AACRA
10.7K subscribers
7.97K photos
194 videos
221 files
707 links
Addis Ababa City Roads Authority (AACRA) is a government organization under the Addis Ababa City Adminstration. It was established on March 1998 with the aim of realizing sustainable road infrastructure and creating interchangeable road transport to A.A.
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ 27.3 ኪሎ ሜትር የፔዳል ሳይክል መንገድ ተገንብቷል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት 9 ወራት ውስጥ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ 27.3 ኪሎ ሜትር የፔዳል የሳይክል መንገዶችን ገንብቷል፡፡
በከተማዋ በየዓመቱ ጥራታቸውን የጠበቁ የፔዳል የሳይክል መስመሮች ግንባታ እያደገ መምጣቱ ለነዋሪዎች የትራንስፖርት አማራጭ ከመፍጠሩም ባሻገር የዜጎችን ጤንነትን በመጠበቅ ረገድ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
2
ባለፉት 9 ወራት ከ1 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ ተከናውኗል
መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በአለፉት ዘጠኝ ወራት፤ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች 1 ሺህ 180 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ እና የጥገና ስራዎች አከናወነ፡፡
የበጀት ዓመቱ የ9 ወራት አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር፤ በግንባታ 4.53 በመቶ እና በጥገና 10.25 በመቶ እድገት ተመዝግቧል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ 258 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ከ 921 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና ሥራዎችን ያከናወነ ሲሆን፤ ይህም የአስፋልት፣ የኮብል ንጣፍ፣ የጠጠር መንገዶች፣ የድሬኔጅ እና የድጋፍ ግንብ ሥራዎችን፣ እንዲሁም የእግረኛና የሳይክል መንገዶች ግንባታ ያካትታል።
በሌላም በኩል፤ የአስፋልትና የኮብል ንጣፍ ጥገና፣ የጠጠር መንገዶች እድሳት፣ የድሬኔጅ መስመሮች ጽዳትና ጥገና፣ የእግረኛ መንገዶች እና ከርቭ ስቶን ስራዎች እንዲሁም የእግረኛ መከላከያ አጥር ጥገና ባለፉት 9 ወራት ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት 9 ወራት በመንገድ ልማት ዘርፍ ላከናወናቸው ሥራዎች ማስፈፀሚያ፤ በጥቅሉ ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ጥቀም ላይ አውሏል።
👍4
ትላንት ማምሻውን ውብና ማራኪ ተደርጎ በ1.3 ሄክታር ቦታ ላይ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለህዝብ የተገነባውን የሳር ቤት ፕላዛ መርቀን ስራ አስጀምረናል።
በከተማችን የምናከናውናቸው የልማት ስራዎች ለሰው ልጅ ክብርና ጥቅም የሚሰጡ፣ የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉ እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች ማህበራዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩባቸው ናቸው።
የመንግስትን የልማት ስትራቴጂ በመከተል የግል ሴክተሩም በከፍተኛ ፍጥነትና ተነሳሽነት አብሮን እየሰራ ይገኛል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከራሱ የግል ይዞታ 1.3 ሄክታር መሬት በመወሰን አልምቶ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል ማድረጉ አዲስ እሳቤና ትልቅ ለውጥ በመሆኑ፤ እንዲሁም የወንዝ ዳር ልማትም ስንሰራ አብሮን የሰራ ስለሆነ በከተማችን ነዋሪዎች እና በራሴ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለትንሳዔ በዓል የሸቀጦች አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል፡- የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ የሸቀጦች አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰትና ገበያው እንዲረጋጋ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቋል።
የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ከተማ አስተዳደሩ በዓሉን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የፍላጎት መጨመር ታሳቢ በማድረግ ካለፈው ወር ጀምሮ ከተለያዩ ክልሎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ምርት የማሰባሰብ ሥራ ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።
ወቅታዊው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ችግር በምርት ስርጭት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር የተቀናጀ ዝግጅት መደረጉን ኃላፊዋ አመላክተዋል፡፡
በዚህም ለኅብረተሰቡ አማራጭ የገበያ ቦታዎችን ለማቅረብ በተሰራው ሥራ በመንግሥት በተዘጋጁ 6 ዋና ዋና የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከላት፣ በ246 የሰንበት ገበያዎችና በ2 ሺህ 56 የኅብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች በቂ ምርት እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል።
በተለይም መሰረታዊ ሸቀጦችንና እንደ ዘይት ያሉ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለተጠቃሚው ለማድረስ ሰፊ የገበያ ትስስር መፈጠሩ የተገለጸ ሲሆን፤ የሥጋ ምርትን በተመለከተም ኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ በህብረት ሥራ ማህበራት በኩል አንድ ኪሎ ሥጋ በ650 ብር እንዲቀርብ መወሰኑ ተመላክቷል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በበዓሉ ወቅት የዋጋ ንረትና የንግድ ማጭበርበር እንዳይኖር ቢሮው በሁሉም የገበያ ማዕከላት፣ ባዛሮችና መደበኛ ሱቆች ላይ ቁጥጥር የሚያደርግ ግብረ ኃይል አሰማርቷል።
በዚህም መሰረት ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ በምርት ላይ ባዕድ ነገር በሚቀላቅሉና በሚዛን በሚያጭበረብሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።
ኅብረተሰቡ የምርት እጥረት ሳያጋጥመው በዓሉን እንዲያከብር የሚያስችሉ እነዚህ የገበያ ማረጋጋት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ቢሮው አስታውቋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
https://linktr.ee/aacracom
4👍1