Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.41K subscribers
8.02K photos
76 videos
20 files
331 links
Download Telegram
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች 1ሺ ሄክታር የለማ መሬት አዘጋጅቶ ለማስተላለፍ ማቀዱን ገለፀ።

ይህ የተገለፀው ቢሮው በ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ እቅድ ላይ በተወያየበት መድረክ ላይ ነው ።

ነሀሴ 07/2018(መልአ)
****

ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ስርዓት የተዘረጋበትና የላቀ አገልግሎት የሚሰጥበት ተቋም ለመፍጠር ራዕይ ሰንቆ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የዘርፉን የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ እቅድ እና የሰው ተኮር ተግባራትን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገምግሟል ።

የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮው ኃላፊ አቶ መላኩ ታምሩ መድረኩ የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ እቅድ የተሟላ እንዲሆን ግብዓት ለመሰብሰብ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀው ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ብቁና ተወዳዳሪ ተቋም ለመፍጠር አመራሩ ከምንጊዜውም በላይ የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

በየደረጃው ተጠያቂነትን በማስፈን ሌብነትን ማክሰም እንደሚገባም በማከል ።

የበጀት ዓመቱን ረቂቅ እቅድ ሪፖርት ያቀረቡት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ዓለሙ በበኩላቸው በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ለተለያየ አገልግሎቶች 929 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ መተላለፉን አስታውሰው ፤ በተያዘው 2019 በጀት ዓመት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን ጨምሮ 1ሺ ሄክታር የለማ መሬት አዘጋጅቶ ለማስተላለፍ ውጥን መያዙን ተናግረዋል ።

አያይዘውም በተመቻቸው ኦንላይን አገልግሎት በመታገዝ ከ1988 እስከ 1997 አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ የተያዙ 10,500 ሰነድ አልባ ይዞታዎችን የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ አዘጋጅቶ ለማሰራጨት እና አገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ ከይዞታና ከሊዝ 36.7 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱንም አብራርተዋል ።

በዚሁ መድረክ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ የማዕከል ሰራተኞች እና የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ ላበረከቱ የመማክርት ጉባኤ አባላት እውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል ።

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
������
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
10
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በአዲስ አበባ ጉብኝት አደረጉ

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራንን ያካተተ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ::

የልዑካን ቡድኑ የአብርሆት ቤተ መጽሀፍ፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ የአራዳ ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማት እና የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል:: በጉብኝታቸው ባዩት የቱሪዝም ሀብትና በአዲስ አበባ ፈጣን የልማት ጉዞ እጅግ መደነቃቸውን ገልጸዋል::

አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የልማት ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋት እና የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
2