Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.08K subscribers
6.32K photos
66 videos
18 files
256 links
Download Telegram
አንዲት ድምጽ ትልቅ ዋጋ አላት - መባከን የለባትም !

54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች፤ 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም 80 የግል እጩዎች የተወዳደሩበት ታሪካዊዉ የ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እስከ ዕኩለ ለሊት ድረስ ቀጥሏል
ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡

ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ
3
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የድምፅ መስጫ ሂደቱ እስከ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ሲከናወን ቆይቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ግንቦት 24 ቀንም ሆነ ሌሊት ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙ ተገልጿል።

ድምጽ የመስጠት ስርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ መራጩ ህዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ መላው የጸጥታ አካላት ኮማንድ ፖስቱ ምስጋናውን አቅርቧል።

ድምጽ ቆጠራው ቀጥሏል።

ድህረ ምርጫ ያለው ሂደት በተመሳሳይ በስኬት እንዲከናወን ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት ጥሪውን አቅርቧል።
1
‎ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ስራ አስጀምረናል።

‎ይህ ትልቅ ተነሳሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል።

‎በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፤ የማይቆራረጥ የልማት ስራችን ህያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሃገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ