሲታሰሩ በርካቶች በፖሊሶች ተደበደቡ
ትላንት(ጳጉሜ 1፣ 2015) የታሰሩት የሶስቱ ፓርቲዎች ሊቃነመናብርት ካደሩብት ተወስደው የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል።
በትግራይ ክልል የተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጠራው ሰልፍ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ላይ ያላቸውን ጥያቄ ለማቅረብ ሲሆን በትላንትናው እለት የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንቱ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ እንዲሁም ከቀናት በፊት የመቀሌ ከተማ አስተዳደር እንዳስታወቁት የክልሉ “የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም” እንዲሁም “ከበዓላት ጋር ተያይዞ ሰልፉን ለመጠበቅ የሚያስችል የፀጥታ ሀይል አቅም የለም” የሚሉ ማሳሰቢያዎች ሲሰጡ ነበር።
ከማክሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር የተያያዘ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት መታሰር የጀመሩ ሲሆን በትላንትናው እለት የሳልሳይ ወያነ ሊቀ መንበር ሃያሉ ጎደፋይ፣ የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀ መንበር ደጀን በርሀ እንዲሁም የባይቶና ዓባይ ትግራይ አመራር አቶ ክብሮም በርሀ የታሰሩ ሲሆን በዛሬው እለት “የት እንደተወሰዱ አልታወቀም” ተብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/more-than-120-people-were-arrested-during-the-mekele-protest-and-many-were-beaten-by-the-police...

👍2❤1
🚫አጎአን ጨምሮ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለአንድ ዓመት አራዘመ
👉 እ.ኤ.አ. መስከረም 2021 ከሁለት ዓመታት በፊት በአሜሪካ ኤግዚኪዩቲቭ ኦርደር 14046 መሰረት በብሄራዊ ደህንነት እና የውጭ ፖሊሲ ላይ የተደቀነ ስጋትን ለመቋቋም በሚል ከትግራይ ክልል ጦርነት ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለአንድ ዓመት አራዝሟል።
👉 የኢትዮጵያ መንግስት እና ባለስልጣናት ማዕቀቡን በተደጋጋሚ “በውስጥ ጉዳይ ተገብቶ የተጣለ ማዕቀብ” በማለት የሚጠሩት ሲሆን በ2013 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ የተደረገውን ጨምሮ የአሜሪካ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ላይ ሊያሳድር በሚችለው ጫና ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ሲደረጉ ተስተውሏል።
👉 ማዕቀቦቹ የኢትዮጵያ እንዲሁም የኤርትራ ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ ሰራተኞች እና ሌሎች ግለሰቦች የቪዛ እገዳ፣ በትግራይ ክልል እና በኢትዮጵያ ለተስፋፋው ብጥብጥ፣ ግፍ እና ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ የሆኑ አካላት እና ግለሰቦች ላይም ልዩ ማዕቀቦችን ያካተተ ነው።
👉 በተጨማሪም የመከላከያ አገልግሎቶችም ሆኑ መሳሪያዎች ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ የታጠቁ ኃይሎች፣ ለፖሊስ፣ ለስለላ ወይም ለሌሎች የውስጥ ደኅንነት ኃይሎች እንዳይላኩ እንዲሁም ኢትዮጵያ በዓመት እስከ 100 ሚልየን ዶላር ገቢ ታገኝበት የነበረው የአፍሪካ የዕድገትና ዕድል ሕግ (አጎአ) ከቀረጥ ነፃ የአሜሪካን ገበያ ተጠቃሚነትን ማሳጣት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት ከሚቀጥሉ ማዕቀቦች ዋነኞቹ ናቸው።
👉 ማዕቀቦቹ አሁን ለሁለተኛ ጊዜ የተራዘሙ ሲሆን እስከ መስከረም 2024 ይፀናሉ

👍6❤3👎1🔥1
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ 11ኛው የኢትዮጵያ ቅርስ ሆኖ ተመዘገበ ፡፡
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ እየተካሄደ ባለው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የአለም ቅርስ ጉባኤ ላይ የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በዛሬው ዕለት በአለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ እንዲሁም ኢትዮጵያ በዓለም ያስመዘገበችው 11ኛው ቅርስ በመሆን መመዝገብ ችሏል።
የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ ኢትዮጵያ በ45ኛው የአለም የቅርስ ጉባኤ ላይ ከጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በመቀጠል ያስመዘገበችው ሁለተኛው ዓለም ቅርስ ሆኗል፡፡
ፓርኩን በዩኔስኮ የማስመዝገብ አጠቃላይ ሂደቱ 15 ዓመት ያህል ጊዜ የፈጀ መሆኑን የገለፀው የቱሪዝም ሚኒስቴር የሰሜን ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ ከተመዘገበ ከ45 ዓመታት በኋላ ሁለተኛውን የዓለም የተፈጥሮ ቅርስ ማሰመዝገብ መቻሉን አስታውቋል፡፡
የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ በ 1962 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን የቆዳ ሥፋቱ 2150 ካሬ ኪ.ሜትር ቦታ የሚሸፍን እንዲሁም የመሬት ከፍታው ከባሕር ጠለል በላይ ከ1500 እስከ 4337 ሜትር እንደሚደርስ የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
#unescoworldheritage #Ethiopia

📢 የመንግስታቱ ድርጅት አባላት ያፀደቁት 'ዘላቂ የልማት ግቦች' ችላ መባላቸው ዋጋ እያስከፈለ ነው ተባለ
✍ ዘላቂ የልማት ግቦች የሚባሉት 17 እቅዶች በቀዳሚነት ድህነትን እና ረሃብን ማጥፋት ሲሆን ጠንካራ የጤና እና ደህንነት አገልግሎት፣ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት፣ የፆታ እኩልነት፣ የንፁህ ውሃና ንፅህና ጥበቃ፣ በዋጋ ተመጣጣኝና አየር የማይበክል ታዳሽ ኃይል አጠቃቀም፣ በቂ የስራ እድል እና የኢኮኖሚ እድገት፣ ኢንዱስትሪ፤ ፈጠራና መሰረተ ልማት፣ ሁለገብ እኩልነት፣ የማያቋርጥ የከተማ እና ማህበረሰብ እድገት፣ ምርቶችን ማምረትና መጠቀም ላይ ኃላፊነት መፍጠር፣ የአየር ንብረት ጥበቃ፣ በውሃ ውስጥ ያሉ ህይወቶችን መጠበቅ፣ የመሬት ሀብትን መጠበቅ፣ ሰላም፤ ፍትህ እና ጠንካራ ተቋማት እንዲሁም እነዚህን ግቦች ለማሳካት መተባበር ናቸው።
✍ ከዘላቂ የልማት ግቦች እቅድ እስካሁን 15 ከመቶ የሚሆኑት ኢላማዎች ብቻ በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን እቅዶቹን ለማሳካት ከሰባት ዓመታት ያነሰ ጊዜም ይቀራል። ይሁን እንጂ እንደ ተመድ ዋና ፀሐፊ ገለፃ ከእቅዱ 15 በመቶ ውጭ ያሉት “በተቃራኒ እየተጓዙ ነው”።
👉ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ።
.........................................
YouTube|Facebook|Twitter|LinkedIn|TiKTok|website

📻 የጦር እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እንዳይመረመሩ የኢትዮጵያ መንግስት ጫና እያደረገ መሆኑን ተመድ አስታወቀ
✍ የኢትዮጵያ የሽግግር ጊዜ ፍትህ ሂደት በመንግስት ጫና የተጠለፈ እና ተጎጂዎች “ተስፋ የቆረጡበት” መሆኑን የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን የኮሚሽኑ የስልጣን ዘመን እንዲራዘም ምክረ ሀሳብ ቀርቧል
✍ ከ500 የሚበልጡ የዓይን እማኞች ቃለ መጠይቅ የተደረጉበት ሪፖርት በትላንትናው እለት የቀረበ ሲሆን “የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ህገ መንግስትም ጭምር ግዴታው የሆነውን የዜጎቹን ደህንነትና ሰብዓዊ መብት መጠበቅ እንደተሳነው” ጠቁሟል።
✍ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ሁኔታዎች ሳቢያ ታኅሣሥ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. የተመሰረተው የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽኑ ለአንድ አመት እንዲቆይና እንደ አስፈላጊነቱ እንዲራዘም ተወስኖ ነበር የተቋቋመው።
✍ የፌደራል መንግስት ከህወሓት ጋር ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀመሩት ጦርነት ምክንያት የተቋቋመው ኮሚሽን ሰብሳቢ ሞሀመድ ቻንዴ እንደገለፁት፤ በፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ግጭቶችን በዘላቂነት ማስቆምም ሆነ ሰላም መፍጠር አልቻለም ብለው በታጣቂ ኃይሎች የሚፈፀሙ ወንጀሎች መበራከታቸውን ጠቁመዋል።
ሙሉ ዘገባውን በዚህ ሊንክ ያንብቡ።

ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር እንደሚቀጥል ተገለፀ
መስከረም 10፤ 2016 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ የአስራር ለውጦች እያደረገ ቢሆንም በተያዘው ዓመት የተማሪዎች ቅበላ በምደባ እንደሚሆን አስታወቀ።
የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ የተቋሙን ሽግግር በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ፤ በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ አንድ ዓመት ተኩል ይፈጃል ተብሎ በሚጠበቅ የሽግግር ሂደት ላይ እንዳለ የተናገሩት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ ራስ ገዝ መሆን ሲችል አዳዲስ ተማሪዎችን በዩኒቨርስቲው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ እንደሚቀበልም ጠቁመዋል።
የተቋሙ ራስ ገዝ መሆን ከፍለው መማር የማይችሉ ተማሪዎችን አይቀበልም ማለት አይደለም ያሉት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ፤ የዩኒቨርስቲውን መግቢያ የሚያሟሉ ብቁ ተማሪዎች በመንግስት ድጋፍ ዩኒቨርስቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር ለማገዝ ቻንስለር ጨምሮ የቦርድ አመራሮችና ፕሬዝዳንቶች መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በዓለም አቀፍ መስፈርቶች ተወዳድረው እንደሚቀጠሩ ተጠቁሟል።
ተቋሙ ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ተማሪዎችን በምደባ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር።

👍3😁3
የመንግሥት ኃይሎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት የጅምላ ግድያና የድሮን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ሲሉ አምስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠየቁ
መስከረም 10፤ 2016 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤አዲስ አበባ) አምስት የተፎካካሪ ፓርቲዎች ዛሬ ባወጡት ወቅታዊ መግለጫ በዘመነ ኢሕአዴግ ለተፈጠሩ ስህተቶች ሁሉ ይቅርታ ጠይቆ መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ሕዝብ እምነትና ተስፋ አምክኗል ሲሉ አስታወቁ።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ፣ እናት ፓርቲ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በጋራ መግለጫቸው የመንግሥት ኃይሎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት የጅምላ ግድያና የድሮን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀዋል።
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው አሁንም ብቸኛዉ መንገድ “ዉይይትና ድርድር” በመሆኑ መንግስት ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን በመወጣት የድርድር ጥያቄ እንዲያቀርብ፣ የመንግሥት ኃይሎች ከሰፈሩባቸዉ የመደበኛና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአስቸኳይ እንዲለቁ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አክለውም ባልታወቁ ሥፍራዎች በጅምላ ማጎሪያዎች የታሰሩ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ተዋጊ ኃይሎች ዓለም አቀፍ የጦር ሕጎችንና ይህንኑ የሚደነግገውን የጄኔቫ ስምምነት እንዲጠብቁ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት ግጭቶች በድርድር እንዲፈቱ ጫና ማድረግ አለባቸው ሲሉ ፓርቲዎቹ በሰጡት መግለጫ አሳስበዋል።
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የብልፅግና ፓርቲ የመፍትሔ ሀሳቦች ቸል በማለት ችግሮችን በኃይል አማራጭ ለመፍታት በሚያደርገው ሙከራ በሀገር ላይ ለሚደርሰው የከፋ ጉዳት በታሪክም፣ በሞራልም በሕግም ተጠያቂ ይሆናል ብለዋል። ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

👍6❤3👎2
#ማሳሰቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ የሞተር ሳይክል እንዲሁም የባጃጅ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ይቆማሉ
መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከዛሬ ማታ 12 ሰዓት ጀምሮ የሞተር ብስክሌተኞች፣ ባለ አራት እና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ ከእንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ቢሮው እንዳስታወቀው ከዛሬ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ድረስ ማለትም ለ15 ቀናት ማሽከርከር አይችሉም።
ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አያካትትም ያለው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው እየገለፀ፤ ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ቢሮው አሳስቧል።

👎2👍1
የመስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕለታዊ ዋና ዋና ዜናዎች
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ)
✍ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በተከሰተ ድርቅ 452 ሺህ ዜጎች ሲጎዱ 202 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው መንግስት አስታወቀ።
በዞኑ በሚገኙ ጃናሞራ፣ ጠለምት፣ የበየዳ ወረዳዎችን ጨምሮ፣ ምሥራቅና ምዕራብ ጠለምት እና የተወሰኑ የደባርቅ አካባቢዎች ላይ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ምክንያት፣ ድርቁ በሰዎች ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት ባለፈ ከ19 ሺህ በላይ ሄክታር ሰብል ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።
✍ የዓለም ጤና ድርጅት እየተባባሰ የመጣውን የኮሌራ ስርጭት ለመከላከል 16 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መልቀቁን አስታወቀ
በአሁኑ ወቅት የኮሌራ በሽታ ስርጭት ከፍተኛ ስጋት ከሆነባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ሄይቲ፣ ኢራቅ እና ሱዳን ይገኙበታል። የዓለም ጤና ድርጅት በቅርብ ጊዜ ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰባት ክልሎች ከ20ሺ በላይ ሰዎች በኮሌራ ሲያዙ 271 ሰዎች መሞታቸውን ትገልጾ ነበር።
✍ አሜሪካ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች እንዳሳሰባት ገለጸች
አሜሪካ በኢትዮጵያ የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ግጭት መባባስ እንዳሳሰባት በመግለጽ፤ ግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግለትና በፖለቲካዊ ንግግር እንዲፈታ እንደምትፈልግ አስታውቃለች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እንዲደረግ መጠየቃቸውንም ቃለ አቀባያቸው ማት ሚለር ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።
✍ ለመቐለ ከተማ ሕዝብ የውሃ ፍላጎት በቀን 120 ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ውሃ ያስፈልጋል ፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በመቅረብ ላይ ያለው 30 ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ውሃ ብቻ መሆኑን ተግልጿል።

👍6❤2
በኦሮሚያ እና ሶማሊ የክልል ፀጥታ ኃይሎች መካከል በተደረገ ተኩስ ልውውጥ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል ተባለ
መስከረም 21፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች የፀጥታ አካላት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ ስድስት ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባቢሌ አቅራቢያ በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የሞቱት ሰዎች በአካባቢው የሚገኝ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ ተፈናቃዮች መሆናቸውንም ኮሚሽኑ ገልጿል።
ኢሰመኮ በክስተቱ ላይ ዛሬ ባወጣው መግለጫ “በአሁኑ ወቅት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም፤ በተኩስ ልውውጡ ወቅት ቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ ቢያንስ ስድስት ተፈናቃዮች ተገድለዋል፣ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል” ብሏል።
በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና እገዛን አስመልክቶ የተደረገው ‘የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት’ ወይም ‘ካምፓላ ስምምነት’በሚገልፀው መሠረት የመንግሥት የፀጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ እንደሚገባ ኢሰመኮ አሳስቧል።
ኮሚሽኑ የግጭቱን መንስዔ በመለየት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲሰጥ፣ የነዋሪዎች እና የተፈናቃዮች ደኅንነት በዘላቂነት እንዲረጋገጥ፣ ተጎጂዎች እንዲካሱ እና ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ባለማድረግ በንፁሀን ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ የፀጥታ ኃይል አባላትም በህግ አግባብ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥቷል።

❤11👍7