AACRA
9.16K subscribers
3.22K photos
42 videos
128 files
498 links
Addis Ababa City Roads Authority (AACRA) is a government organization under the Addis Ababa City Adminstration. It was established on March 1998 with the aim of realizing sustainable road infrastructure and creating interchangeable road transport to A.A.
Download Telegram
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በ2016 አፈፃፀምና የ 2017 ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች በ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና በቀጣይ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ተወያይተው የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡

አጠቃላይ ከሰራተኞች ለቀርቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከመድረክ ማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ በአዲሱ በጀት ዓመት ስኬታማ ስራዎችን ለማከናወን በተያዘው የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ሁሉም የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ኢንጂነር ሙህዲን አያይዘውም በ2016 በጀት ዓመት የተገኙ ስኬቶችና መልካም ተሞክሮችን እንደመልካም አጋጣሚ በመውሰድ በቀጣይ 2017 በጀት ዓመትም አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የባለስልጣኑ የተቋም ለውጥ እና ድጋፍ ሠጪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል ዶሌቦ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ራሷን ለመለወጥ ለምታደርገው ከፍተኛ ጥረት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ከፍተኛውን ሚና እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ፀጋዬ ቦርሴ በቀጣይ 2017 በጀት ዓመት በከተማዋ የሚገነቡ መንገዶች ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከመንገድ ሀብት አስተዳደር ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የመንገድ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አወል ሁሉም የባለስልጣኑ ሰራተኞች የከተማው መንገድን በመጠበቅና በመንከባከብ አምባሳደር ሊሆኑ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 በጀት ዓመት የተገኘውን የመንገድ መሰረተ ልማት ስኬት አጠናክሮ በማስቀጠል፤ በ2017 በጀት ዓመትም ተመሳሳይ ድሎችን ለመድገም ሁሉም አመራርና ሠራተኞች በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
አዲስ ልሳን ሰኔ 22.pdf
941.7 KB
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፡ በአዲስ ልሳን የቅዳሜ ሰኔ 22 2016 ዕትም ”እጃችንን በእጃችን” በሚል ርዕስ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ 2016 በጀት ዓመት ያከናወነውን የድሬኔጅ መስመር ፅዳት እና ጥገና ስራ አስነብበናል፤ ተጋበዙልን!
አዲስ ልሳን ሐምሌ 6.pdf
1.3 MB
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፡ በአዲስ ልሳን የቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዕትም “መሰረተ ልማቱ የፈጠረው የስራ እድል ” በሚል ርዕስ አስነብበናል፤ ተጋበዙልን!
የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራሮች እና ሰራተኞች "የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል ለ6ኛ ጊዜ እየተካሄደ ባለው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ ተካፋይ ሆነዋል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 6 በተለምዶ ወይራ ኮንደሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ስፍራ 10,000 የተለያዩ ሀገር በቀልና የውጭ ዝርያ የጥላና የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሩን ያስጀመሩት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ፤ የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች በየዓመቱ በርካታ ችግኞችን በጋራ መትከላቸውን አስታውሰው፤ የችግኞቹ መተከል የአየር ብክለትን ለመቀነስ፣ በክረምት ወቅት የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው ብለዋል፡፡


በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ 50 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱንና፣ ከእነዚህ ውስጥ 3ሺ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ የፍራፍሬ ዝርያዎች መሆናቸውን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የተቋሙ ሠራተኞች በቀጣይም የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ለውጤት እንዲያበቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።


ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በዘንድሮ የክረምት ወራት ከችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በተጨማሪም የአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት፣ የደም ልገሳ፣ የህፃናት ድጋፍ እና የተለያዩ በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ኢንጅነር ሙህዲን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በችግኝ መርሃ-ግብሩ የተሳተፉ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በበኩላቸው፤ የከተማዋን አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ ለሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ የአካባቢ የአየር ብክለነትን ለመከላለከልና በምቹ ከባቢያዊ አየር ንብረት ውስጥ ለመኖር ችግኞችን መትከልና መንከባበከብ እንደሚያስፈልግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et