Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
1.66K subscribers
891 photos
27 videos
7 files
40 links
Download Telegram
አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ድርሻ ጉልህ ነው፡፡

ክፍተቶቻችን ላይ ትኩረት አድርገን ለላቀ ስኬት በአርበኝነት ስሜት መስራት ያስፈልጋል፡፡ (አቶ መኮንን ያኢ)

ሚያዚያ 30/2017 (መልአ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር በቅርቡ ባደረገው የአመራር ሽግሽግ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮን እንዲመሩ የተመደቡት አቶ መኮንን ያኢ ከተቋሙ አመራርና ሠራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡

ኃላፊው በመልዕክታቸው መንግስት አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚያደረገው ርብርብ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ድረሻ ጉልህ መሆኑን በመጥቀስ ለዚህም በየደረጃው የሚገኘው የተቋሙ ሠራተኞች ከምንጊዜውም በላይ ለላቀ ስኬት በአርበኝነት ስሜት ሊሰሩ ይገባዋል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ጉድለቶቻችን ላይ ትኩረት በማድረግ ለዕቅዶቻችን ስኬት ተናቦ መስራት እንደሚገባም በመልዕክታቸው አፅንኦት ሰጥተውበታል፡፡

አክለውም ስራዎቻችን በጊዜና በጥራት ሊለኩ ይገባል ያሉት ኃላፊው ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባም አሳስበዋል ፡፡

የቢሮው ተግባራት ጥረትን የሚጠይቁ ናቸው ያሉት የአገልግሎት ማሻሻያና የመሬት መረጃ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተመደቡት አቶ አእምሮ ካሳ እና አዲሱ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ፈይሳ የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት በጋራ ልንረባረብ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ6177 ልዩ ልዩ የፍርድ ቤት ትዕዛዞች ቀልጣፋ ምላሽ ተሰጥቷል ፡፡   አቶ ደረጀ ላቀው

ግንቦት 07/2017(መልአ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2016 ዓ.ም ባደረገው ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ ሪፎርም በአዲስ መልክ ከተቋቋሙት አስራ ሶስት የስራ ክፍሎች ( ዳይሬክቶሬቶች ) የህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ክትትል ዳይሬክቶሬት አንዱ ነው፡፡

ዳይሬክቶሬቱ በዋነኝነት ቢሮው የሚጠቀምበትን የህግ ማዕቀፎችና ከፍርድ ቤት የሚቀርቡ ልዩ ልዩ ትዕዛዞች፤ክስና ክርክሮች ማብራሪያና ማስረጃ አደራጅቶ የሚያቀርብ የስራ ክፍል መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ላቀው ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ከቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይክቶሬት ጋር በዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ዙሪያ ቆይታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት ዳይሬክቶሬቱ ቢሮው ከተቋማዊ ሪፎርም በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን ውስብስብ ደንቦች ፡ መመሪያዎችና ሰርኩላሮችን በአዲስ መልክ በመሰብሰብ የከተማ መሬት ሊዝ ደንብ 162/2016 እና የመብት ፈጠራ ይዞታ አገልግሎት ደንብ ቁጥር 163/2016 በሚል ሁለት ደንቦችን አዘጋጅቶ ስራ ላይ በማዋል ቀደም ሲል  ለአገልግሎት አሰጣጡ ማነቆ የነበሩ በርካታ ችግሮችን ከመቅረፉ ባሻገር ለፍትሐዊ አገልግሎት መደላድል መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ከአፈፃፀም ጋር በተያያዘ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 6304 ልዩ ልዩ የፍርድ ቤት ትዕዛዞችን በመቀበል ለ6177 ትዕዛዞች አፋጣኝ ማስረጃና ማብራሪያ ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል በቀሪ ሁለት ወራት የትኩረት መስኮችን በመለየት የማፍጠኛ እቅድ ላይ ውይይት አድርጓል።

ግንቦት 07/2017(መልአ)
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዓመታዊ ዕቅድን በጊዜና በጥራት መፈፀም ያስችል ዘንድ በየ15 ቀናት በቢሮ ጠቅላላ ካውንስል ያስገመግማል።
ሂደቱ ጠንካራ ተግባራትን ከማስቀጠል ባለፈ ጉደለቶቹን ለይቶ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል።

በዚህ መነሻነት የቢሮው የ10 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን  የቀሪ ሁለት ወራት ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን ያመላከተ የሁለት ወራት ዕቅድ  በጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ፈይሳ ቀርቦ በቢሮ ካውንስል ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን በማመላከት የቀረበው የቀሪ ሁለት ወራት ዕቅድ ከእቅድ ባለፈ በባለፉት አስር ወራት የነበሩ የአፈፃፀም ጉድለቶችንና ጥንካሬዎችን በመለየት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያመላከተ ነው።

በውይይቱም በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፤ የተቋሙን ገቢ የማሰባሰብ አቅም ማሳደግና የተቋሙን ተግባርና ሀላፊነት ለማሳካት የጋራ ጥረት መደረግ አለበት ያሉት የቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያዒ በእቅዶቻችን ላይ ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራትም ለዕቅዶቻችን ስኬት ጉልህ አስተዋፆኦ እንዳለውም ተናግረዋል።

አያይዘውም በየትኛውም የስራ ዘርፍ የሚታዩ ብልሹ አስራሮችን  በማረም ትጉ ባለሞያዎችን መለየትና እውቅና መስጠትም በቀሪ ወራት ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆን እንደሚገባው አሳስበዋል።