ለከተማችን ነዋሪዎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል!
ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር (በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ)
አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት የተገልጋዮችን እንግልት በማስቀረት ለነዋሪዎች በቅርበት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው።
የከተማ አስተዳደሩ ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከላት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በፍጥነት ተገንብተው ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ በገባው ቃል መሰረት፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዛሬውን 5ኛ የአዲስ መሶብ አዲስ ከተማ ማዕከል ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል።
በአዲስ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት፦በዋና መስሪያ ቤት 22 ተቋማት 140 ዓይነት አገልግሎቶችን እየሰጡ ይገኛሉ። በቅርቡ ወደ ስራ የገቡት 3 የክፍለ ከተማ ማዕከላት ላይ ደግሞ 20 ተቋማት 112 ዓይነት አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ናቸው። በተበታተነና በተንዛዛ መልኩ ይሰጡ የነበሩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማዘመን፣ በተቀናጀ አግባብ በአንድ ማዕከል እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል።
የአዲስ ከተማ "አዲስ መሶብ" የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት በ85 ካውንተሮች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ በውስጡም፦ምቹ የተገልጋዮች ማረፊያ፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ የሕፃናት ማቆያ እና ካፌቴሪያዎችን አካቷል።
አስተዳደሩ በመንግስት ተቋማት የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችን ለማስተካከልና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ፣ ባለፉት 3 ዓመታት ሰፋፊ የሪፎርም እና የተቋም ግንባታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል።

❤4👍1
ዛሬ ከማለዳዉ አንስቶ በአዲስ አበባ በተካሄደዉ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተላለፉ ዋና ዋና መልዕክቶች
• ከመጋቢት ብርሃን ወደ ዓለም አቀፍ ልዕልና!
• በመጋቢት የተገባው ትውልድ ተሻጋሪ ቃል፣ የአዲስ አበባን ልዕልና አረጋግጧል!
• የለውጥ ጮራ ፈንጣቂው አንፀባራቂ ድል!
• መጋቢት ኢትዮጵያን የማላቅ፣ ታሪክን የማደስ የቆራጥነት ወር!
• ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገርነት!
• ከመጋቢት እስከ መጋቢት፤ በትሩፋት የደመቀ፣ በተግባር የተረጋገጠ ጉዞ!
• በፈተና ያልተንበረከከች፣ በመጋቢት የታደሰች ሉዓላዊት ኢትዮጵያ!
• አስተሳሳሪ የወል ትርክታችን ለዘላቂ አንድነትና አብሮነታችን!
• መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ከተሞች ትንሳኤ!
• ከአሮጌው ስብራት ወደ አዲስ ከፍታ!
• መጋቢት 24 የአይበገሬዎች መድረክ፣ የከፍታችን መጀመሪያ!
• መጋቢት 24 ለከተማችን ሁለንተናዊ ለውጥ የማይደበዝዝ አሻራ ያኖረ ቀን!

👍3❤2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን! ዛሬ በታሪካዊቷ መጋቢት 24 ቀን፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 6ተኛውን ‘አዲስ መሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከል’ የመንግሥት አገልግሎት በይፋ አስጀምረናል።
Waaqni nu gargaare haa galatoomu! Har'a guyyaa seena qabeessa bitootessa 24 tti, kutaa magaalaa Gullalleetti 'Addis Masoob' tajaajila mootummaa dijitaalawaa giddugala tokkoo ifatti eegalchiisnee jirra.

❤5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ 27.3 ኪሎ ሜትር የፔዳል ሳይክል መንገድ ተገንብቷል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት 9 ወራት ውስጥ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ 27.3 ኪሎ ሜትር የፔዳል የሳይክል መንገዶችን ገንብቷል፡፡
በከተማዋ በየዓመቱ ጥራታቸውን የጠበቁ የፔዳል የሳይክል መስመሮች ግንባታ እያደገ መምጣቱ ለነዋሪዎች የትራንስፖርት አማራጭ ከመፍጠሩም ባሻገር የዜጎችን ጤንነትን በመጠበቅ ረገድ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡

❤2
ባለፉት 9 ወራት ከ1 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ ተከናውኗል
መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በአለፉት ዘጠኝ ወራት፤ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች 1 ሺህ 180 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ እና የጥገና ስራዎች አከናወነ፡፡
የበጀት ዓመቱ የ9 ወራት አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር፤ በግንባታ 4.53 በመቶ እና በጥገና 10.25 በመቶ እድገት ተመዝግቧል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ 258 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ከ 921 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና ሥራዎችን ያከናወነ ሲሆን፤ ይህም የአስፋልት፣ የኮብል ንጣፍ፣ የጠጠር መንገዶች፣ የድሬኔጅ እና የድጋፍ ግንብ ሥራዎችን፣ እንዲሁም የእግረኛና የሳይክል መንገዶች ግንባታ ያካትታል።
በሌላም በኩል፤ የአስፋልትና የኮብል ንጣፍ ጥገና፣ የጠጠር መንገዶች እድሳት፣ የድሬኔጅ መስመሮች ጽዳትና ጥገና፣ የእግረኛ መንገዶች እና ከርቭ ስቶን ስራዎች እንዲሁም የእግረኛ መከላከያ አጥር ጥገና ባለፉት 9 ወራት ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት 9 ወራት በመንገድ ልማት ዘርፍ ላከናወናቸው ሥራዎች ማስፈፀሚያ፤ በጥቅሉ ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ጥቀም ላይ አውሏል።

👍4