AACRA
7.35K subscribers
2.88K photos
37 videos
86 files
444 links
Addis Ababa City Roads Authority (AACRA) is a government organization under the Addis Ababa City Adminstration. It was established on March 1998 with the aim of realizing sustainable road infrastructure and creating interchangeable road transport to A.A.
Download Telegram
ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆኑ ቦታዎች ፈጣን ማስተካከያ እንዲደረግባቸው የሥራ መመሪያ ተሰጠ

አዲሱ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተለያዩ የሥራ ክፍል መሪዎችን አነጋግረዋል

ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በቅርቡ የተሾሙት ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ ፈጣን ምላሽ በሚጠይቁ የመንገድ ጥገና ሥራዎች ላይ ከሚመለከታቸው የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በክረምቱ ዝናብ ሳቢያ በትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ መስተጓጎል የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን በቀጣዮቹ 15 ቀናት ማስተካከል ይቻል ዘንድ፤ የመንገድ ሀብት አስተዳደርና የኦፕሬሽን ዘርፎች በቅንጅት ሊፈፅሟቸው በሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ትኩረት በማድርግ ዛሬ ከቀትር በፊት የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይ ቀናትም፤ ወቅታዊ ሥራዎች በፍጥነት እንዲፈፀሙና የ2017 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎችን ከወዲሁ ማጠናቀቅ የሚያስችሉ ተከታታይ ውይይቶች በተለያዩ ዘርፎች ስር ከተደራጁ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍል መሪዎች ጋር ይካሄዳል፡፡

በሌላም በኩል፤ የባለሥልጣን መስሪያቤቱን የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን ለመፈፀም የሚያስችሉ የተለያዩ ኮሚቴዎች ተደራጅተው ወደ ተግባር እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቅርቡ የሚመረቀው የቦሌ ኮሪደር ልማት በከፊል
በበጀት ዓመቱ በመዲናዋ የተከናወኑ የኮርደር ልማት ስራዎች
***

1. በመንገድ መሠረተ ልማት

• ከ48 ኪ.ሜ በላይ የተሽከርካሪ መንገድ፣

• ከ96 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣

• 100 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ፣

• 4 የመሬት ውስጥ የእግረኛ (underpass) መንገዶች፣

• 5 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣

• ⁠2 የተሽከርካሪ ድልድዮች፣

• ⁠3 ዘመናዊ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች፣

2. በኮሪደር ልማቱ የትራንስፖርት ሥርዓት ለማሳደግ

• በአንድ ጊዜ 6,369 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 32 ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች፣
 
• በአንድ ጊዜ 517 ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያላቸው 9 የባስ እና ታክሲ ተርሚናሎች፣
 
• በአንድ ጊዜ 268 ባሶችንና ታክሲዎችን ለአጭር ጊዜ የመጫንና ማውረድ አገልግሎት የሚሰጡ 85 የመንገድ ዳር የባስና ታክሲ ማዉረጃ ቦታ፣

• 50 ኪሎ ሜትር የትራንስፖርት ደህንነት ማረጋገጥ የሚያስችል  (ITS) መስመር ዝርጋታ

• በኮሪደር ልማቱ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት

እስክሪንና ዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎች የተገጠሙለት 450 ዘመናዊ ስማርት ፖሎች፣ በኢትዮጵያ አምራቾች ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረተ፣

• 48 ኪሎ ሜትር የደህንነት ካሜራ መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣

• 1,582 መደበኛ የመንገድ መብራቶች (Normal street lights)፣

• ከ96 ኪሎ ሜትር ለአደጋ መንስዔ የኤሌክትሪክ መስመሮች እና ፖሎችን አንስቶ በምድር ውስጥ መቅበር ሥራ፣

3. በኮሪደር ልማቱ የሕዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎችን ማስፋፋት

• 32 የውሃ ፏፏቴዎች፣

• 20 ሄክታር የሚሸፍን መልሶ ማልማት፣

• 8 ወንዞች በተቀናጀ መልኩ ማልማት፣

• 120 ዘመናዊ የመንገድ ዳር የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች (Public toilets)፣

• 50 ሄክታር በላይ የከተማ አረንጓዴ ልማት ሥራዎች፣

• 70 የሕዝብ መናፈሻ ሥፍራዎች እና የፈጣን ምግብ አገልግሎት መሸጫ ቦታዎች፣

4. በኮሪደር ልማቱ የውሃና ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራዎች

• 48 ኪ.ሜ የጎርፍ ማስወገጃ ሥርዓት ዝርጋታ፣

• ከ17.8 ኪ.ሜ በላይ አዲስ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ዝርጋታ፣

• ከ69 ኪ.ሜ በላይ የመጠጥ ውሃ ማሰራጫ መስመር ዝርጋታ፣

• ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠሪያ አገልግሎት የሚውል ባለ 110 ሚሊ ሜትር HDPE የቧንቧ ዝርጋታን ተከትሎ 71 የፋየርሃይድራንት (Fire Hydrant) መትከል፣

5. በኮሪደር ልማቱ የቴሌኮሚኒኬሽን መሠረተ ልማት ሥራዎች

• ከ70 ኪሎ ሜትር በላይ የቴሌኮም መገልገያ ዳክት ግንባታ፣

• 75 ኪሎ ሜትር የመዳብ ኬብል ዝርጋታ፣

• 152 ኪሎ ሜትር የፋይበር ኬብል አዘዋውሮ የመዘርጋት ሥራ፣

• 57 የኔትዎርክ ማከፋፈያ ሳጥኖች ተከላ፣

• 1,627 ምሰሶዎች ተከላ መከናወናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ባቀረቡት ሪፖርት ገልፀዋል።
የፕሮጀክት አፈፃፀም በተመለከተ በበጀት አመቱ 18,091 ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለህዝብ አገልግሎት ክፍት አድርገናል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በ2016 አፈፃፀምና የ 2017 ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች በ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና በቀጣይ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ተወያይተው የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡

አጠቃላይ ከሰራተኞች ለቀርቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከመድረክ ማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ በአዲሱ በጀት ዓመት ስኬታማ ስራዎችን ለማከናወን በተያዘው የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ሁሉም የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ኢንጂነር ሙህዲን አያይዘውም በ2016 በጀት ዓመት የተገኙ ስኬቶችና መልካም ተሞክሮችን እንደመልካም አጋጣሚ በመውሰድ በቀጣይ 2017 በጀት ዓመትም አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የባለስልጣኑ የተቋም ለውጥ እና ድጋፍ ሠጪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል ዶሌቦ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ራሷን ለመለወጥ ለምታደርገው ከፍተኛ ጥረት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ከፍተኛውን ሚና እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ፀጋዬ ቦርሴ በቀጣይ 2017 በጀት ዓመት በከተማዋ የሚገነቡ መንገዶች ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከመንገድ ሀብት አስተዳደር ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የመንገድ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አወል ሁሉም የባለስልጣኑ ሰራተኞች የከተማው መንገድን በመጠበቅና በመንከባከብ አምባሳደር ሊሆኑ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 በጀት ዓመት የተገኘውን የመንገድ መሰረተ ልማት ስኬት አጠናክሮ በማስቀጠል፤ በ2017 በጀት ዓመትም ተመሳሳይ ድሎችን ለመድገም ሁሉም አመራርና ሠራተኞች በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et