Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.08K subscribers
6.34K photos
67 videos
18 files
256 links
Download Telegram
ለዚህ አስደናቂ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች ማህበረሰብ ስለሰራንለት ደስ ይለናል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ በተመረቀው የእንጦጦ እስከ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ ለአካባቢው ታታሪ ማህበረሰብ መስራት በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የቀጨኔና እንጦጦ ነዋሪዎች በሸማና ሸክላ ስራ የሚደነቁ ቢሆንም የሚገባቸውን ክብር አላገኙም ያሉት ከንቲባዋ፣ ፕሮጀክቱ ይህንን የተሳሳተ አመለካከት እንደሚቀይር ጠቁመዋል።

ቀደም ሲል የሚመረተውን አክምባሎ በማስታወስ፣ የእጅ ጥበብ ስራዎች ለጎብኚዎች የሚቀርቡባቸው ሱቆች መዘጋጀታቸውንና የባህል ማስታወሻ ቅርጻ ቅርጾች መካተታቸው ለአካባቢው ሙያተኞች “ስራችሁ ክቡር እንጂ የሚታፈርበት አይደለም” የሚል መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑን ገልጸዋል።

አካባቢው በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ በዚህ ልማት አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑ እስከ 10 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል አግኝተዋል።

ወጣቶችም ከአደገኛ ሁኔታዎች ርቀው በካፌዎች፣ ልብስ ስራና ስፖርት ማዕከላት ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።

እያንዳንዱ ተቋም የራሱ ታሪክ እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ሲሆን፣ የሀገር ባህልን ከሚያንጸባርቁ ቅርጻ ቅርጾች ባሻገር የኢትዮጵያን ክብር ያሳዩ አትሌቶችን የሚዘክሩ ሃውልቶችም ተቀምጠዋል። ከንቲባዋ ነዋሪዎች የጋራ ሀብታቸው የሆነውን ስፍራ እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ለማህበረሰቡ፣ ለወጣት ኮንትራክተሮችና ፕሮጀክቱን በግንባር ቀደምትነት ላስተባበሩት የከንቲባ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ምስጋና አቅርበው፣ ወንዙን በማጽዳት ሂደት የተከፈለውን መስዋዕትነት አድንቀዋል።

የተሰራው ስራ ታሪካዊ ስኬት መሆኑን በመግለጽም “እኛ እናልፋለን፤ ታሪክ ግን አያልፍም” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
1
የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡
በሀገር በቀል እዉቀት ፣ በህዝብ እና በመንግስት ትብብር የተገኘ ድንቅ ውጤት !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማጎልበት የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው - የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የቡድኑን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያ ግምገማ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ውቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሠራውን ሥራ እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።

አጠቃላይ የምርጫው ሂደትም የኢትዮጵያን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች ማዕቀፍን በተከተለ መልኩ መካሄዱን በግምገማው ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።

ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ የነበረው ሂደት አበረታች እንደነበር የገለጹት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የአፍሪካ ኅብረት ከምርጫው ዋዜማ አንሥቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ በተመለከተም ሕዝቡ እንዴት መምረጥ እንዳለበት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉን እና በምርጫው ዕለት የነበረው የተቀናጀ መናበብ ለመራጮች ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን አስረድተዋል።

በምርጫው ሂደት ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ በተለይም ለወጣቶች የፈጠረው ዕድል ከፍተኛ መሆኑን የታዛቢ ቡድኑ መሪ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

የድምፅ መስጫ ሰዓት መራዘሙ ለመራጮች ተጨማሪ ዕድል መፍጠሩን፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ቅድሚያ መሰጠቱ የዜጎችን ተሳትፎ በእጅጉ ማነቃቃቱንም ጠቁመዋል።

በመላው ኢትዮጵያ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና የፀጥታ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጥሩ ሁኔታ መወጣታቸውን፣ የመገናኛ ብዙኃንም በተመሳሳይ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ሥራቸውን ማከናወናቸውን አድንቀዋል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው ያሳየው ተሳትፎ እና ትልቁን ኃላፊነቱን በጀግንነት መወጣቱ እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።