Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.37K subscribers
7.85K photos
74 videos
20 files
319 links
Download Telegram
ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የምናሳካው ሳይሆን በግሉ ዘርፍ የሚገነቡትንም ታሳቢ በማድረግ ስለሆነ፣ ዛሬ ያስመረቅነው የኒው ሊፍ ሜዲካል ሆስፒታልም የዚህ አንዱ ማሳያ ነው ።

ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ በሃገራችን ከላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው PET-CT SCAN CAT LAB እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ትልቅ የጤና ማዕከል ነው። በጤናው ዘርፍ የምናደርገው ኢንቨስትመንት ክፍያው ከሁሉ የላቀ ስለሆነ እንደዚህ አይነት በጤናው ዘርፍ ለሚሰሩ የጤና ተቋማት እና ሆስፒታሎች ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ስራአስኪያጅ ዶ/ር ኢማን አብዱልራህማን እና ባለቤታቸው አቡበከር መሃመድ ሳላህን በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም በጣም እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1
ይህን ያውቁ ኖሯል?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅኝት

#PMOEthiopia
ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተጠቃሚነት የሰራነዉ ልማት በተጨባጭ አዳዲስ የአኗኗር ባህል እየገነባ ማህበራዊ መስተጋብሩ ይበልጥ እያጠናከረ ነዉ።

በዉቧ ካዛንችስ የገንባነዉ ስፓርት ፓርክ ለከተማችን ነዋሪዎች የጤንነት መጠበቂያ ፣ የአካልና አእምሮ ማጐልበቻ ፣ የህፃናት መቦረቂያ፣ የብሄራዊ ጀግኖች አትሌቶቻችን ዉለታ መታሰቢያ አከታች ልማት በመሆኑ ለሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት እየሰጠ ነዉ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2
በተቋሙ ላይ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መመሪያና አሰራርን መሰረት አድርገው ሊፈቱ ይገባል። አቶ ካሳሁን ዓለሙ

ነሀሴ 18/2018 መልአ

**********************
ተቋማት ይብዛም ይነስ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አያጣቸውም ። ለሚነሱ የመልካም እሰተዳደር ችግሮች የሚሰጡ ምላሾች አሰራርን የተከተሉ አለመሆኑ ደግሞ የሚያድሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲኖሩ የህዝብ እሮሮም እንዲበራከት በር ይከፍታል።

በከተማዋ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከሚበራከትባቸው ተቋማት መካከል የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አንዱ ነው ያሉት የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ካሳሁን ዓለሙ ይህን ለመቅረፍ እንደ ተቋም የሚያድሩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዳይኖሩ ለሚነሱ ጥያቄዎች አሰራርን መሰረት ያደረገና በእውቀት ላይ የተመሰረት ምላሽ መስጠተ ይገባል ብለዋል።

በዘርፉ ላይ የሚታቀዱ እቅዶችም የህብረተሰቡን ጥያቄ መመልስ በሚያስችል መልኩ መተግበር ይኖርበታ ለዚህም የከንቲባ ጽ/ቤት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በቢሮው የለውጥና መልካም እሰተደዳር ዳይሬክቶሬት ከከንቲባ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳርና አቤቱታ ዘርፍ ጋር በመተባበር በመልካም አሰተዳደር ዕቅድ ዝግጅትና አተገባበር ላይ ያተኮረ ስልጠና ከማዕከል እና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለተወጣጡ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው እንደ ተቋም በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ አቅም ይፈጥራልም ተብሏል።
 
 
ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

👇👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email: -addisabababacityland@gmail.com
3
እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ

የነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ መክፈል፤ የተጠሩበትን ለሌሎች ማካፈል፤ የተጠሩበትን አክብሮ መኖር - እነዚህ ሁሉ ሺ መጻሕፍት የሚወጧቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

ነቢዩ የተጠሩበትን ዓላማ በሚገባ ስለተገነዘቡ አክብረው ኖረዋል፡፡ የተጠሩት ለተራና ርካሽ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የተጠሩት ትውልድን ለመቅረጽና ታሪክን ለመቀየር መሆኑን አምነዋል፡፡ ያንንም በቃላቸው፣ በሥራቸውና በኑሯቸው አክብረውት ነኖረዋል፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ተጠርተናል ብለን የምናምን ከሆነ ይህ የነቢዩ ሕይወት ታላቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡ የተጠራንበትን ዓላማ በንግግራችን፣ በሥራችንና በሕይወታችን እንግለጠው፡፡

ነቢዩ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ከቦታቸው ተሰደዋል፤ ምግብና መጠለያ ተነፍገዋል፤ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፡፡ ለሞት በሚያበቁ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአላህ ኃይል አሸንፈዋል፡፡ ክብር ያለ መከራ አይገኝምና፡፡ እውነተኛ ሰው ለዓላማው እንደ ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ)ዋጋ ይከፍላል፡፡ ዓላማው የሚያስገኘውን ክብርና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ዓላማው የሚያስከፍለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ይሆናል፡፡

ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ከአላህ የደረሳቸውን መልእክት ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፡፡ የተጠሩበትን ለሌሎች ለማካፈል ተግተዋል፡፡ መጀመሪያ በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በኋላም ለቅርብ ሱሐባዎች፣ በመጨረሻም ለዓለም መልእክቱን አዳርሰዋል ፡፡ እሳቸው የዘሩት ዘር እያፈራና እየጎመራ ተጉዟል፡፡ ዓላማችንን እኛ ማወቃችንና ማመናችን ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ልክ እንደነቢዩ ተገትተን መድከም አለብን፡፡

የነቢዩን መውሊድ ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፤ የተማርነውንም ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን እየተጠቀምን እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
1