AACRA
10.7K subscribers
7.96K photos
193 videos
221 files
707 links
Addis Ababa City Roads Authority (AACRA) is a government organization under the Addis Ababa City Adminstration. It was established on March 1998 with the aim of realizing sustainable road infrastructure and creating interchangeable road transport to A.A.
Download Telegram
"የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ፣ የነገ ተስፋን ያበሩ ሰው ተኮር የመጋቢት ፍሬዎች!"

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም፣ የለውጡ መንግስት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ያደረገበት ታሪካዊ ቀን ሲሆን መንግስት ሀገራዊ ኃላፊነቱን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ "ሰው ተኮር" ስራዎችን ዋነኛ መገለጫው በማድረግ፣ የዜጎችን ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ያለሙ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ፣ በበጋና ክረምት የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ፤-የቤት ዕድሳት፣ የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት ማስፋፋት፣ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም፣ ማዕድ ማጋራት እና ሌሎች መሰል ተግባራትን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራባቸዉ የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ፣ የነገ ተስፋን ያበሩ ሰው ተኮር የመጋቢት ፍሬ ዉጤቶች ናቸዉ፡፡

በተጨማሪም እንደ “የነገዋ” ያሉ የነገን ብሩህ ተስፋ የሚያሰንቁ የሴቶች የክህሎት ማበልፀጊያ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ የሚሰጡ ማዕከላትን በመገንባት ሙያዊ ክህሎት በማስጨበጥ እና ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ እህቶቻችን ነገአቸውን እንዲያልሙ በዚህም ተስፋቸው እንዲገለጥ እና እፎይታን እንዲጎናፀፉ ማድረግ መቻሉ ሌላዉ ማሳያ ነዉ፡፡

በሌላ በኩልም ከውጭ ለሚመጡ ስደተኞች ዜጋ ተኮር ፖሊሲ በመቅረፅ ህይወታቸዉ በአዲስ መልክ እንዲለወጥ፤የሃገር እና የወገን ኩራት ስሜት እንዲያድርባቸዉ በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ ማድረግ መጀመሩ መንግስት ለዜጎች ክብር የሰጠዉ መገለጫ ነዉ ማለት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ እነዚህን በመሳሰሉት እና ሰው ላይ ኢንቨስት የማድረግ ቀዳሚ ጉዳዮች ለሀገር የወደፊት ተስፋ መሰረት ነው በሚል እሳቤ እየተከናወኑ የሚገኙ ሸክም አቅላይ፣ እፎይታ ሰጪ “ሰው ተኮር” ስራዎች ዛሬ ብቻ ሳይሆን ወደፊትም የበለጠ ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ የመጋቢት ፍሬዎች እና አሳቤዎች ናቸው፡፡
2
በነዳጅ አቅርቦት እጥረት ሳቢያ የሚፈጠርን ጫና ለመቀነስ መንግሥት ያሳለፈው የቅድሚያ አሰጣጥ ውሳኔ
*********************
ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ በቅድሚያ የሚያገኙ አካላት፦
1. ነዳጅ የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች በማደያ የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው
2. ከፍተኛ አምራችና የኤክስፖርት ድርጅቶች በቀጥታ ፣
3. ልዩ ትኩረት የሚሹ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች በቀጥታ፣
4. የገቢና ወጪ ንግድን ጨምሮ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች
5. ግብርናን የሚያዘምኑ ትራክተሮች፣
6. የከተማና ሀገር አቀፍ የብዙሃን ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች
7. እንዲሁም በናፍጣ የሚሰሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በቅድሚያ እንዲያገኙ የሚያደርግ የቅድሚያ የነዳጅ አጠቃቀም አሠራር የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።
ከህብረተሰቡ የሚከጠበቁ ተግባራት፦
1) ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም፣
2) የታዳሽ ኃይል አማራጮችን የመጠቀም ስልትን መከተል፣
3) የእግር ጉዞ ባህልን ማጎልበት
4) አላስፈላጊ የጉዞ ፕሮግራሞችን መሰረዝና ማቆም
5) የሕዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም
6) በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ማጋለጥ
#Ethiopia #MOTRI
4
የጨረታ ማስታወቂያ ፡-
የሰብ ቤዝና ቤዝ ኮርስ ምርት ግዥ ጨረታ