Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.08K subscribers
6.35K photos
67 videos
18 files
256 links
Download Telegram
አዲስ አበባ ድምፅ እየሰጠች ነው!! ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!
የምርጫ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲሚካሄድ ያላቸውን ተስፋ የአፍሪካ ሕብረት የታዛቢ ቡድን መሪ ገለጹ

7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንደሚካሄድ ያላቸውን ተስፋ የአፍሪካ ሕብረት የታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የኬንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የምርጫ ዝግጅትን በየምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውረው እየጎበኙ ይገኛሉ።

በጉብኝታቸው በሰጡት አስተያየት ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ ፣ የኢትዮጵያ ስኬት ለመላ አፍሪካ በጎ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል፡፡

የድምጽ አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ምኞታቸው መሆኑንና ይህም እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው በጉብኝታቸው ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
አዲስ አበባ እየመረጠች ነው!

የከተማችን ነዋሪዎች በሌሊት በመውጣት የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የውሳኔ ሰጪነት መብቱን በተግባር እያረጋገጠ ነው።

የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው።

በምርጫ ብቻ!
1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።