አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
7.5K subscribers
4.47K photos
149 videos
15 files
3.52K links
ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ

Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC


ስልክ +251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com
Download Telegram
በዩኔስኮ የተመዘገበው የአፄ ፋሲል መዋኛ ገንዳ እና ጥምቀተ ባህር በርካታ ታሪኮች አሉት። በቀደመው ጊዜ ገንዳውን በውሃ ለመሙላት አመቺ እንዲሆን በወንዝ አቅራቢያ የተገነባ ሲሆን አሁን በቧንቧ ገንዳውን ለመሙላት 96 ሰዓታት ይወስዳል። ዝርዝሩን ያንብቡ
http://bit.ly/3HanwGg
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
ህግ አስፈፃሚ የገነነበት የፍትህ ስርዓት - ያማረ ዱካ
ምሽት 12፡30 በአዲስ ዘይቤ ዩቲዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://youtube.com/c/AddisZeybe
በባህር ዳር ከተማ አስጎብኚ የሆነው ወጣት አንዷለም ጌታሁን የጣና ሀይቅ ገዳማትን በጀልባ የማስጎብኘት የቆየ ልምድ ያለው ሲሆን አዲሱ የባህር ዳር ጥምቀት በዓል መዳረሻ በዲዛይኑ መሰረት ተሰርቶ ሲጠናቀቅ አዲስ የቱሪስት መዳረሻ ይሆናል የሚል ተስፋ ሰንቋል። ዘንድሮም በዓሉ ከ40 ዓመታት በኋላ በጣና ዳርቻ ይከበራል። መሉ ዝርዝሩን ያንብቡ
https://bit.ly/3ZHznD3
#Ethiopia #Bahirdar
@AddisZeybe
Addis Zeybe Wishes you a Happy Epiphany and Ketera celebrations!
በጎንደር የጥምቀት በአል አከባበር በድምቀት ተጀምሯል

ጥር 09፤ 2015 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፣ጎንደር) የጥምቀት በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል በጎንደር ከተማ በድምቀት ተጀምሯል። በከተማዋ እንደሚገኙ የሚታወቁት 44 ታቦታት ከያሉበት ወደ ጥምቀተ ባህሩ መጓዝ ጀምረዋል።
___
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዳይሬክተር የነበሩት ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የማዕድን ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

ጥር 12፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩት ሀብታሙ ተገኝ በቅርቡ ከስልጣኛቸው የተነሱትን ታከለ ኡማን በመተካት የማዕድን ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

አለሙ ስሜ (ዶ/ር) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር እንዲሁም ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የግብርና ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተሾሙ ሲሆን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ሹመቶቹን እንዲያፀድቅ ጠይቀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ዛሬ ጠዋት እንዳስታወቀው ክጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ማሞ ምሕረቱ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ የነበሩት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላልሴ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው ሲሾሙ በሌላ በኩል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ተደርገዋል።

ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሲሆኑ አቶ መለሰ አለሙ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
___
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
በአማራ ክልል 4 ሚሊየን ነዋሪዎች በጦርነቱ ሳቢያ አሁንም ውሃ ተቋርጦባቸዋል

ጥር 12፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ባህር ዳር) በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት 8 ሚሊየን ነዋሪዎች ውሃ ተቋርጦባቸው የነበረ ሲሆን አሁንም ግማሽ ያህሉ በችግር ውስጥ መሆኑ ተገለፀ።

የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ እንዳስታወቀው በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከ1.6 ሚሊየን ህዝብ በላይ ውኃ መግኘት የቻለ ሲሆን ከ2.4 ሚሊየን በላይ የሚሆነው ደግሞ በመንግስትና ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ ውኃ ማግኘት ችለዋል።

በአማራ ክልል ጦርነቱ በነበረባቸው 9 ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች 1 ሺህ 429 የውኃ ተቋማት ዝርፊያና ውድመት ደርሶባቸው እንደነበረ ቢሮው ገልጿል።

በክልሉ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ዝርፊያ እና ውድመት የደረሰባቸው የውሃ መሰረተ ልማት 2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው መሆኑን የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ አመልክቷል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያዘ የአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ፅህፈት ቤት ባወጣው መረጃ በክልሉ በአጠቃላይ ከ288 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ዝርፊያና ውድመት ደርሷል።
___
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
ሰዋሰው መልቲሚድያ አገልግሎቱን መጀመሩን ተከትሎ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ተጠቃሽ መነቃቃት ፈጥሯል። ኩባንያው አገልግሎቱን የጀመረበት የተቀናጀ እንቅስቃሴና እንደ ቴዲ አፍሮ ያሉትን የዘመኑን አውራ ሙዚቀኞች ማስፈረም መቻሉ የኪነ-ጥበብ መንደሩን ትኩረት ስቧል። የአዲስ ዘይቤው አብይ ሰለሞን የኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረገው ቆይታ አገልግሎቱን በጀመሩበት በዚህ አጭር ጊዜ ስለነበራቸው ልምድ ሰፊ ውይይት አድርጓል።
https://bit.ly/400CHtg
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
የአማራ ክልል የልዩ ኃይል የብርጌድ አዛዥ ኮሚሽነር ዋኘው አዘዘው በጥይት ተመተው መቁሰላቸው ተሰማ

ጥር12፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ባህር ዳር) የአማራ ክልል የልዩ ኃይል የብርጌድ አዛዥ ኮሚሽነር ዋኘው አዘዘው እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ ዳኛቸው በለጠ በጥይት መመታታቸውን አዲስ ዘይቤ አረጋግጣለች።

የከተራ በዓል በተከበረበት ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ሁለቱ የፀጥታ አመራሮች በጥይት ተመተው ሆስፒታል እንደገቡ የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ገልፀዋል።

ሁለቱ የስራ ኃላፊዎች በጥይት የተመቱት በአዝማሪ ቤት እየተዝናኑ በነበሩበት ወቅት እንደሆነም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ኮሚሽነር ዋኘው አዘዘው እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ ዳኛቸው በለጠ በጥይት የመቁሰላቸውን መንስኤ ምን እንደሆነ እና የጉዳት መጠናቸውንም ለጊዜው በግልፅ ማወቅ አልተቻለም።

የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ጥቃቱን አድርሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።
___
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe
ብሔራዊ ባንክ ምንም ዓይነት ገንዘብ እንዳልሰጣቸው የወጋገን ባንክ መቀለ ዲስትሪክት አስታውቋል። በትግራይ ክልል አገልግሎት የጀመሩ ባንኮች በጥሬ ገንዘብ እጥረት እየተቸገሩ ሲሆን በአስገዳጅ ሁኔታዎች ደንበኞች የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን ለመገደብ ግዴታ ውስጥ ገብተዋል። ዝርዝሩን ያንብቡ
http://bit.ly/3QSKi8U
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
ከነገ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚደረግ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ።
ጥር 12 1982 ዓ.ም በሶቪየት ሠራዊት በአዛርባጃን ላይ የተፈጸመው ወታደራዊ ጥቃት በአዘርባጃን ብሄራዊ ማንነት ምስረታ ላይ ወሳኝ ተፅእኖ እንደነበረውና የአዘርባጃን ነፃነት እንዲመለስ ትልቅ ምዕራፍ እንደከፈተ የሃገሪቱ መንግስት ይገልፃል። ሙሉ ዝርዝሩን ያንብቡ
http://bit.ly/3XrNBX2
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
It's announced that Safaricom Ethiopia's customers can now access the mobile airtime top-up service through the USSD menus and mobile apps of Bank of Abyssinia, Awash Bank, and NIB International Bank. Read more...
https://bit.ly/3HjlJ1G
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
ከኮሚሽነር ዋኘው የግድያ ሙከራ ጋር በተያያዘ አንድ የልዩ ኃይል አባል በቁጥጥር ስር ዋለ

ጥር 13፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ባህር ዳር) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በእነ ኮማንደር ዋኘው የግድያ ሙከራ ጉዳይ የቀድሞ የርዕሰ መስተዳደሩ የህግ አማካሪ የነበሩ የባለስልጣን አጃቢ እና የልዩ ኃይል አባል የሆነውን አለባቸው አንተነህን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተነገረ።

የአማራ ክልል የልዩ ኃይል የብርጌድ አዛዥ ኮሚሽነር ዋኘው አዘዘው እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ ዳኛቸው በለጠ በጥይት ተመተው በህክምና ላይ እንደሚገኙ አዲስ ዘይቤ መዘገቧ ይታወሳል።

ጥቃቱ የተፈፀመው የከተራ በዓል በተከበረበት ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ቀን ሲሆን ሁለቱ የፀጥታ አመራሮች በጥይት ተመተው ሆስፒታል እንደገቡ የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ገልፀው ነበር።
___
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/AddisZeybe