Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.08K subscribers
6.33K photos
67 videos
18 files
256 links
Download Telegram
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ ድምፅ ሰጡ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በቦሌ ምርጫ ክልል ምርጫ ጣቢያ 17/19 በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል።
አዲስ አበባ እየመረጠች ነው !

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በየካ ክፍለ ከተማ ሐጅዙሊ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት መርጠዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ ድምፃቸውን ሰተዋል።
1
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ትዕግስታችሁና ጽናታችሁ እጅግ በጣም የሚደነቅ ነው።
በዘንድሮው ምርጫ ኢትዮጵያችንን ለማጽናት፣ ዘላቂ ሰላምንም ለማረጋገጥ እና የሀገረ መንግስት ግንባታችንን ለማጠናከር ያላችሁን ቁርጠኝነት ዳግም አሳይታችኋል።

ለረጅም ሰዓት እስካሁን ድረስ ተሰልፋችሁ ያላችሁ፣ ሕፃን ልጃችሁን በጀርባችሁ ያዘላችሁ እመጫቶች፣ ነፍሰ ጡር እናቶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ አዛውንቶች፣ ጎልማሶች እና ወጣቶች፤ ምዝገባው ዲጂታል የነበረ እና በወረቀት ፕሪንት የተደረገ በመሆኑ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች የስም ፍለጋ ጊዜ መውሰዱ የፍጥነት ላይ ችግር በማጋጠሙ ይቅርታ ጠይቋል ።

በመሆኑም ይህንን በመረዳት እንደጀመራችሁት በጽናት ይበጀኛል ያላችሁትን ለመምረጥ በትግስት ምርጫችሁን እንድታከናውኑ እጠይቃለሁ።

#ኢትዮጵያእየመረጠችነው #ኢትዮጵያ #ዲሞክራሲ #የሕዝብሉዓላዊነት

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1