አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
7.49K subscribers
4.47K photos
149 videos
15 files
3.52K links
ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ

Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC


ስልክ +251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com
Download Telegram
የህወሓት እና የመንግስት ሀይሎች ዋና አዛዦች በናይሮቢ እንደተገናኙ ተገልፀ

ጥቅምት 28፤ 2015ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ መንግስት የጦር አዛዥ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የህወሓት ሀይሎች ዋና አዛዥ ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በናይሮቢ እንደተገናኙ ተገለጸ።

የበላይ አዛዦቹ የተገናኙበት ምክንያት በደቡብ አፍሪካ የተደረሰዉን የሰላም ስምምነት የማስፈፀም አካል በሆነዉ ’ህወሓትን ትጥቅ የማስፈታት’ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር እንደሆነ እና ውይይቱ ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥል ቢቢሲ ዘግቧል።

በውይይቱ ላይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እና የቅድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንደተገኙም ማወቅ ተችሏል።

በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የሰለም ስምምነት “በአንድ ሉዓላዊ ሀገር አንድ መከላከያ ሰራዊት” ብቻ የሚደነግገው ህገ መንግስት እንዲከበር መስማማታቸው ይታወሳል።
____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
Ali Birra had been fortuned to reign as a towering artistic figure in the Ethiopian Afaan Oromo music for over half a century. Awash, Hinyaadini, Ammalele, and Nindeman’indima are among his most memorable songs. Read more...
https://bit.ly/3E4WmiB
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
የክብር ዶ/ር አርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ወደ መስቀል አደባባይ እየተሸኘ ነው

ጥቅምት 29፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) ከቢሾፍቱ የተነሳው የክብር ዶ/ር አርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ወደ መስቀል አደባባይ እየተሸኘ ይገኛል።

የአንጋፋው የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስከሬን ከአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ፤ ከዚያም በሠረገላ ወደ ወዳጅነት አደባባይ ሽኝት ይደረግለታል።

በወዳጅነት አደባባይ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች የጀግና ስንብት እንደሚደረግለት እና በድሬዳዋ ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈፀም ታውቋል።
____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
የነዳጅ ዋጋ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ህዳር መጨረሻ በነበረበት እንደሚቀጥል ተገለፀ

ጥቅምት 29፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) የህዳር ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን ይፋ ያደረገው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፤ አብዛኛው በጥቅምት ወር በነበረበት እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር እንዳስታወቀው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በነበረበት የሚቀጥል ሲሆን ከጥቅምት 28 ሌሊት ስድስት ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ ያሉት የነዳጅ ዓይነቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል።

የአውሮፕላን ነዳጅ “በወቅታዊ የዓለም አወፍ ዋጋ” መሰረት አዲስ አበባ ላይ በሊትር 75 ብር ገደማ እንዲሸጥ ተወስኗል።
____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
በኢትዮ- ኬንያ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የሙከራ ሥራ ስኬታማ እንደሆነ ተገለፀ

ጥቅምት 29፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በኢትዮ- ኬንያ የኮንቨርተር ስቴሽንና የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ላይ ኃይል የማስተላለፍ የሙከራ ሥራ በዛሬው ዕለት በስኬት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የኢትዮ- ኬንያ የማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ስቴሽን ፕሮጀክት በ334 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንደተገነባ ያስታወቀው የኤሌከትሪክ ኃይል ኩባንያው እስከ 2000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፍ አቅም እንዳለው ገልጿል።

ከቀናት በፊት የኮሙዩኒኬሽን ሲግናል በመላክ ሲግናሉን ከኬኒያ ኔትወርክ ጋር ማገናኘት መቻሉን ያስታወቀው ተቋሙ ፕሮጀክቱ ኃይል ማስተላለፍ ሲጀምር በህብረተሰቡ ላይ አደጋ እንዳያደርስ መስመሩ ከሚያልፋባቸው ዞኖች በየደረጃው ከሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ከወረዳና ከቀበሌ ተወካዮች ጋር የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መካሄዳቸውን ገልጿል።

በኢትዮጵያ በኩል በተገነባው የኢትዮ - ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ላይ 994 የመስመር ተሸካሚ ታወሮች የተተከሉ ሲሆን 440 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና የዳታ ሲግናል ማስተላለፊያ ኬብሎችም ተዘርግተውለታል።
____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
የትግራይ፣ አማራ እና አፋር ማህበረሰቦች በአግባቡ ያልተወከሉበት ድርድር በመሆኑ ስጋት አለኝ ሲል እናት ፓርቲ አስታወቀ

ጥቅምት 29፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) የጦርነቱ ቀጥተኛ ሰለባ የሆኑት የአማራ እና የአፋር ማህበረሰቦች እንዲሁም የትግራይ ህዝብ በአግባቡ ያልተወከለበት የሰላም ንግግር መሆኑ ያሰጋኛል ሲል እናት ፓርቲ አስታወቀ።

በተጨማሪም እናት ፓርቲ የድርድሩ ስምምነት ወደትግበራ ከመግባቱ በፊት በፓርላማው ለውይይት እንዲቀርብና እንዲያጸድቀው በአጽንዖት ጠይቋል።

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የድርድሩ መጀመር ቢዘገይም መልካም ነው ያለ ሲሆን በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ላይ ሂደት ውጤትን ይወስናል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጿል።

እናት ፓርቲ በመግለጫው “በድርድሩ የጦርነቱ ቀጥተኛ ሰለባ የሆኑት የአማራ እና የአፋር ማኅበረሰቦች አለመወከላቸው እንዲሁም የትግራይ ማኅበረሰብም በሕወሓት ብቻ ተወክሎ ድርድሩ መካሄዱ እንዲመጣ የተፈለገውን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ አዳጋች ያደርገዋል የሚል ከፍተኛ ሥጋት አለን” ብሏል።
____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
Coca-Cola the idea of buying a sugar factory arose in the framework of the company’s ongoing efforts of sourcing local inputs and tackling the ever-growing foreign currency shortage in the nation. Read more...
https://bit.ly/3DTF1Yy
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
ነፍስ ይማር 🕊
የደራሲ በአሉ ግርማ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ አበራ አረፉ።
አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ በወርልድ ማራቶን ደረጃ በሴቶች ቀዳሚ ሆነች 🇪🇹
የወልቃይት እና ራያ አካባቢዎች በአማራ ክልል ስር ህጋዊ እውቅና እንዲያገኙ ሲል አብን ጠየቀ

ጥቅምት 30፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡አዲስ አበባ) የወልቃይት እና ራያ አካባቢዎች በአማራ ክልል ስር በአፋጣኝ ህጋዊ እውቅና እንዲያገኙ ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ።

ፓርቲው በመግለጫው “የአማራ ሕዝብ ክፋይ የሆኑት እና ከ30 ዓመት በላይ በአማራዊ ማንነታቸው ምክንያት የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመባቸው የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች አሁን ባሉበት አማራ ክልል ሥር ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኙ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፌዴራሉ መንግስት በአፋጣኝ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ” ሲል ጥሪ አቅርቧል።

“የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ ውድ ዋጋ የተከፈለበት የማንነት ጥያቄ ብቻ አይደለም” ያለው አብን “ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ቁልፍ ሚና ያለው እና የሀገራችን ኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት የሚረጋገጥበት ጉዳይ ነው” ብሏል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በመግለጫው ህወሓትን ትጥቅ የማስፈታት ጉዳይ እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ እና መሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነት ትኩረት እንዲደረግባቸው ጥሪ አቅርቧል።
____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
ሜታ ኩባንያ ከ11 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ሊያሰናብት መሆኑ ተገለፀ

ህዳር 1፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) ፌስቡክን የሚያስተዳድረው የሜታ ኩባንያ ከተቋሙ የሰው ኃይል ውስጥ 13 በመቶ የሚሆነውን ማለትም ከ11 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ሊያሰናብት መሆኑን ማስታወቁ ተሰምቷል።

የኮሮና ቫይረሰ ወረርሺኝ ስርጭት ከፍተኛ በሆነበት እና የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ሲበራከት ለአገልግሎት ተደራሽነት በርካታ ሰራተኞችን መቅጠሩ ይታወሳል።

የሜታ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከንበርግ ለሰራተኞቹ ባስተላለፈው መልዕክት የማክሮኢኮኖሚ መዳከም እና በገበያው ከፍተኛ የንግግድ ፉክክር በመኖሩ ምክንያት ገቢያችን ከታቀደው በታች ሆኗል። በተጨማሪም “ይህ አንድ ችግር መኖሩን የሚያመለክት በመሆኑ እኔ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ” ሲል ዙከንበርግ ገልጿል።

ሜታ ኩባንያ በዓመቱ ከፍተኛ ኪሳራ ማስተናገዱ የተገለፀ ሲሆን የኩባንያው አጠቃላይ ዋጋ አንድ ትሪልየን ዶላር ደርሶ የነበረው ሜታ፤ አሁን ዋጋው ወደ 256 ቢልየን ዶላር እንደወረደም ተዘግቧል።
It’s just 3 to 4 km away from the major asphalt road and interested visitors can access the lake by walking or driving up. However, there are no shops or any shelter that can accommodate tourists. The nearest town where tourists can stay is Butajira. Read more...
https://bit.ly/3DSx8Tf
#Ethiopia #Hawassa
@AddisZeybe