የአዲስ አበባ ለውጥ ያስደነቃቸው አፍሪካውያን
በመዲናዋ እየታየ ያለው ፈጣን የከተማ ልማት እና የውበት ለውጥ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆን በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የታደሙ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች ገለጹ።
አዲስ አበባን ለመጀመሪያ ጊዜ ከስድስት ዓመታት በፊት ጎብኝተው እንደነበር ያስታወሱት
ከኢስዋቲኒ የመጡት የጉባዔው ተሳታፊ ኪንታፒ ሮቢንስ፤ አሁን ያገኟት ከተማ ግን ፈጽሞ የተለየች መሆኗን ተናግረዋል።
"አዲስ አበባ በየጊዜው እየተዋበች እና ንፁህ እየሆነች መጥታለች" ያሉት ተሳታፊው፤ ይህ ለውጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ መመዝገቡ እጅግ አስደናቂ እንደሆነ አግራሞታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ እያሳየችው ያለው ዕድገት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ሊሆን የሚችል ሲሆን፤ ለዚህም ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ሌላዋ የጉባዔው ተሳታፊ ከደቡብ አፍሪካ የመጡት ሲተን በሌሞ በበኩላቸው፤ ከተማዋ የቱሪዝም መዳረሻዎቿን በማስፋት ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹ እየሆነች መምጣቷን አድንቀዋል።
በመዲናዋ እየታየ ያለው ለውጥ የአፍሪካን ብልፅግና ከሚያልመው "አጀንዳ 2063" ጋር ቀጥተኛ ትስስር እንዳለው የገለጹት ሲተን በሌሞ፤ አፍሪካ ሕልሟን ለማሳካት የሁሉንም ዜጎች ብርቱ ጥረት ትፈልጋለች ብለዋል።
በተለይም በቱሪዝም እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሠራ እንደሚገባም አመልክተዋል። አፍሪካውያን በሚያሰባስቧቸው የጋራ እሴቶች ላይ አተኩረው ሊሠሩ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

❤1
39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 2ኛው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ ከወትሮው በተለየ ታላቅ ድምቀትና ስኬት ተጠናቋል።
ጉባኤዎቹ በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ ፍጹም ስኬታማ በሆነ መንገድ መካሄዱ፤ እንግዶቻችን የኢትዮጵያዊያንን ለዘመናት የዘለቀ እንግዳ ተቀባይነት እንዲሁም የመዲናችንን አስደናቂ ለውጥና ለጉባኤዉም ትልቅ ሞገስ በመሆኑ ጭምር ነዉ።
መላው የከተማችን ነዋሪዎች ላሳያችሁት እንግዳ አክባሪነት፣ ትዕግስትና አጋርነት ፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለሰጣችሁት ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት፤ ከተማችንን ሁሌም አዲስ ገፅታ እና መንፈስ በማላበስ ይህ ጉባኤ እንዲሳካ ላደረጋችሁ የከተማችን አመራሮች እና ሰራተኞች፤ በተለይም ከካዛንቺስ እስከ ቦሌ ብራስ ያላችሁ የግል ተቋማትና ግለሰቦች ለሌት ተቀን ትጋታችሁና ቀና ትብብራችሁ፤ እንዲሁም ከነዋሪው ጋር በመቀናጀት በቁርጠኝነት ለሠራችሁ የጸጥታ አካላት በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

❤7😁1
ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚዎች የመቀየር ብቃት የአሸናፊነት ጥበብ ነው።(ዶ/ር ጃራ ሰማ)
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዛሬው የወርቃማ ሰኞ መረሃ ግብሩ "አዎንታዊ አስተሳሰብና አመለካከት ለጋራ ዕድገት" በሚል የማነቃቂያ ሰልጠና ሰጥቷል
የካታት 9/2018(መልአ)
*******************************
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በሳምንቱ መጀመሪያ በሆነው ሰኞ በህይወት ልምዳቸው አንቱታን ያተረፉ በቀለም ትምህርታቸውም የካበት እወቀት ያላቸውን ግለሰቦች በመጋበዝ የማነቃቂያ ስልጠና እንዲሰጡ ያደረጋል።
ከሳምንት በቀጠል ክፍል ሁለት ስልጠና "አዎንታዊ አስተሳሰብና አመለካከት ለጋራ ዕድገት" በሚል ርዕስ የሕይወት ልምዳቸውን ያጋሩን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬትና የግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ጃራ ሰማ ናቸው።
አዎንታዊ አስተሳሰብ የመፍትሄ ሰው ያደርግኃል የሚሉት ዶ/ር ጃራ በጎ አሰተሳሰብና አመለካከትን ለመገንባት በራስ መተማመን፣ በትምህርት ራስን ማብቃትና ማመስገንን መለማመድ ይኖርብናል ብለዋል።
በተቃራኒው አሉታዊ አሰተሳሰብ የማይሆን ነገር ላይ እንደሚጥለን በማከል።
ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚዎች የመቀየር ብቃት የአሸናፊነት ጥበብ ነው በማለትም የህይወት ልምዳቸውን አጋርተዋል።
ውስጣችን ሲጠንክር ችግሮችን መጋፈጥ እንችላለን ሲሉ በመድረኩ የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ ጉድለታችንን ለመሙላት ችግሮችን የጋራ በማድረግ በቅንጅት መስራትን ልምድ እናድርግ በማለት አሳስበዋል።
አያይዘውም በባለፈው ሳምንት በነበረው አፈፃፀም የነቃ ተሳትፎ ለነበራቸው ዘርፎችና ባለሙያዎች እውቅና ሰጥተዋል ።
ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland

❤2
“Technology must unite human values with machine intelligence — positioning Africa as a global contributor in the age of intelligence.” — Prime Minister Abiy Ahmed at the 39th African Union Summit
#AUSummit
#PMOEthiopia
#AUSummit
#PMOEthiopia
❤1