የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ለሶስተኛ ጊዜ የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት እያልኩ የተሰማኝን ደስታ እገልጣለሁ።
የባርቤዶስ ሕዝብ ላደረገው ስኬታማ የዴሞክራሲ ልምምድ እያደነኩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞትሊ ለባርባዶስ ሕዝብ እድገት፣ ብልጽግና እና ዘላቂ ልማት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም እድል እንዲገጥምዎ እመኛለሁ።
በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር እና ትብብራችንን ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር

❤2
“Every river we manage, every city we design, and every digital platform we deploy must generate resilience, opportunity, and dignity.” — Prime Minister Abiy Ahmed at the 39th African Union Summit
#AUSummit
#PMOEthiopia
#AUSummit
#PMOEthiopia
❤1
“We have planted more than 48 billion trees — building a living legacy for future generations.” — Prime Minister Abiy Ahmed at the 39th African Union Summit
#AUSummit
#PMOEthiopia
#AUSummit
#PMOEthiopia
❤2
“Sovereignty means owning our narrative.”— Prime Minister Abiy Ahmed at the 39th African Union Summit
#AUSummit
#PMOEthiopia
#AUSummit
#PMOEthiopia
❤3
የአዲስ አበባ ለውጥ ያስደነቃቸው አፍሪካውያን
በመዲናዋ እየታየ ያለው ፈጣን የከተማ ልማት እና የውበት ለውጥ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆን በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የታደሙ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች ገለጹ።
አዲስ አበባን ለመጀመሪያ ጊዜ ከስድስት ዓመታት በፊት ጎብኝተው እንደነበር ያስታወሱት
ከኢስዋቲኒ የመጡት የጉባዔው ተሳታፊ ኪንታፒ ሮቢንስ፤ አሁን ያገኟት ከተማ ግን ፈጽሞ የተለየች መሆኗን ተናግረዋል።
"አዲስ አበባ በየጊዜው እየተዋበች እና ንፁህ እየሆነች መጥታለች" ያሉት ተሳታፊው፤ ይህ ለውጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ መመዝገቡ እጅግ አስደናቂ እንደሆነ አግራሞታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ እያሳየችው ያለው ዕድገት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ሊሆን የሚችል ሲሆን፤ ለዚህም ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ሌላዋ የጉባዔው ተሳታፊ ከደቡብ አፍሪካ የመጡት ሲተን በሌሞ በበኩላቸው፤ ከተማዋ የቱሪዝም መዳረሻዎቿን በማስፋት ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹ እየሆነች መምጣቷን አድንቀዋል።
በመዲናዋ እየታየ ያለው ለውጥ የአፍሪካን ብልፅግና ከሚያልመው "አጀንዳ 2063" ጋር ቀጥተኛ ትስስር እንዳለው የገለጹት ሲተን በሌሞ፤ አፍሪካ ሕልሟን ለማሳካት የሁሉንም ዜጎች ብርቱ ጥረት ትፈልጋለች ብለዋል።
በተለይም በቱሪዝም እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሠራ እንደሚገባም አመልክተዋል። አፍሪካውያን በሚያሰባስቧቸው የጋራ እሴቶች ላይ አተኩረው ሊሠሩ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 2ኛው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ ከወትሮው በተለየ ታላቅ ድምቀትና ስኬት ተጠናቋል።
ጉባኤዎቹ በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ ፍጹም ስኬታማ በሆነ መንገድ መካሄዱ፤ እንግዶቻችን የኢትዮጵያዊያንን ለዘመናት የዘለቀ እንግዳ ተቀባይነት እንዲሁም የመዲናችንን አስደናቂ ለውጥና ለጉባኤዉም ትልቅ ሞገስ በመሆኑ ጭምር ነዉ።
መላው የከተማችን ነዋሪዎች ላሳያችሁት እንግዳ አክባሪነት፣ ትዕግስትና አጋርነት ፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለሰጣችሁት ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት፤ ከተማችንን ሁሌም አዲስ ገፅታ እና መንፈስ በማላበስ ይህ ጉባኤ እንዲሳካ ላደረጋችሁ የከተማችን አመራሮች እና ሰራተኞች፤ በተለይም ከካዛንቺስ እስከ ቦሌ ብራስ ያላችሁ የግል ተቋማትና ግለሰቦች ለሌት ተቀን ትጋታችሁና ቀና ትብብራችሁ፤ እንዲሁም ከነዋሪው ጋር በመቀናጀት በቁርጠኝነት ለሠራችሁ የጸጥታ አካላት በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

❤7😁1