የፋኑኤል፣ በረከቴና ወታደር ሰፈር ሎት 2 የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በመከናወን ላይ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ የፋኑኤል፣ በረከቴና ወታደር ሰፈር ሎት 2 የአስፓልት መንገድ ግንባታ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል በድሪባ ደፈርሻ ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ ሲከናወነ የቆየ ቢሆንም፤ ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ በፍጥነት ባለመከናወኑ፤ የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለህብረተሰቡ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የኮንትራት ውሉን በማቋረጥ፤ አሁን ላይ በማህበራትና በራስ ኃይል ግንባታው በማከናወን ላይ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 2.86 ኪሎ ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ከ16 እስከ 20 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት የሚሸፍን ሲሆን፤ አሁን ላይ የቁፋሮና የገረጋንቲ ሙሌት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም 700 ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው ከፋኑኤል ኮንዶሚኒየም - ስልጤ ሰፈር - ዓለም ባንክ የሚወስደውን መንገድ ግንባታ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ፣ ከፋኑኤል ኮንዶሚኒየም - በረከቴና ወታደር ሰፈርን አቋርጦ እስከ ዓለም ባንክ ያለውን የትራፊክ ፍሰት በማሳለጥ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ለረጅም ጊዜ ሲያነሱት ለነበረው የትራንስፖርትና የመሠረተ ልማት ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

❤4👍4
አዲስ አበባ ስሟን መሆን የቻለችበት እጅግ ፈጣን፣ ሁለንተናዊ ለውጥ - ቃልን በተግባር!
አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ ባቀድነው መሠረት፣ በ24/7 የተለወጠ የሥራ ባሕል፣ በትጋት እና ታማኝነት ከተማችንን በሁሉም መስፈርቶች ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የላቀ መዲና የማድረግ ሕልማችን በአስተማማኝ መንገድ ላይ ነው።
ከተማችን እየተገበረች ባለችው ሁለንተናዊ ልማት ለሁሉም የምትመች፣ ሁሉንም በፍትሀዊነት የምታገለግል ፣ ማንንም ያልዘነጋች የአካታች ልማት ማሳያ ከተማ እያደረግናት ነው።
ለሕፃናት፣ ለወጣቶች፣ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች፣ ለእግረኛው፣ ለባለ መኪናውና ለባለ ሳይክሉ የትራንስፖርት አማራጮችንና መሠረተ-ልማቶችን በፍትሐዊነት ያመቻቸች፤ ለስማርት ከተማነት፣ ለአገልግሎት አሰጣጥ፣ ለሸማቹ፣ ለባለሀብቱ ፣ ለንግድና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን የፈጠረች እና የኮፍረንስ ቱሪዚም ማዕከል ከተማ እየሆነች ነው።
ብዝሃ የምርት አቅርቦትን ለሸማቹ የሚያቀርቡ ተደራሽ የገበያ ማዕከላት፣ ሸማች ብቻ ሳሆን አምራችም እየሆነች የመጣችበት እንዲሁም የትናንት ቀደምቶች ታሪክና አሸናፊነትን ከዛሬና ከነገ ጋር የሚያስተሳስሩ እንደ አድዋ ድል ሙዚየም፣ የአብረሆት የእውቀት መሸመቻ ማዕከል፣ አስደናቂ አረንጓዴ የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎችና የአደባባይ የኪነ-ጥበብ ትዕይንት ማቅረቢያዎችን አካትታ፤ የዲፕሎማሲ፣ የብዝሃ ማንነት፣ የብዝሃ ባህል ድምቀት እና የጠንካራ የአንድነት ማዕከል “አዲስ አበባ “የሁላችንም ከተማ ናት ።
በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባን የኢትዮጵያ የብልጽግና ተምሳሌት ከማድረግ ባሻገር፣ የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑን በአዲስ አበባ ልማት በተግባር እያስመሰከርን እንገኛለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

❤6