Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.37K subscribers
7.86K photos
74 videos
20 files
319 links
Download Telegram
የገጠር ልማት መለካት ያለበት በሚገነቡት መሠረተ ልማቶች ብቻ ሳይሆን፣ ተከትሎ በሚመጣው የሰዎች ሕይወት ለውጥ መሆን አለበት።

‎በመሆኑም የገጠር ኮሪደር ልማት ውጥን ተግባራዊና ሰውን ማዕከል ያደረገ አካሄድን በመከተል ላይ ይገኛል። ይህም ትስስርን ማሻሻል፣ ምቹ የኑሮ ሁኔታዎችን መፍጠር እና በገጠር ማሕበረሰብ ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋፋት ነው።

‎የዚህ ዐበይት ግብ የተበታተነና የተቆራረጠ ሐብትን በማስተካከል አምራች፣ እርስ በርስ የተሳሰሩ፣ ዘላቂ ልማት ያላቸው እንዲሁም ለመኖርና ለመሥራት ማራኪ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን መገንባት ነው።

#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
ማይክሮ ተነሊንግ፦ የአዲስ አበባ የዘመነ መሰረተ ልማት ግንባታ

አንድ ከተማ ዘመናዊ ስትሆን የሚታዩት ከፍተኛ ህንፃዎች፣ ሰፊ መንገዶችና ዲጂታል አገልግሎቶች ብቻ አይደሉም፤ ከመሬት በታች የሚሰሩ ነገር ግን ለእይታ ግልፅ ያልሆኑ የውሃና ፍሳሽ እና የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች የዘመናዊ ከተማ መሠረት ናቸው።

በአዲስ አበባ ከመሬት በላይ ከተገነቡት መሰረተ ልማቶች እኩል ከመሬት በታችም ተገንብተዋል።

ንፁህና ጤናማ አካባቢ፣ የተሻለ የፍሳሽ አገልግሎት፣ የተቀነሰ የትራፊክ መዘጋትና የተሻለ የከተማ ኑሮ ሲገነባ በመሬት ላይ የሚታየው ውጤት ከመሬት በታች በሚሰራው ቴክኖሎጂ ይጀምራል።

አዲስ አበባ ወደ ስማርትና ዘመናዊ ከተማ በምትሸጋገርበት ጉዞ ላይ ማይክሮ ተነሊንግ ከሰው ሕይወት እስከ ከተማዋ የወደፊት ልማት የሚዘልቅ የቴክኖሎጂ አቅም ነው።

ዛሬ አዲስ አበባ በሕዝብ ቁጥርና በከተማ እድገት እየሰፋች በመሆኗ ከተማዋን ንፁህ፣ ጤናማና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የፍሳሽ መሠረተ ልማት ማስፋፋት ወሳኝ ሆኗል። በዚህ ሂደት ማይክሮ ተነሊንግ ቴክኖሎጂ ከሰው ሕይወት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ዘመናዊ መፍትሔ እየሆነ ይገኛል።

የዚህ ቴክኖሎጂ ትልቁ ጥቅም የከተማዋን ዕለታዊ እንቅስቃሴ ሳይቋርጥ አስፈላጊውን የፍሳሽ መስመር ከመሬት በታች ማስቀመጥ መቻሉ ነው። በቀድሞ አሠራር የፍሳሽ መስመር ትልቅ መንገድ ለማሻገር ወይም ሌላ መሠረተ ልማት ለማቋረጥ መንገድ መቆፈር/መቁረጥ/ የተለመደ ነበር። መንገድ ሲቆረጥ ደግሞ የትራፊክ መጨናነቅ፣ የንግድ ሥራ መስተጓጎልና የነዋሪዎች ጊዜ መባከን ይፈጠራል።

ማይክሮ ተነሊንግ ይህንን ውስብስብ ችግር የሚፈታ በከተማዋ ላይ ትልቅ ቁፋሮ ሳይደርግ ሥራውን ከመሬት በታች በመፈጸም የነዋሪውን ጊዜ፣ የንግድ እንቅስቃሴና የከተማዋን ትራፊክ ፍሰት እንዲሳለጥ የሚያደርግ ነው ።

ይህንን ዘመናዊ አሠራር በመጠቀም የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አሁን በከተማዋ ውስብስብ የሆኑ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ከእነዚህ ሥራዎች መካከል የባቡር ሀዲድን ማቋረጥ የሚጠይቁ ከባድ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታዎችም ይገኙበታል።
የማይክሮ ተነሊንግ ስራ በከተማዋ እየተሰራ ያለው የምስራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ መሰረተ ልማት አካል የሆነው በመገናኛ ደራርቱ ህንጻ ወረድ ብሎ ያለው የ55 ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር ሀዲድ እና የአስፓልት መንገድ እንዲሁም ከሲኤም ሲ ቤቶች ወደ አለምዓቀፍ ኮንቬሽን ሴንተር የሚያሻግረው የ92 ሜትር ርዝመት ያለው ውስጥ ለውስጥ በመቦርቦር 600 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር ስፋት ያለው የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራ ተጀምሮ በመጠናቀቅ ላይ ነው ፡፡

ይህ በከተማዋ የሚታየው ቴክኖሎጂን በመሠረተ ልማት ሥራ ላይ የማዋል አቅም ከፍ እያለ መምጣቱን የሚያሳይ ሲሆን፣ አዲስ አበባም የነገዋን ከተማ በቴክኖሎጂ እየገነባች መሆኗን ያረጋግጣል።
1
"የሀገር ብርታት ጥበብ ብልሃቱ ምክክር ነው"፦ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያን አሸናፊነት የሚያረጋግጡ እና አንድነትን የሚያጸኑ የጋራ መሻቶች መገለጻቸውን ገልጸዋል።

ምክክሩ ለትውልድ የሚበጅ ጠንካራ ሐሳብ የተንሸራሸረበት ልዩ ቀን መሆኑን በማንሣት፣ ምክክር የሀገር ብርታት እንዲሁም የጥበብ እና ብልሃት መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመልእክታቸው 130 ሚሊዮን ሕዝብን በመወከል ለ46 ቀናት በቆየው ውይይት ላይ የተሳተፉትን ተመካካሪዎች በልዩ ሁኔታ አመስግነዋል።

ተሳታፊዎቹ የአካባቢያቸውን መልካም ተሞክሮ በማምጣት ለኢትዮጵያ በሚበጅ መልኩ ማቅረባቸውን አድንቀው፣ ይኸው የሰላም ውይይት እንዲሳካ ላስቻሉ የመከላከያ ሠራዊት እና መላው የጸጥታ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም ብሔራዊ ጥቅምን ያማከለ ምቹ የመወያያ መድረክ ላዘጋጁት የምክክር ኮሚሽኑ አባላት እና የዛሬ ሳንሆን የነገው ትውልድ ተስፋ እንድንሆን ላስቻሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ከፍ ያለ ዕውቅና ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንት ታየ ምክክር የነባር ባሕላችን አካል ቢሆንም ለፖለቲካ እና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ለማዋል ከዚህ ቀደም ተሞክሮ እንደማያውቅ አስታውሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደዚህ ዓይነት የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ በቁርጠኝነት ኃላፊነታቸውን በመወጣታቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ውይይቱ ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ የተወጠነ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ ጉባኤው የሁላችንንም ኢትዮጵያ የሚያጸና እና ለመጻኢው ዕጣ ፈንታ ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀ መሆኑን አስረግጠዋል።
2