Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.08K subscribers
6.33K photos
67 videos
18 files
256 links
Download Telegram
የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!

ዛሬ በምርጫ ማግስት የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ተመርቀው ለህዝብ ክፍት አድርገናል።

በከተማችን ለሚገኙ ለብዙዎቹ ወንዞች መነሻና የከተማችን ሳምባ የሆነው ደን የሚገኝበት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ ያለው አካባቢ ወደ ተፈጥሯዊ ይዘቱ ተመልሶ የአካባቢውን ማህበረሰብ አኩሪ የስራ ባህል የሚዘክሩ ሃውልቶችና ቅርሶች ተገንብተውለት አካባቢው ፍፁም ማራኪ እና የሚያስደንቅ ገፅታን ተላብስሶ ተጠናቋል።

የቀጨኔ አካባቢ ከዚህ ቀደም ለሰው ኑሮ ምቹ ያልሆነ፣ ለአደጋ የተጋለጠ እና የተጎሳቆለ አካባቢን መልሶ በማልማት ውስን የሆነውን የከተማዋን የመሬት ሀብት ለብዙሃን አገልግሎት እንዲሰጥ በሚያስችል መልኩ ለምቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

597 ሄክታር ቦታ እና 9.6 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ለመዝናኛ፣ ለንግድና ለተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች ተስማሚ በሆነ መልኩ የተገነባ ሰፊ የከተማ መናፈሻ ሆኗል።

በከተማ ግብርና ስራዎች 15 ሄክታር ቦታ በአረንጓዴ የተሸፈነ ሲሆን፣ ቀሪው ደግሞ በ210 ቀፎ ዘመናዊ ንብ እርባታ፣ በአበባ ጋርደን እና በእፀዋት ጋርደን ለምቷል።

እንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ያካተታቸው ሌሎች መሰረተ ልማቶች፦
6.4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፣ 8 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ፣ 22 ክሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 4 ኪሎ ሜትር ሃይኪንግ መንገድ፣ 39 ቼክ ዳም ተገንብተዋል።

2 አዲስ የተሽከርካሪ ድልድዮች ሲገነቡ፣ 3 ነባር የተሽከርካሪ ድልድዮች እድሳት ተደርጎላቸዋል። እንዲሁም ሌሎች የእረንጓዴ ልማት ጥንቅቅ ብለው ለምተዋል።
የከተማችን ነዋሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ይህንን ልዩ ሆኖ የተጠናቀቀ የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት አዕምሮችሁን ዘና አካላችሁን ፈታ እያደረጋችሁ እንድትገለገሉበት እና ረጅም አገልግሎት እንዲሰጥ እንድትንከባከቡት አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያና እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ኢትዮዽያ አሸነፈች!!!

የሀገረ መንግስቱን ግንባታ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አቅጣጫ ውጭ ባንዳና ባዳ ጥምረት ፈጥረው በአመፅና በኃይል ሀገራችንን ወደ ጥፋት መንገድ ለመክተት ያሴሩትን ደባ ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊው ምርጫ እምቢተኝነቱንና ለሀገር ያለውን ፅኑ ፍቅር በተግባር በማሳየት አክሽፎታል።

በተለይ በአዲስ አባባ ረጃጅም ሰልፍ ቢፈጠርም ህዝቡ በእንቅልፍ እና በብርድ ሳይበገር ተራ እስኪደርሰው እስከ ለሊቱ 10:30 ሰአት ድረስ ተሰልፎ በሚገርም ጨዋነት፣ መሰጠት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት መርጧል።

የሀገራችን ፖለትከኞችና ልሂቃን ይህንን ታላቅ ጽኑ ጨዋና ቆራጥ ሕዝብ የምንረዳውና የሚንመጥነው መሆን ይጠበቅብናል።

ፈጠሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1
የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች ፕሮጀክት በውስጡ ምን ይዟል፦

👉 597 ሄክታር ቦታ የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት፤

👉 15 ሄክታር መሬትን በማልማት በአረንጓዴ ተሸፍኗል፤

👉 የ210 ቀፎ ዘመናዊ የንብ እርባታ፤

👉 የአበባ እና የእጽዋት ጋርደኖች ልማት፤

👉 የአካባቢውን ማህበረሰብ የስራ ባህል የሚዘክሩ ሃውልቶችና ቅርሶች ግንባታ፤

👉 22 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፤

👉 8 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤

👉 6 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፤

👉 4 ኪሎ ሜትር የሃይኪንግ መንገድ፤

👉 2 አዲስ የተሽከርካሪ ድልድዮች ግንባታ፤

👉 3 ነባር የተሽከርካሪ ድልድዮች ዕድሳት ፤

👉 39 የውሃ መከላከያ ግድቦች ግንባታ (ቼክ ዳም) ወዘተ... በስጡ አጠቃልሎ ይዟል።